Back to top

Sabbath Bible Lessons

ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (II)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሰኔ 29፣ 2016 1ኛ ትምህርት
ተአምረኛው ማምለጫ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።” (2ኛ ጴጥሮስ 1፡4)።
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 737–746; 
  Thoughts From the Mount of Blessing, pp. 76–78. 
ኦ፣ እነዚያ ጥቅት መንፈሳዊ ሕይወት ልምድ ያላቸው የዘላለም ሕይወት ሊሰጣቸው የሚችለው የመለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋዮች ለሆኑና በዓለም ውስጥ ካለው ብልሹነትና ፍትወት ላመለጡ ብቻ እንደሆነ ምን አለ ቢገነዘቡ!”—Testimonies for the Church, vol. 9, p. 155.

1. ዓላማ ያለው መልእክት እሁድ ሰኔ 23
ሀ. ይህ መልእክት የተላከው ለማን እና ለምን ነው፣ እና ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን ቻለ? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡1 “ይህ የእግዚአብሔር እና የመድኃኒታችን የየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ — ለማሰላሰል እንዴት ያለ ታላቅ ጭብጥ ነው። ስለ ክርስቶስ እና ስለ ጽድቁ ማሰላሰል ራስን ለማጽደቅ፣ ራስን ለማክበር ቦታ አይሰጥም። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ምንም ማቆሚያ የለም። በእያንዳንዱ የክርስቶስ የእውቀት ደረጃ ቀጣይነት ያለው እድገት አለ።”— The SDA Bible Commen- tary [E. G. White Comments], vol. 7, p. 942. ለ. በቅንነት እግዚአብሔርን በቃሉ ስንፈልግ ምን አይነት ሽልማቶች ወደ ልባችን ይጎርፋሉ? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡2 “ሰው መለኮታዊ ተፈጥሮን ከያዘ፣ በመደመር እቅድ ላይ እየሰራ፣ ክርስቲያናዊ ባህሪን በማሟላት ጸጋን ከጨመረ፣ እግዚአብሔር የማባዛት እቅድ ላይ ይሰራል። በቃሉ፡- በእግዚአብሔርና በጌታችን በየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ይላል።” —Testimonies for the Church, vol. 6, p. 148.

2. እግዚአብሔርን የማወቅ በረከት ሰኞ ሰኔ 24
ሀ. በተለይ በአስቸጋሪ ጊዜያት የምንቀበለውን ለእያንዳንዳችን ምን የተባረከ ማረጋገጫ ይሰጠናል? ኤርምያስ 24:7ኢዮብ 22:21–23፣ 29 “ተስፋችን ክርስቶስ ጽድቃችን መሆኑን በማወቃችን ያለማቋረጥ ይበረታል። እምነታችን በዚህ መሠረት ላይ ይኑር፣ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና። በሰይጣን ጨለማ ላይ ከመቀመጥ እና ኃይሉን ከመፍራት፣ ከክርስቶስ ብርሃን ለመቀበል እና ለዓለም እንዲበራ፣ እርሱ ከሰይጣን ኃይል ሁሉ በላይ እንደሆነ፣ በእርሱ የሚታመነቱን ሁሉ ደጋፊ ክንዱ እንደሚደግፈን በመረዳት ልባችንን መክፈት አለብን።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 742. ለ. ከየሱስ ጋር ይበልጥ እየተተዋወቅን ስንሄድ ውጤቱ ምንድ ነው? ሆሴዕ 13:4ኤፌሶን 3፡17-19 “ብዙዎች ስለ ከፍ ያለ የክርስቶስ ባህሪ እና አገልግሎት የነበራቸው ትንሽ አመለካከቶች ሃይማኖታዊ ልምዳቸውን ጠባብ እና በመለኮታዊ ህይወት ውስጥ እድገታቸውን በእጅጉ አግዶታል። በመካከላችን እንደ ሕዝብ በግለሰብ ደረጃ ሃይማኖታችን በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው። በብዙ መልክ፣ በብዙ ቁሳዊ፣ በብዙ ቋንቋ ያለ ሃይማኖት አለን፤ ነገር ግን በሃይማኖታችን ውስጥ ጥልቅ እና ጠንካራ የሆነ ነገር ማምጣት አለብን።”—Ibid., p. 743.“የሱስም፦ “አብ ራሱ ይወዳችኋል” አለ። እምነታችን በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ ከሆነ፣ ‘እንደ ነፍስ መልሕቅ፣ አስተማማኝና ጽኑ፣ ቀዳሚውም ወደ መጋረጃውም ውስጥ እንደሚገባ” ያረጋግጣል። እውነት ነው ተስፋ መቁረጥ ይመጣል፤ መከራም የሚጠበቅ ነገር መሆን አለበት፤ ነገር ግን ሁሉንም ነገር ከትልቅ እስከ ትንሹ ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት አለብን። እርሱ በጥያቄአችን ብዛት ግራ አይጋባም ወይም በሸክማችን ክብደት አይሸነፍም። ተንከባካቢው የእሱ እጅ እያንዳንዱን ቤተሰብ እና እያንዳንዱን ግለሰብ ይከብባል፤ እሱ በእያንዳንዱ ጉዳዮቻችን እና ሀዘኖቻችን ጊዜ ሁሉ ያስብልናል። እንባዎችን ሁሉ ምልክት ይመዘግባል፤ በድካማችን ስሜቱ ይነካል። እዚህ የሚያጋጥሙን መከራዎች እና ፈተናዎች ሁሉ የተፈቀዱት፣ ለእኛ ያለውን የፍቅር አላማዎች እንዲፈጸሙ፣ 'የእርሱ ቅድስና ተካፋዮች እንድንሆን' እና በዚህም በእርሱ ፊት ባለው የደስታ ሙላት ተካፋዮች እንድንሆን ነው።“የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን የአምላክን እውቀት የማግኘትን አስፈላጊነት በፊታችን ይገልጥልናል።”—Ibid., p. 742

3. መፈለግ እና ማግኘት ማክሰኞ ሰኔ 25
ሀ. የዘመኑን (የዚህ) ዓለም ሁኔታ ግለጽ። 1ኛ ዮሐንስ 5፡19 ቢሆንም፣ እግዚአብሔር በቃሉ ምን ሰጥቷል? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡3 “የሰዎች አእምሮ የአምላክን እውቀት እንዳያገኙ በሚከለክሏቸው ነገሮች እንዲጠመድ ማድረግ የሰይጣን የማያቋርጥ ጥናት ነው። ማስተዋልን በሚያጨልመው እና ነፍስን በሚያደክም ነገር ላይ እንዲያተኩሩ ይፈልጋል። እኛ የክርስቶስ ተከታዮችን በሚያማልሉ ወይም ተስፋ በሚያስቆርጡ ተጽዕኖዎች በተከበበ ኃጢአትና ብልሹ ዓለም ውስጥ ነን። አዳኙ እንዲህ አለ፡- 'ኃጢአት ስለሚበዛ የብዙዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።' ብዙዎች ዓይኖቻቸውን በዙሪያቸው ባለው አስከፊ ክፋት፣ በሁሉም አቅጣጫ ያለውን ክህደት እና ድክመት ላይ ያተኩራሉ፣ እናም ልባቸው በሀዘንና በጥርጣሬ እስኪሞላ ድረስ ስለእነዚህ ነገሮች ይናገራሉ። የሰማይ አባትን ኃይል እና አቻ የለሽ ፍቅሩን የሳቱ ቢመስሉም የታላቁን አታላይ ስራ በአእምሮ ፊት ከፍ አድርገው ይጠብቃሉ እና በሕይወታቸው ተስፋ አስቆራጭ ገፅታዎች ላይ ያተኩራሉ። ይህ ሁሉ ሰይጣን እንደሚፈልገው ነው። ስለእግዚአብሔር ፍቅር እና ኃይሉ ጥቅት ብቻ ስንናገር ነገር ግን የጽድቅን ጠላት ይህን ያህል ታላቅ ኃይል እንደለበሰ አድርገን ማሰብ ስህተት ነው። ስለ ክርስቶስ ኃያልነት መናገር አለብን። ራሳችንን ከሰይጣን መዳፍ ለማዳን ፈጽሞ አቅም የለንም፤ እግዚአብሔር ግን መውጫውን አዘጋጀቷል። የልዑል ልጅ ስለ እኛ ጦርነቱን የሚዋጋበት ኃይል አለው፣ እና 'በወደደን' በእርሱ በኩል 'ከአሸናፊዎች ይልቅ' ልንበረታ እንችላለን።”—Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 740, 741. ለ. መንፈሳዊ ድል ስለ አምላክ የላቀ እውቀት ከመሻት ጋር በቀጥታ የሚዛመደው እንዴት ነው? ምሳሌ 9:10፤ 15፡14 (የመጀመሪያ ክፍል)። “እግዚአብሔርን ማወቅ (የእግዚአብሔር እውቀት) የእውነተኛ ትምህርትና የእውነተኛ አገልግሎት ሁሉ መሠረት ነው። ከፈተና የሚጠብቀው ብቸኛው ትክክለኛ መከላከያ ነው። በባህሪያችን እግዚአብሔርን እንድንመስል የሚያደርገን ይህ ብቻ ነው።“ይህ ለባልንጀሮቻቸው መዳን ለሚሰሩ ሁሉ የሚያስፈልጋቸው እውቀት ነው። የባህሪ ለውጥ፣ የህይወት ንፅህና፣ የአገልግሎት ቅልጥፍና፣ ትክክለኛ መርሆዎችን ማክበር፣ ሁሉም የተመካው በእግዚአብሔር ትክክለኛ እውቀት ላይ ነው። ይህ እውቀት ለዚህ ሕይወትም ሆነ ለሚመጣው ሕይወት አስፈላጊው ዝግጅት ነው።”—The Ministry of Healing, p. 409.

4. እጅግ በጣም ጥሩ እና ውድ የሆኑ ተስፋዎች ረቡዕ ሰኔ 26
ሀ. በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ በሚያሳዝን ሁኔታ የምንገምተው ነገር ምንድን ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡4 “ከዚያ መጥፎ ልምምድ ማምለጥ ከፈለግን፣ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችንን መዳን ለመሥራት ሳንዘገይ በትጋት መጀመር አለብን። ለጥምቀት ቃልኪዳን የገቡትን ቃል በትክክል ስለመፈጸማቸው ምንም ዓይነት ቁርጥ ያለ ማስረጃ የማይሰጡ ብዙዎች ናቸው። ቅንዓታቸው የሚቀዘቅዘው በወግ አጥባቂነት፣ በዓለማዊ ምኞት፣ በኩራት እና ራስን በመውደድ ነው። አልፎ አልፎ ስሜታቸው ይነሳሳል፣ ነገር ግን በዓለቱ በክርስቶስ የሱስ ላይ አይወድቁም። በንስሐና በኑዛዜ የተሰበረ ልብ ይዘው ወደ እግዚአብሔር አይመጡም። በልባቸው ውስጥ የእውነተኛ ለውጥን ሥራ የሚለማመዱ ግን የመንፈስ ፍሬዎችን በሕይወታቸው ይገልጣሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 9, p. 155.“በክርስቶስ በአስተማማኝ ሁኔታ ስንቆም፣ ማንም ሰው ሊወስድብን የማይችለው ኃይል ይኖረናል። ይህ ለምን ሆነ? ምክንያቱም እኛ የመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች ነን በፍትወትም ዓለም ካለው ጥፋት አምልጠን በሰው ዘር ቦታ ይቆም ዘንድ የሰውን ልጅ ፍጥረት ለብሶ ወደዚህ ምድር ከመጣው እና የኃጢአት ነቁጣ ወይም እድፍ የሌለበትን ገጸ ባህሪ ባለቤት ከሆነው ከእርሱ ባሕርይ ተካፋዮች ነን።“ለምን ብዙዎቻችን ደካማ እና ውጤታማ ያልሆንነው? ክርስቶስንና ባሕርዩን ከማጥናት ይልቅ ወደ ራሳችን በመመለከት፣ የራሳችንን ባሕርይ በማጥናት ት ለራሳችን፣ ለግላችንና ለልዩነቶቻችን እንዴት ቦታ መፍጠር እንደምንችል ስለምናስብ ነው።”—Ibid., vol. 9, p. 187. ለ. እነዚህን ተስፋዎች በትክክል ስንረዳ ምን ለውጥ ይመጣል? ሮሜ 3:31፤ 8፡14። “እንደ ክርስቲያኖች ኃላፊነታችንን ለመገንዘብና ለመወጣት፣ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለን ለአለም ለማሳየት ለራሳችን ቃል ገብተናል። ስለዚህ በደቀ መዛሙርቱ አምላካዊ ቃል እና ስራ ክርስቶስ መወከል አለበት።“እግዚአብሔር ለባህሪው መገለጫ ለሆነው ለህጉ ፍጹም መታዘዝን ይፈልግብናል። . . . ሕጉ የእግዚአብሔር ድምፅ ማሚቶ ነው፣ ቅዱስ ሆይ፣ ዛሬም ቅዱስ ነህ ይለናል። የክርስቶስን ጸጋ ሙላት ተመኙ፤ አዎን ጽድቅን ፍለጋ፣ ታላቅ ረሃብና ጥማት ሊኖረን ያስፈልጋል። የተስፋው ቃሉም “ታገኛላችሁ” ይላል። የእግዚአብሔር ቃል ሥራው ሰላም ነውና ጸጥታና መረጋጋት የዘላለም ተስፋ ነውና ለዚህ ጽድቅ ልባችሁ በትልቅ ምኞት ይሞላ።“በሥጋ ምኞት በዓለም ውስጥ ካለው ጥፋት አምልጠን ከመለኮታዊው ባሕርይ ተካፋዮች መሆናችን ትልቅ መብት ነው።”—Bible Training School, February 1, 1904.

5. በሚያስደንቅ ሁኔታ ተዘጋጅቷል ሐሙስ ሰኔ 27
ሀ. ለሰው ልጅ ሁሉ የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ አስረዳ። ዮሐንስ 17:17፤ መዝሙረ ዳዊት 119:151 “እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው የእርሱን መልክ እንዲንመስል ነው። ቅድስና ከሕዝቡ የከበረ የክብሩ ጨረሮች ነጸብራቅ ነው። ይህንን ክብር ለማንጸባረቅ ግን ከእግዚአብሔር ጋር መስራት አለብን። ልብ እና አእምሮ ወደ ስህተት ከሚመራው ነገር ሁሉ ባዶ መሆን አለበት። ከቃሉ መንፈሳዊ ኃይል ለማግኘት ከልብ በመሻት፣ የእግዚአብሔር ቃል መነበብና መጠናት አለበት። የሕይወታችን አካል ይሆን ዘንድ የሰማይ እንጀራ መበላትና መፈጨት አለበት። በዚያም የዘላለምን ሕይወት እናገኛለን። ከዚያም 'በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህም እውነት ነው የሚለው የአዳኙ ጸሎት መልስ ያገኛል።“መላእክት የእኛን ቦታ ሊወስዱ አይችሉም፤ ነገር ግን ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ለመሳብ ከእኛ ጋር ለመተባበር ዝግጁ ሆነው ይቆማሉ፤ ከእነሱ ጋር በኅብረት እንድንሠራ ይጠይቁናል።”—Bible Training School, February 1, 1904.“እግዚአብሔር ፍጹማን እንድንሆን እንደሚፈልግ በግልጽ ተናግሯል። ይህንንም ስለሚፈልግ የመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች እንድንሆን ዝግጅት አድርጓል። የዘላለም ሕይወት ለማግኘት በምናደርገው ጥረት ስኬት ማግኘት የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው። ኃይሉ የተሰጠው በክርስቶስ ነው።”—Ibid. ለ. የወቅቱ የእግዚአብሔር ጥሪ ምንድነው? 2ኛ ቆሮንቶስ 6:15–18፤ 7፡1። “የዩኒቨርስ ፈጣሪ እንደ አፍቃሪ አባት ሆኖ ይጠራችኋል። በፍላጎት ፣ በአለም ካለው በፍትወት ከሚፈጠረው ክፋት አምልጣችሁ፣ ከአለም ከተለያችሁ እና ከብክለት ነፃ ከሆናችሁ፣ እግዚአብሔር አባታችሁ ይሆናል፣ እናንተን ወደ ቤተሰቡ ይወስዳችኋል፣ እናንተም ወራሽ ትሆናላችሁ። በዓለም ምትክ፣ ስለመታዘዝ ሕይወታችሁ፣ ከሰማያት ሁሉ በታች ያለውን መንግሥት ይሰጣችኋል። እርሱ የዘላለም የክብር እና እንደ ዘላለም የሚጸና ሕይወት ይሰጣችኋል።”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 44.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ሰኔ 28
1. ታላቅ እምነት የሚመጣው ከየት ነው? 2. አምላክ ለእኔ ስላለው ፍቅር ሙሉ በሙሉ ማድነቅ ያቃተኝ ነገር ምንድን ነው? 3. በዛሬው ጊዜ ያሉት “መልካምንና ክፉን የማወቅ ዛፎች” ትኩረቴን የሳቡት እንዴት ነው? 4. ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከክርስቶስ በአስተማማኝ ሁኔታ ከተጣበቅኩ ምን ይሆናል? 5. በዚህ ትምህርት መሰረት የእኔ ጉድለት ያለበት ባህሪ እንዴት ሊሟላ ይችላል?
 <<    >>