Back to top

Sabbath Bible Lessons

የትንቢት አስፈላጊነት

 <<    >> 
ሰንበት፣ መጋቢት 26፣ 2018 1ኛ ትምህርት
ስለ ትንቢት መግቢያ የማስታወሻ ጥቅስ፡ “ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።” (2ኛ ጴጥሮስ 1፡19)
ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ፡   The Great Controversy, pp. 593–602. 
“ታሪክና ትንቢት የምድር ሁሉ አምላክ የብርሃን ተሸካሚ በሆኑት ምርጦቹ ለዓለም ምሥጢርን እንደሚገልጥ ይመሰክራሉ።”—Bible Training School, December 1, 1912.

1. ወሰን የሌለው አእምሮ እሁድ፣ መጋቢት 20
ሀ. እግዚአብሔር ብቻ ሊያየው የሚችለው ምንድነው? ኢሳይያስ 46:9፣ 10 “እኔ ነኝ ማለት ዘላለማዊ መገኘት ነው። ያለፈው፣ የአሁኑ እና የወደፊቱ በእግዚአብሔር ዘንድ አንድ ናቸው። በሩቅ ያለፉትን የታሪክ ክስተቶች እና የወደፊቱን ጊዜ ልክ እኛ በየቀኑ ሲከሰት እንደምናያቸው እርሱ የሚከሰቱትን ነገሮች በግልፅ ያያል”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 1, p. 1099. ለ. ጌታችን በጥበቡ ምን ያደርጋል? ዳንኤል 2:20–22 “ከምድር ጥፋት ሁሉ በላይ እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፤ ሁሉም ነገር ለመለኮታዊው ቅኝት ክፍት ነው፤ እናም ከታላቁና ከተረጋጋው ዘላለማዊነቱ እርሱ ከሁሉ የተሻለውን ያዛል።”—The Ministry of Healing pp. 417.“በሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ የግዛቶች ማደግ፣ የነገሥታት መነሳትና ውድቀት፣ የታሪክ ይዘት፣ እነዚህን የመሳሰሉት ሁሉ በሰው ኃይልና ውሳኔ የሚከናወኑ መስለው ይታያሉ። ነገር ግን እግዚአብሔር መጋረጃውን ገልጦ ሲያሳየን ኃያልና መሐሪ የሆነው አምላክ በጥበቡ የሰውን ልጆች ሽኩቻና የኃይል ትግል ይቆጣጠራል።—Prophets and Kings, pp. 499, 500.

2. ምስጢሮች ተገለጡ ሰኞ፣ መጋቢት 21
ሀ. እግዚአብሔር ፈቃዱን በምድር ላይ ለማድረግ ዝግጁ ሲሆን ምን ያደርጋል? አሞጽ 3:7፤ ራዕይ 1:1 “በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም” አሞጽ 3:7፣ “ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው።” ዘዳግም 29:29 እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ሰጥቶናል፤ ትንቢታዊ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአክብሮት እና በጸሎት በማጥናት በረከት ይገኛል።”—The Desire of Ages, p. 234. ለ. እግዚአብሔር እንዲህ ያሉ መልእክቶችን ለምን ይልክልናል? 1ኛ ዮሐንስ 3:1ዮሐንስ 1:12፤ ቆላስይስ 1:25–28 “መጽሐፍ ቅዱስ ድንቅ መጽሐፍ ነው። ያለፉትን ምዕተ ዓመታት የሚከፍትልን ታሪክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ባይኖር ኖሮ ስላለፉት ዘመናት ክስተቶች ለግምቶችና ለተረቶች እንሰጥ ነበር። የወደፊቱንም የሚገልጥ ትንቢት ነው። የመዳንን እቅድ የሚገልጥልን ሲሆን፣ ዘላለማዊ ሞትን የምናመልጥበትን መንገድም የሚያመለክተን የእግዚአብሔር ቃል ነው።ምንም እንኳ ዋጋ ቢኖራቸውም፤ ዓለምን ካጥለቀልቁት መጻሕፍት ሁሉ ይልቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ሊደነቅ እና ሊጠና የሚገባው የመጽሐፍት ሁሉ መጽሐፍ ነው። የዚህን ዓለም ታሪክ ብቻ ሳይሆን ስለሚመጣውም ዓለም መግለጫን ይሰጣል። ስለ ዩኒቨርስ ድንቅ የሆኑ ስርአቶችንና መመሪያን ይዟል፣ የሰማያትና የምድርን ባለቤት ባሕርይ እንድንረዳም ይገልጥልናል። ለሰው ልጆችም በውስጡ የእግዚአብሔር መገለጥ አለበት።”—The Signs of the Times, January 30, 1893. ሐ. ልንፈልገው የሚገባን በጣም አስፈላጊው እውቀት ምንድን ነው? ኤርምያስ 9:23፣ 24፤ ዮሐንስ 17:3ኤፌሶን 3:17–19 “በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ሲሆን አእምሮአችን ጥልቅ ለሆኑ ሀሳቦችና ለከፍተኛ ፍላጎት ተገዢ ይሆናል። በእርሱም ከአበውና ከነቢያት ጋር ኅብረት በማድረግ ዘላለማዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን ድምፅ በሰዎች ውስጥ ሲናገር መስማት እንችላለን። በእርሱ ውስጥ የሰማይ ባለግርማ ስለ እኛ ራሱን ዝቅ በማድረግ የጨለማን ኃይሎች ብቻውን በመቋቋም፤ በእኛ ምትክ ድልን ለማግኘት ዋስትናችን ሲሆን እናያለን። እንደዚህ ባሉ ጭብጦች ላይ በአክብሮት ማሰላሰል ልብን ያለሰልሳል፣ ያጠራል፣ ያበለፅግማል፤ በተመሳሳይ ጊዜም አእምሮን በአዲስ ጥንካሬ እና ጉልበት ማነሳሳት ይችላል።—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 25.

3. ቃሉን መረዳት ማክሰኞ፣ መጋቢት 22
ሀ. ትንቢትን ጨምሮ ቅዱሳት መፅሃፍትን ለመረዳት የማን እገዛ ያስፈልገናል? ዮሐንስ 16:7–13 እግዚአብሔር በዚህ ምድርም ቢሆን እውነት ሁልጊዜ ለሕዝቡ እንዲገለጥ ይፈልጋል። ይህም እውቀት የሚገኝበት በአንድ መንገድ ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት የምንችለው ቃሉ በተሰጠበት በመንፈሱ ብርሃን ብቻ ነው።—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 703. “መጽሐፍ ቅዱስን በምንም ዓይነት ያለፀሎት ማጥናት የለብንም፡፡ ገፆቹን ከመግለጣችንና ከማንበባችን በፊት መንፈስ ቅዱስ ቃሉን እንዲገልጥልንና እንድናስተውል እንዲረዳን ልንጠይቀው ይገባል፡፡ እግዚአብሔርም ይገልጥልናል፡፡ አንድ ጊዜ ናትናኤል ወደ የሱስ ሲመጣ አዳኛችን ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ «ተንኮል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ» ናትናኤልም ሲመልስ «ከወዴት ታውቀኛለህ» አለው፡፡ የሱስ ሲመልስ «ፊሊጶስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ» አለው፡፡ (ዮሐ. 1፡ 47-48)፡፡ ዛሬም የሱስ የእውነትን ብርሃን ለማግኘት በስውር ሆነን ወደእርሱ ስንፀልይ እያንዳንዳችንን ያየናል፡፡ ቅዱሳን መላዕክት እራሳቸውን ዝቅ አድርገው በትህትና የእግዚአብሔርን አመራር ከሚሹ ሁሉ ጋር ይሆናሉ።”—Steps to Christ, p. 91. ለ. ትንቢትን ስናጠና የራሳችንን አመለካከት አለመከተል ለምን ይጠቅማል? 2ኛ ጴጥሮስ 1:19–21 “በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችሁ ከዚህ በፊት በአእምሮአችሁ ይዛችሁት የነበረውን ግምትም ሆነ በውርስና በሂደት ያዳበራችሁትን አሳብ በምርምር በር ላይ አስቀምጡት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳችሁ አሳብ ድጋፍ እንዲሆን የምታጠኑ ከሆነ በፍጹም እውነትን ማግኘት አትችሉም፡፡ እነዚህን አሳቦች በበር ላይ ተውና ዝቅ ባለ ልብ ጌታ የሚላችሁን ለመስማት ሂዱ፡፡ ትሁት የሆነ የእውነት ፈላጊ በክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ከእርሱ ሲማር ቃሉ ማስተዋልን ይሰጠዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት በራሳቸው ማስተዋል እጅግ ጠቢባን ለሆኑ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፡- ለደህንነት ጠቢባን መሆን ከፈለጋችሁ በልባችሁ ትሁታንና የዋሃን ሁኑ፡፡“ቃሉን ከዚህ በፊት በነበራችሁ አስተሳሰብ አታንብቡ፡፡ ነገር ግን አስቀድሞ ከመወሰን ነፃ በሆነ አእምሮ በጥንቃቄ በጸሎት መርምሩ፡፡ ስታነቡ ሳለ ለአእምሮአችሁ የሚያሳምን አሳብ ከመጣላችሁና ከዚህ በፊት ይዛችሁ የኖራችሁት አሳብ ከቃሉ ጋር የማይስማማ ከሆነ ቃሉ ከእናንተ አሳብ ጋር እንዲገጥም ለማድረግ አትሞክሩ፡፡ እናንተ የነበራችሁ አስተሳሰብ ከቃሉ ጋር ገጣሚ እንዲሆን አድርጉ፡፡ ከዚህ በፊት የምታምኑትም ሆነ ስትለማመዱት የኖራችሁት ነገር ማስተዋላችሁን እንዲቆጣጠር አትፍቀዱ፡፡ ከሕጉ ተዓምራትን ለማየት የአእምሮ ዓይኖቻችሁን ክፈቱ፡፡ የተጻፈው ምን እንደሆነ አግኙና እግራችሁን በዘላለማዊው ዓለት ላይ አቁሙ።—Messages to Young People, p. 260.

4. መስመር በመስመር ረቡዕ፣ መጋቢት 23
ሀ. እግዚአብሔር ቃሉን እንዴት ይሰጠናል? እንዴትስ ማጥናት አለብን? ኢሳይያስ 28:9፣ 10 “የእግዚአብሔር ቃል እውነትነት ማስረጃው በራሱ በቃሉ ውስጥ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚፈተቱት ራሳቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው። የእግዚአብሔር ቃል እውነት ጥልቅ ትርጉም ለአእምሯችን የሚገለጠው በመንፈሱ ነው።” —Testimonies for the Church, vol, 8, p. 157.“ትምህርቱን በአድናቆት የሚቀበል መንፈስ ያለው ማናቸውም ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚያነብበት ጊዜ አንዲት ገጽ እንኳ ብትሆን ጠቃሚ ሀሳቦች ሳያገኝ አያልፍም፡፡ ነገር ግን ዋናው ጥቅም የሚገኘው አልፎ አልፎ በሚደረግና ባልተያያዘ ጥናት አይደለም፡፡ ታላቁ የእውነት ሥርዓት ችኩልና ግዴየለሽ በሆነ አንባቢ አማካይነት የሚሰጥ አይደለም፡፡ ብዙዎቹ የወርቅ መዝገቦች ከላይኛው የመሮት ልባስ ሥር በጣም ጠለቅ ብለው ነው የሚገኙት፡፡ ሊደርስባቸው የሚችሉትም ትጋት በተሞላበት ምርምርና ባላቋረጠ ጥረት ነው፡፡ በታላቁ ጥቅል ውስጥ የሚካተቱ እውነቶች ተፈልገው መሰብሰብ አለባቸው፡፡ «ከዚህም ጥቂት ከዝያም ጥቂት፡፡» ኢሳ 28፡10“እንግዲህ እንዲህ እየተፈለጉ ሲሰበሰቡ አንደኛው ከሌላው ጋር ፍፁምና በትክክል የሚስማማ ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ወንጌል የሌሎቹ ደጋፊ፣ እያንዳንዱ ትንቢት የሌላው መግለጫና ማብራሪያ፣ እያንዳንዱ የልማት እውነት ለሌላው ውነት መግለጫ ይሆናል፡፡ የአይሁዶች የኢኮኖሚ አያያዝ ዓይነት በወንጌል ውስጥ ተብራርቷል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እያንዳንዱ መሠታዊ ሀሳብ የራሷ ቦታ አላት፡፡ እያንዳንዷ እውቀትም የራሷ የሆነ ፍሬ አላት፡፡ በንድፍና በአፈፃፀም ላይ ያለው የተሟላ ቅርጽ ባለቤት ለሆነው ደራሲ ምስክርነት ይሰጣሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ግሩም ድንቅ ቅርጽ ፈልፍሎ ሊያንጸው የሚችለው የሰው አእምሮ ሳይሆን ሊያስበው የሚችለው ወሰን የሌለበት አምላክ ብቻ ነው።”—Education, pp. 123, 124. ለ. ሁሉም የመፅሃፍ ቅዱስ አንቀፆች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ማቴዎስ 4፥4፣ ሉቃስ 24፥27 “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትን በተመለከተ ማንም ሰው የሚለንን ተከትለን መሄድ የለብንም። የእግዚአብሔርን ቃል በግላችን ልናጠናው ይገባል። . . . አዕምሮአችን እየበሰለ የሚሄደው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በተመለከተ አንድን ጥቅስ ከሌላው ጥቅስ ጋር እያጣቀስን ፣ መንፈሳዊ ነገርን ከመንፈሳዊ ነገር ጋር እያነፃፀርን በምናጠናበት ጊዜ ነው።“በማስተዋልና በፀሎት ካላጠናነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ እውቀትን ማግኘት አንችልም፡፡ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ግልፅ በመሆናቸው ምንም አያሳስቱም ቢሆንም ትርጉማቸው ሙሉ በሙሉ ግልፅ ያልሆኑ በጥንቃቄ ሊጠኑ የሚገባቸው አንዳንድ ጥቅሶች አሉ፡፡ እነዚህን ጥቅሶች ከሌሎች ጥቅሶች ጋር ማነፃፀር ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ለማድረግ መፀለይና በጥንቃቄ መመርመር ግድ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ከመረመርን ትልቅ ሽልማት እናገኝበታለን፡፡ ልክ አንድ ማዕድን ቆፋሪ በከርሰ ምድር ውስጥ የሚገኘውን የከበረ ድንጋይ በጥልቀት ቆፍሮ እንደሚያወጣ፣ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተደበቁትን እንቁዎች ለማግኘት ተግቶ የሚፈልግ ማንም ሰው ለሕይወቱ እጅግ ጠቃሚ እውነቶችን ያገኛል፡፡ ላይ ላዩን ለሚያነብ ሰው ግን እነዚህ እውነቶች አይታዩትም፡፡ ወደ ልባችን የምናስገባቸውና የምናስቀምጣቸው የእግዚአብሔር ቃሎች ከሕይወት ፏፏቴ እንደሚፈስ ምንጭ ይሆኑልናል።”—Steps to Christ, pp. 89–91.

5. በጥበብ ማጥናት ሐሙስ፣ መጋቢት 24
ሀ. አመለካከታችን እና ምርጫዎቻችን የትንቢቶቹን ትርጉም የመለየት ችሎታችን ላይ እንዴት ተፅዕኖ ያደርጋሉ? ዳንኤል 12:10፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3:1–8 “ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመመርመር የተነሳህበት መንፈስ ከጎንህ የሚቆመውን ረዳት ባሕርይ ይወስናል። ከብርሃን አለም የመጡ መላእክት በትህትና መለኮታዊ መመሪያን ከሚፈልጉ ጋር ይሆናሉ። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት በጎደለዉ ሁኔታ፣ በራስ በመመካት ስሜት፣ ልብ በጭፍን ጥላቻ በተሞላበት ሁኔታ ከተከፈተ፣ ሰይጣን ከጎንህ ይሆናል፣ እናም የእግዚአብሔርን ቃል ጠማማ በሆነ መንገድ በፊታችን ያስቀምጣል።”—Testimonies to Ministers, p. 108.“ሰይጣን ዳንኤልንና የዮሐንስ ራዕይን ማስተዋል አይቻልም ብሎ ብዙ አማኞችን አሳምኖአቸዋል። ነገር ግን እነዚህን ትንቢቶች በማጥናት ስለሚገኘው በረከት የተሰጠው ተስፋ ግልጽ ነው።”—Prophets and Kings, p. 547. ለ. እውነትን በግል የመተግበር አስፈላጊነትን አብራራ። ራዕይ 22:7፤ ማቴዎስ 7:24–27ዮሐንስ 7:17 “ትሑታን ለመማር ፈቃደኛ ስለሆኑ በጌታ ይመራሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅና ለማድረግ ልባዊ ፍላጎት አላቸው። የአዳኙ ቃል ኪዳን “ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል።” ይላል። ዮሐንስ 7:17። በሐዋርያው ያዕቆብም “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።” ብሎ አውጇል። ያዕቆብ 1:5። ነገር ግን የተስፋ ቃሉ ጌታን ሙሉ በሙሉ ለመከተል ፈቃደኛ ለሆኑት ብቻ ነው።”—Patriarchs and Prophets, p. 384.“የእግዚአብሔርን ምሥጢር ማወቅ ከፈለክ፣ በምንም አይነት ሁኔታ የእውነትን ግልጽ ቃል መከተል አለብህ። ታዛዥነትን እንደ መርህ አድርገህ መቀበልና በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ትክክለኛ የሆነውን ነገር መፈለግ አለብህ።—Fundamentals of Christian Education, p. 125.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ፣ መጋቢት 25
1. በእውቀት ረገድ እግዚአብሔር ራሱን ከሌሎች ሁሉ የሚለየው እንዴት ነው? 2. እግዚአብሔር በነቢያት ጽሑፎች ውስጥ ምን ይገልጥልናል፤ ለምን? 3. የእግዚአብሔርን ቃል ስንከፍት ምን ዓይነት እርዳታ ለማግኘት መጸለይ አለብን? 4. በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ ምን ዓይነት ጥረት ማድረግ አለብኝ? 5. በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያገኘሁትን እውነት ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝን?
 <<    >>