Back to top

Sabbath Bible Lessons

የእውነት ውድ ሀብቶች (1) - ከፈጣሪያችን ጋር መወያየት

 <<    >> 
ሰንበት፣ ጥር 20፣ 2015 4ኛ ትምህርት
በመብራቴ ውስጥ ዘይት ስጠኝ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” (ዘካርያስ 4፡6)
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   The Acts of the Apostles, pp. 47–56. 
መቀደሳችን የአብ፣ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ለሚቆራኙት፣ ከእርሱ፣ ከልጁና ከመንፈሱ ጋር በቅዱስ ኅብረት እንደሚያቆማቸዉ እግዚአብሔር የገባው የቃል ኪዳን ፍጻሜ ነው። ዳግመኛ ተወልዳችኋልን? በክርስቶስ የሱስ አዲስ ሰው ሆናችኋልን? ከዚያም እናንተን ወክለው ከሚሠሩት ከሦስቱ ታላላቅ የሰማይ ኃይሎች ጋር ተባበሩ። ይህን በማድረጋችሁ የጽድቅን መመሪያዎች ለዓለም ሁሉ ትገልጣላችሁ።”—The Signs of the Times, June 19, 1901.

1. መንፈስ ቅዱስ ማን ነው? እሁድ ጥር 14
ሀ. መንፈስ ቅዱስ ከመቼ ጀምሮ ነበረ? ዘፍጥረት 1:2፤ መዝሙረ ዳዊት 51:11፤ ዕብራውያን 9፡14 ለ. የእግዚአብሔርን መንፈስ ሰፊ ተፈጥሮ ግለጽና አብራራ። መዝሙር 139:7-12፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 2:9–12፤ 2ኛ ጴጥሮስ 1፡21 በአይሁዶች ጊዜ በኢኮኖሚያቸዉ ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ ተጽእኖ በታላቅ ሁኔታ ታይቷል፣ ነገር ግን በሙሉ አቅም አልነበረም። አምላክ መንፈሱን ለመስጠት የገባውን ቃል እንዲፈጸም ለብዙ ዘመናት ጸሎቶች ሲቀርቡ ነበር፣ እና ከእነዚህ ልባዊ ልመናዎች መካከል አንዳቸውም አልተረሱም።”—My Life Today, p. 36.በኃጢአት ከመዉደቁ በፊት አዳም ከፈጣሪው ጋር ግልጽ የሆነ ግንኙነት ነበረው፤ ነገር ግን ሰው ራሱን ከእግዚአብሔር ስለለየው በመተላለፍ የሰው ልጅ ከዚህ ታላቅ መብት ተቆርጠዉ ቀረ። በዳግም ድነት እቅድ ግን፣ የምድር ነዋሪዎች አሁንም ከሰማይ ጋር የሚገናኙበት መንገድ ተከፍቷል። እግዚአብሔር በመንፈሱ ከሰዎች ጋር ተነጋግሯል፣ እና መለኮታዊ ብርሃኑን ለተመረጡት አገልጋዮቹ በመገለጥ ለአለም ሰጥቷል።”—God’s Amazing Grace, p. 190.

2. እርሱ አካላዊ ተፈጥሮ ያለዉ ነውን? ሰኞ ጥር 15
ሀ. የመንፈስ ቅዱስን ባሕርይ የሚያሳዩ አንዳንድ የባሕርይ መገለጫዎችን ጥቀስ። 1. መንፈስ ያውቃል። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡9-122. መውደድ የሚችል። ሮሜ 15፡303. መግባባት የሚችል። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡144. መግባባት የሚችል ከሆነ መናገር አለበት። 1ኛ ጢሞቴዎስ 4:15. እንደዚሁ ያስተምር ዘንድ ይችላል። 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡136. እርሱ መመስከር የሚችል ነው። ሮሜ 8፡16ክርስቶስ ለተከታዮቹ ከዕርገቱ በኋላ መንፈሱን እንደሚልክላቸው አዎንታዊ ቃል ገባ። “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ [በመለኮት አምላክ]፣ በወልድ [በራሱ አለቃና አዳኝ]፣ በመንፈስ ቅዱስም [ክርስቶስን በመወከል ከሰማይ በተላከው] ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው። እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” አላቸው።”—The Review and Herald, October 26, 1897.እንደ እግዚአብሔር አካል የሆነ አካል የሆነው መንፈስ ቅዱስ በእነዚህ መሠረቶች እየተመላለሰ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናል።መንፈስ ቅዱስ አካል ነው፣ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራልና። ይህ ምስክርነት ሲሰጥ የራሱን ማስረጃ ይይዛል። በዚህ ጊዜ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን እናምናለን እናም እርግጠኞች እንሆናለን።...መንፈስ ቅዱስ ባህሪ አለው፣ይህ ካልሆነ ግን እኛ የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ለመንፈሳችን እና ከመንፈሳችን ጋር መመስከር አይችልም። እርሱ ደግሞ መለኮታዊ አካል መሆን አለበት፣ አለበለዚያ በእግዚአብሔር አእምሮ ውስጥ የተደበቁትን ምስጢሮች ማወቅ አይቻለዉም። በሰዉ ውስጥ ካለው ከራሱ መንፈስ በቀር ስለግለሰቡ የሚያውቅ ሌላ ሰው ማን ነው? እንደዚሁም የእግዚአብሔርን ሃሳብ ከእግዚአብሔር መንፈስ ሌላ ማንም አያዉቅም።”—Evangelism, pp. 616, 617በሰውነት ተሞልቶ፣ ክርስቶስ በሁሉም ቦታ በአካል ሊሆን አልቻለም። ስለዚህ እነርሱን ትቶ ወደ አባቱ ሲሄድና መንፈስ ቅዱስን በምድር ላይ ተተኪ እንዲሆን ሲልክላቸው በአጠቃላይ ለጥቅማቸው ነበር። መንፈስ ቅዱስ ራሱ ከሰው ልጅ ማንነት የተለየ እና ራሱን የቻለ ነው። እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በሁሉም ቦታ እንዳለ፣ በሁሉም ቦታ እንደሚገኝ ራሱን ይገልጻል።”—Manuscript Releases, vol. 14, p. 23.ከመለኮታዊ ሦስቱ ሕያዋን አካላት ውስጥ ሦስትም ሕያዋን ናቸው፡ በነዚህ በሦስቱ ታላላቅ ኃይላት-አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ስም ክርስቶስን በሕያው እምነት የተቀበሉ ይጠመቃሉ፣ እናም የሰማይ ተገዢዎች በክርስቶስ አዲስ ሕይወት ለመኖር በሚያደርጉት ጥረት እነዚህ ኃይላት ታዛዥ ከሆኑት ጋር ይተባበራሉ።”—Evangelism, p. 615.

3. እርሱ አካላዊ ተፈጥሮ ያለዉ ነውን? (የቀጠለ) ማክሰኞ ጥር 16
ሀ. የመንፈስ ቅዱስን ባሕርይ የሚያሳዩ ሌሎች ባሕርያት የትኞቹ ናቸው? 1. በምንጸልይበት ጊዜ ስለ እኛ ይማልዳል። ሮሜ 8:26፣ 272. የልዩ ስጦታዎች አከፋፋይ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡7—113. ኃጢአተኛውንም ወደ ንስሐ ይጋብዛል። ራእይ 22፡17።4. ኃጢአተኛውን ንስሐ እንዲገባ መጋበዙ ብቻ ሳይሆን በእምነትም ያትመዋል ወይም ያጸናዋል።ኤፌሶን 1፡135. እርሱ ስለሚያትመን ወይም ስለሚያጸናን፣ ምን እንዳናደርግ ማስጠንቀቂያ ነው የተሰጠን? ኤፌሶን 4፡306. አካላዊ ማንነት ስለሆነ የሱስ “እርሱ” እና “እሱ” የሚለውን የግል ተውላጠ ስም ለመንፈስ ቅዱስ 24 ጊዜ ተጠቅሞበታል። ከእነዚህ ምሳሌዎች አንዱ ዮሐንስ 14:16፣ 17 ነው።አማላጃችን ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ ስለ ሰው ዘወትር ይማልዳሉ፤ ነገር ግን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈሰሰ ደሙን እንደሚያቀርብ እንደ ክርስቶስ ስለ እኛ አይማልድም። መንፈስ በልባችን ላይ ይሰራል፣ ወደ ጸሎትና ወደ ንስሃ፣ ወደ ዉዳሴና ወደ ምስጋና ልባችን ይስባል። ከከንፈሮቻችን የሚፈሰው ምስጋና መንፈስ ቅዱስ የነፍስን ክሮች በቅዱስ ትውስታ በመነካካት የልብን ዜማ ሲያነቃቃ የሚገኝ ውጤት ነው።The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 6, pp. 1077, 1078.ደስታ በጥቃቅንና በታላላቅ ነገሮች ስብጥር ነዉ። . . . እንደ ክርስቶስ በመሆን የእርሱን ባሕርይ መዉረስ ከፈለግን ነፍስን በየዕለቱ በትንንሽ ነገሮች መቀደስን ማሰልጠን አለብን። የምናባክነዉ ጊዜ የለንም። በሰም ላይ ግልጽ የሆነ የማሕተሙን ምልክት ለማግኘት የሚፈልግ ሰዉ ማኅተሙን በኃይል በሰሙ ላይ አይጫነዉም (አይጥለዉም)፤ ነገር ግን ማህተሙን በጥንቃቄና በጥብቅ ያስቀምጣል፤ ከዚያም ሰሙ የማህተሙን ቅርጽ እስኪያገኝ ድረስ በእርጋታ ይጫነዋል እንጂ። ልክ እንደዚሁ ነዉ ጌታ ከነፍሳችን ጋር የሚገናኘዉ።”—In Heavenly Places, p. 66.መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም እውነተኛ ጸሎት ይመራል። በምልጃዎቼ ሁሉ መንፈስ ስለ እኔና ስለ ቅዱሳን ሁሉ እንደሚማልድ አውቃለሁ። ነገር ግን ምልጃው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ ከፈቃዱ ፈጽሞ የሚቃረን አይደለም። “መንፈስ ደግሞ ድካማችንን ያግዛል። መንፈስም እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔርን አሳብ ያውቃል። ስለዚህ ለታመሙ ወይም ለሌሎች ፍላጎቶች በምናቀርባቸዉ ጸሎቶች ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድ መታከል ይኖርበታል።”—The Signs of the Times, October 3, 1892.

4. ሥራው ምንድን ነው? ረቡዕ ጥር 17
ሀ. የሱስ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ ሊማልድ እንደሄደ፣ መንፈስ ቅዱስ የአዳኙ የግል ተወካይ መሆኑን የሚያሳየው ምንድን ነው? ዮሐንስ 15:26፤ 16:13፣ 14 ለ. የምንወደው ወዳጃችን በሌለበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለብቸኛ ልባችን ምን ይሰጣል? ዮሐንስ 16፡7 ሐ. ወደ መለወጥ እንዴት ይመራናል? ዮሐንስ 16:8 (ህዳግ)፤ ዘካርያስ 4፡6 መንፈስ ቅዱስ የተሰጠዉ ምዕመናንን ለማደስና ለማነቃቃት ሲሆን ያለመንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ የከፈለዉ መስዋዕት ዉጤት አይኖረዉም። የሰይጣን ኃይል ለብዙ ዘመናት እየተጠናከረ የመጣ ሲሆን ሰዎች ለዚህ ሰይጣናዊ ኃይል ያሳዩት የተገዥነት መንፈስ አስገራሚ ነዉ። ኃጢአትን መከላከልና ማሸነፍ የሚቻለዉ ከሶስቱ ስላሴዎች አንዱ በሆነዉና ሙሉ መለኮታዊ ኃይል ባለዉ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ብቻ ነዉ። የዓለም መድህን የሆነዉ ጌታ የሱስ ክርስቶስ የሠራዉን ሁሉ ለዉጤት የሚያበቃዉ መንፈስ ቅዱስ ነዉ። ልብ የሚነጻዉም በመንፈስ ቅዱስ ነዉ። አንድ አማኝ የመለኮታዊ ባሕርይ ተሳታፊ የሚሆነዉ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነዉ። ክርስቶስ መለኮታዊ ኃይል ያለዉን ቅዱስ መንፈስ የሰጠበት ምክንያት ሰዎች በዘር ዉርስም ሆነ በልምድ ያካበቱትን ኃጢአት የመስራት ዝንባሌ ለማሸነፍ እንዲችሉና የእርሱን ባሕርይ በቤተክርስቲያኑ ላይ ለማተም ነዉ።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 707፣ 708በልብ ላይ የተቀረጸው የክርስቶስ ምስል በባህሪ፣ በተግባራዊ ህይወት፣ ከእለት ከእለት ይገለጣል፣ ምክንያቱም እኛ አዳኙን እንወክላለን። መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጣቸዉ ለሚለምኑት ሁሉ እንደሚያገኙ ቃል ገብቷል። ቅዱሳት መጻሕፍትን ስትመረምር፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ የሱስ ክርስቶስ እያመለከተ ከጎንህ ይሆናል።”—General Conference Daily Bulletin, February 15, 1895.ያለ መንፈስ ቅዱስ መገኘትና እርዳታ ቃሉን መስበክ ምንም አይጠቅምም፤ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ብቸኛው የመለኮታዊ እውነት አስተማሪ ነውና። እውነት ሕሊናን የሚያነቃቃው ወይም ሕይወትን የሚለውጥዉ ወደ ልብ ሲገባ በመንፈስ ቅዱስ ከታጀበ ብቻ ነው። አንድ አገልጋይ የእግዚአብሔርን ቃል ደብዳቤ ማቅረብ ይችል ይሆናል፤ እሱ ሁሉንም ትእዛዛቱን እና ተስፋዎቹን ሊያውቅ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ ዘር በሰማይ ጠል ወደ ሰዎች ሕይወት ካልገባ በቀር የወንጌል ዘር መዝራቱ የተሳካ አይሆንም። ያለ እግዚአብሔር መንፈስ ትብብር፣ ምንም ዓይነት ትምህርት፣ ምንም ዓይነት ጥቅም፣ ምንም ያህል ትልቅ ቢሆንም እንኳ አንድን ሰው የብርሃን መስመር ሊያደርገው አይችልም።”—Gospel Workers, p. 284.

5. መንፈስ ቅዱስ ከቤተክርስቲያን ጋር ያለው ግንኙነት ሐሙስ ጥር 18
ሀ. አንድ ሰው የእውነትን ሙሉ እውቀት ማግኘት የሚችለው እንዴት ነው? ዮሐንስ 16፡13 ለ. ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ስለሆነ እኛ እውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን እንድናገኝ ሲረዳን ሚናዉ ምንድን ነው? 1ኛ ጢሞቴዎስ 3:15 ሐ. መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ ሊኖረን በጣም አስፈላጊ ስለሆነ፣ የመንፈስ ቅዱስን ሙሉ ኃይል ለማግኘት ምን ማድረግ አለብን? ሉቃስ 11:9-13 “የክፉው ኃይል አለቃ የሚገታዉ በእግዚአብሔር ኃይል በመለኮት ሦስተኛ አካል በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።”—Evangelism, p. 617.ቤተክርስቲያን በጥቃቅን ነገሮች እስከረካች ድረስ፣ የእግዚአብሔርን ታላቅ ነገር ለመቀበል ብቁ አትሆንም። ነገር ግን ልብ ንጹሕ የሚሆንበት መንገድ ይህ ነውና የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ለምን አንራብምና አንጠማምም? መለኮታዊ ኃይል ከሰው ጥረት ጋር እንዲተባበር ጌታ ያቅዳል። ጌታችን የሱስ ለሁለተኛ ጊዜ ከመምጣቱ በፊት የመንፈስ ቅዱስን የተስፋ ቃል ትርጉም ለክርስቲያን መረዳቱ በጣም አስፈላጊ ነው። ተነጋገሩበት፣ ስለርሱም ጸልዩ፣ ስለ እርሱ ስበኩ። ምክንያቱም ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም ስጦታን ለመስጠት ከሚጓጉት በላይ ጌታ ለእኛ መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት ፈቃደኛ ነውና።”—The Review and Herald, No-vember 15, 1892

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ጥር 19
1. መንፈስ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ዘመን ንቁ ወኪል እንደነበረ እንዴት እናውቃለን? 2. የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ መገለጫዎች ምንድን ናቸው? 3. በክርስቶስ የምልጃ ሥራ እና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 4. በመዳን እቅድ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ አንዳንድ በጣም አስፈላጊ ሚናዎች ምንድን ናቸው? 5. ሰዎች እውነተኛይቱን ቤተ ክርስቲያን እንዲረዱ የመንፈስ ቅዱስ ተሳትፎ ምንድን ነው?
 <<    >>