Back to top

Sabbath Bible Lessons

ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (I)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሰኔ 01፣ 2016 10ኛ ትምህርት
አዲስ ሕይወትን መኖር የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ከእንግዲህ ወዲህ በሥጋ ልትኖሩ በቀረላችሁ ዘመን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሰው ምኞት እንዳትኖሩ” (1ኛ ጴጥሮስ 4፡2)።
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   That I May Know Him, p. 104; Prophets and Kings, pp. 701, 702. 
“በእርግጥ የተቀደሱት የአምላክን ቃል በተከፈተላቸው ፍጥነት ያከብራሉ፣ ይታዘዛሉም ፤ እናም በእያንዳንዱ የትምህርት ነጥብ ላይ እውነት የሆነውን የማወቅ ከፍተኛ ፍላጎት ያሳያሉ።”— Faith and Works, p. 121. “እነዚያ በእውነት የተቀደሱ የእግዚአብሔር ቃል እንደተገለጠላቸው (እንደተከፈተላቸው) ወዲያውኑ በቅዱስ ፍርሐት ያከብሩታል፣ ይታዘዛሉም ፤ እንዲሁም በእያንዳንዱ የእውነት አስትምህሮ ነጥብ እውነት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ ጠንካራ መሻታቸውን ይገልፃሉ።”—Faith and Works, p. 121.

1. ሁልጊዜ የሚያበረታታ ሐሳብ እሁድ ግንቦት 25
ሀ. በብዙ ልዩ ልዩ ፈተናዎችና መከራዎች በምንጠቃበትና በምንሰቃይበት ጊዜ፣ እንድንጠነክርና ድፍረት እንዲኖረን ሐዋሪያው ጴጥሮስ ምንን እናስታውስ ዘንድ ነው የመከረን ? 1ኛ ጴጥሮስ 4:1 ፤ ዕብራዊያን 12:3 “ወደ ክርስቶስ እግር ስር ብዙ ጊዜ ደጋግመን በመምጣት እምነታችንን ማጠናከርና ፍቅራችንን ማቀጣጠል እንችላለን ፤ በዚያም የአዳኛችንን አቻ የለሽ ስቃይ እናሰላስል”—Our High Calling, p. 361.“[1ኛ ጴጥሮስ 4:1 የተጠቀሰ] እንዲህ ብለን እንጠይቅ፡- አዳኛችን በእኛ ሁኔታ ለመድረስ ምን አደረገ? . . . ይህ ጥያቄ በክርስቶስ ምሳሌ መልስ አግኝቷል፡፡ እርሱ ንጉሳዊነቱን ተወ፣ ክብሩንም ጣለ ፤ ሃብቱንም ሰውቷል ፤ እንዲሁም ሰብዓዊውን ዘር ባለበት ደረጃ መገናኘት ይችል ዘንድ መለኮታዊነቱን በሰብዓዊነት ደረበ፡፡ የእርሱ ምሳሌነት ህይወቱን ለኃጢአን አሳልፎ መስዋዕት አድርጎ ማቅረቡን ያሳያል፡፡ ”—Testimonies for the Church, vol. 4, p. 79.“ክርስቶስ እኛ በምንፈተንባቸው በሁሉም ፈተናዎች ተፈትኗል፡፡ በመከራዎችና በፈተናዎች በቁዘማ ራሳቸውን የሚደፉ (የሚቆዝሙ)፣ እንዲሁም በወዳጆቻቸው እንደተከዱ ብለው ብሶት የተሰማቸው እነርሱ፣ ስለ ክርስቶስ ያስቡ ፤ . . . ክርስቶስ በምድረበዳ ብቻውን በማናቸውም ላይ ሊደርሱ ከሚችሉ ፈተናዎች እጅግ የበለጡ ክፉ ፈተናዎችን ተፈትኗል፡፡ማንም ተስፋ በመቁረጥ እጃቸውን አይስጡ ፤ ነገር ግን ለማዳን ተዘርግቶ ያለውን እጅ ለመጨበጥ የሚንቀጠቀጥ የእምነት እጃቸውን ይዘርጉ፡፡ እነዚያ ረዳት አልባ ነፍሳቸውን በክርስቶስ ላይ ያሳርፉ ፤ እርሱ እነርሱ በተፈተኑበት ቦታ ላይ የቆ እርሱ የፈተኑት ርዳት ያውቃልና፡፡”—Manuscript Releases, vol. 21, p. 12.

2. በስቃይ ወደ ድል ነሽነት ሰኞ ግንቦት 26
ሀ. አምላክ ሆን ብሎ በመከራና በስቃይ እንድናልፍ ለምን ይፈቅዳል? 1ኛ ጴጥሮስ 4፡1 (የመጨረሻው ክፍል)። 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡7-10 “. . . አዳኛችን በክብሩ ደማቅ የብርሃን ጅረት ራሱን ለጳውሎስ በገለፀለት ጊዜ፣ እርሱ ይሰድበው በነበረው በእርሱ መገኘት ክብር አይኑ ታውሮ ነበር ፤ ነገር ግን መንፈሳዊ አይኑ ይገለጥለት ዘንድ፣ ግንዛቤውን ካደነዘበት መደነዝ (ድንዛዜ) ይነቃ ዘንድ የስጋዊ አይኑ መታወር አስፈላጊ ነበር።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 6, p. 1058.“እኔን ያስጨነቀኝ አንድ ታላቅ ፍርሃት ቢኖር፣ የግዳጅ (የተግባር) ጥሪን ታዘዤ፣ በልዑል አምላክ ዘንድ በራዕይና በመገለጥ የተቸራት አድርጌ ራሴን ለሰዎች በመግለጽ፣ ምናልባትም ኃጢአታዊ ለተሞላ ሙገሳ (ኩራት) እጅ ልሰጥ እችላለሁ ነው፤ . . . በራሴም ላይ የእግዚአብሔርን ቁጣ አወርዳለሁ ፤ በመጨረሻም የገዛ ራሴን ህይወት ላጣ እችላለሁ የሚል ነው። . . .“ጌታ ያሳየኝ ለመግለጽ ወደ ህዝቡ መሄድና መግለጽ ካለብኝ፣ ከከንቱ ሙገሳ እጠበቅ ዘንድ አሁን ተማጽዕኖየን ማቅረብ ይኖርብኛል፡፡ መልአኩም እንዲህ አለ፡- ‘ጸሎትሽ ተደማጭነት አግኝቷል፤ መልስም ይሰጥሻል። ይህ የምትፈሪው ክፉ ነገር ስጋት ከፈጠረብሽ፣ ያድንሽ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ ይዘረጋልሻል ፤ በስቃይ ወደ ራሱ ይስብሻል፣ ትህትናሽንም ይጠብቃል። የገለጽኩልሽን መልእክት በታማኝነት አስተላልፊ ፤ እስከ ፍጻሜም በጽናት ታገሺ፣ የሕይወትንም ዛፍ ፍሬ ትበያለሽ፣ የሕይወትንም ውኃ ትጠጫለሽ። ”—Christian Experience and Teachings of Ellen G. White, pp. 67, 68. ለ. በኃጢአት የሥጋ ምኞት የሚፈተን እንኳ ቢሆንም፣ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ግብ ምን መሆን አለበት? 1 ጴጥሮስ 4:2፣ 15፤ ኤፌሶን 4:17፣ 22–24 “ብዙዎች ከሚያስቡት በላይ እግዚአብሔር ከተከታዮቹ ብዙ ይጠብቃል (ይሻል)። የሰማይ (ወደ ሰማይ የመግባት) ተስፋችንን በውሸት መሠረት ላይ ካልገነባን በቀር መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚነበበው አድርገን መቀበል እና ጌታ ማለት እንደተናገረው ማለት መሆኑን ማመን ይኖርብናል። እንፈጽመው ዘንድ፣ ጸጋውን ባልሰጠን ነገር ላይ፣ ምንም ነገር አይፈልግብንም። በቃሉ እንደርስበት ዘንድ ከፊታችን ወደተቀመጠልን ደረጃ መድረስ ከተሳነን በእግዚአብሔር ቀን ይቅርታ አይኖረንም።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 171.“መለወጥ (ልባዊ ለውጥ) ብዙዎች የማያደንቁት ስራ ነው። ምድራዊውን፣ ኃጢአት ወዳዱን፣ አእምሮ የመለወጥ ለውጦ በቃላት ሊነገር የማይችለውን የክርስቶስን ፍቅር እንዲያስተውል ማድረግ ቀላል ነገር አይደለም። . . . አንድ ነፍስ እነዚህን ነገሮች ማስተዋል ሲጀምር፣ የቀድሞ ህይወቱ አስደንጋጭ እና የሚጠላው ሆኖ ይታየዋል። ኃጢአትን ይጠላል። . . . ቀድሞ ደስታ ያገኝባቸው የነበሩ መደሰቻዎቹን (መዝናኛዎቹን) እርግፍ አድርጎ ይተዋቸዋል ፤ አሁን አዲስ አእምሮ፣ አዲስ ፍቅር፣ አዲስ ፍላጎት፣ አዲስ ፈቃድ አለው።”—The Faith I Live By, p. 139.

3. መሸነፍ ያለባቸው አንዳንድ ልማዶች ማክሰኞ ግንቦት 27
ሀ. ጴጥሮስ የትኞቹን የኃጢአት ምኞቶችን ነው የተለመዱና ለማሸነፍም አስቸጋሪ መሆናቸውን የገለፃቸው? 1ኛ ጴጥሮስ 4፡3 ኃፍረተቢስነት፣ ፍትዎት፡- “ይህ የተበላሸ ዓለም የሚሰጠው ነፃነት ለክርስቶስ ተከታዮች መመዘኛ ሊሆን አይገባም። እነዚህ ጊዜ አመጣሽ ትርኢቶች ለዘላለም ገጣሚ በሚሆኑ ክርስትያናት መካከል መከሰት ለባቸውም። . . . ኃፍረተቢስነት፣ ብክለት፣ ዝሙት በእነዚያ እውነትን በማያውቁ መካከል ተንሰርፍቶ ከታየ ፤ . . . ይህን ስር የሰደደ እርኩሰት ገሃድ በማውጣት ክርስቶስን እንከተላለን የሚለው ወገን . . . ይህ የረከሰው ምኞት ከተቆጣጠራቸው ሰዎች ተለይተው ጉልህ በሆነ ልዩነት መቆማቸው እንዴት አስፈላጊ ነው! ”—The Adventist Home, p. 329.የወይን ጠጅ ስካር (Excess of wine)፡- “ማንኛውም ሰው ራስን ካለመግዛት ኃይል ደህንነቱ የተጠበቀ የሚሆንበት ብቸኛው መንገድ ሙሉ በሙሉ ከወይን፣ ከቢራ እንዲሁም ከጠንካራ መጠጦች መታቀብ ነው። . . . ክብር የሚያገኘውና ስሙም ከሕይወት መጽሐፍ ሊፋቅ የማይችለው አሸናፊ መሆን የቻለ ሰው ብቻ ነው።”—Child Guidance, pp. 401, 402.የቡረቃ ግብዣዎች (Revellings, banquetings):- “በባህሪይ እና በሃይማኖታዊ ተሞክሯቸው ከላይ ከላይ (ስር ያልያዙ የታይታ) የታወቁ ክርስቲያናት ፈታኙ እንደ መጫወቻ አሻንጉሊቶቹ መጠቀሚያ ያደርጋቸዋል። ይህ ወገን ለደስታ ወይም ለስፖርት ቡረቃዎች (መዝናዎች) ዝግጁ ነው ፤ በተጽእኖአቸውም ሌሎችንም ይስባሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያናት ለመሆን የሚጥሩሩ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ግብዣቸውን ለመካፈል ይታለላሉ፡፡ . . . እነዚህ መዝናኛዎች ነፍሳት የክርስቶስ ጽድቅ የሆነውን ነጩን የባህርይ ልብስ እንዳይቀበሉ ነፍሳትን ለማገድ የተዘጋጁ በእርግጥም የሰይጣን ግብዣዎች መሆናቸውን ማስተዋል አይችሉም። ክርስቲያናት እንደሚያደርጉት ለማድረግ የትኛው ትክክል እንደሆነ ግራ ይጋባሉ፡፡”—The Adventist Home, p. 518.“የጤና ተሐድሶን ተግባራዊ ያደረጉ ብዙዎቹ ሁሉም ነገር በአሳዛኝ ሁኔታ አዝረክርከው ትተውታል፣ ነገር ግን ያንን ቢከተሉት. . . እስኪያስደስታቸው ድረስ መብላት ይችላሉ? በገበታቸው ዙሪያ ተቀምጠው ለምግብ አምሮት ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት ያለ መጠን አግበስብሰው ይመገባሉ። . . .“እናስ ከመጠን በላይ መብላት በጨጓራችን ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል? ጨጓራ ደካማ ይሆናል፣ የምግብ መፍጫ አካላት ይዳከማሉ ፣ ከዚያም ውጠቱ በሽታ ከመላ ኮተቱ እና ክፋቱ ጋር ተግተልትሎ ይመጣል ። . . .“ለራሳቸው መጥፎ ስሜት ይሰማቸዋል፣ ልጆቻቸውም እንዲሁ በጣም የከፉ (መጥፎ) ይመስሏቸዋል። ልጆቻቸውን በእርጋታ ሊያግሯቸው አይችሉም ፤ ወይም የተለየ ፀጋ ካላገኙ በቀር በቤተሰቦቻቸው ውስጥ በእርጋታ መምራት አይችሉም፡፡ በዙሪያቸው ያለው በሙሉ እነርሱን ባጠቃቸው በሽታ ተጎጂ ይሆናል ፤ ሁሉም የእነርሱ ደካማነት ባስከተለው መዘዝ ተጎጂ መሆን የግድ ይለዋል። . . .“የጤና ተሐድሶ አራማጆች እንኳ ሳይቀሩ በሚወስዱት የምግብ መጠን ሊሳሳቱ ይችላሉ።”—Counsels on Diet and Foods, pp. 135, 136.አስጸያፊ የጣዖት አምልኮዎች፡- “እነርሱ ከአረማውያን ልማዶች ጋር መስማማት የለባቸውም፤ እንዲሁም አስጸያፊ የጣዖቶቻቸውን ቅርፃቅርፆች መጠበቅ የለባቸውም። ምንም እንኳ ቁሳቁሶቹ እጅግ የከበሩ እቃዎች ቢሆኑም፣ ወይም የእጅ ስራዎቻቸውም እፁብ ድንቅ ቢሆኑም ለአረማውያን አምልኮ የመቡ ነገሮች በሙሉ መውደም አለባቸው፡፡”—The Signs of the Times, January 13, 1881.

4. በሁሉም ቦታ እና ሁልጊዜ ክርስቶስን ውደድ ረቡዕ ግንቦት 28
ሀ. እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመኖር እስከመረጥን ድረስ በዚህ ሕይወት የሚያጋጥመን በጣም የተለመደው ውጤት ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 4:4፣ 12 “የፍጻሜው ዘመን እያጠረ ሲሄድ ሰይጣን . . . ‘ቅጥሩን በሚገነቡ’ ሰዎች ላይ ሊያላግጥባቸውና የስብ ናዳ ሊያወርድባቸው ሰብዓዊ ወኪሎችን ይጠቀማል። ”—Prophets and Kings, p. 659.“ኃጢአተኞች መለኮታዊውን ሕግ በመርገጣቸው ስለሚደርስባቸው አደጋ “[የእግዚአብሔር ሰዎች] እያነቡ ያስጠነቅቋቸዋል፤ እንዲሁም በቃላት ሊነገር በማይቻል ሀዘን በንስሃ በጌታ ፊት ራሳቸውን ያዋርዳሉ። ክፉዎች በሐዘናቸው ላይ ያፌዛሉ፣ በሚያቀርቡላቸው ልባዊ ተማጽዕኖም ይቃለዱበታል፡፡ ይሁን እንጂ በአምላክ ሕዝቦች ዘንድ የሚታየው ልባዊ ሐዘን እና ራስን ማዋረድ በኃጢአት ምክንያት ጠፍቶ ጥንካሬና የባህርይ ክቡርነት ለመቀዳጀታቸው (ለማግኘታቸው) የማያሻማ ማስረጃ ነው።”—Ibid., p. 590. ለ. እያንዳንዱ ክርስቲያን ሲዘበትበትና ሲናቅ ምንድን ነው ማስታወስ ያለበት? 1ኛ ጴጥሮስ 4:5፣ 13–16፤ 2ኛ ጴጥሮስ 2፡12 ሐ. በእኛ ላይ የሚያላግጡ ሰዎች ሲበለጽጉ—እንዲሁም ወይም አንድ መጥፎ ነገር ሲደርስባቸው ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? በእኛ ላይ ክፉ ለበያደርሱብን ሁሉ ላይስ? 1ኛ ጴጥሮስ 4:17–19፤ ማቴዎስ 5፡44 መ. ለሚነቅፉንና መላገጫ በሚያደርጉን ሰዎች ላይ በልባችን ልንይዘው የሚገባን ነገር ምንድን ነው—ወደዚህ የአዕምሮ አስተሳሰብ ደረጃ መድረስ የምንችለውስ እንዴት ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 4:6፤ ኤፌሶን 2:3-5፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2:24-26 “በእውነት ላይ ጭፍን ጥላቻ ያለባቸውን ሰዎች ስታገናኟቸው፣ የራሳችሁን የተለየ አመለካከት ይቀበሉ ዘንድ በግድ አትጫኑባቸው። በመጀመሪያ ከእነርሱ ጋር መስማማት የምትችሉባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ተነጋገሩ። ከእነርሱ ጋር በጸሎት በርከክ በሉ። . . . እናንተና እነሱም ከሰማይ ጋር ጥብቅ በሆነ ትስስር ትተሳሰራላችሁ ፤ ጭፍን ጥላቻም ይዳከማል፣ ከዚያም ወደ ልብ ለመድረስ ቀላል ይሆናል።”—Evangelism, p. 446.

5. በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ማስታወስ ሐሙስ ግንቦት 29
ሀ. ባለፀጋዎች፣ ጤናማና ደስተኛ ብንሆን ወይም ህመምተኞች፣ ብስጩዎች ወይም በእጦት የተሰቃየን ብንሆንም ምንጊዜም ማስታወስ ያለብን ነገር ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 4:7 “ከጥርጣሬያችን እና ከፍርሃታችን ጋር ብንማከር፣ ወይም ያለእምነት በትክክል ልናያቸው የማንችላቸውን ነገሮች ሁሉ ለመፍታት ብንታገል፣ ጭንቀታችን እየጨመረና እየጠነከረ ከመሄድ ውጭ ሌላ የሚሆን ነገር አይኖርም፡፡ ነገር ግን ራሳችንን ረዳተቢስ እንደሆንና ድጋፍ እንደሚያስፈልገን በመረዳት ራሳችንን በማዋረድ፣ እውቀቱ ወሰን ለሌለው በፍጥረተ ዓለም ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ለሚያየውና በፈቃዱና በቃሉ ሁሉን ለሚያስተዳድረው ለእግዚአብሔር በእምነት የሚያስፈልገንን ነገር ብናቀርበው ጩኸታችንን ሊሰማን ይችላል ፤ ደግሞም ይሰማናል ፤ በልባችን ላይ ብርሀን ያበራል። ልባዊ በሆነ ፀሎት አማካኝነት ወሰን የለሽ ከሆነው መለኮታዊ አእምሮ ጋር እንገናኛለን። የአዳኛችን ፊት በርኅራኄ እና በፍቅር ወደ እኛ የዞረ ላይመስለን ይችላል ፤ ነገር ግን በሐዘኔታና በፍቅር እጆቹን በእኛ ላይ ጣል አድርጎአል፡፡. . .“የምንፈልገውን /የሚያሻንን ጠይቀን ለመቀበል በጸሎት መጽናት ቀድመ መስፈርት ነው። በእምነት እና በተሞክሮ ማደግ ከፈለግን ሁልጊዜ መጸለይ ያስፈልገናል። . . . ጴጥሮስ አማኞችን ‘በጸሎት ንቁ፣ ትጉም’ በማለት አሳስቧቸዋል። 1ኛ ጴጥሮስ 4፡7 . . . ሳያቋርጡ መጸለይ ማለት ከእግዚአብሔር ዘንድ ሕይወት ወደ ሕይወታችን እንዲፈስና ከእኛም ሕይወት ደግሞ ንጽህና እና ቅድስና ወደ እርሱ መልሶ እንዲፈስ ከአምላክ ጋር ነፍስን ማቆራኘት ማለት ነው፡፡”—Steps to Christ, pp. 96–98.“የሐዋርያው መልዕክቶች በእያንዳንዱ ዘመን ለሚኖሩ አማኞች መመሪያ ይሆናቸው ዘንድ ተጽፈው ተቀምጠዋል፤ እናም ‘የነገሮች ሁሉ ፍጻሜ በደጅ በቀረበበት’ ጊዜ ለሚኖሩ ለእነርሱ የተለየ አስፈላጊነት አላቸው። የእርሱ ተማጽዕኖዎችና ማስጠንቀቂያዎች፣ የእምነትና የማደፋፈሪያ ቃላቶች ሁሉ እያንዳንዱ ነፍስ ዘንድ ተፈላጊም አስፈላጊም ናቸው።”The Acts of the Apostles, p. 518.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ግንቦት 30
1. በመከራና በጭንቀት ሳለሁ በእምነት 'ወዴት መሄድ አለብኝ' እና ለምን? 2. እግዚአብሔር በመከራና በመከራ ውስጥ የሚመራን ለምን ዓላማ ነው? 3. አሁንም ለቀደመው፣ ለዓለማዊ ምኞቴ ባሪያ ነኝ? አዎ ከሆነ፣ ሙሉ በሙሉ መሰጠቴን ለምን ያህል ጊዜ ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ እቅድ አለኝ? 4. ለሚሳለቁብኝ ሰዎች ያለኝ አመለካከት ምን መሆን አለብኝ? 5. ማድረግ የሚገባኝን ያህል የተጠናከረ የጸሎት ሕይወት እንዳላገኝ የሚከለክለኝ ምን ሊሆን ይችላል?
 <<    >>