Back to top

Sabbath Bible Lessons

ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (I)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 3ኛ ትምህርት
ታዛዥ የእግዚአብሔር ልጆች መታሰቢያ ጥቅስ፡- “ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደደ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።” (1ኛ ጴጥሮስ 1፡22)።
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Steps to Christ, pp. 43–48. 
“ክርስቶስን በእምነት ስንይዝ፣ ሥራችን ገና ተጀመረ። እያንዳንዱ ሰው በጠንካራ ትግል ማሸነፍ ያለባቸው ብልሹና ኃጢአተኛ ልማዶች አሉት። እያንዳንዱ ነፍስ የእምነትን ዉጊያ መዋጋት ይጠበቅባታል።”— Selected Messages, bk. 2, p. 20.

1. ሃሳቦቻችንን በጥንቃቄ መምረጥ እሁድ ሚያዝያ 06
ሀ. እንደ እግዚአብሔር ቃል እውነተኛ መታዘዝ ይጀምራል? 1ኛ ጴጥሮስ 1: 13፣ 14፤ ሮሜ 12፡2 “እውነተኛ ተሐድሶ ሁሉ የሚጀምረው ነፍስን በማጽዳት ነው። በሕይወታችን ውስጥ ለውጥ የሚመጣው በሚያድስ በመንፈስ ቅዱስ ሃይል በመታጠብና አእምሮን በማደስ ነው።“ክርስቶስን በመመልከታችን ተለወጥን። አእምሮ በጊዜያዊ ነገሮች ላይ ያለማቋረጥ የሚያሰላስል ከሆነ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ቀልቡን የሚስቡ ይሆኑና፣ ባህሪን ያበላሻሉ፣ ስለዚህም የእግዚአብሔር ክብር አይታይም እንዲሁም ይረሳል። ከሰማያዊ ነገሮች ጋር ለመነጋገር ሊደርሱባቸው የሚያስችሉ የነበሩ እድሎች ችላ ይባላሉ። መንፈሳዊ ሕይወትም ይሞታል።”— Sons and Daughters of God, p. 105. ለ. የሰው ልጅ አስተሳሰቦች እና ፍላጎቶች ተፈጥሯዊ አካሄድ ወዴት ነው የሚሄደው? ዘፍጥረት 6ኤርምያስ 17፡9 ሐ. አስተሳሰባችን እና ፍላጎታችን ንጹህ እንዳልሆኑ ከተገነዘብን ምን እናድርግ? የሐዋርያት ሥራ 8፡22

2. የአስተሳሰብ ጨዋነት ሰኞ ሚያዝያ 07
ሀ. ተግባራዊ በሆነ መንገድ 'የልባችንን ወገብ መታጠቅ' የምንችለው እንዴት ነው? ዘፍጥረት 4፡7 “በሰይጣን ሽንገላ እንዳይወድቁ የነፍሳቸዉን አዳራሽ በሚገባ መጠበቅ አለባቸው። ርኩስ አስተሳሰቦችን የሚያበረታቱ ማንኛዉም ነገሮች ከማንበብ፣ ከማየት ወይም ከመስማት መራቅ አለባቸው። አእምሮ የነፍስ ጠላት በሚያቀርበው እያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በዘፈቀደ እንዲቀመጥ መተው የለበትም። ልብ በታማኝነት መገለጥ አለበት፣ ወይም ዉጫዊ ክፋቶች በውስጣቸው ያሉትን ክፋት ያነቃቁና ነፍስ በጨለማ ውስጥ ትቅበዘበዛለች። ጴጥሮስ ‘የልባችሁን ወገብ ታጥቃችሁ በመጠን ኑሩ’ ሲል ጽፏል።”—The Acts of the Apostles, p. 518. ለ. የልባችንን ሐሳብ መቆጣጠር በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ምሳሌ 23:7 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ 24፡9 (የመጀመሪያ ክፍል)። “ሐሳቦች ለእግዚአብሔር ፈቃድ፣ እንዲሁም ስሜቶች በምክንያትዊነትና በሃይማኖት ቁጥጥር ሥር መገዛት አለባቸው። ሀሳባችን ምንም አይነት ገደብና ተግሣጽ ሳይደረግ አመጽ እንድናደርግና የራሳችን መንገድ እንድንከተል አልተሰጠንም። ሀሳቦቹ የተሳሳቱ ከሆኑ ስሜቶቹ የተሳሳቱ ይሆናሉ፤ እና ሀሳቦችና ስሜቶች ሲዋሃዱ የሞራል ባህሪን ይፈጥራሉ። እንደ ክርስቲያኖች ሀሳባችንንና ስሜታችንን መግታት እንደማይጠበቅብን ስናስብ፣ በክፉ መላእክት ተጽዕኖ ሥር እንሆናለን፣ እናም እነሱ እንዲገቡና እንዲቆጣጠሩን እንጋብዛለን። ለምናስበው ነገር ከተገዛንና ሀሳቦቻችን በጥርጣሬ፣ በአለማመንና በማመንታት መንገድ እንዲሄዱ ከፈቀድን ደስተኞች አንሆንም እንዲሁም ህይወታችን ከንቱ ይሆናል (ይከሽፋል)።”—The Review and Herald, April 21, 1885. ሐ. ሐዋርያው ጴጥሮስ በመጠን እንድንኖርና ጸጋን ለማግኘት 'እስከ መጨረሻው ተስፋ እንድናደርግ' የሚለምነን ለምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 1፡13 ከ5፡8 ጋር ሲወዳደር። “ሀሳብህን በታማኝነት ጠብቅ። ወደ ልብህ የሚወስዱትን እያንዳንዱን መንገድ ምሽጉን በደንብ አጠናክር። የሰይጣንን አካሄድ መቃወም አለብህ። ሌላ በኩል ቸል ተብለዉ በአንድ በኩል ብቻ ነቅቶ መጠበቅ አይጠቅምም። . . . ከፊታችን ልንጋፈጣቸው የሚገቡ አደጋዎች አሉ፣ እንዲሁም ደህንነታችን በእግዚአብሔር ብቻ ነውና።”—This Day With God, p. 174.

3. ከቀድሞ ምኞት ሽሹ እና ቅዱሳን ሁኑ ማክሰኞ ሚያዝያ 08
ሀ. በየትኞቹ የሕይወታችን ዘርፎች ውስጥ ቅዱሳን ለመሆን ከመጠን በላይ የመጠን አእምሮ ይኑረን? 1ኛ ጴጥሮስ 1:14፣ 15፤ 4:2፣ 3 “አሁን ለጊዜው የምንከባከቡት ኃጢአቶች በቀላሉ ሊተዉ (ሊቀሩ) እንደሚችሉ በማሰብ ማንም አይዘናጋ። ይህ እንደዚያ አይደለም። የምታንከባክቡት የትኛዉም ኃጢአት ሁሉ ባህሪን ያዳክማል፣ የሃጢአት ልማድን ያጠናክራል፤ እንዲሁም የአካል፣ የአዕምሮና የሞራል ዝቅጠት ደግሞ ውጤቱ ነው። ለበደላችሁት በደል ንስሐ ትገቡ፣ እግሮቻችሁንም በቀና መንገድ ትመሩ ይሆናል። ነገር ግን በአዕምሯችሁ ላይ የሚቀረዉ ክፉ ሃሳብና ከክፉ ጋር የነበራችሁ ቁርኝት ምክንያት ትክክልና ስህተት የሆነውን ለመለየት ያስቸግራችህዋል። በተፈጠሩት የተሳሳቱ ልማዶች አማካኝነት ሰይጣን ደጋግሞ ያጠቃችሁዋል።”— Christ’s Object Lessons, p. 281. ለ. ቅዱሳን እንድንሆን ዘወትር ማሳሰቢያ ቢሰጠንም (1ኛ ጴጥሮስ 1:15፣ 16)—ይህም በሆነ መንገድ በራሳችን ጥረት ሊገኝ የሚችል ሊመስለን ይችላል—በእርግጥ ቅዱስ ለመሆን የምንችለው በምን መንገድ ነው? ዘሌዋውያን 20:7፣ 8፤ ፊልጵስዩስ 2:13ቲቶ 3፡5 ምንም እንኳን በራሳችን ምንም መልካም ወይም በጎ ነገር ባይኖረንም በታላቅ የእግዚአብሔር ቸርነትና ፍቅሩ የእርሱ መልካምነት የራሳችን እንድሆን ተደርገናል። ማድረግ የምንችለውን መልካም ነገር ሁሉ ብንሰራም እንኳን፣ አሁንም የማንጠቅም አገልጋዮች ነን። . . . የፈጸምነዉ ተግባር ሁሉ በክርስቶስ ጸጋ ብቻ ተፈጽሟል፣ እንጂ በሥራችን መሠረት ቢሆን ከእግዚአብሔር የምናገኘዉ ምንም ሽልማት አይኖረንም።”—The Review and Herald, June 27, 1893. ሐ. በመጠን እንድንኖር ከተማጸነ በኋላ ሐዋርያው ስለሚመጣው ፍርድ ለምን ያስታውሰናል? 1ኛ ጴጥሮስ 1:17፤ ቆላስይስ 3:5፣ 6 “የእያንዳንዱ ሰው ሥራ በእግዚአብሔር ፊት ይገመገማል እንዲሁም በታማኝነት ወይም ታማኝ ባለመሆን ይመዘገባል። በሰማይ መጽሐፍት ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ስም በአስደናቂ ሁኔታ እያንዳንዱ የተሳሳተ ቃል፣ ራስ ወዳድነት ድርጊት፣ የትኛውም ያልተፈፀመ ግዴታ፣ እና እያንዳንዱ ሚስጥራዊ ኃጢአት ተጽፏል። ችላ የተባሉ ከሰማይ የተላከ ማስጠንቀቂያ ወይም ተግሣጽ፣ የሚባክኑ ጊዜዎች፣ ያልተሻሻሉ አጋጣሚዎች፣ ለበጎም ሆነ ለክፉ የሚደረጉት ተፅዕኖዎች፣ ከፍተኛ ውጤቶቹ ያሉት ሁሉም በመዝገቡ መዘግበው መልአክት ይዘዉታል።”— The Great Controversy, p. 482.

4. በክርስቶስ የተዋጀ ረቡዕ ሚያዝያ 09
ሀ. ጴጥሮስ የቀድሞ ምኞቶችን ለማሸነፍ ጥረት ማድረጋችን አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም የሚሆንበት ጥሩ ምክንያት ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 1: 4፣ 18፣ 19፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡18-20 “ሁሉም ሰዎች በዚህ ወደር በሌለው ዋጋ ተገዝተዋል። የሰማይን ሀብት ሁሉ ወደዚህ ዓለም በማፍሰስ፣ ሰማያትን ሁሉ በክርስቶስ በመስጠት፣ እግዚአብሔር የእያንዳንዱን ሰው ፈቃድ፣ ፍቅር፣ አእምሮ፣ ነፍስ፣ ገዝቷል። አማኞችም ሆኑ የማያምኑ ሰዎች ሁሉ የጌታ ንብረት ናቸው። ሁሉም የተጠሩት እሱን እንዲያገለግሉት ነው፤ እናም ይህን የይገባኛል ጥያቄ መመለሳቸዉ ወይም አለመመለሳቸውን፣ ሁሉም በታላቁ የፍርድ ቀን መልስ እንዲሰጡ ይጠበቅባቸዋል።”— Christ’s Object Lessons, p. 326. ለ. የመዳን እቅድ መቼ ነው የተቋቋመው? 2ኛ ጢሞቴዎስ 1:፥ 9 “እግዚአብሔር ዓለም ከመፈጠሩ በፊትም ቢሆን የወደፊቱን ጊዜ ያውቃል። አላማውን ከሁኔታዎች ጋር እንዲስማማ አላደረገም፣ ነገር ግን ነገሮች እንዲዳብሩና በራሳቸዉ እንዲሰሩ ፈቅዷል። የነገሮችን የተወሰነ ሁኔታ ላይ ለማምጣት (ለመፈጸም) አላደረገም፣ ነገር ግን እንዲህ አይነት ሁኔታ እንደሚኖር ያውቅ ነበር። ከየትኛውም የሰማያት ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ ካላቸዉ እንኳን ይህ ውድቀት ሲሆን መደረግ ያለበት እቅድ - ከዘመናት ጀምሮ የተደበቀ ምስጢር ነው። አምላክ ለወደቁት የሰው ልጆች የሠራውን ሥራ ለመፈጸም በዘላለማዊ ዓላማም መስዋዕት አዘጋጀ።”— The Signs of the Times, March 25, 1897. ሐ. በአምላክ ላይ ያለው እምነት ከየት ይመጣል? ሮሜ 10:17፤ 1ኛ ጴጥሮስ 1፡21 “ማንም ሰው እምነትን መፍጠር አይችልም። በሰው አእምሮ ላይ የሚሰራ እና የሚያበራ መንፈስ፣ በእግዚአብሔር ላይ እምነትን ይፈጥራል። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እምነት የእግዚአብሔር ስጦታ እንደሆነ ተገልጿል፣ ለመዳን ኃይል ያለው፣ እንደተሰወረ ሀብት እውነትን በሚፈልጉ ሰዎች ልብ እንደሚያበራ ተገልጿል። የእግዚአብሔር መንፈስ እውነትን በልብ ላይ ይዘራል። ወንጌል ለማዳን የእግዚአብሔር ኃይል ተብሎ ተጠርቷል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ብቻ ነዉ እውነትን፣ ነፍስን የሚቀድስ ኃይል ሊያደርግ ይችላል።”— The SDA Bible Commentary [E. G. White Com- ments], vol. 7, p. 940.

5. የመታዘዝ አክሊል ሐሙስ ሚያዝያ 10
ሀ. ሐዋርያው የቀደመውን ምኞታቸዉን እንዲዋጉ አማኞችን ከተማጸናቸው በኋላ፣ ፍጹም ለመታዘዛችን ዓላማ ምን ግብ አስቀምጧል? 1ኛ ጴጥሮስ 1፡22 “ጴጥሮስም እንዲህ አለ፡- በንጹሕ ልብ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ። የእግዚአብሔር ቃል - እውነት - ጌታ መንፈሱንና ኃይሉን የሚገልጥበት መንገድ ነው። ቃሉን የሚታዘዝ የሚፈለገውን ፍሬ - ግብዝነት የሌለበት የወንድማማቾች ፍቅር - ያፈራል። ይህ ፍቅር ከሰማይ የተወለደ ሲሆን ከፍ ወደሉ ዝንባሌዎችና ከራስ ወዳድነት ነፃ ወደሆኑ ድርጊቶች ያሳድጋል።”— The Acts of the Apostles, p. 519“ለእውነት እየታዘዛችሁ በመንፈስ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፥ ግብዝነትም ለሌለው የወንድማማች መዋደድ። . . . እንግዲያው ሥራውን የሚቆጣጠሩት ሁሉ፣ በጥናት ላይ ያሉና በቢሮ ውስጥ የሚሠሩ ሁሉ ከሁሉ የላቀውን የአምላክ ቃል መሠረታዊ ሥርዓቶችን በታማኝነት ጠብቀው መተግበራቸው ምንኛ አስፈላጊ ነው።”— The Publishing Ministry, p. 297.“ፍቅርን በልባችን ልናከብረው ይገባል። በወንድሞቻችን ላይ ክፉ ለማሰብ ዝግጁ መሆን የለብንም። እነሱ በሚሠሩት ወይም በሚናገሩት ላይ ጥቅትም ቢሆን ልንረዳቸዉ ይገባል። የመጽሐፍ ቅዱሱ ክርስቲያኖች መሆን አለብን። (1ኛ ጴጥሮስ 1:22)። . . .“የአስተሳሰባችንን እና ስሜታችንን፣ ቁጣችንን፣ አላማችንን፣ ቃሎቻችንን እና ድርጊቶቻችንን ባህሪይ መመርመር አለብን። . . . በአምላክ ቃል ብርሃን ልባችንን በትጋት እስካጣራን ድረስ ለራሳችን በፍቅር ሊኖረን ከሚገባው በላይ የተሻለ አመለካከት እንዲኖረን ያደርገናል።”— his Day With God, p. 83.“በእራሳችን ልምድ አንዳንድ እጥረት ባይኖር ኖሮ ወንድሞቻችንን ያን ያህል አንጠራጠርም ነበር። ህሊናው ራሱን የሚፈርድበት ሰው ነው ወዲያው ፍርድ የሚሰጠው። ሁሉም ሰዉ እራሱን ይፍራ ይንቀጠቀጥ። . . . ለእውነት እየታዘዛችሁ በመንፈስ ግብዝነት ለሌለው ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችኋልና። ” — The Review and Herald, October 29, 1901.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ሚያዝያ 11
1. ኃጢአተኛ ወይም ርኩስ ሐሳብ ወደ አእምሮዬ ከገባ ምን ማድረግ አለብኝ? 2. የፍላጎቴን ባህሪይ በተመለከተ ልቤን ምን ያህል ጊዜ መመርመር አለብኝ? 3. በሕይወቴ ውስጥ ጥልቅ የንጽሕና ስሜትን እንዴት ማዳበር እችላለሁ? 4. የሱስ ለእኔ ለከፈለው ዋጋ ያለኝን አመስጋኝነት የበለጠ ሊያጎለብት የሚችለው ምንድን ነው? 5. ለወንድሞቼ እና ለእህቶቼ ያለኝ ፍቅር ምን ያህል እውነተኛ ነው?
 <<    >>