ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (I) << >> ሰንበት፣ ግንቦት 17፣ 2016 8ኛ ትምህርት የክርስቲያን አመለካከት መታሰቢያ ጥቅስ፡- “በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፥ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፥ እንደወንድሞች ተዋደዱ፥ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡8)። ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡ The Adventist Home, pp. 421–429. “የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ፤ ጨካኞች፣ ደግነት የጎደላቸውና በሸካራ ቃላትና በግዴለሽነት የተሞሉ ከሆኑ ስለ የሱስ አልተማሩም። የሚያደበዝዝ፣ የሚሸከም፣ ስህተት የሚፈልግ ሰው ክርስቲያን አይደለም። ክርስቲያን መሆን ክርስቶስን መምሰል ነውና።”—The Adventist Home, p. 427. 1. እውነተኛ ክርስቲያን ሲገልጥ እሁድ ግንቦት 11 ሀ. ጴጥሮስ እውነተኛውን ክርስቲያን የገለጸው እንዴት ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 3፡8 “የትህትና ዋጋ በጣም ዝቅ ተደርጓል። ልባቸው ደግ የሆኑ ብዙ ሰዎች የባሕርይ ትሕትና የላቸውም። በቅንነታቸውና በመልካምነታቸው በአክብሮት የሚታዘዙ ብዙዎች በአሳዛኝ መልኩ ትሕትና የጎደላቸው ናቸው። ይህ እጦት የራሳቸውን ደስታ የሚያበላሽ ከመሆኑም ሌላ ለሌሎች የሚሰጡትን አገልግሎት የሚቀንስ ነው።”—Education, p. 240. ለ. ጴጥሮስ በተለይ ለየትኛው የክርስቶስ ዓይነት አመለካከት ጎላ አድርጎ ገልጿል? 1ኛ ጴጥሮስ 3:9፤ ማቴዎስ 5፡44 “ሁሉንም ሰዎች እንደ እግዚአብሔር ወንድና ሴት ልጆች በትህትናና በቅንነት ልንከባከባቸዉ ይገባል።“ክርስትና ሰውን የዋህ ያደርገዋል። ክርስቶስ ለአሳዳጆቹ እንኳን ቸር ነበር፤ እውነተኛ ተከታዮቹም ያንን መንፈስ ያሳያሉ።”—The Ministry of Healing, p. 489“ይህ ሃይማኖት ጭካኔ የተሞላበትና ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ ስንያዝና መከራን ስንቀበል ትዕግሥትን እንድናሳይ ያስተምረናል። . . .“በመጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖት ውስጥ ሁልጊዜ ትዕግሥት፣ ገርነት፣ ራስን መካድና የራስን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ ያስፈልጋል።”—God’s Amazing Grace, p. 248 2. ቃሎቻችንን መመልከት ሰኞ ግንቦት 12 ሀ. ጴጥሮስ በዚህም ሆነ በሚመጣው ሕይወት ደስተኛ ሕይወት እንዳለን በድጋሚ አጽንዖት የሰጠው የትኛውን ጠቃሚ መሠረታዊ ሥርዓት ነው? መዝሙር 34:12፣ 13፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡10 “ሰይጣን የእግዚአብሔርን መንጋ ለማበላሸት በየቤተክርስቲያኑ እየሰራ ነው። . . . የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ለምትለው ነፍስ ሁሉ ምላሳችሁን ከክፉ ተንኰል እንዳይናገሩ ከንፈሮቻችሁንም ጠብቁ እንድል ታዝዣለሁ። ራስን ከፍ ከፍ በማድረግ ሰይጣን ነፍስን ለማበላሸት ይሠራልና ሥራው በሁሉም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሊታይ ይችላል። ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ለመንፈሳችሁ ጥብቅ የሆነ ጥበቃ አድርጉ። ሰይጣን የራሱን ታሪክ እንድትደግም እንዳይመራህ ቃልህን (አንደበትህን) ጠብቅ።”— The Upward Look, p. 114. ለ. ይህንን መርህ የጣሱ ሰዎችን እና በተለይም ለሚናገረው ሰው እንዴት አሳፋሪና ውርደት እንደፈጠረባቸው ምሳሌዎችን ስጥ። 1ኛ ሳሙኤል 14:24–27፣ 43–45፤ አስቴር 6:6-10 “ከከንፈራችሁ አንድም የቁጣ፣ የጭካኔ፣ ወይም በጋለ ስሜት አንዲት ቃል ከቶ አይውጣ። የክርስቶስ ጸጋ መሻትህን ይጠብቃል። መንፈሱ ቃላቶቻችሁንና ድርጊቶቻችሁን እየመራ ልባችሁንና ህሊናችሁን ይቆጣጠራል። ለራስህ ያለህን ክብር በችኮላና ባለማስተዋል በፍፁም አታጥፋ። ቃላችሁ ንጹሕ እንደ ሆነ፥ አካሄዳችሁም የተቀደሰ እንዲሆን ተጠንቀቁ። - Child Guidance, p. 219. ሐ. ይህን መሠረታዊ ሥርዓት መጣስ ብዙዎች የዘላለም ሕይወትን እንዳያገኙ እንቅፋት የሚሆነው እንዴት ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 3:10 (የመጨረሻው ክፍል) ከራእይ 14:5፤ 21፡27። “እነዚህ ሻይና ቡና ተጠቃሚዎች ለማህበራዊ መዝናኛ ሲገናኙ . . . አንደበታቸው ልጓም ያጣል፣ እናም በሌሎች ላይ የመናገርን ክፉ ነገር ይጀምራሉ። ቃላቶቻቸው ጥቂት አይደሉም ወይም በደንብ የተመረጡ አይደሉም። የሐሜት ወሬዎች በየቦታው ይተላለፋሉ፣ ብዙ ጊዜ የቅሌት መርዝም ጭምር ነው። እነዚህ ማስተዋል የጎደላቸዉ ሀሜተኞች የሚታዘባቸዉ ምስክር እንዳላቸው ይረሳሉ። አንድ የማይታይ ጠባቂ ቃላቶቻቸውን በሰማይ መጻሕፍት ውስጥ እየጻፈ ነው። እነዚህ ሁሉ ደግነት የጎደላቸው ትችቶች፣ እነዚህ የተጋነኑ ዘገባዎች፣ በአንድ ሲኒ ሻይ ደስታ የተገለጹት እነዚህ የምቀኝነት ስሜቶችን የሱስ እርሱ ላይ እንደተደረጉ አድርገዉ ይመዝግባቸዋል።”— Counsels on Diet and Foods, p. 423. 3. ሰላምን መፈለግ ማክሰኞ ግንቦት 13 ሀ. ጴጥሮስ ምን ሌሎች የክርስቲያናዊ ሕይወት መሠረታዊ ሥርዓቶችን ያስታውሰናል? 1ኛ ጴጥሮስ 3:1፤ ኢሳይያስ 1:16፣ 17 ለ. ‘ከክፉ መራቅና መልካም ማድረግ የምንችለው’ እንዴት ነው? ኤርምያስ 13:23 ከ1ኛ ቆሮንቶስ 6:9–11 ጋር አወዳድር፤ ዮሐንስ 3:5፤ ያእቆብ 4:7 “[ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፋቸው] በክርስቶስ በሚለወጠው ጸጋ የተደረገውን የከበረ ለውጥ በሕይወታቸው መግለጥ አለባቸው። . . . ልባቸውን መቀየር አልቻሉም። እናም በጥረታቸው ነፍሶች ከሰይጣን ወገን ተመልስዉ የክርስቶስን አቋም እንዲይዙ ሲመሩ፣ ለመጣው ለውጥ ምንም አይነት ክብር ለራሳቸዉ ልወስዱ አይገባም። . . .“የእግዚአብሔር ኃይል በዓለም፣ በሥጋና በዲያብሎስ ላይ ድልን በማግኘት ታላቅ ሥራ ውስጥ የውጤታማነት ምንጭ ነው። . . . ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም ነገር ማድረግ አይችልም እና እግዚአብሔር እቅዱን ያዘጋጀው፣ የሰው ልጅ ተሃድሶ ሥራ ውስጥ ከመለኮታዊው ጋር ሳይተባበር ምንም ነገር እንዳይፈጽም አድርጎ ነው። ሰው እንዲሠራ የሚያስፈልገው ክፍል እጅግ በጣም ትንሽ ነው፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ ስራውን ስኬታማ ለማድረግ የሚያስፈልገው ወሳኝ ክፍል ብቻ ነው።“በኃጢአተኛ ሰው ሕይወት ውስጥ ከተለወጠ በኋላ የሚታየው ታላቅ ለውጥ በየትኛውም የሰው ልጅ መልካምነት ልመጣ የምችል አይደለም።”— God’s Amazing Grace, p. 319. ሐ. ራሳቸውን ለወንጌል ለውጥ ኃይል ለሰጡ፣ አሁንም በተለያዩ ፈተናዎች እየተሸነፉ ላሉ ምን ተስፋ እና ቃል ኪዳን ተሰጥቷቸዋል? 1ኛ ጴጥሮስ 3:12፤ ዮሐንስ 14:13, 14 “በእምነትና በጸሎት ሁሉም የወንጌልን መስፈርቶች ሊያሟሉ ይችላሉ። ማንም ሰው እንዲሠራ አይገደድም። የራሱን ፈቃድ በመጀመሪያ ማግኘት አለበት፤ ስሜት በምክንያታዊነት ላይ ከመሰልጠኑ ወይም በሕሊና ላይ ሃጢአት ድል ከመንሳቱ በፊት ነፍስ የኃጢአተኛውን ተግባር ማቀድ አለባት። ፈተና ቢበረታም ለኃጢአት ሰበብ አይሆንም። 'የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል።' የተፈተነ ነፍስ ወደ ጌታ ይጩኽ። ረዳት የለሽ፣ ብቁ ያልሆነ፣ ራሱን በየሱስ ላይ ይጣል፣ እና የተስፋውን ቃል ይቀበል። አምላክ ይሰማል። የተፈጥሮ የልብ ዝንባሌዎች ምን ያህል ጠንካራ እንደሆኑ ያውቃል ፣ እናም በፈተና ጊዜ ሁሉ ይረዳል።“በኃጢአት ወድቀሃልን? ከዚያም ሳትዘገይ አምላክን ምሕረትና ይቅርታ ጠይቅ።”— Testimonies for the Church, vol. 5, p. 177. 4. ያለ ፍርሃት መልካምን መስራት ረቡዕ ግንቦት 14 ሀ. በግንኙነት ውስጥ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት የሚረዳን ጴጥሮስ የሰጠው ምን ተግባራዊ ምክር ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 3:13፤ ምሳሌ 15፡1 ለተቆጣ ሰው የሚነገር ቃል አብዛኛውን ጊዜ እንደ ጅራፍ ሆኖ ቁጣውን ወደ ታላቅ ቁጣ ይመራዋል። ነገር ግን ቁጣዉ እስክበርድ በዝምታ ከታለፈ በፍጥነት ይጠፋል። እያንዳንዱ ክርስቲያን ጨካኝና ትዕግሥት የሌላቸውን ቃላት ላለመናገር ቁርጥ ውሳኔ በማድረግ አንደበቱን ይቆጣጠር።”— Messages to Young People, p. 136. ለ. የእኛን የተረጋጋ ማስጠንቀቂያ ከግምት አስገብተዉ ሊለሰልሱ በማይችሉ ሰዎች ላይ የእኛ አካሄድ ምን መሆን አለበት? 1ኛ ጴጥሮስ 3:14፣ 16፣ 17 “የሱስ ራሱ ሰላምን በድርድር አላገኘም። . . . የክርስቶስ አገልጋዮች ለተመሳሳይ ሥራ ተጠርተዋል እና አለመግባባትን ለመከላከል በመፈለግ እውነትን እንዳይሸጡ መጠንቀቅ አለባቸው። . . . መርሆን በመተላለፍ እውነተኛ ሰላም በፍፁም ሊረጋገጥ አይችልም። ማንም ሰው ያለ ተቃውሞ ለመርህ እውነተኛ ታማኝ ሊሆን አይችልም። መንፈሳዊ የሆነ ክርስትና በአመጻ ልጆች ተቃዉሞ ይገጥመዋል። የሱስ ግን ደቀ መዛሙርቱን፡- ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ አላቸው። ለአምላክ ታማኝ የሆኑ ሰዎች የሰውን ኃይል ወይም የሰይጣንን ጠላትነት መፍራት የለባቸውም። በክርስቶስ የዘላለም ሕይወታቸው ዋስትና አስተማማኝ ነው። ሊፈሩት የሚገባዉ ብቸኛዉ ነገር እውነትን አሳልፈው እንዳይሰጡ እና አምላክ የሰጣቸውን ክቡር አደራ እንዳይከዱ ብቻ ነው።”— The Desire of Ages, p. 356. ሐ. የመልካም ሥራችንና የደግ ንግግራችን ምንጭ ሊሆን የሚገባዉ ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 3:16 (የመጀመሪያ ክፍል)። የሐዋ. ሥራ 24:16፤ ዕብራውያን 9፡14 “በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ጥሩና መጥፎ ህሊናዎች እንዳሉ እናነባለን፣ እናም ህሊናችሁ የእግዚአብሔርን ህግ ባለመጠበቅዎ የማይፈርድባችሁ መሆኑ በእርሱ ፊት ያልተፈረደባችሁ መሆናችሁን አያረጋግጥም። ሕሊናህን ወደ የአምላክ ቃል ውሰድና ሕይወትህና ባሕርይህ አምላክ በዚያ ከገለጠው የጽድቅ መለኪያ ጋር እንደሚስማማ ተመልከት።”—The Review and Herald, September 3, 1901. 5. ጎራችንን (አቋማችንን) ማወቅ ሐሙስ ግንቦት 15 ሀ. የእግዚአብሔርን ቃል በየቀኑ የምናጠናበት ዋና ዋና ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ኢያሱ 1:8፤ መዝሙረ ዳዊት 119:11፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3:15፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2:15 ለ. በወቅቱ እውነት እናምናለን የሚሉ ብዙዎች ዛሬ ምን ትልቅ አደጋ ላይ ናቸው? ሆሴዕ 4፡6 “ወጣቶቹ በየዋህነትና በፍርሃት የተስፋቸውን ምክንያት ለሚጠይቁት ሁሉ መልስ መስጠት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸውን? ወጣቶቹ አቋማችንን መረዳት ሲሳናቸው አይቻለሁ። አስፈሪ ትዕይንቶች ከፊት ለፊታቸው ቀርበዋል፤ የችግር ጊዜ ደግሞ የባሕርይን ዋጋ የሚፈትን ነው።”— Testimonies for the Church, vol.1, pp. 507, 508.“የወቅቱ መልእክት - በእምነት መጸደቅ - የእግዚአብሔር መልእክት ነው። . . .“በየቀኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ብርሃንና እውቀት መፈለግን ቸል ካልን ደህና አንሆንም። . . . በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለአሁኑና ለዘላለማዊ ደኅንነታችን በጣም አስፈላጊ የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለራሱ የሚረዳ ከመቶ አንዱ እንኳን የለም።”— Selected Messages, bk. 1, p. 359.“ብዙዎች የእግዚአብሔርን ብርሃን እንዲያመጡላቸው ወደ አገልጋዮቻቸው ይመለከታሉ። . . . እነዚህ ብዙ ነገር ያጣሉ። በየቀኑ ክርስቶስን ቢከተሉ . . ስለ ፈቃዱ ግልጽ የሆነ እውቀት ሊያገኙና በዚህም ጠቃሚ ልምድ እያገኙ ይሄዱ ይሆናል። እውነትን የሚናገሩ ወንድሞች ይህን ልምዳቸው በማጣት በሌሎች ሰዎች ብርሃን ይመላለሳሉ። ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር አይተዋወቁም እንዲሁም ስለ ፈቃዱ እውቀት የላቸውም፤ ስለዚህም በቀላሉ ከእምነታቸው ሸርተት ይላሉ። እነሱ ያልተረጋጉ ናቸው፣ ምክንያቱም ለራሳቸው ተሞክሮ ለማግኘት በሌሎች ላይ ተማምነዉ ነበርና።”— Testimonies for the Church, vol. 2, p. 644. የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ግንቦት 16 1. ለባለቤቴ፣ ለልጆቼ፣ ለወንድሞቼ እና ለሥራ ባልደረቦቼ ያለኝ አመለካከት ምንድን ነው? 2. አንደበታችንን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብን ለማበረታታት አንዳንድ ቁልፍ እርምጃዎችን ጥቀስ። 3. በፈተና ከተሸነፍኩ ምን ማድረግ አለብኝ? 4. ከንጹሕ ሕሊና በሚመጡ መልካም ሥራዎችና መልካም ቃላት መካከል ያለውን ልዩነት መልካም ስምን ለመገንባት ከሚደረገው ራስ ወዳድነት ጥረት ጋር አወዳድር። 5. የምናገረውን እምነት በጥልቀት መረዳት የምንችለው እንዴት ነው? << >>