Back to top

Sabbath Bible Lessons

ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (I)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሰኔ 08፣ 2016 11ኛ ትምህርት
የጠበቀ ፍቅር የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ከሁሉም በላይ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና።” (1ኛ ጴጥሮስ 4፡8)።
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Education, pp. 113–118 
“የፍቅር ወኪሎች አስደናቂ ኃይል አላቸው፣ መለኮታዊ ናቸውና።”—Education, p. 114.

1. የፍቅር ጥልቀት - ታላቁ አመላካች እሁድ ሰኔ 02
ሀ. ኃጢአት የፍቅራችንን ጥልቀት እንዴት አጣመመ? ዘፍጥረት 3፡12 “ፍቅር፣ ምስጋና፣ ለፈጣሪ ያለው ታማኝነት—ሁሉም [አዳም] ለሔዋን ባለው ፍቅር እጅ ሰጡ። እሷ የአካሉ ክፋይ ነበረች፤ [የተከለከለውን የዛፍ ፍሬ ከበላች በኋላ] ከእርሷ የመለየቱን ሀሳብ መቋቋም አልቻለም . . . እጣ ፈንታዋን ለመካፈልና እርስዋ መሞት ካለባት አብሮ ሊሞት ቁርጥ ውሳኔ አደረገ። . . .“[በኋላ፣ በእግዚአብሔር ፊት]፣ አዳም ኃጢአቱን መካድ ወይም ማመካኘት አልቻለም። ነገር ግን ንስሐ ከመግባት ይልቅ ጥፋቱን በሚስቱ ላይ እንዲሁም በአምላክ ላይ ለመለጠፍ ጥረት አደረገ።”—Patriarchs and Prophets, pp. 56, 57. ለ. እውነተኛ ክርስቲያን መሆኔን ለማወቅ ቀላሉ መንገድ ምንድን ነው? 1 ዮሐንስ 2:9; 4:20; ዮሐንስ 13፡35 “ትናንት ማታ አንድ ትንሽ ቡድን ሃይማኖታዊ ስብሰባ ለማድረግ አንድ ላይ ተሰብስበው እንደነበር አየሁ። በዚያም ወደ ስብሰባው የገባና ብዙም ትኩረት ላለመሳብ በስውር በጨለማው ጥግ የተቀመጠ አንድ ሰው ነበር፡፡ የነፃነት መንፈስ አልነበረም፡፡ የክርስቶስ መንፈስ ታስሮ ነበር፤ አንዳንድ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። . . . እውነትን እናምናለን በሚሉ ሰዎች ልብ ውስጥ የየሱስ ፍቅር እንደሌለ ግልጽ ነበር ፤ አይቀሬው የተረጋገጠው ውጤቱም የክርስቶስ መንፈስ እጦት ተከሰተ። . . . በጋራ የተሰባሰቡ ሰዎች አንዱ ሌላውን ማነቃቃት አልቻለም።“ስብሰባው ሊዘጋ ሲል፣ እንግዳው ተነሳ እና በሀዘንና በእንባ በተሞላ ድምፅ፣ በነፍሶቻቸው እና በተሞክሯቸው የየሱስ ፍቅር ከፍተኛ እጦት እንዳለባቸው ነገራቸው።”—This Day With God, p. 157.

2. የፍቅርን መርህ መረዳት ሰኞ ሰኔ 03
ሀ. በዚህ ዓለም ላይ የፍቅር ጽንሰ-ሐሳብ በምን መርህ ላይ የተመሰረተ ነው? ሉቃስ 6፡32-34 ለ. እውነተኛ መለኮታዊ ፍቅር በምን መርህ ላይ ተመሰረተ? ማቴዎስ 5:44፣ 45 ፤ ዮሐንስ 15:13፤ 1ኛ ዮሐንስ 4፡7-11 “ፍቅር ከስሜትና ከስሜታዊነት እጅግ የገዘፈ ነው። ሕያው፣ ንቁና የሥራ መርህ ነው። ይህም በፍላጎት እንጂ በስሜቶች አይመራም። በፍቅር ውስጥ “እስከ ሞት ድረስ አገለግልሃለሁ” የሚለው የወሰን የለሹ ጥንካሬ የጨበጠው ራሱን ያስረከበውና የለሰለሰው የአዕምሮን ቆራጥ ውሳኔ ተሟልቶ ይገኛል፡፡ በማለት የዘላለምን ኃይል የሚይዘው፣ የተገዛው እና የለዘበ አእምሮ ያለው ከባድ ቁርጠኝነት ይገነዘባል።”—The Signs of the Times, June 20, 1900.“እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን በመሻት የክርስቶስን ሥራ ለመሥራት ሁልጊዜም ዝግጁ ቢሆን ኖሮ፣ ወደ ሰማይ የሚወስደው መንገድ እንዴት እጅግ ቀላል ይሆን ነበር! የእግዚአብሔር በረከቶች ወደ ነፍስ ይጎርፉ ነበር ፤ የጌታም ምስጋና ሁልጊዜ ከአንደበታችሁ አይለይም ነበር። ከዚያም እግዚአብሔርን በመርህ ታገለግሉት ነበር። ሁልጊዜ የደስታ ስሜት ላይሰማችሁ ይችላል ፤ አንዳንድ ጊዜ ደመናዎች በልምምዳችሁ አድማስ ላይ የጨለማ ግርዶሻቸውን ሊጥሉ ይችላሉ ፤ ነገር ግን የክርስትያን ተስፋ በስሜት የአሸዋ መሰረት ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ እነዚያ መርህን መሰረት አድርገው የሚሠሩ፣ ከግርዶሹ ባሻገር የእግዚአብሔርን ክብር ይመለከታሉ ፤ እርግጠኛ በሆነው የተስፋ ቃል ላይ ያርፋሉ። ጎዳናቸው ምንም ያህል በጨለማ የተዋጠ ቢመስልም እግዚአብሔርን ከማክበር የሚያግዳቸው ነገር የለም። መከራና ፈተና የእምነታቸውንና የፍቅራቸውን ቅንነት እንዲያሳዩ ለማድረግ እድል ከመፍጠር በዘለለ ሌላ የሚያመጡት ነገር የለም።”— The Review and Herald, October 20, 1910. ሐ. ተጠመቀን እያለን ይቅር ለማለት፣ ለመሸነፍ እንዲሁም ፍቅርንና ትዕግሥትን ለማሳየት አሁንም በጣም አስቸጋሪ ጊዜ እያሳለፍን ከሆነ ምንድን ነው የረሳነው ነገር? ሮሜ 8:7-10 ፣ 1ኛ ዮሃንስ 4:8 “እውነተኛ ቅድስና አማኞችን ከክርስቶስ ጋር እና ከእርስ በርሳቸው ጋር በርኅራኄ ገመድ ያስተሳስራቸዋል። ይህ ህብረት በክርስቶስ የፍቅር ሞገድ ተሞልቶ ወደ ልብ እንዲፈስ ያደርጋል ፤ ከዚያም ከአንዱ ወደሌላው የፍቅር ጎርፍ ይፈሳል፡፡“ሁሉም ሰው ይወርሷቸው ዘንድ የሚያስፈልጓቸው የባህርይ ችሎታዎች አንዳች ያልተጓደለ ፍጽምና በሙላት የያዙት የክርስቶስ ባህርያት ናቸው— ማለትም ፍቅሩ ነው። . . .ሰው ለወንድሙ የክርስቶስ ዓይነት ፍቅር ሳይኖረው ለዘላለም ሕይወት የሚበቃ ህኃይማኖት ሊኖረው ይችላል ብሎ ማሰብ እጅግ ታላቁና ለሞት የሚያበቃ ማታለያ ነው ።.”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 5, p. 1141.

3. መማር የሚገባ መርህ ማክሰኞ ሰኔ 04
ሀ. ጴጥሮስ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እንድንማርና እንድንለማመድ የነገረን የትኛውን ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 4:8 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ 1፡22። ለ. ልግስና “የኃጢአትን ብዛት የሚሸፍነው” ከምን አንጻር ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 4፡8 (የመጨረሻው ክፍል) ከምሳሌ 17:9፤ ያእቆብ 5:19፣ 20 “ወንድምህ የጎዳህ ከመሰለህ በደግነትና በፍቅር ወደ እርሱ ሂድ፤ ከዚያም ወደ መግባባትና ወደ እርቅ መድረስ ትችላላችሁ። ከተሳሳተው ሰው ጋር በምትነጋግርበት ጊዜ፣ እየተነጋገርክ ያለኸው በአካል በቅዱሳኑ በኩል ከክርስቶስ ጋር እየተነጋገርክ መሆንህን ሁለልጊዜም ቢሆን ማስታወስ አለብህ፡፡ ተሳስቷል ብለህ ወደወንድምህ ሂድ፤ ከዚያም ለብቻው በፍቅር አነጋግረው። በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት ውጤታማ መሆን ከቻልክ፣ ደካማ ጎኑን (ገመናውን) ለሌሎች ሳታጋልጥ ወንድምህን ገንዘብህ አደረከው ማለት ነው። እናም ከአንተ ጋር በመካከላችሁ የሚደረገው ችግሩን የማስወገድ ሁኔታ ሌሎች እንዳይመለከቱት የኃጢአትን ብዛት መሸፈን ማለት ይህ ነው። ሌሎች አንተ ያጋጠመህን ችግር ማወቅ አያስፈልጋቸውም፤ ይህም የሌሎች ምልከታ ነው። ሌሎችም ስለችግርህ ማወቅ አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም አንተ ጥፋተኛ ነዉ ብለህ የምታስበው ሰው የሚያደርገዉን ማንኛውንም ነገር በጥርጣሬ እንዲመለከቱና በእርሱ ዓላማ ላይ የተሳሳተ ነገር ለመፈለግ ንቁ እንዲሆኑ ታደርጋለህና።”—The Re¬view and Herald, February 24, 1891.“ቅዱሳት መጽሐፍት (መጽሐፍ ቅዱስ) የተሳሳቱ ሰዎች በትዕግሥትና በታላቅ ጥንቃቄ መያዝ እንዳለባቸው በግልጽ ያስተምራሉ። ትክክለኛውን መንገድ ብንከተል ኖሮ፣ እጅግ ደንዳናው ልብ ለክርስቶስ ይሸነፍ ነበር። የየሱስ ፍቅር የኃጢያትን ብዛት ይሸፍናል። ማጋለጡ አስፈላጊ ካልሆነ በቀር የእርሱ ፀጋ የሌላውን ስህተት ወደማጋለጥ አይመራም። የእሱ ጸጋ አወንታዊ ካልሆነ በስተቀር የሌላውን በደል ለማጋለጥ ፈጽሞ አያመራም።”—Counsels to Parents, Teachers, and Students, p. 267.“ሐዋርያው “ከሁሉም በላይ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ” ሲል ጽፏል (1ኛ ጴጥሮስ 4:8)። በወንድም ወይም በእህት ላይ የሚነገሩ ወሬዎችን አታዳምጡ (አትስሙ)። በባልንጀራህ (በጎረቤትህ) ላይ ነቀፋን እንዳታደርሱ በጣም ተጠንቀቁ። ክሱን ያመጣውን ነገር አመላላሹን ሰው ይህን ጉዳይ በተመለከተ የእግዚአብሔርን ቃል ስለመታዘዙ ጠይቁት። ክርስቶስ ምን መደረግ እንዳለበት ግልጽ መመሪያዎችን ሰጥቷል። ወደ ወንድምህ ሄደህ አንተ እና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ የሰራውን ጥፋት ለብቻው ንገረው። በተከሰሰው እና በእኔ መካከል ንዳች ግላዊ ቅራኔ የለም በሚል ይህን ላለማድረግ ሰበብ በመጠቀም ከኃላፊነት አትስስ። የክርስቶስ መመሪያዎች እጅግ የተብራሩ፣ ግልፅ በመሆናቸው ይህ ሰበብ ዋጋ የለውም።“በደሉ (ቅራኔው) በአንተ እና በተከሳሹ ቢሆንም የክርስቶስ ትዕዛዝ ያው ነው። ወንድምህ እርዳታን ይሻል። ወሬው እንዳይዛመት አንተ ንገረው እንጂ ሌላ ሰው ይደለም። ዘርዘር አድርጎ እንዲያብራራ ዕድል ስጠው።”—In Heavenly Places, p. 292.

4. የፍቅር አስፈላጊ ፍሬ ረቡዕ ሰኔ 05
ሀ. ጴጥሮስ የእግዚአብሄር ፍቅር በልብ ውስጥ እንዲኖር መልካም ምልክት የሆነውን የትኛውን የባህርይ ባህሪ ነው የጠቆመው? 1ኛ ጴጥሮስ 4:9 ለ. እንግዳ መቀበል አስፈላጊ ክርስቲያናዊ በጎነት የሆነው ለምንድን ነው? ዕብራውያን 13:2; ሮሜ 12፡13 “ክርስቲያን ነን በሚሉ ሰዎች መካከል እንኳ እውነተኛ የእንግዳ መስተንግዶ በተግባር የሚታየው እምብዛም ነው። በገዛ ወገኖቻችን መካከል እንኳ እንግዳን መቀበል መሆን እንደሚገባው እንደ መልካም እድል እና እንደ በረከት ተደርጎ አልተቆጠረም። በቤተሰብ ህብረት መካከል ሃፍረት ሳይሰማው፣ በኩራትም ሳይግደረደር ደስ ተሰኝተው ሁለት ወይም ከሶስት በላይ የሆኑ ቦታዎችን (እድልን) በመስጠት ወደ ቤተሰባዊ ህብረት ለመቀበል እንደ አጠቃላይ ሲታይ እጅግ በጣም ያነሰ ማህበራዊነትና በጣም አነስተኛ ፍላጎት ይታያል፡፡ አንዳንዶቹ 'ይህ በጣም ችግር ነው' በማለት ይናገራሉ። . . .‘ለእኔና ለቤተሰቤ’ በሚል በሚታየው የራስ ወዳድነት ፍላጎት እግዚአብሔር እጅግ አዝኗል። ይህን የራስ ወዳድነት መንፈስ እያሳየ ያለው እያንዳንዱ ቤተሰብ በክርስቶስ ሕይወት በተግባር በታዩት ንጹሕ መርሆዎች መለወጥ አለበት። እነዚያ ራሳቸውን በራሳቸው ዘግተው እንግዶችን (ጎብኚዎችን) ለመቀበል ልባቸውን ለመክፈት አሻፈረነ የሚሉ ብዙ በረከቶችን ያጣሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 343, 344.“ከፍተኛ ሙያ ያላቸው፣ ነገር ግን በራስ ወዳድነት እና ለእኔ ብቻ በሚል ህይወት ልባቸው ዝግ የሆኑ ሰዎችን አውቃለሁ። . . . ሕይወታቸውን በሙሉ ያስተማሩት ለራሳቸው እና ለራሳቸው ብቻ በመሆኑ የኖሩትም ለራሳቸው ብቻ ነው። ለሌሎች የበጎነት አድራጎትን ለማበርከት፣ መስዋዕትነትን ለመክፈል፣ ሌሎችን ለመጥቀም ራሳቸውን መጉዳት በእነርሱ ዘንድ ጥያቄቸው አይደለም። . . . ራስ ጣዖታቸው ነው። እግጅ ውድ የሆኑ ሳምንታት፣ ወራት፣ ብሎም ዓመታት ወደ ዘላለማዊነት እነጎዱ ቢሆንም ፤ ነገር ግን ስላበረከቱት ደግነት ምግባራቸው፣ ለሌሎች ጥቅም መሥዋዕት ስለ መክፈላቸው፣ የተራቡትን ስለመመገባቸው፣ የታረዙትን ስለማልበሳቸው፣ ወይም እንግዶችን ስለመቀበላቸው በሰማይ ምንም ዓይነት መዝገብ የላቸውም።”—Ibid., vol. 2, p. 26. ሐ. በብዙዎቹ የክርስቲያን ቤተሰቦች ምን ዓይነት ጥልቀት የሌለው የውሸት “እንግዳ ተቀባይነት” ነው የሚታየው? ኢዮብ 1:4; 2ኛ ነገ 20፡13-15 “ለእርሱ እናውልለት ዘንድ የሚጠይቀውን፣ በትክክል የጌታ የሆነውን ጊዜ ለእንግዶች (ለጎብኚዎች) ዝግጅት ማዋል ክርስቶስን መካድ ነው። . . .“ጎብኚዎችን ለማዝናናት በሚኖር ፍላጎት የተነሳ አላስፈላጊ ጭንቀቶች እና ሸክሞች ይፈጠራሉ። ለምግብ ገበታው የተለያዩ ምግብ ዓይነቶችን ለማዘጋጀት የቤት እመቤትዋ ከባድ የሥራ ጫና ያርፍባታል፡፡ በተዘጋጀው ብዙ ዓይነት ምግቦች የተነሳ እንግዶቹም ያለመጠን አብዝተው ይመገባሉ ፤ በውጤቱም በአንዱ ወገን ከአቅም በላይ መስራትን በሌላው ወገን ደግሞ በብዛት በመመገብ በውጤቱ በሽታ፣ ስቃይና ማስከተል ይሆናል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የተንበሸበሸ ድግስ (ግብዣ) ሸክምና ጉዳት ይሆናል፡፡ ”—Ibid., vol. 6, p. 343.

5. እውነተኛ የክርስቲያን አገልግሎት ሐሙስ ሰኔ 06
ሀ. ልግስና በአንድ እውነተኛ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ እንዴት እንደሚገለጥ አንዱን ገጽታ ጥቀስ። 1ኛ ጴጥሮስ 4:10 “እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው እንደ አቅሙና ችሎታው ሥራ መድቦለታል። ሰዎች ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ችግሮች መፍትሀተ ለመስጠት በትምህርት እና በተግባር ብቁ መሆን ይችላሉ፤ እናም ኃላፊነቱን መሸከም ይችል ዘንድ አስፈላጊውን ልምድ እንዲያገኝ እያንዳንዱን ሰው በተገቢው ቦታ ለማስቀመጥ ጥበብ የተሞላበት ዕቅድ ማውጣት ያስፈልጋል።”—Testimonies for the Church, vol. 9, pp. 221, 222.“ወጣቶች ውድ ህይወቱን መስዋዕት አድርጎ ላቀረበላቸው ለእርሱ ተቀባይነት ያለውን አገልግሎት ማቅረብ ይችሉ ዘንድ በተለይም አእምሮአቸውን ማሰልጠን እንዳለባቸው እንዲሁም እያንዳንዱን እድል በሚገባ መጠቀም እንዲችሉ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ . . . በራዕይም ሆነ በሳይንስ የሚቻለውን ሁሉ ለማግኘት እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር ሥልጣን የሚደገፍበትን ዕድል ሁሉ ያሻሽል። . . .“ለሰዎች የተሰጠው ማንኛውም መክሊት ዋጋው ይጨምር ዘንድ በስራ መተግበር አለበት፤ እናም የተገኘው እድትም (መሻሻል) መልሶ ለእግዚአብሔር መሰጠት አለበት። በፀባይ (በምግባር)፣ በድምጽ ፣ በትምህርት ጉድለት ካለብዎ ሁልጊዜ በዚህ ሁኔታ መቆየት የለብዎትም። በትምህርትም ሆነ በሃይማኖት ተሞክሮ ከፍ ወዳለው ደረጃ ላይ ለመድረስ ያለማቋረጥ ጥረት ማድረግ ይኖርብዎታል። . . . ማንም ሰው የተዝረከረከ የግድ-የለሽነት ሥራን በመሥራት ሰበብ ይሆንለት ዘንድ እግዚአብሔር መንገድ አላዘጋጀም ፤ ዳሩ ግን ይህ ዓይነቱ የመናኛ ሥራ በእርሱ ዓላማ ውስጥ በሚሠሩ ሰዎች ይቀርብለታል፤ በእርሱ ዘንድ ግን ተቀባይነት የለውም።”—Fundamentals of Christian Education, pp. 213–215. ለ. ለአገልግሎታችን ብቸኛው ዓላማ ምን መሆን አለበት? 1 ጴጥሮስ 4:11; ቆላስይስ 3፡23

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ሰኔ 07
1. በመለኮታዊ ፍቅር እና በዓለማዊ "ፍቅር" መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 2. በክርስቲያናዊ ፍቅር መሠረት የሚጥለው የትኛው መሠረታዊ ሥርዓት ነው? 3. ጥሩ የእንግዳ ተቀባይነት ልማዶችን ማዳበር የምችለው እንዴት ነው? 4. ምን ዓይነት ክርስቲያናዊ አገልግሎቶችን ማዳበር ይጠቅመኛል? 5. ሥራዬ ከግድየለሽነት እና ልግመኝነት ይልቅ ለእግዚአብሔር መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?
 <<    >>