ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (I) << >> ሰንበት፣ ግንቦት 03፣ 2016 6ኛ ትምህርት ለአለም መመስከር መታሰቢያ ጥቅስ፡- “በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና።” (1ኛ ጴጥሮስ 2፡15)። ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡ Testimonies for the Church, vol. 1, pp. 358–361. “የክርስቶስ አክሊል ከምድራዊ ኃያላን ዘውዶች ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ልል ይገባል።”— The Acts of the Apostles, p. 68. 1. ከነፍስ ጋር የሚዋጋውን ያንን ማስወገድ እሁድ ሚያዝያ 27 ሀ. ለእያንዳንዱ የሃይማኖት ተጓዥ በጣም አስፈላጊ ግን በጣም ፈታኝ ከሆኑት ጦርነቶች ውስጥ አንዱ የትኛው ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 2:11፤ 1 ዮሐንስ 2:15፣ 16 “ሐዋርያው ጴጥሮስ በአእምሮና በሥጋ መካከል ያለውን ዝምድና ተረድቶ ድምፁን ከፍ አድርጎ ለወንድሞቹ እንዲህ ሲል አስጠንቅቋል፡- 'ወዳጆች ሆይ፣ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ፣ ነፍስን ከሚዋጋ ከሥጋዊ ምኞት እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።' ብዙዎች ይህንን ጽሑፍ ከሴሰኝነት ብቻ ላይ እንደተሰጠ ማስጠንቀቂያ አድርገው ይመለከቱታል፤ ግን ሰፋ ያለ ትርጉም አለው። ማንኛውንም ጎጂ የሆነ የምግብ ፍላጎት ወይም የፍላጎት እርካታን ይከለክላል። እያንዳንዱ የተዛባ መሻት የሚዋጋን ምኞት ይሆናል። መሻት የተሰጠን ለበጎ ዓላማ ነው እንጂ በተጠማመዱ የሞት አገልጋይ እንድንሆን እና በዚህም ‘ነፍስን ወደ ሚዋጉ ምኞቶች’ እንድንሸጋገር አይደለም። . . .“መሻትን የማርካት ፈተና ጥንካሬ የሚለካው በዚያ ረጅም ጾም በምድረ በዳ በቤዛችን የማይገለጽ ጭንቀት ነው። የተዛባ የምግብ ፍላጎት መጠመዱ የሰውን አመለካከት እንደሚያጠፋና ቅዱስ ነገሮችን መለየት እንዳይችል እንደሚያደርግ ያውቅ ነበር። . . . በሰዉ ዘር ላይ ይህ ኃይል በጣም ጠንካራ ከሆነ፣ መለኮታዊው የእግዚአብሔር ልጅ፣ ሰውን ወክሎ፣ ወደ ስድስት ሳምንታት የሚጠጋ ጊዜ መጾም ነበረበት፣ ይህ በክርስቲያኑ ፊት እንዴት ያለ ድንቅ ሥራ ነው! ሆኖም ትግሉ ምንም ያህል ቢበዛ፣ በዚያ መለኮታዊ ኃይል እርዳታ ማሸነፍ ይችላል።. . . ደግሞም ከክፉ ጋር በሚደረገው ጦርነት ሙሉ በሙሉ ስኬታማ ሊሆን ይችላል፤ በመጨረሻም በአምላክ መንግሥት ውስጥ የድል አድራጊውን ዘውድ ሊለብስ ይችላል።”— Counsels on Diet and Foods, pp. 166, 167. 2. በመልካም ስራዎች መስበክ ሰኞ ሚያዝያ 28 ሀ. ሁሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደ እንግዳ አልፎ ተርፎም የዚህ ዓለም ጠላቶች ተደርገው የሚታዩት ለምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 2:12፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 1:18፣ 2፤ 2፡14። “[ጳውሎስን] ከሚሰሙት አይሁዳውያን መካከል እርሱ ሊያውጅ ባለው መልእክት የሚናደዱ ብዙዎች ነበሩ። በግሪኮች ግምት ቃላቱ የማይረባ ሞኝነት ይሆናሉ። መስቀሉ ከዘር ከፍታ ወይም ከሰው ልጅ መዳን ጋር ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ለማሳየት ሲሞክር ደካማ አስተሳሰብ እንዳለው ይታይ ነበር።“ለጳውሎስ ግን ከሁሉ የላቀ ትኩረት የሚሰጠው መስቀል ነበር።”— The Acts of Apostles, p. 245.“የዓለም መንፈስ ከቀድሞው ዘመን ይልቅ ዛሬ ከክርስቶስ መንፈስ ጋር አይስማማም፤ የእግዚአብሔርን ቃል በንጽሕና የሚሰብኩም ዛሬ ከዚያ ጊዜ የሚበልጥ ሞገስ አያገኙም። እውነትን የመቃወሚያ ቅርጾች ሊለወጡ ይችላሉ፣ ጠላትነቱ የበለጠ ስውር ስለሆነ ብዙም ክፍት ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ተመሳሳይ ተቃዋሚዎች አሁንም አሉ እና እስከ ዘመን ፍጻሜ ድረስም ይገለጣሉ።”— The Great Controversy, p. 144. ለ. ጴጥሮስ ወንጌልን በመስበክና 'ከሰነፎች ሰዎች ድንቁርና' ጋር በተያያዘ ከሁሉ የተሻለው ዘዴ እንደሆነ የጠቆመው ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 2:12፣ 15 “አገልጋዮቻችን እና አስተማሪዎች ለወደቀው ዓለም የእግዚአብሔርን ፍቅር መወከል አለባቸው። ልቦች በእርሱ ፍቅር ቀልጠው የእውነት ቃል ይነገር። የተሳሳቱ ሁሉ በክርስቶስ ፍቅር ይያዙ። የምትደክሙባቸው ሰዎች ወዲያውኑ እውነቱን ካልተረዱ አትዉቀሱ፣ አትንቀፉ ወይም አታዉግዙ። ክርስቶስን በየዋህነቱ፣ በተዕግሥቱ እና በፍቅር እንደምትወክሉ አስታውሱ። አለማመን እና ተቃውሞ እንደሚያጋጥመን መጠበቅ አለብን። እውነት ሁል ጊዜ እነዚህን ነገሮች መጋፈጥ ይኖርበታል። ነገር ግን በጣም መራራ ተቃውሞ ቢገጥማችሁም ተቃዋሚዎቻችሁን አታውግዙ። . . .“ለሚሳሳቱ በየዋህነት አስብ፣ አንተስ በቅርብ ጊዜ በኀጢአትህ ዕውር የነበርክ አይደለህምን? ክርስቶስ ለእናንተ ስላደረገው ትዕግሥት ለሌሎች ርኅሩኆችና ታጋሽ መሆን አይገባችሁምን? ነፍስን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ እንዳንመራ እግዚአብሔር ለሚቃወሙን ሰዎች ታላቅ ደግነት እንድናሳይ ብዙ ምክሮችን ሰጥቶናል።”— Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 120, 121. 3. የክርስቲያን መገዛት ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ሀ. ለሲቪል ባለስልጣናት እና ለሀገሪቱ ህጎች ሊኖረን የሚገባውን አመለካከት ግለጽ። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡13-17 “ሐዋርያው ‘ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ’ በማለት አማኞች ለሲቪል ባለ ሥልጣናት ሊኖራቸው የሚገባውን አመለካከት በግልጽ ገልጿል።”—The Acts of the Apostles, p. 522. ለ. የአገሪቱ ሕግ ከአምላክ ሕግ ጋር በሚጋጭበት ጊዜ ምን መደረግ እንዳለበት እና በምን ዓይነት ዝንባሌ ላይ ምን መደረግ እንዳለበት የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ጥቀስ። የሐዋርያት ሥራ 5:29፤ ዘጸአት 1:15–17፤ ዳንኤል 6:7-10፣ 21፣ 22 “እግዚአብሔር ከሲና ሆኖ በሚሰማ ድምፅ ከተናገረው ከከፍተኛው ሕግ ጋር ካልተቃረኑ በስተቀር በማንኛውም ሁኔታ የአገራችንን ሕጎች መታዘዝ የኛ ግዴታ እንደሆነ አይቻለሁ።”—Testimonies for the Church, vol. 1, p. 361.“ባለሥልጣናት መቃወም አይጠበቅብንም። የምንናገረውም ሆነ የተጻፈው ቃላችን በጥንቃቄ ሊታሰብበት ይገባል፤ ይህም . . . ህግ እና ስርዓትን የሚጻረር ይመስላል።መንገዳችንን የሚዘጋውን አላስፈላጊ ማንኛውንም ነገር መናገርም ሆነ ማድረግ የለብንም። ለእኛ የተሰጠንን እውነቶች እያወጅን በክርስቶስ ስም ወደፊት መሄድ አለብን። ይህን ሥራ እንዳንሠራ በሰዎች ከተከለከልን እንደ ሐዋርያት ልንል እንችላለን።”—The Acts of the Apos- tles, p. 69.“የእግዚአብሔር ሕግ በልቡ የተጻፈው ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ይታዘዛል። . . . የመለኮታዊ ሕግ ጥበብና ሥልጣን ከሁሉ የላቀ ነውና።“የእሱ ልዩ ሀብት የሆኑት የእግዚአብሔር ሕዝቦች በዚህ ግራ የሚያጋባ ጦርነት [የአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት፣ 1861–1865] ውስጥ መሳተፍ እንደማይችሉ አሳየኝ፤ ምክንያቱም ከእምነታቸው መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር የሚቃረን ነው። በሠራዊቱ ውስጥ እውነትን መታዘዝ አይችሉም እና በተመሳሳይ ጊዜ የመኮንኖቻቸውን መስፈርቶች ያከብራሉ። በዚህም የማያቋርጥ የኅሊና ጥሰት ይኖራል።”—Testimonies for the Church, vol. 1, p. 361. ሐ. “አገልጋዮች” ከሆንን በሥራ ቦታችን ምን ዓይነት ሠራተኞች መሆን አለብን? 1ኛ ጴጥሮስ 2:18፤ ቆላስይስ 3፡23 “በጣም ትሁት በሆነው ሥራ ውስጥ ሳይንስ አለ፤ እና ሁሉም ይህን ቢመለከቱት በሥራቸዉ ውስጥ ክብርን ያያሉ።”—Fundamentals of Christian Education, p. 315. 4. በስህተት መሰቃየት ረቡዕ ሚያዝያ 30 ሀ. ለሚበድሉን፣ ለሚያስቀይሙን፣ ለሚንቁን ወይም ለሚዘበቱብን ሰዎች ያለን አመለካከት ምን መሆን አለበት? 1ኛ ጴጥሮስ 2:19፣ 20፤ ሮሜ 12፡19-21 “በእራሳችን ላይ ተደርጎብናል ብለን በምናስበው ወይም በተደረጉ ጥፋቶች መንፈሳችን እንዲቆጣ ማድረግ አንችልም። እራሳችንን በጣም ልንፈራው የሚገባ ጠላት ነው። በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር ካልሆነ በስተቀር ከሰው ልጅ ፍላጎት የበለጠ ሌላ የትኛውም አይነት ክፋት በባህሪው ላይ ከፍ ያለ ተጽዕኖ የሚያሳድር የለም። በራሳችን ላይ የምንቀዳጀውን ድል ያህል ልናገኘው የምንችለው የትኛውም ድል ውድ አይሆንም።“ስሜታችን በቀላሉ እንዲጎዳ መፍቀድ የለብንም። መኖር ያለብን ስሜታችንን ወይም ስማችንን ለመጠበቅ ሳይሆን ነፍሳትን ለማዳን ነው። . . . ሌሎች ስለ እኛ የሚያስቡ ወይም የሚያደርጉብን ምንም ይሁን ምን ከክርስቶስ ጋር ያለንን አንድነት ሊያናጋው አይገባም። . . .“አትበቀሉ። ማድረግ እስከቻሉት ድረስ ሁሉንም የተሳሳቱ ምክንያቶችን ያስወግዱ። የክፋትን ገጽታ ያስወግዱ። መርሆዎችን መስዋዕት ሳታደርጉ ሌሎችን ለማስታረቅ በአንተ አቅም የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ። . . .“ትዕግሥት የጎደላቸውን ቃላቶች ከተነገሯችሁ በዚያዉ መንፈስ አትመልሱ።”— The Ministry of Healing, pp. 485, 486. ለ. አምላክ በጨካኞችና በክፉ ሰዎች እንድንሠቃይ የፈቀደልን ለምንድን ነው? ማቴዎስ 5:11፣ 12፣ 43–48 “ጻድቃን በኃጥኣን እጅ ስደት እንዲደርስባቸው የሚፈቅደው ምስጢራዊ አሰራር በእምነት ደካማ ለሆኑ ለብዙዎች ግራ የሚያጋባ ነበር። አንዳንዶች ደግሞ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ለመተው ዝግጁ ናቸው ምክንያቱም እርሱ ክፉዎችን እንዲበለጽጉ እና ምርጦችና ንጹሐን ደግሞ በእነርሱ ጭካኔ እየተሰቃዩና እየተሰደዱ እንዲኖሩ ፈቅዶአል ብለው ስለሚያስቡ ነው። ፍትሐዊና መሐሪ የሆነ፣ በሥልጣንም ላይ ገደብ የሌለው፣ እንዲህ ያለውን ግፍና ጭቆና እንዴት ሊታገሥ ይችላል? ይህ እኛ ልንፈታው የማንችለው ጥያቄ ነው። እግዚአብሔር ስለ ፍቅሩ በቂ ማስረጃ ሰጥቶናል፣ እናም የእርሱን አሰራር መረዳት ስለማንችል ቸርነቱን መጠራጠር የለብንም። . . .“[ጌታ] ልጆቹን አይረሳም ወይም አይተዉም፤ ነገር ግን ፈቃዱን ለማድረግ የሚሹ ሁሉ በእነርሱ ላይ እንዳይታለሉ ለክፉዎች እውነተኛ ባሕርያቸውን እንዲገልጹ ይፈቅዳል። ጻድቃን ደግሞ እንዲነጹ በመከራ እቶን ውስጥ ያልፋሉና።”— The Great Controversy, pp. 47, 48. 5. ምሳሌውን መከተል ሐሙስ ግንቦት 01 ሀ. ጴጥሮስ መከራንና ስደትን በደስታ እንዲቋቋሙ ክርስቲያኖችን ካበረታታ በኋላ ይህን ለማድረግ ጠንካራ መከራከሪያ ያቀረበው ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 2፡21-24 “የሱስ ስለ እኛ የተቀበለው የትኛውም ተከታዮቹ በክፉ ሰዎች ጭካኔ ሊሰቃዩ ከሚችሉት በላይ ነው። መሰቃየትንና ሰማዕትነትን እንዲቀበሉ የተጠሩት የአምላክን ውድ ልጅ ፈለግ በመከተል ላይ ናቸው።”— The Great Controversy, p. 47. ለ. ሐዋርያው መከራዎችን እንዴት መቋቋም እንደምንችል በሐሳቡ መጨረሻ ላይ ምን የሚያበረታታ ምሳሌ ሰጥቷል? 1ኛ ጴጥሮስ 2:25፤ ዮሐንስ 10፡11 “ክርስቶስ የጠፋውን በግ በማደን፣ በመፈለግ ተመስሏል። የከበበን ወደ መንጋው የሚመልሰን ፍቅሩ ነው። ፍቅሩ ከእርሱ ጋር በሰማያዊ ስፍራ የመቀመጥ መብት ይሰጠናል።”— Testimonies for the Church, vol. 6, p. 479.“ሰራተኞቻችን—አገልጋዮቻችን፣ አስተማሪዎች፣ ሐኪሞች፣ ዳይሬክተሮች—ሁሉም ከክርስቶስ ጋር ለመተባበር ቃል እንደገቡ ማስታወስ አለባቸው። . . . የማያቋርጥ የአዳኝን ፍቅር፣ የብቃቱን፣ የእሱን ንቁነት፣ የርህራሄ ስሜትን ሊንከባከቡ ይገባቸዋል። እንደ ነፍሳቸው እረኛ እና መጋቢ አድርገው ሊመለከቱት ይገባል። ያኔ የሰማይ መላእክት ርኅራኄ እና ድጋፍ ያገኛሉ። ክርስቶስ ደስታቸው እና የደስታ አክሊላቸው ይሆናል። ልባቸው በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ይሆናል፤ እንዲሁም ስመ አማኞች ፈጽሞ ሊያገኙ የማይችሉትን የእውነት እውቀት ያገኛሉ።”— Counsels to Parents, Teachers, and Students, p. 284. የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ግንቦት 02 1. መሻትን ካለመግዛትና ከፍላጎት ባርነት እንዴት መዳን እችላለሁ? 2. ሕይወቴን የወንጌል ኃይል ሕያው ምስክር የሚያደርገው ምንድን ነው? 3. ለባለሥልጣን ታዛዥነትን በተሻለ መንገድ ማሳየት የምችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? 4. በሐሰት ሲከሰስ ወይም ሲጮሁብኝ፣ የእኔ ምላሽ ምን መሆን አለበት? 5. ለየሱስ በእውነት ለመሠቃየት ፈቃደኛ እንድሆን የሚያደርገኝ ምንድን ነው? << >>