Back to top

Sabbath Bible Lessons

ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (I)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሰኔ 15፣ 2016 12ኛ ትምህርት
ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች የቀረበ ተማጽኖ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ” (1ኛ ጴጥሮስ 5፡6)።
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Testimonies to Ministers, pp. 347–359. 
“የሰዎች ተወካይ ሆነው የቆሙ ሰዎች ሁሉ የተከበሩ ክርስቲያኖች የሆኑት አይደሉም። በሌሎች ላይ የበላይ ለመሆን የመፈለግ መንፈስ በስፋት ይታያልና።”—Testimonies to Ministers, p. 260.

1. እያንዳንዱ መሪ የሚያስፈልገው ልምድ እሁድ ሰኔ 09
ሀ. ሐዋርያው ጴጥሮስ ለሌሎች ነፍስ ጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጁ በመሆን እውነተኛ መጋቢ የሆነው መቼ ነበር? ማቴዎስ 26:75ዮሐንስ 21:15–17፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5:1 “ጴጥሮስ የሐዘኑን ሰው [ክርስቶስን] ክዶ ነበር። . . . ነገር ግን ከዚያ በኋላ ንስኃ በመግባት ተለወጠ። ስለ ነፍስ እውነተኛ ግንዛቤ ስላገኘ ለአዳኙ ራሱን እንደ አዲስ አስረከበ። . . . ከዚያም ለተፈተኑት ለመራራት ዝግጁ ሆነ። ራሱን አዋረደ ደግሞም ለደካሞችና ለሚሳሳቱት ሊራራላቸው ይችላል። ትዕቢተኞችን ማሳሰብና የሚዳፈሩትን ማስጠንቀቅ ይችላል ፤ እንዲሁም ወንድሞቹን ለማበረታታት ሙሉ በሙሉ ብቁ ሆነ። ”—Testimonies for the Church, vol. 3, p. 416. ለ. እንደዚሁም ዛሬ እያንዳንዱ ፓስተር እና የቤተ ክርስቲያን መሪ ምን ልምድ ሊኖረው ይገባል? ዮሐንስ 3፡1-3 “ኒቆዲሞስ ሊለወጥ የቻለው በዚህ የውይይት ውጤት ነው። የክርስቶስ ቃላት ለኮንፍራንስ ፕሬዘዳንቶች፣ ለቤተክርስትያናት ሽማግሌዎች እንዲሁም በተቋማችን ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊነት በተሰጣቸው አገልጋዮች ሁሉ የተሰጡ ናቸው፡- ‘እውነት እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም'፡፡ ”—Testimonies to Ministers, p. 369.“ ለዋጩ የእግዚአብሔር ኃይል በአገልጋዮች [በሚኒስተሮች] ልብ ላይ መፍሰስ አለበት፣ አለዚያ ሌላ ጥሪ መፈለግ አለባቸው። . . .“አገልጋዮቹ የተለወጡ ሰዎች ካልሆኑ፣ ቤተክርስቲያናት ክፉኛ በመታመም ለመሞት ዝግጁ ይሆናሉ። ”—Evangelism, p. 643.

2. በስልጣን ላይ ያሉትን መማፀን EXHORTING WITH AUTHORITY ሰኞ ሰኔ 10
ሀ. አንድን ሰው ለአገልግሎት ከመጥራቱ በፊት እና ግለሰቡ ጥሪውን ከመቀበሉ በፊት በቤተ ክርስቲያን ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ነገር ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 (የመጀመሪያ አጋማሽ)። “እርሱ እንደጠራቸው የማያሳስት ማስረጃ መኖሩ ሳይረጋገጥ ወደ ሥራው መስክ እንዲገቡ ሰዎችን ማበረታታት እንደማይገባ እግዚአብሔር ደጋግሞ አሳይቷል። ጌታ የመንጋውን ሸክም ብቁ ላልሆኑ ግለሰቦች አደራ አይሰጥም። አምላክ የሚጠራቸው ሰዎች የጠለቀ ልምድ ያላቸው፣ የተፈተኑና የተረጋገጡ፣ ትክክለኛ የማመዛዘንና የመፍረድ ችሎታ ያላቸው፣ በየዋህነት መንፈስ ኃጢአትን ለመገሠጽ የሚደፍሩ፣ መንጋውን እንዴት መመገብ እንዳለባቸው የሚረዱ ሰዎች መሆን አለባቸው።”—Testimonies for the Church, vol. 1, p. 209.“እንደ አማካሪ ኃላፊነቶችን የሚቀበል እያንዳንዱ ሰው፣ ከሰው ነፍስ ጋር የሚሰራ ሁሉ ሁሉ . . . በራሱ ግምት በጣም አነስተኛ መዘዝ እንዳለው እስኪደርስ ድረስ በፍፁም ጠቢብ ሊሆን አይችልም ። . . . ይህ ለውጥ ከአምላክ ቅዱስ ሥራ ጋር በተሳሰረ የመሪነትን ወይም የአስተዳዳሪነትን ኃላፊነት ከመቀበሉ በፊት በእያንዳንዱ ሰው መሆን ያለበት ነው።”—Testimonies to Min¬isters, pp. 370, 371. ለ. ጴጥሮስ በጌታ ወይን ቦታ የሚደክሙትን ስለ ምን አደጋ አስጠንቅቋቸዋል? 1ኛ ጴጥሮስ 5፡2 (ሁለተኛው ክፍል)። “አምላክ የሰጣቸውን የሌሎችን መብት ለማሳጣት በመወሰን ብዙ ደመወዝ የማግኘት ፍላጎት መነሻው ከሰይጣን አእምሮ ነው። . . . በደንብ ካልተለወጡና ካልታደሱ በስተቀር በዚህ ወጥመድ ውስጥ በተያዙ ሰዎች እምብዛም መታመን አስፈላጊ አይደለም።”—Ibid., p. 393.“በአደራ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎች የሚይዙትን ሀብት እንደ እግዚአብሔር ሀብት አድርገው ሊቆጥሩትና ጥበብ በተሞላበት መንገድ ሊጠቀሙበት ይገባል። . . .“የጌታን ገንዘብ የመጠቀምና የማውጣት ሥልጣን በአንድ ሰው ፍርድ ብቻ የሚቀር አይደለም። ለወጣ እያንዳንዱ ገንዘብ ሂሳብ ማወራርድ አለበት። የአምላክን ገንዘብ በተገቢው ጊዜና ቦታ ሊያዉል ይገባል።”—Medical Ministry, p. 165 ሐ. ምንም እንኳን ለጌታ መሥራት ብዙ የሚያስከፍል ሥራ ባይሆንም ቤተ ክርስቲያን ምን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባት? 1ኛ ጢሞቴዎስ 5:17፣ 18 “በተቋሞቻችን ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰራተኛ ፍትሃዊ ካሳ ማግኘት አለበት። ሰራተኞቹ ተስማሚ ደሞዝ ከተቀበ፣ ለጉዳዩ መዋጮ በማድረግ ደስተኞች ናቸው። አንዳንዶች ከፍተኛ መጠን፣ ሌሎች ደግሞ አስፈላጊና ታማኝ የሆኑ ሥራዎችን የሚያከናውኑት በጣም ጥቂት መቀበላቸው ትክክል አይደለም።”— The Publishing Ministry, p. 239.

3. ትሑት የሆነ አመለካከት ያስፈልጋል ማክሰኞ ሰኔ 11
ሀ. በከባድ የኃላፊነት ቦታ ላይ ባሉ ወንድሞች መካከል የችግር መንስኤ ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 5:3፤ 3ኛ የዮሐንስ መልእክት 9 “የመግዛት መንፈስ በዩኒየኖቻችን ፕሬዚዳንቶች መካከል እየሰፋ ነው። አንድ ሰው በራሱ ሥልጣን ላይ የተመሠረተ ከሆነና በወንድሞቹ ላይ የበላይነትን ለመያዝ የሚፈልግ ከሆነ፣ መሻቱን የመግዛት ሥልጣን እንዳለው ከተሰማው፣ የራሱንና የሌሎችን ነፍስ ላይ ትልቅ ጉዳት እንዳይደርስበትና እርሱም እንዳይጠፋ ታላቅና ብቸኛው አስተማማኝ መንገድ እርሱን ከሥልጣኑ ማስወገድ ነው። የራሱን ነፍስ ያጣል እንዲሁም የሌሎችን ነፍስ ያሰቃያልና።”—Testimonies to Ministers, p. 362. ለ. ለመላው የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና ሽማግሌዎች ምን ዓይነት ጥሪ ተሰጥቷል፣ ይህም፣ ከተከተሉት በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ ባሉ ወንድሞች መካከል ያለውን ኩራት እና በራስ የመተማመን መንፈስ የሚያስወግደው እንዴት ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 5:2 (የመጀመሪያ ክፍል); 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡2-5 “በባትል ክሪክ ልዩ ሀላፊነት ቦታ ላይ ያሉ ወንዶች ከተራ ሰዎች እጅግ የላቀ ጥበብ አላቸው ብሎ ማሰብ ስህተት እንደሆነ አይቻለሁ። . . .“ብዙዎች ወደ አስቸጋሪ ቦታዎች ሲመጡ ምክር እንዲጽፉ ወይም እንዲጠይቁ ራሳቸውን አስተምረዋል። ነገር ግን በተለያዩ ተቋሞቻችን ውስጥ በኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡ ሰዎች በሰዎች ላይ ጥገኛ መሆናቸው ስህተት ነው። . . . ደካማ፣ አቅመ ቢስ የሚሆኑ ሰዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ በሌሎች ላይ የሚመኩ ናቸው። . . .“በባትል ክሪክ ያሉ ሰዎች ወደር የሌለው ጥበብ እንዳላቸው ይቆጠራሉ?”—Ibid., pp. 374, 375.“ለብርታት እንዲሆናችሁ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ያሉትን ሰዎች አትመልከቱ፣ ምክንያቱም እነርሱ የእግዚአብሔር ልዩ ኃይል እንደ ሆነ አድርገው የኃላፊነት ቦታን የመቁጠር አደጋ ላይ ያሉ ሰዎች ናቸውና። ቤተ ክርስቲያናችን ደካማ የሆነችው አባላቶቹ የተማሩት በሰው ኃይል ላይ መረኮዝን በመሆኑና ብዙ ሺህ ዶላሮችን ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በማጓጓዝ አነስተኛ ችግሮችን ለመፍታት አላስፈላጊ ወጪ በመውጣቱ ነው።”—Ibid., p. 380. ሐ. ብዙ ልምድ ያላቸዉ ሰራተኞች ለስኬት የበለጠ ግንዛቤን እንዲያገኙ የሚረዳዉ ምንድን ነዉ? ይህ ጉድለት ውድቀት ሲያስከትል አንድ ምሳሌ ስጥ። 1ኛ ጴጥሮስ 5:5 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ 1ኛ ነገሥት 12:6–8፣ 16፤ ሉቃስ 6፡39 “ወጣቶቹ ኩራታቸውንና ራስ ወዳድነታቸውን ትተው ራሳቸውን ለአምላክ ካስገዙ ኃይለኛ ተጽዕኖ ማሳደር ይችላሉ።”— Testimonies for the Church, vol. 1, p. 485“ወጣቶቹ ሊረዷቸው የሚፈልጉ ሰዎች በሚያደርጓቸው ጥረቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሊማር የሚችል መንፈስ እንዲያዳብሩ ያስፈልጋል።”—The Youth’s Instructor, August 31, 1893.

4. የጴጥሮስ የትህትና (ራስን ያዋረደ) ምሳሌ ረቡዕ ሰኔ 12
ሀ. የአንድ ጊዜ እውነተኛ መለወጥ ወይም ከአምላክ ጋር ያለ ተሞክሮ፤ ለአንድ ፓስተር ወይም ለማንኛውም አማኝ በቂ እንዳልሆነ እንዴት እናውቃለን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13:5፤ ዕብራውያን 3፡13 “ጴጥሮስ ከጊዜ በኋላ አንጾኪያን በጎበኘ ጊዜ፣ ከአህዛብ ለመጡ ሰዎች ባሳየው አስተዋይነት የብዙዎችን እምነት አተረፈ። ለተወሰነ ጊዜ ከሰማይ በተሰጠው ብርሃን መሠረት ተገበረ። ከአሕዛብ ከተመለሱት ሰዎች ጋር በማዕድ ለመቀመጥ ያለበትን ተፈጥሯዊ ጭፍን ጥላቻ እስከዚያ ድረስ አሸንፎ ነበር። ነገር ግን ለሜዳዊው ሥርዓት ሕግ የሚቀኑ አንዳንድ አይሁዳውያን ከየሩሳሌም በመጡ ጊዜ ጴጥሮስ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና እምነት በተለወጡ ሰዎች ላይ የነበረውን አመለካከት ማስተዋል በጎደለው ምግባር ለወጠው። . . . ይህ የደካማነት ባህርይ እንደ መሪነት ላቅ ያለ ክብርና ተወዳጅነት በሚኖራቸው መሪዎች ዘንድ በይፋ መታየቱ ከአህዛብ ወደ ክርስትና በተለወጡት አዕምሮ ላይ እጅግ በጣም ህመም የሚፈጥር ጠባሳ አሳረፈ፡፡ ቤተክርስቲያኗም የመከፋፈል ስጋት ተጋረጠባት።.”—The Acts of the Apostles, pp. 197, 198. ለ. አንድ ስህተት ሲፈጠር፣ ወይም በአገልጋዩ፣ ወይም በወንጌላዊዩ፣ ወይም በቤተ ክርስቲያን መሪው አማካኝነት ወደ ቤተክርስቲያን ግልጽ የሆነ ዓመጽ ወይም ውዝግብ እንዲፈጠር ቢያደርግ ሊወገዙ የሚገባቸው እንዴት ነው? ገላትያ 2:14; 1 ጢሞቴዎስ 5:20 ሐ. በይፋ ወይም በሰዎች ፊት በሚገሰጽበት ጊዜ የተለወጠ መሪ ባህርይ ምን መሆን አለበት? 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5 (ሁለተኛ ክፍል)፣ 6፤ ያእቆብ 5:16 “ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ የፈፀመው ሁለት ገጽታ በቤተክርስቲያን ሊያደርስ የሚችለውን የአፍራሽነት ተጽዕኖ የተመለከተው ጳውሎስ፣ በዚህ ሁኔታ እውነተኛ ስሜቱን ይፋ ለማውጣት በህዝብ ፊቴ በይፋ ገሰፀው፡፡ ጳውሎስ በቤተክርስቲያን አካላት ፊት ጴጥሮስን ጠየቀው። . . .“ጴጥሮስም የወደቀበትን አደጋ ተገነዘበ ፤ ወዲያውኑም በእርሱ አቅም ሥር እስካለ ድረስ የተፈፀመውን ጥፋት ለማስተካከል ተነሣ። የመጨረሻውን ከመጀመሪያው የሚያውቀው እግዚአብሔር፣ በፈተናዎች የተሞረደው ሀዋሪያ ሊኮራበት የሚችልበት ምንም ነገር በራሱ እንደሌለው ይመለከት ዘንድ ጴጥሮስ ይህን የባህርይ ድክመት ይገልጥ ዘንድ ፈቀደ፡፡ ከሰዎች መካከል እጅግ ምርጥ የሚባሉት ለራሳቸው ከተተው በፍርጃቸው ይሳሳታሉ። . . .“ይህ ከትክክለኛ መርሆዎች የማፈንገጥ ታሪክ በእግዚአብሔር ጉዳይ እምነት በሚጣልበት የኃላፊነት ቦታ ለተቀመጡ ሰዎች አስፈሪ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ቆሞአል፡፡. . . በሰብዓዊው ወኪል ላይ ታላቅ ኃላፊነት በተሰጠው መጠን፣ ለመወሰንና ለመቆጣጠር ያለው እድል እጅግ ከፍ እያለ በሄደ መጠን፣ የበለጠ ጉዳት ማደረሱ የተረጋጠ ይሆናል።”—Ibid., pp. 198, 199.

5. ለደከሙ ሰራተኞች ማበረታቻ ሐሙስ ሰኔ 13
ሀ. በወንጌል ሠራተኛ ሕይወት ውስጥ ብዙውን ጊዜ የተስፋ መቁረጥ መንስኤ ምንድን ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 5፡5 (የመጨረሻው ክፍል)። “በልምድ የደከሙ፣ የክርስቲያን ጸጋዎች ጉድለት ያለባቸው፣ መቀደስ የሚጎድላቸው እና በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጡ ስሜታቸው የሚነካባቸው በጣም ብዙ አገልጋዮች አሉን። . . . የሱስ የተወላቸው ውርስ አካል መሆኑን አውቀው በችግርም ሆነ በፈተና የማያጉረመርሙ ወይም የማይሰላቹ ሰዎች በዚህ ሥራ ይፈለጋሉ። ከአከባቢያቸው ውጭ ሄደው ነቀፋ ሊደርስባቸውና እንደ ጥሩ የክርስቶስ ወታደሮች ሸክሞችን ሊሸከሙ ፈቃደኞች መሆን አለባቸው።”—Testimonies for the Church, vol. 3, p. 423. ለ. ሰይጣን ማናችንም ብንሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ችግሮችን በመጠቆም ተስፋ ሊያስቆርጠን ሲሞክር ከምን ቃል ኪዳን ጋር መጣበቅ አለብን? 1ኛ ጴጥሮስ 5:4፣ 7 “እግዚአብሔር እንደሚሰማንና እንደሚመልስልን በማያወላውል እምነት በማመን ልመናችንን በየሱስ ስም ከማቅረብ ምንም አይከለክልን። ራሳችንን በፊቱ እያዋረድን ችግራችንን ወደ እግዚአብሔር እናምጣ። ታላቅ ሥራ አለ፤ አብረን መመካከር፤ ያለን እድል ቢሆንም፣ በሁሉም ጉዳይ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመምከር በጣም እርግጠኛ መሆን አለብን፣ እርሱ ፈጽሞ አያሳስተንም። ሥጋን ክንዳችን ማድረግ የለብንም። ካደረግን . . . አለማመን ይገባና እምነታችንም ይሞታል።”—Testimonies to Ministers, p. 487“የእውነተኛው እረኛ መንፈስ ራስን መርሳት (መስዋት) ነው። የእግዚአብሔርን ሥራ ይሠራ ዘንድ ራስ ወዳድነት መተው አስፈላጊ ነው። . . . ከታላቁ ሸክም ተሸካሚ ጋር ስንተባበር መከራችንን ይካፈላል፣ ችግራችንም ያጽናናል፣ የነፍሳቸውን ረሃብ ያስታግሳል እንዲሁም ልባችንን ለአምላክ ያነሳሳል።”— The Acts of the Apostles, p. 527.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ሰኔ 14
1. ለመጨረሻ ጊዜ በእንባ በመስቀሉ ስር የተንበረከኩት መቼ ነበር? 2. ከፍ ያለ ቦታ ካገኘሁ ለጌታ የበለጠ መስራት እንደምችል በሆነ መንገድ አስብ ይሆን? 3. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፍ ያለ ቦታ የማግኘት ዓላማ ወደ አእምሮዬ መግባት የሌለበት ለምንድን ነው? 4. ስህተቶቼን ለሚያመለክቱ ሰዎች ያለኝ አመለካከት ምንድን ነው? 5. ለተስፋ መቁረጥ ጊዜዬ እንደ ጥፋተኛ የማየው ማንን ነው?
 <<    >>