ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ << >> መቅድም የያዕቆብ መልእክት ቀጥተኛ ነው። በውስጡ ያሉትን መልእክቶች ምን ያህል አስፈላጊ ናቸውን! ስለዚህ፣ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የያዕቆብ መልእክት ያጠናሉ። በዚህ ጥናት ስለአንደበት (በጥሩም ሆነ በክፉ)፣ በእምነት ለእግዚአብሔር ስለመታዘዝ፣ የጸሎት ሃይል እና ከኤልያስ ምሳሌ የሚገኙ ጠቃሚ ነጥቦች ጥቂቶቹ ቁልፍ ርዕሶች ናቸው። ዛሬ ይህ ሁሉ ጠቃሚ የሆነው ለምንድነው? “የዚህ ዘመን ኃጢአት የእግዚአብሔርን ግልጽ ትእዛዛት ችላ ማለት ነው። ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚመራ ኃይል በጣም ትልቅ ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 3, p. 483. ሆን ብለው የአምላክን መርሆች እየጣሱ ቅዱሳን ሊሆኑ እንደሚችሉ በማመን ራሳቸውን አያታልሉ። የታወቀውን ኃጢአት መደበቅ የመንፈስን የምሥክርነት ድምጽ ጸጥ ያደርገዋል እና ነፍስን ከእግዚአብሔር ይለያል። ‘ኃጢአት ሕግን መተላለፍ ነው።’ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም። 1ኛ ዮሃንስ 3:16።”—The Great Controversy, p. 472. “ዛሬ የከባድ ተግሣጽ ድምፅ ያስፈልጋል። ሕዝቡን ከእግዚአብሔር የለዩአቸው ከባድ ኃጢአቶች ናቸውና። ክህደት በፍጥነት ፋሽን እየሆነ ነው። 'ይህ ሰው በላያችን እንዲነግሥ አንፈልግም' የሚለው የሺህዎች ቋንቋ ነው። ሉቃስ 19፡14 ብዙውን ጊዜ የሚሰበኩት ለስላሳ ስብከቶች ዘላቂ ስሜት አይፈጥርም፤ መለከት ቁርጥ ያል ድምጽ እየሰጠ አይደለም፡፡ ሰዎች በእግዚአብሔር ቃል ግልጽ በሆነ፣ ስለታም እውነት በልባቸው አልተቆረጡም። “እውነተኛ ስሜታቸውን እንድገልጹ ቢጠየቁ ብዙ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች፣ እንዲህ በግልጽ መናገር ምን ያስፈልጋል? ይሉ ይሆናል፡፡ እንዲሁም መጥምቁ ዮሐንስ ለፈሪሳውያን፡- እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አስጠነቀቃችሁ? ሉቃስ 3፡7 ሄሮድስን ከወንድሙ ሚስት ጋር መኖር ክልክል እንደሆነ በመንገር የሄሮድያዳ ቁጣን ማስንሳትስ ለምን አስፈለገ? የክርስቶስን መንገድ ጠራጊ የሆነው በግልፅ በመናገሩ ህይወቱን አጥቷል። በኃጢአት ውስጥ የሚኖሩትን ሰዎች ሳያስከፋቸው አብሮ መሄድ ያልቻለው ለምንድን ነው? “ስለዚህ የአምላክ ሕግ ታማኝ ጠባቂዎች ሆነው መቆም ያለባቸው ሰዎች ፖሊሲ ታማኝነት እስኪተካ ድረስ፣ ኃጢአትም ሳይቀጣ እንዲቀር እስኪፈቀድ ድረስ ለምን ዝም ይላሉ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የታማኞች ተግሣጽ ድምፅ የሚሰማው መቼ ነው?”—Prophets and Kings, pp. 140, 141. እንዲያውቁ ፣ ክርስቲያናዊ ጠባይ እንዲኖራቸውና በእውነት እንዲነጹ በቂ ዝግጅት ተደርጎላቸዋል።”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 644. በእርግጥም የአምላክን እርዳታ እንፈልጋለን፤ እንዲሁም “ለማንኛውም በእምነት ለሚጸልዩት ጸሎት ሁሉ መልስ እንደሚሰጥ በግልጽ እርግጠኞች ነን። መልሶቹ እኛ እንደጠበቅነው ላይመጡ ይችላሉ፤ እነሱ የሚመጡት ምናልባት እንዳሰብነው ሳይሆን በጣም በምንፈልጋቸው ጊዜ ነው።”—Ibid., vol. 3, p. 209. አሜን! የአጠቃላይ ኮንፈረንስ ሰንበት ትምህርት ቤት መምሪያ << >>