ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ << >> የመጀመሪያ ሰንበት ለኮሎምቢያ ዩኒየን ዋና መሥሪያ ቤት ሰንበት፣ ህዳር 28፣ 2017 ኮሎምቢያ በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ ሀገር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ51 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አሉት። ኢንዱስትሪዎች ነዳጅ፣ ማምረቻ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ኮንስትራክሽን፣ ግብርና፣ ባንክና አገልግሎቶችን በማቅረብ ይታወቃል። ከሕዝቡ መካከል 73% ካቶሊኮች፣ 9.1% የክርስትና እምነት ተከታዮች ያልሆኑት ሲሆን፣ 6.9% ወንጌላውያን፣ 6.5% ሃይማኖት የሌላቸውም፣ 2.9% ፕሮቴስታንቶች፣ እና 0.9% አምላክ የለሽ እንደሆኑ ይናገራሉ። ይህ ሁኔታ እዚህ ላለችው የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ትልቅ ፈተና እንዳለባት ያሳያል። በ1960ዎቹ የሦስተኛው መልአክ መልእክት ኮሎምቢያ ደረሰ። በዚህ ግርግር መሃል ቤተክርስቲያኑ በይፋ በተመዘገበበት በ1971 ዓ.ም 100 ያህል አባላት ደርሰናል። በዚያን ጊዜ ሠራተኞቹ ጥቂት ነበሩ፣ ነገር ግን ለሚወዱት ዓላማ ሁሉንም ነገር ለመስጠት ድፍረትና ቅንዓት ነበራቸው፡፡ ሀገራቸውንና የምቾት ኑሯቸዉን ትተው በሙሉ ልባቸው በኮሎምቢያ ያለውን ስራ ለመደገፍና እዚህ መልእክቱን ለማሰራጨት በደስታ የመጡትን ፓስተሮችና አገልጋዮችን ላደረጉት ነገር ሁለም እናመሰግናለን። በእግዚአብሔር ቸርነት በ2006 የኮሎምቢያ ህብረት የተደራጀ ሲሆን ዛሬ ሶስት ፊልዶች አሉት፡፡ የእኛ ዩኒየን ዋና መስሪያ ቤት በባርቦሳ፣ ሳንታንደር ማዘጋጃ ቤት ገጠራማ አካባቢ ይገኛል። ወንድሞቻችንንና ለእውነት ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ለማገልገል በዛሬው ጊዜ ያሉትን አገልግሎቶች ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን እናስተውላለን። በአሁኑ ጊዜ፣ ቢሮዎቻችን፣ ሚሲዮናዊ ትምህርት ቤቶቻችንና መልቲሚዲያ ክፍል የሚሰሩበት መሬት አለን። እዚህ ለአባሎቻችንና ለመልእክቱ ፍላጎት ላላቸው አዲስ ጉባኤዎች፣ ሴሚናሮችና መንፈሳዊ ጉዞዎችን (Retreats) እናስተናግዳለን። የመሠረተ ልማት አውታሩ በከፊል በዚህ ንብረት ላይ ተገንብቷል፣ እና ተጨማሪ መገልገያዎች ግንባታ በአሁኑ ጊዜ በሂደት ላይ ናቸው፣ ነገር ግን እነሱን ለመጨረስ የሚያስችል ግብዓቶች ይጎድለናል። ለዚያም ነው በዓለማችን ላሉ ሰፊ ቤተሰብ ለሆኑት ቤተ ክርስቲያናት ልግስና የምንለምነው። የልግስና ሥጦታችዎ ድጋፍ የጌታን እውቀት የተራቡ ነፍሳትን ለማገልገል የበለጠ ተስማሚ መገልገያዎች እንዲኖረን ያስችለናል። የእርስዎን ልገሳ በጣም እናደንቃለን። የእርስዎ ልገሳና ስጦታዎች ምን ያህል መልካም ነገር እንዳደረጉ ማየት የሚቻለው በፍርዱ ቀን ብቻ ነው። ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ ከኮሎምቢያ ዩኒየን << >>