ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ << >> ሰንበት ታህሳስ 19፣ 2017 13ኛ ትምህርት በኃይማኖት እስከመጨረሻ መጽናት መታሰቢያ ጥቅስ፡- “እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ ፤ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይፀልይ፡፡ የጻድቅ ሰው ፀሎት በሥራዋ እጅግ ታደርጋለች” (ያዕቆብ 5፡-16)፡፡ ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡ The Ministry of Healing, pp. 225–233; Testimonies for the Church, vol. 3, pp. 271–293. “ትሁትና ትጋት የሞላበት ፀሎት፣ ነፍስን ከሞት ያድናል ፤ መናዘዝና የህይወት መመለስ (ወደመጀመሪያው መመለስ) የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል፡፡”— The Review and Herald, December 16, 1902. 1. ተስፋ እሁድ ታህሳስ 13 ሀ. በየትኛው የባህርይ መገለጫ ነው ኢዮብ በተለየ ሁኔታ የታወቀው—ይህስ ስለ እግዚአብሔር ምን ይነግረናል ? (ያዕቆብ 5፡- 11) “የአስቸጋሪውን ሰው የኃጢአት ኑዛዜ ለመስማትና ንስኃውን ለመቀበል ጌታ በማይታክት ፍቅር እየተጠባበቀ ነው፡፡ እናት ከምትወደው ልጇ ለእናትነቷ የእውቅና ፈገግታ ለማየት እንደምትናፍቅ ሁሉ እርሱም ለውለታው የአመስጋኝነት መልስን ለማግኘት ከእኛ ይጠብቃል፡፡ ለእኛ ምን ያህል ልቡ እንደሚራራና ሰፍሰፍ እንደሚል እንናስተውል ዘንድ ይናፍቃል፡፡ በፈተናዎቻችን የእርሱን ርህራሄ፣ በድካማችን ጥንካሬውን፣ በባዶነታችን ሙሉነቱን እንወስድ ዘንድ ይጋብዘናል፡፡ ወደ እርሱ መጥቶ በሐዘን የተመለሰ አንድ ሰው እንኳ የለም፡፡‘ ወደ እርሱ ተመለከቱ ገጽታቸውም አበራ ፤ ፊታቸውም በሀፍረት አልተከደነም፡፡’ “ ለጌታ በሚስጥር መሻታቸውን በመንገር እና እርዳታውንም በመማፀን፣ እግዚአብሔርን የፈለጉ ሁሉ፣ ተማጽኟቸው ከንቱ ሆኖ አልቀረም፡፡”—Thoughts From the Mount of Blessing, pp. 84, 85. ለ. ያዕቆብ ታማኝነትን (እውነተኛነትን) አስመልክቶ የክርስቶስ ቃላት ያስተጋባው እንዴት ነው ? ያዕቆብ 5:12 ፤ ማቴዎስ 5:37. “ክርስቲያናት የሚያደርጉት እያንዳንዱ ነገር ልክ እንደ ፀሐይ ብርሃን የሚያንጸባርቅ መሆን አለበት፡፡”—Ibid., p. 68. 2. እውነተኛ እምነት ከድፍረት ጋር ሲነፃፀር (FAITH VS. PRESUMPTION) ሰኞ ታህሳስ 14 ሀ. በበሽታ ብንሰቃይ፣ እንዴትና ለምንድን ነው ወደ ህይወት ሰጪያችን ለመምጣት የምንደፋፈረው? ያዕቆብ 5:13–15 ፤ መዝሙር 103:1–3. “ እግዚአብሔር በሽተኛውን ወደ ሙሉ ጤንነት ለመመለስ መንፈስ ቅዱስ እነዚህን ቃላት በዘማሪው አማካይነት በተናገረበት ጊዜ ፈቃደኛ የሆነውን ያህል አሁንም ፈቃደኛ ነው፡፡ እንዲሁም ክርስቶስ ያኔ በምድራዊ የአገልግሎቱ ጊዜ እንደነበረው ዛሬም እንደዚያው ሩህሩህ ሃኪም ነው፡፡ በእርሱ ዘንድ ማንኛውንም ጉዳት ወደ ሙሉ ጤንነት መመለስ የሚችል ለእያንዳንዱ በሽታ የተዘጋጀ ፈዋሽ መድሃኒት (ቅባት) አለው፡፡ በዚህ ጊዜ የሚገኙ ደቀመዛሙርት፣ በጥንት ጊዜ የነበሩ ደቀመዛሙርት እንደፀለዩት እነርሱም ለበሽተኞች መፀለይ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚያም ፈውስ ይከተላል ፤ ምክንያቱም ‘የእምነት ፀሎት ድውዩን (በሽተኛውን) ያድናልና’፡፡ እኛ የእግዚአብሔርን ተስፋ ይገባናል ብለን መጠየቅ የምንችልበት፣ የተረጋጋው የእምነት ማረጋገጫ፣ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አለን፡፡፡፡ ‘እጃቸውንም በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ’ (ማርቆስ 16:18) በማለት ጌታ የገባው የተስፋ ቃል በሐዋሪያት ጊዜያት እንደነበረው ዛሬም የታመነ ነው፡፡”—The Ministry of Healing, p. 226. ለ. ጤንነትን ስንሻ ከምን ሚዛናዊነት ነው መጠንቀቅ ያለብን? መዝሙር 66:18. “እኛ [ለጌታ] ምህረት የተገባን አይደለንም ፤ ነገር ግን ራሳችንን ለእርሱ ስንሰጥ እርሱ ይቀበለናል፡፡ እርሱን በሚከተሉት በእነርሱና በእነርሱ በኩል ሥራውን ይሰራል፡፡“ነገር ግን ቃሉን በመታዘዝ ስንኖር ብቻ ነው ተስፋዎቹ እንዲፈፀሙልን መጠየቅ የምንችለው፡፡. . . ለእርሱ የምንሰጠው ታዛዥነት በከፊል፣ በሁለት ልብ ከሆነ፣ ተስፋዎቹ ሊፈፀሙልን አይችሉም፡፡”—Ibid., p. 227.“ክርስቶስ ይሰራበት የነበረው መንገድ ቃሉን መስበክና በተዓምራት ድውያንን መፈወስ ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን በዚህ መንገድ መስራት እንደማንችል መመሪያ ተሰጥቶኛል ፤ ምክንያቱም ሰይጣን ተዓምትራን በመስራት ኃይሉን ይጠቀማልና፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች አሁን በተዓምራት አማካይነት መሥራት አይችሉም ፤ ምክንያቱም መለኮታዊ ናቸው በማለት አስመሳይ የሆኑ የፈውስ ተዓምራቶች ይፈፀማሉና፡፡“በዚህ ምክንያት ሕዝቡ አካላዊ የፈውስ ስራን ከቃሉ ትምህርት ጋር አጣምረው የሚሰሩበትን መንገድ ጌታ ቀይሷል፡፡ የጤና ማገገሚያ የህክምና ጣቢያዎች (Sanitariums) መገንባትና በእነዚህ ተቋማት እውነተኛውን የህክምና ሚሽነሪ ስራን ወደጊት እንዲገፋ የሚያስችሉ ሰራተኞች ሊመደቡ ይገባል፡፡ ይህም ሲሆን ለህክምና ወደ እነዚህ የጤና ተቋማቱ (ጣቢያዎች) በሚመጡ ህሙማን ዙሪያ አስተማማኝ ተጽዕኖ ማሳደር ይቻላል፡፡“የወንጌል ህክምና አገልግሎት ለብዙ ሰዎች ይከናወን ዘንድ ጌታ ያዘጋጀው አቅርቦት ይህ ነው፡፡”—Medical Ministry, p. 14. 3. ሁለት የተለያዩ የድፍረት አይነቶች ማክሰኞ ታህሳስ 15 ሀ. በአሳዛኝ ሁኔታ ችላ ተብሎ ወደ ጎን የተገፈተረውን በጣም አስፈላጊውን ፈውስ ይጥቀሱ፡፡ ያዕ 5:16. “ የኃጢአት ኑዛዜ ማድረግ ክብራችንን ያዋርዳል፣ በባልንጀሮቻቸውም መካከል ያላቸውን ተጽዕኖ ያዳክማል ብለው የሚያስቡ ሰዎች በጣም በጣም ተሳስተዋል፡፡ ከዚህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ጋር በመጣበቅ፣ ስህተት መስራታቸውን ማየት እንኳ ቢችሉም፣ ነገር ግን ብዙዎቹ ከመናዘዝ ተደናቅፈው ይቀራሉ ፤ ይቁንም በሌሎች ላይ ያደረሱትን በደል እንዳላዩ ሁነው በማለፍ፣ የራሳቸውን ህይወት ክፉኛ መራራ ያደርጉታል ፤ በሌሎችም ሕይወት ላይ መጥፎ የጥላ ግርዶሽ ያሳርፉበታል፡፡ ኃጢአታችሁን መናዘዛችሁ ክብራችሁን አያወርደውም፡፡ ይህን የውሸት ክብር አሽቀንጥራችሁ ወዲያ ጣሉት፡፡ በአለቱ ወድቃችሁ ተሰበሩ ፤ ክርስቶስ ደግሞ እውነተኛውንና ሰማያዊውን ክብር ይሰጣችኋል፡፡ የተስፋ ቃሉ እንዲሰጠው መጠየቅ ይችል ዘንድ ኩራት፣ የራስ ክብር፣ ወይም የራስ ጽድቅ ኃጢአቱን ከመናዘዝ ማንንም ቢሆን አይከልክለው፡፡ ‘ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምህረት ያገኛል’ (ምሳሌ 28:13)፡፡ አንዳች ነገር ከእግዚአብሔር አትሰውሩ ፤ የሰራችሁትንም ጥፋት (በደል) ለወንድሞቻችሁ መናዘዛችሁን ችላ አትበሉ፡፡ ‘እርስ በርሳችሁ ኃጢአታችሁን ተናዘዙ ፤ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይፀልይ’ (ያዕቆብ 5:16)፡፡ መዝገቡ በመጨረሻው ቀን ኃጢአተኛውን ይጋፈጠው ዘንድ ብዙ ኃጢአት ንስኃ ሳይገባበት ችላ ተብሎ ቀርቷል ፤ የሚያስተሰረየው መስዋዕት ስለ አንተ (ስለ አንቺ) እየተማፀነ ባለበት አሁን፣ ኃጢአቶቻችሁን ፊት ለፊት ተጋፍጣችሁ ብትናዘዙትና ጨርሶም ብታስወግዱት በጣም የተሻለ ነው፡፡ በዚህ ርዕስ ላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከመማር አትውደቁ፡፡ የነፍሳችሁ ጤንነት እንዲሁም የሌሎችም ድነት (መዳን) በዚህ ነጥብ ላይ በምትከተሉት መንገድ ላይ የተማከለ ነው፡፡”—Selected Messages, bk. 1, pp. 326, 327. ለ. ስለ ህዝቡ መንፈሳዊ ክህደት በጣም ባሰበ ጊዜ፣ ኤልያስ ምን እርምጃ ነበር መውሰድ የቻለው —እግዚአብሔርስ የጠበቀው እንዴት ነው? 1ኛ ነገሥት 17፡-1–3. “ በአንድ ወቅት ተወዳጅ የነበሩ ሕዝቦቹን ከክፉ መንገዳቸው ይገታቸው ዘንድ፣ ከሰማይ ምን ያህል እንደራቁ በእውነተኛው ብርሃን ማየት እንዲችሉ ካስፈለገም በፍርድ እንዲጎኛቸው ኤልያስ በንፍስ ጭንቀት (ልቡን ጭንቀት ከብዶት) ፀለየ፡፡ በክፉ የኃጢአት ተግባራቸው መመለስ የማይችሉበት ርቀት በመድረስ እግዚአብሔር ፈጽሞ ያጠፋቸው ዘንድ ቁጣው እንዲቀጣጠል ከማድረጋቸው በፊት ንስሐ ሲገቡ ለማየት ነፍሱ አጥብቃ ናፈቀች፡፡. . . .“የሰማይን የፍርድ መልዕክት ለአክዓብ የማድረስ ተልዕኮ ለኤልያስ ተሰጠው. .፡፡ ከቤተመንግስቱ እንደደረሰ መምጣቱ እንዲነገርለት ወይም በይፋ ግባ እስኪባል አልጠበቀም፡፡ በዚያን ጊዜ የነበሩ ነብያት የሚለብሱትን ተራ ልብስ ለብሶ፣ ዘበኞቹ ልብ ሳይሉት አልፎ በደነገጠው ንጉሥ ፊት በድንገት ቆመ፡፡ ”—Prophets and Kings, pp. 120, 121. 4. ከኤልያስ መማር ረቡዕ ታህሳስ 16 ሀ. ከሐዲ የሆነውን የገዛ ህዝቡን ለመማነቃቃት ወደ እግዚአብሔር ያደረገው የኤልያስ ጸሎት ለእኛ ምሳሌ ሆኖ የተሰጠን ለምንድን ነው? ያዕቆብ 5:17 “ተማጽዕኖ፣ ምክርና ማስጠንቀቂያ በተደጋጋሚ ቢቀርብም እስራኤልን ወደ ንስሐ መመለስ አልቻለም፡፡ እግዚአብሔር በፍርድ አማካይነት መናገር የግድ የሚልበት ጊዜ ደረሰ፡፡ የበዓል አምላኪዎች የሰማይ ሐብት፣ ዝናብና ጠል ሁሉ የሚወርዱት ከጅሆባ ሳይሆን ነገር ግን ተፈጥሮን በሚቆጣጠሩ ኃይላት አማካይነት ነው ብለው ያመኑ እንደመሆናቸው፣ እንዲሁም ምድር በሐብቷ የበለፀገችውና የተትረፈረፈች ምርቷን በገፍ እየለገሰች ያለችው በፀሐይ የመፍጠር ኃይሏ ነው ብለው ሽንጣቸውን ገትረው እስከሞገቱ ድረስ፣ የእግዚአብሔር እርግማን በተበከለችው ምድር ላይ ክፉኛ ሊወርድ ነበር፡፡ ከሐዲዎቹ የእስራኤል ነገዶች ለጊዜያዊ በረከት ሲሉ በበዓል ኃይል መታመናቸው ምን ያህል ከንቱ እና ገልቱ (ሞኝነት) እንደሆነ ማየት ነበረባቸው፡፡ ተፀጽተው ወደ እግዚአብሔር ካልተመለሱና የበረከት ሁሉ ምንጭ እርሱ መሆኑን ካላመኑ በምድር ላይ ጠልም ሆነ ዝናብ አይወርድም፡፡”—Prophets and Kings, p. 120. ለ. እስራኤላዊያን ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ታማኝነት ካደሱ በኋላ፣ የኤልያስ ፀሎት በድጋሜ አርዓያ ሊሆነን የሚችለው እንዴት ነው? ያዕቆብ 5:18፤ 1ኛ ነገሥት 18:39–45. “[ኤልያስ] ስድስት ጊዜ በታላቅ ትጋት ፀለየ ፤ ሆኖም ተማጽዕኖው ተቀባይነት ስለማግኘቱ የታየ ምልክት አልነበረም ፤ ነገር ግን ወደ ፀጋው ዙፋን ተማጽዕኖውን በጠንካራ እምነት ማቅረቡን ቀጠለ፡፡ ተስፋ በመቁረጥ ፀሎቱን በስድስተኛው ዙር ቢያቆም ኖሮ፣ ተማጽዕኖው ባልተመሰለት ነበር፡፡ እርሱ ግን መልሱ እስኪመጣለት ድረስ ፀንቶ ቀጠለ፡፡ ለምናቀርበው ተማጽዕኖ ጀሮዎቹ በፍፁም የማይዘጉ አምላክ አለን ፤ እናም የቃሉን እውነታነት ማረጋገጥ (መፈተን) ከቻልን፣ እርሱ እምነታችንን ያከብረዋል፡፡ ፍላጎቶቻችን ከእርሱ ፍላጎቶች ጋር ድርና ማግ አድርገን እናስተሳስራቸው ዘንድ ይሻል ፤ ያኔ ያለ አንዳች ስጋት ይባርከናል ፤ ምክንያቱም በረከቶቹ የእኛ በሚሆኑበት ጊዜ ክብሩን ለራሳችን መውሰድን ትተን ውዳሴን ሁሉ ለእርሱ የምናቀርብ እንሆናለንና፡፡ እግዚአብሔር በጸሎታችን ስሙን በጠራንበት በመጀመሪያ ሁልጊዜ አይመልስልንም ፤ ምክንያቱም ይህን ቢያደርግ እርሱ በእኛ ላይ አትረፍርፎ የቸረንን ባርኮቶችና ጸጋውን እንደ መብት የምንቆጥረው እንሆናለንና፡፡ ይህ ከሆነ፣ ያስተናገድነው አንዳች ክፉ ነገር (ክፋት) ይኖር ይሆን ብለን ልባችንን መመርመር ሲገባን፣ ግድየለሾች እንሆናለን ፤ እርዳታው እንደሚያሻንና በእርሱ ላይ መተማመን እንዳለብን መገንዘብ ይሳነናል፡፡“ኤልያስ ክብሩን ለራሱ መውሰድ እንደሌለበት ጨርሶ መገንዘብ ወደሚችልበት ሁኔታ እስኪደርስ ድረስ ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡ ጌታ ለጸሎት መልስ የሚሰጥበት ቅድመ ሁኔታ ይህ ነው ፤ ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ውዳሴን ለእርሱ እናበረክታለንና፡፡”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 2, pp. 1034, 1035. 5. ክርስቶስን መሳይ ደግነት ማጎልበት (ማስፋፋት) ሐሙስ ታህሳስ 17 ሀ. በጠማማ ሰዎች አማካይነት በወደቀው ዓለም መከፋትና ሐዘን በላያችን ላይ ቢወረድም፣ ያዕቆብ ለእኛ የሚያስተላልፈውን ደብዳቤ (መልእክት) በምን ተማጽዕኖ ነው የዘጋው? ያዕቆብ 5፡-19፣ 20. “ በስህተት ለወደቁ ሰዎች ምንም ቢሆን ተስፋ አስቆራጭ ምክንያት መሆን የለብህም፡፡ በፈሪሳዊ ልበ-ደንዳናነት ወንድምህን ከመጉዳት መቆጠብ አለብህ፡፡ ልብን የሚያደማ መራራ አሽሟጣጭነት በአዕምሮና በልብ ውስጥ ብቅ እንዲል መፈቀድ የለበትም፡፡ ስትናገር በድምጽህ ውስጥ ትንሽም ቢሆን የንቀት ወይም የማንቋሸሽ ድምጽ መሰማት የለበትም፡፡ የራስህን ንግግር የምታደርግም ከሆነ ትንሽም እንኳን የቸልተኝነት፣ የጥርጣሬ ወይም ያለማመን ሁኔታ ካሳየህ የአንድ ነፍስን መጥፋት የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ይህ ወንድም እንደ ታላቁ ወንድሙ (ክርስቶስ) ልብ ዓይነት ርኅራሄ በማሳየት የእርሱን ሰብዓዊ ልቡን የሚነካ ወንድም ነው የሚፈልገው፡፡ በመሆኑም ይህን ወንድህን በርህራሄ በተሞላ አጥብቆ በሚጨብጠው እጅና በሹክሹክታ እንጸልይ በሚል ድምጽ እንዲሰማ አድርገው፡፡ እግዚአብሔር ለሁለታችሁም የበለፀገ የህይወት ተሞክሮ ይሰጣችኋል፡፡ ፀሎት እርስ በእርስ እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር እንድንቆራኝ ያደርገናል፡፡ ፀሎት የሱስ ከጎናችን እንዲቆም በማድረግ፣ ለደከመውና ለተጨነቀው ነፍስ ዓለምን፣ ሥጋን እና ዲያብሎስን ማሸነፍ የሚችልበት አዲስ ብርታት ይሰጠዋል፡፡ ጸሎት የሰይጣንን የጥቃት ኃይል አሽመድምዶ ያባርረዋል፡፡“አንድ ሰው፣ ከሰብዓዊ ፍጡር ጉድለቶች ዘወር ብሎ፣ ወደ የሱስ የሚመለከት ከሆነ በባህሪይው ላይ ፍፁም መለኮታዊ ለውጥ ይፈጠራል፡፡ በልብ ላይ የሚሰራው የክርስቶስ መንፈስ ከራሱ ከየሱስ ምስል ጋር ያስማማዋል፡፡ እንግዲያውስ ጥረታችን ሁሉ የሱስን ከፍ ከፍ ለማድረግ ይሁን፡፡ የአይምሯችንን አይኖች ሁሉ ‘የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ እግዚአብሄር በግ’ (ዮሐ 1፡-29) ላይ የሚያነጣጥሩ ይሁኑ፡፡ በዚህ ዓይነቱ ላይ ሥራ ስንጠመድ ‘ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ ሰው ነፍሱን ከሞት ያድነዋል ፤ ብዙ ኃጢአትንም ይሸፍናል’ የሚለውን ቃል ልናስታውስ ይገባል (ያዕ 5:20) . . .፡፡“በእግዚአብሔር ይቅርታ ስህተት ፈፃሚው ፍቅር ወደሆነው ወሰንየለሽ አምላክ ልብ እየቀረበ ይመጣል፡፡ መለኮታዊ የርህራሄ ሞገድ ወደ ኃጢአተኛው ነፍስ ያልፍል ፤ ከእርሱም ወደሌሎች እየተላለፈ ይሄዳል፡፡ ”—Christ’s Object Lessons, pp. 250, 251. የግል ክለሳና የመያያ ጥያቄዎች አርብ ታህሳስ 18 1. እግዚአብሔርን አትረፍርፎ ያበዛልኝን ምህረቱን በህይወቴ ማየት የቻልኩት መቼ ነው 2. የራሴን ጤንነት አስመልክቶ በምን ሁኔታ ነው በመዳፈር ጥፋተኛ ልሆን የምችለው? 3. ኤልያስ ስለ ሕዝቡ የፀለው ፀሎት እንዴት (በምን ሁኔታ) ነበር ሊመለስለት የቻለው ? 4. ኤልያስ ዝናቡ ይመለስ ዘንድ ኤልያስ ብዙ ጊዜ መፀለይ ያስፈለገው ለምንድን ነው ? 5. ለማን ነው ብዙ የርህራሄ አመለካከት ሊኖረኝ የሚገባው ለምን? << >>