ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ << >> ሰንበት፣ መስከረም 25፣ 2017 1ኛ ትምህርት የእግዚአብሔር መልእክት በያዕቆብ በኩል የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “የእግዚአብሔርና የጌታ የየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለአሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡” ያዕቆብ 1፡1 ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡ Testimonies for the Church, vol. 9, pp. 190–203. በእያንዳንዱ ልማድና አስተሳሰብ ፍጹም የሆነ ሰው ወይም ሕዝብ የለም። አንዱ ስለሌላው መማር አለበት። ስለዚህ እግዚአብሔር የተለያዩ ብሔረሰቦች እንዲቀላቀሉ፣ በፍርድ አንድ እንዲሆኑ፣ በዓላማም አንድ እንዲሆኑ ይፈልጋል። በዚያም በክርስቶስ ውስጥ ያለው አንድነት በምሳሌነት ይገለጻል።”—Testimonies for the Church, vol. 9, pp. 180, 181. 1. የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት እሁድ መስከረም 19 ሀ. ከክርስቶስ ጋር የተቆራኙት “ያዕቆብ” የተባሉት ሦስቱ ሰዎች እነማን ነበሩ? ብዙውን ጊዜ የምናስተውለው የትኛውን ነው? ማቴዎስ 10:2፣ 3፤ 13፡55። ለ. የዮሐንስ ወንድም ያዕቆብ ከየሱስ ጋር ያሳለፉትን አንዳንድ ልዩ ጊዜዎች ጥቀስ። ሉቃስ 8:51-55፤ ማቴዎስ 17:1፣ 2፤ ማርቆስ 14:32-34 “የዘብዴዎስ ልጅ ዮሐንስ ክርስቶስን ከተከተሉት የመጀመሪያ ሁለት ደቀ መዛሙርት አንዱ ነበር። እርሱና ወንድሙ ያዕቆብ ሁሉን ነገር ትተው ክርስቶስን ለማገልገል ከተከተሉት ከመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሐዋርያት መካከል ነበሩ። እነዚህ ሁለት ወንድማማቾች ከየሱስ ጋር ለመሆን ሲሉ ያለ አንዳች ቅሬታ ቤታቸውንና ወዳጆቻቸውን ሁሉ ትተዋል፣ ከእርሱ ጋር ተጉዘዋል፣ ተጫውተዋልም፣ እንደዚሁም በግል ቤትና በአደባባይ ከእርሱ ጋር ተገኝተዋል። የሱስም ልባቸው ከእርሱ ልብ ጋር እስኪጣመር ድረስ ፍርሃታቸውን አስወገደላቸው፣ ከአደጋ አዳናቸው፣ ሥቃያቸውን አስወገደላቸው፣ ባዘኑ ጊዜ አጽናናቸው፣ በትእግሥትና በርህራሄም አስተማራቸው። እነርሱም ለእርሱ በነበራቸው የጋለ ፍቅር በመንግሥቱ ወደ እርሱ ተጠግተው የመቀመጥ ፍላጐት አደረባቸው።”—The Desire of Ages, p. 548.“ከአትክልቱ ቦታ መግቢያ ሲደርሱ የሱስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ሶስቱን አስከትሎ ሲገባ የቀሩትን ለእርሱና ለራሳቸው እንዲጸልዩ አዘዛቸው። የሱስ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ በአትክልቱ ውስጥ ወደሚገኝ ልዩ ቦታ ገባ። እነዚህ ሶስቱ ደቀ መዛሙርት የየሱስ የቅርብ ጓደኞች ነበሩ። እነዚህ ሶስቱ የሱስ በተለወጠበት ተራራ ላይ ክብሩን አይተዋል፣ ሙሴና ኤልያስ የሱስን ሲያነጋግሩት ተመልክተዋል፣ ከሰማይ የወረደውን ድምጽም ሰምተዋል፣ አሁን ደግሞ በዚህ ታላቅ የትግል ወቅት የሱስ በአጠገቡ እንዲሆኑለት ፈለገ።”—Ibid., p. 686. 2. ዋንጫውን (ጽዋዉን) መጠጣት ሰኞ መስከረም 20 ሀ. የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ የነበራቸውን ዋና ዓላማቸዉን ግለጽ። ማርቆስ 10፡35-38 “አጋጣሚዉን ባገኘ ቁጥር ሁሉ ከአዳኙ ቀጥሎ ባለ ቦታ ላይ ይቀመጥ ነበር፣ እንዲሁም ያዕቆብም ከእርሱ ጋር ባለው የቅርብ ግንኙነት መከበርን ይፈልግ ነበር።“እናታቸው የክርስቶስ ተከታይ ነበረች፣ እንዲሁም በነጻ ታገለግለው ነበር። እናት ለልጆቿ ባላት ፍቅር እና ምኞት በአዲሱ መንግሥት ውስጥ እጅግ የተከበረ ቦታን ትመኛላቸው ነበር። ለዚህም እንዲጠይቁ አበረታታቻቸው።“እናትና ልጆቿ በአንድነት ወደ የሱስ መጡ፣ በልባቸው ያደረዉን መሻት እንዲሰጣቸው ጠየቁት።ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? ሲል ጠየቀ የሱስ።“እናቲቱም መለሰች፡- እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ ሌላውም በግራ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ ስጣቸው።“በልባቸው ውስጥ የነበረውን ስሜት ስላነበበ ስለ እርሱ የነበራቸውን የፍቅር ጥልቀት አወቀ። ምንም እንኳን ሰብአዊ ፍጡራን በመሆናቸው ምክንያት በዓለማዊነት ቢጐድፍም ለእርሱ የነበራቸው ፍቅር ከራሱ ከየሱስ ከአዳኝነት ፍቅሩ የፈለቀ እንጂ ተራ ሰብአዊ ፍቅር አልነበረም። ስለዚህ የሱስ ይህን ዓይነት ፍቅር ጥልቀት ያለውና የጠራ እንዲሆን ያደርገዋል እንጂ በመገሰጽ አያቀዘቅዘውም። «እኔ የምጠጣውን (የመከራ) ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን? እኔስ የምጠመቀውን ጥምቀት መጠመቅ ትችላላችሁን? » ሲል የሱስ ጠየቃቸው። ስለ ፈተናና ስቃይ የተናገራቸው ምስጢራዊ ቃላት ትዝ ቢላቸውም በልበ ሙሉነት «አዎ፣ እንችላለን» አሉ። በጌታቸው ላይ የሚደርስበትን ሁሉ በመካፈል ታማኝነታቸውን መግለጽ እንደ ከፍተኛ ክብር የሚቆጥሩት ነገር ነበር።በፊቱ በዙፋን ፈንታ መስቀልና ሁለት ወንጀለኞች አንዱ በቀኙ፣ ሌላው በግራው ሲሰቀሉ እየታየው «በእርግጥ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ? እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ?» አላቸው።”—The Desire of Ages, pp. 548, 549. ለ. ልክ ክርስቶስ አስቀድሞ እንደተናገረው፣ ከጌታ ዕርገት በኋላ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ ምን ሆነው ነበር? ሥራ 12:1፣ 2፤ ራእይ 1፡9። “ዮሐንስና ያዕቆብ ከመምህራቸው ጋር መከራን መቀበል ነበረባቸው። አንዱ ከወንድሞች መካከል አስቀድሞ በሰይፍ ሲጠፋ ሌላው፣ ድካምን፣ ነቀፋንና ስደትን በጽናት በመቀበል ከሁሉ የበለጠ ረጅም ዕድሜ ኖረ።”—Ibid., 549. 3. ደብዳቤውን የጻፈው ማን ነው? ማክሰኞ መስከረም 21 ሀ. መጽሐፍ ቅዱስ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነውን የእልፍዮስን ልጅ ያዕቆብን (የዮሐንስን ወንድም ዘብዴዎስ ልጅ ያልሆነዉን) እንዴት ይገልጸዋል? ማርቆስ 15:40 “እንደሌዋዊው ማቴዎስ የመሰሉ ቀራጮች የሆኑም ነበሩበት፡፡ ከተራ ሥራ የተጠሩ የሮማ አገልጋይ የነበሩ ናቸው፡፡ ቀናተኛው ሲሞን ጠላቶቹ ከነበሩት ንጉሣዊያን ባለሥልጣኖች ጋር ድርድር የማይወደውና ለራሱ የሚበቃውን ብቻ የሚያስበው የጋለ ልብ የነበረው ጴጥሮስ ከወንድሙ ከእንደርያስ ጋር፤ ሽሙንሙን፣ ትልቅ ችሎታ ያለው ግን ደካማ መንፈስ የነበረው ይሁዳዊዉ ይሁዳ፤ ፊሊጶስና ቶማስ ደግሞ ታማኝና ቀና ሲሆኑ ነገር ግን ለማመን ዳተኛ ልብ ያላቸው ነበሩ፡፡ ያዕቆብና ይሁዳ ወንድሞች መካከል ታናሾቹ ነበሩ፤ ነገር ግን የኃይልና የቀልጣፋ አስተሳሰብ ባለቤቶች ነበሩ፡፡ በእምነት ገና ልጅ የሆነዉ የዚያ ጥል የሚወደው የዘብዴዎስ ልጅ ናትናኤል ነበሩ።”—Education, pp. 85, 86. ለ. ለምን ምናልባት የያዕቆብ መልእክት ጸሐፊ (ሐዋርያ ተብሎ የሚጠራው ጌታን በአካል ስለሚያውቅ ነው) የክርስቶስ ግማሽ ወንድም ሊሆን ይችላል - እና ስለ ራሱ በሰጠው መግለጫ ባህሪው በባህሪው በጌታ ተጽእኖ እንደተለወጠ የሚያሳየው እንዴት ነው? ያዕቆብ 1፡1 (የመጀመሪያ አጋማሽ)። “የክርስቶስ ወንድሞች እርሱን በስህተት ተረድተዉታል፤ እርሱ እንደ እነርሱ አልነበረምና። ስቃይ ላይ ያሉትን ባየ ቁጥር ሁሉ ስቃያቸዉን ለማስታገስ ሠርቷል፣ በዚህም ሁልጊዜም ስኬታማ ነበር። ለመስጠት ትንሽ ገንዘብ ነበረው ነገር ግን ከራሱ የበለጠ ችግረኛ ለሚመስሉት በትህትና የራሱን ምግብ ይሰጥ ነበር። ወንድሞቹ የእሱን ተጽእኖ ለመቋቋም ከሚቻለዉ በላይ በጣም አልፎ እንደሄደ ይሰማቸዉ ነበር፤ ምክንያቱም እነሱ ከድሆች ጋር በተገናኙት ቁጥር ለነዚያ ምስክን ነፍሳት ሸካራ ቃላትን ሲናገሩ፣ ክርስቶስ ግን እነዚህን ፈልጎ የሚያበረታታ ቃል ይነግሯቸዉ ነበር። በቤተሰብ ክበብ ውስጥ እያለ ከዚያ በላይ ማድረግ ባይችል እንኳን በተቻለ መጠን በጸጥታና በድብቅ እርዳታው ለሚያስፈልጋቸው ምስኪኖች ቀዝቃዛ ውሃ ይሰጣቸውና ከዚያም የራሱን ምግብ በእጃቸው ያስቀምጣላቸዉ ነበር። —This Day With God, p. 59. ሐ. ጳውሎስ ለየሱስ ወንድም ለያዕቆብ ያለውን አክብሮት ያሳየው እንዴት ነው? ገላትያ 1:17–19፤ የሐዋርያት ሥራ 21:18 4. አንዳንድ ጉዳዮችን ማብራራት ረቡዕ መስከረም 22 ሀ. የክርስቶስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን በአንድ ትልቅ ጉባኤ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ሰው እንደነበር የሚያሳየው ምንድን ነው? የሐዋርያት ሥራ 15:5፣ 6፣ 13፣ 19፣ 20 “በዚህ አጋጣሚ ያዕቆብ በምክር ቤቱ የደረሰውን ውሳኔ የሚያበስር ሆኖ የተመረጠ ይመስላል። ሜዳዊዉ ሕግ፣ በተለይም የግርዛት ሥርዓት፣ በአሕዛብ ላይ እንዳይበረታ፣ ወይም ለእነርሱ እንደ ግዴታ ባይመከር መልካም ነው የሚለዉ የእርሱ ዉሳኔ ነበር። ያዕቆብ ወደ እግዚአብሔር በመመለስ አሕዛብ በሕይወታቸው ውስጥ ትልቅ ለውጥ እንዳደረጉና ግራ የሚያጋቡና ጥቃቅን በሆኑ ጥቃቅን ጥያቄዎች በማስቸገር ክርስቶስን በመከተል ተስፋ እንዲቆርጡ እንዳያደርጓቸው ብዙ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ የወንድሞቹን አእምሮ ለመማረክ ፈለገ።”—The Acts of the Apostles, p. 195. ለ. በዚህ ጠቃሚ የምክር ቤት ዉሎ ውስጥ ያዕቆብ ትልቅ ሚና በመጫወቱ ምክንያት ውድቅ የሆነው የተሳሳተ የይገባኛል ጥያቄ ምንድነዉ? ማቴዎስ 16፡18 “ያዕቆብ ጉባኤውን ይመራ ነበር፣ እና የመጨረሻ ውሳኔው፣ ‘ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን እንዳናስቸግራቸው ፍርዴ ይህ ነው።’“ይህ የውይይቱ ማጠቃለያ ነበር። በዚህ ምሳሌ በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጴጥሮስ የቤተ ክርስቲያን ራስ ነበር የሚለውን አስተምህሮ ውድቅ እናደርጋለን። እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተተኪዎች ነን የሚሉ ሰዎች ለማጣቀስ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የላቸውም። በጴጥሮስ ሕይወት ውስጥ እርሱ የልዑል ምክትል ሊቀ መንበር ሆኖ ከወንድሞቹ በላይ ከፍ ከፍ አለ ለሚለው አባባል ምንም ማረጋገጫ መስጠት አይችሉም። የጴጥሮስ ተተኪዎች እንደሆኑ የተገለጹት ሰዎች የእሱን ምሳሌ ቢከተሉ ኖሮ ምንጊዜም ቢሆን ከወንድሞቻቸው ጋር በእኩልነት ለመኖር ረክተው ይኖሩ ነበር።”—Ibid., pp. 194, 195.“አዳኛችን የወንጌልን ሥራ ለጴጥሮስ ለብቻው አልሰጠውም። ለጴጥሮስ የተናገራቸውን ቃላት ቆይቶ በሌላ ጊዜ በቀጥታ ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ተናግሮአቸዋል። ይህንኑ ሐሳብ የያዘ ንግግር ምዕመናንን እንደሚወክሉ አድርጐ ለአሥራ ሁለቱም መዛሙርቱ ለአንዱ የተለየ ሥልጣን ሰጥቶ ከመካከላቸው ትልቁ ማን እንደሆነ ብዙ ጊዜ ተናግሮ ነበር። የሱስ ከደቀ ቢሆን ኖሮ ደቀ መዛሙርቱ ሲከራከሩ ባልታዩም ነበር። በዚህ ፈንታ የጌታቸውን ፍላጐት በመቀበል እርሱ የመረጠውን ሰው ያከብሩት ነበር።”—The Desire of Ages, p. 414. 5. የእግዚአብሔር እስራኤል ሐሙስ መስከረም 23 ሀ. ይህ መልእክት የተጻፈው ለማን ነው—የሱስን እንደ ጌታ የሚቀበሉትን ሁሉ የሚያጠቃልለውስ እንዴት ነው? ያዕቆብ 1:1 (ሁለተኛ አጋማሽ)፤ ገላትያ 3፡27-29 “ከእግዚአብሔር እስራኤል መካከል በሥጋ የአብርሃም ዘሮች ያልሆኑ ብዙዎች ይቈጠራሉ።”—Prophets and Kings, p. 367. “የክርስቶስ ሕይወት፣ የዘር መድሎ የሌለበትን ሃይማኖት፣ አይሁዳዊና አሕዛብ፣ ጌታና አሽከር፣ በአንድ ወንድማማችነት የሚተሳሰሩበትና በእግዚአብሔር ፊት እኩል የሆኑበትን ሃይማኖት አቋቋመ።”—Testimonies for the Church, vol. 9, p. 191.“ክርስትና በጌታና በአገልጋይ፣ በንጉሥና በተገዢው፣ በወንጌል አገልጋይ እና በክርስቶስ ከኃጢአት መንጻትን ባገኘው የበዋረደዉ ኃጢአተኛ መካከል ጠንካራ አንድነት ይፈጥራል።”—The Acts of the Apostles, p. 460. ለ. በትንቢቱ ላይ የመጨረሻዎቹ መንፈሳዊ እስራኤላውያን ምን ስም ተሰጥቷቸዋል? ከክርስቶስ መምጣት በፊት የሚያጋጠማቸው ነገርስ እንዴት ተገልጿል? ራእይ 7፡4። “ብዙም ሳይቆይ የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ብዙ ውሃ ሰማን፣ በዚህም የየሱስን መምጫ ቀንና ሰዓቱ ተነገረን። ሕያዋን ቅዱሳን ቁጥራቸው 144,000 ያህሉ ድምፁን አውቀው ተረድተውታል፤ ክፉዎች ግን ነጎድጓድና የመሬት መንቀጥቀጥ መስሏቸው ነበር። . . .“144,000ዎቹ ሁሉም የታተሙና ፍጹም አንድንድነት አላቸዉ። በግንባራቸው ላይ አምላክ፣ አዲሲቱ የሩሳሌም፣ የሚሉት ቃላትና የየሱስን አዲስ ስም የያዘ የከበረ ኮከብ ነበሩ። ደስተኛ፣ ቅዱስ በሆነው ሁኔታችን ክፉዎች ተናደዱ፣ ወደ እስር ቤትም ሊያስገቡን በኃይል ይጣደፉ ነበር፣ ነገር ግን በጌታ ስም እጃችንን ስንዘረጋ አቅመ ደካሞች ሆነዉ በምድር ላይ ይወድቃሉ። ከዚያም የሰይጣን ማኅበር አምላክ እንደወደደን፣ እንዲሁም እርስ በርሳችን እግራችንን መታጠብና ወንድሞችን በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ መስጠት የምችል መሆናችንን ሲያዉቁ በእግራችን ሥር ወድቅዉ ሰገዱ።”— Testimonies for the Church, vol. 1, p. 59. የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ መስከረም 24 1. የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብ ክርስቶስን ወደ መምሰል ያደገው እንዴት ነው? 2. የየሱስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ ክርስቶስን ወደ መምሰል ያደገው እንዴት ነው? 3. ጴጥሮስ የሐዋርያት ራስ እንዳልሆነ የሚያሳዩት የትኞቹ የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች ናቸው? 4. ጳውሎስ የሁሉም ክርስቲያኖች አንድነትና እኩል ጥቅም የገለጸው እንዴት ነው? 5. የአምላክ መንፈሳዊ እስራኤል የመጨረሻውን ድል የሚያሳየው ምንድን ነው? << >>