Back to top

Sabbath Bible Lessons

ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ

 <<    >> 
ሰንበት፣ ህዳር 14፣ 2017 8ኛ ትምህርት
ስለ ምን ማሰብ እንዳለበን መምረጥ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።” (ማቴዎስ 12:34፣ ሁለተኛ አጋማሽ)።
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Thoughts From the Mount of Blessing, pp. 125–129. 
“ከመናገርህ በፊት ጸልይ፣ እና የሰማይ መላእክት ወደ አንተ ሊረዱህ ይመጣሉ፤ ያኔ እግዚአብሔርን የሚያዋርዱ፣ ዓላማውን የሚነቅፉና ነፍሳችሁን የሚያደክሙ ክፉ መላእክት ይሸሻሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 82.

1. የመርዙ መከላከያ እሁድ ህዳር 08
ሀ. ክፉ አስተሳሰብ ባላቸው ሰዎች የንግግር ልማዶች ስንዋጥ፣ በዚህ ሁሉ ውስጥ እንኳን የእግዚአብሔር መልእክት ምንድር ነው? ያእቆብ 3:7፣ 8፤ ዕብራውያን 10፡38 “[ወንድም ጄ] በጨለማ የተከበበ ነውና በሰማያዊ መላእክት አዘኑ። ጆሮዎቹ ያለማመንና የጨለማ ቃላትን ያለማቋረጥ ይሰማሉ። ጥርጣሬዎች እና ጥያቄዎች በፊቱ ይመላለሳሉ፡፡ አንደበት የዓመፅ ዓለም ነው። “ምላስን ሊገራ ማንም አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት የማይታዘዝ ክፋት ነውና።” ወንድም ጄ ከአምላክ ጋር ይበልጥ አጥብቆ ከተጣበቀ እና በአምላክ ፊት ንጹሕ አቋሙን የተፈጥሮ ሕይወቱን መሥዋዕት በማድረግም ቢሆን መጠበቅ እንዳለበት የሚሰማው ከሆነ ከላይ ኃይልን ያገኛል። በዙሪያው ባለው ጨለማና አለማመን፣ በጥርጣሬዎችና በጥያቄዎች እንዲሁም በብዙ ወሬዎች እምነቱ እንዲነካ ከፈቀደ ብዙም ሳይቆይ ጨለማ፣ ጥርጣሬና አለማመን ይሆናል፣ እንዲሁም በእውነት ብርሃን የመጽናት ጥንካሬ አይኖረውም።“በእምነታችን ላይ ከተበሳጩት ጓደኞቹ ጋር ለመስማማት በመፈለጉ ለእርሱ ቀላል ነገር እንደሆነ አድርጎ ማሰብ የለበትም። በማንኛውም ዋጋ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ አንድ ቆራጥ አላማ ይዞ ከቆመ እርዳታና ጥንካሬን ያገኛል። እግዚአብሔር ወንድም ጄን ይወደዋል፣ ይራራለታልም፡፡ ሁሉንም ግራ መጋባት፣ ተስፋ መቁረጥን፣ መራራ ንግግርን ያውቃል። ሁሉንም ያውቀዋል። አለማመኑን ትቶ ሳይነቃነቅ በአምላክ የሚቆም ከሆነ፣ እምነቱ በተግባር ይበረታል።”—Testimonies for the Church, vol. 4, pp. 236, 237.

2. ከባድ ጉዳይ ሰኞ ህዳር 09
ሀ. ስለ አታላይና ቀስቃሽ ንግግሮች የተጻፈው ምንድን ነው—በዚህ የሕይወት ዘርፍ ለማሸነፍ መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው? መዝሙረ ዳዊት 5:8-10 “ንግግር እግዚአብሔር ለሰው ከሰጣቸው ታላላቅ ስጦታዎች አንዱ ነው። አንደበት ትንሽ ብልት ነው፣ ነገር ግን የሚቀርፃቸው፣ በድምፅ የተፈጠሩ ቃላቶች ትልቅ ኃይል አላቸው። እግዚአብሔር ምላስን ሊገራ ማንም አይችልም ይላል። ሕዝብን በሕዝብ ላይ ያስነሳል፣ ጦርነትና ደም መፋሰስንም ያስከትላል። ቃላቶች ለማርገብ የሚከብድ እሳት ይቀሰቅሳሉ። ለብዙ ነፍሳት ደግሞ ደስታንና እፎይታን አምጥተዋል። እንዲሁም እግዚአብሔር ' ቃሌን ንገራቸው' ስለሚል የእርሱ ቃላቶች ሲነገሩ ብዙ ጊዜ ሰዎችን ወደ ንስሃ ያመጣሉ።“የንግግር መክሊት ትልቅ ኃላፊነት ሸክም ያለበት ነዉ። በጥንቃቄ መጠበቅ ያስፈልገዋል፤ ለክፉም ለበጎም ታላቅ ኃይል የያዘ ነውና።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 3, p. 1142.“የማይታዘዝ ብልትን ለመግራት ስትፈተን፣ ኦ እጅግ ከባድ ነዉ! መዝጋቢው መልአክ እያንዳንዱን ቃል እየተመለከተ መሆኑን አስታውስ። ሁሉም ነገር በመጽሐፍ ተጽፈዋል፣ እናም በክርስቶስ ደም ካልታጠበ በቀር፣ እነሱን እንደገና በፍርድ ቀን ታገኛቸዋለህ። አሁን በሰማይ ውስጥ እየታየ ያለ መዝገብ አለ። በእግዚአብሔር ፊት ልባዊ ንስሐ አሁንም ተቀባይነት አለዉ። በስሜታዊነት ለመናገር ሲገፋፉ፣ ላለመናገር አፍህን ዝጋዉ። አንድም ቃል አትናገር።”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 82. ለ. ቃላቶቻችን በቀላሉ እኛ የምናስበውንና ማን እንደሆንን ማንነታችን እንዴት እንደሚያሳዩ ግለጽ። ኤርምያስ 17:9ማቴዎስ 12:33–37፤ 14፡6–8። “የንግግርህ ጭብጥ የልብን ሀብት ወይም ሀሳብህን ያሳያል። ርካሽ፣ ተራ ወሬ፣ የማታለል ቃላት፣ የቂልነት ጥበብ፣ ሳቅ ለመፍጠር የሚነገሩ ተራ ንግግሮች፣ የሰይጣን ሸቀጣ ሸቀጥ ናቸው፣ በዚህ ንግግር የሚዋጥ ሁሉ በሸቀጦቹ እየነገደ ነው። ሄሮድስ የሄሮድያዳ ልጅ በፊቱ ስትጨፍር ከነበረው ጋር የሚመሳሰል ተራ ስሜት ነዉ እነዚህን ነገሮች ለሚሰሙ ሰዎች የሚሰማቸዉ። እነዚህ ሁሉ ግብይቶች በሰማዩ መዝገብ ውስጥ ተመዝግበዋል ፤ እናም በመጨረሻው ታላቅ ቀን በጥፋተኞች ፊት በእውነተኛ ብርሃን ግልጽ ሆነዉ ይታያሉ። በዚያን ጊዜ ሁሉ የዲያብሎስን አሳሳችና ክፉ ሥራ እነርሱን ወደ ሰፊው መንገድ ለጥፋትም ወደተከፈተው ሰፊው ደጅ ይመራቸዉ እንደነበረ ለይተው ያውቃሉ።”—Testimonies to Ministers, pp. 84, 85.

3. በሙሉ ልብ ያስፈልጋል ማክሰኞ ህዳር 10
ሀ. በወቅቱ እውነት ውስጥ አማኞች የማይለዋወጥ ንግግር (የማያወላዉል አንደበት) እንድኖራቸዉ ለምን መጠበቅ አለብን? ያዕቆብ 3:9፣ 10 በዚህ ነጥብ ላይ ከወደቅን ምን ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል? “እግዚአብሔር የምታደርጉትንና የምትናገሩትን ሁሉ እንደሚያይና እንደሚሰማ እንዲሁም ቃላቶቻችሁንና ተግባራችሁን ሁሉ በታማኝነት መዝግቦ እንደሚይዝ፣ በመጨረሻም ለፍርድ እንደሚያመጣዉ ካመናችሁና ሁሉንም መስፈርቶቹን ማሟላት እንዳለባችሁ የሚሰማችሁ ከሆነ፣ በምትሰሩትና በምትናገሩት ነገር ሁሉ በንቁና በበራ ሕሊና የአምላክን መመሪያዎችን ተከተሉ። በዚያን ጊዜ አንደበትህ ለእግዚአብሔር ክብር ጥቅም ላይ ይውላል፤ እንዲሁም ለራስህና ለሌሎች የበረከት ምንጭ ይሆናል። ነገር ግን እንዳደረጋችሁት ከእግዚአብሔር ከተለያችሁ፥ አንደበታችሁ የዓመጻ እንዳያደርግና የሚያስፈራ ፍርድ እንዳያመጣብህ ተጠንቀቅ። በአንተ ምክንያት ነፍሳት ይጠፋሉና።”—Testimonies for the Church, vol. 4, p. 244. ለ. ሁልጊዜ አስበን እንድንናገር የሚረዳን የትኛው ጸሎት ነው? መዝሙረ ዳዊት 86:11 “የመጽሐፍ ቅዱስን እውቀት የሚቀበለው ሰው ከእውነት ብርሃን ጋር የሚመጣጠን በልማዱ ወይም በድርጊቶቹ ላይ ምንም ለውጥ ካላመጣ፣ ምን ዋጋ አለዉ? መንፈስ ከሥጋ ጋር ሥጋም ከመንፈስ ጋር ይዋጋል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ማሸነፍ አለበት፡፡ በእውነት ነፍስህ ከተቀደሰ ኃጢአትን ትጠላለህ፣ ምክንያቱም ክርስቶስ በልብህ እንደተከበረ እንግዳ ተቀባይነት አግኝቷልና፡፡ ክርስቶስ ግን የተከፋፈለን ልብ ከሌላ ጋር ሊጋራ አይችልም፤ ኃጢአትና የሱስ ፈጽሞ አጋር አይሆኑምና።”—Testimonies to Ministers, p. 160.“ትጋ እና ሁል ጊዜ ጸልይ። ያለ እረፍት ራስህን ለጌታ ስጥ፣ ከዚያ በኋላ እሱን ማገልገል አስቸጋሪ አይሆንም። የተከፋፈለ ልብ አለህ። በብርሃን ፈንታ ጨለማ የሚከብብህም ለዚህ ነው። የመጨረሻው የምሕረት መልእክት አሁን እየታወጀ ነው። ይህም የእግዚአብሔር ትዕግስትና ርህራሄ ምልክት ነው። ና ግብዣው አሁን ተሰጥቷል። ና ፣ ሁሉም ነገር አሁን ዝግጁ ነውና። ይህ የምሕረት የመጨረሻ ጥሪ ነው። ከዚህ ቀጥሎ በቅርቡ በአንተ ባሕርይ የተከፋዉ አምላክ በበቀል ይመጣልና።”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 225.“አሁን ጸንተዉ የሚቆሙት በሙሉ ልብ፣ በሚገባ የወሰኑ ወንዶች እና ሴቶች ብቻ ናቸው። ክርስቶስ ተከታዮቹን ደጋግሞ ያነጥራል፣ በአንድ ወቅት የክርስቲያን ቤተክርስቲያንን መሰረት ለመጣል አስራ አንዶቹ እና ጥቂት ታማኝ ሴቶች ብቻ ቀርተዉ ነበር። ሸክም ሲመጣ ወደ ኋላ የሚቀሩ (ከኋላ የሚቆሙ) አሉ፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያኑ በጋለ ጊዜ፣ ግለቱ ይይዛቸዋል፣ ይዘምራሉ፣ ይጮኻሉ፣ ይወራጫሉ፤ ነገር ግን ተመልከቷቸው። ስሜቱ ሲጠፋ ወይም ሲቀዘቅዝ ጥቂት ታማኝ ካሌቦች ብቻ ወደ ግንባር መጥተው የማይናወጥ አቋም ያሳያሉ። እነዚህ ጣዕሙን የያዙ ጨው ናቸው።”—Ibid., vol. 5, p. 130.

4. ውሃ ከንጹህ ምንጭ ረቡዕ ህዳር 11
ሀ. በእግዚአብሄር ፀጋ የታደሰ ልብ ብቻ ወጥ የሆነ ተግባር ማምጣት እንደሚችል የሚያሳየው የትኛው መርህ ነው? ያዕቆብ 3:11፣ 12 አንዳንድ ተግባራዊ ምሳሌዎችን ስጥ። “ንጹህና ሥርዓት ያለዉ አለባበስ፣ እንዲሁም ንጽህና በሁሉም መኖሪያ ቤቶች፣ ሁልጊዜ በዚህ ምድር ላይ እንደ እንግዳ በሚታዩ እና ስህተታቸውን ለማየት በሚጠበቁ በሰንበት ጠባቂዎች በጥብቅ ሊጠበቁ ይገባል። የእነሱ ተጽዕኖ ቅዱስ መሆን አለበት፡፡ የምንላቸው ቅዱሳን እውነቶች ተቀባዮችን ፈጽሞ የሚያዋርዱ፣ እንዲሁም ሸካራ፣ ለግል ጉዳያቸው ቸልተኞችና በቤታቸው ውስጥ ያልተስተካከሉ አያደርጋቸዉም። ተቀባዩ ደካማ ልማዶች ካለው፣ እውነት ከፍ ታደርጋለች፣ በጥልቅ ተሐድሶ ይሠራል። እውነት ይህን ውጤት ካላመጣበት፣ ለግለሰቡ የማዳን ኃይሉ አልተሰማውም ማለት ነዉ። ጥንቃቄ የጎደለውና የተዘበራረቀ ልብስ የትህትና ምልክት አይደለም፡፡ በዚህም አንዳንዶች እራሳቸውን አታልለዋል፡፡ ህይወቱ፣ ድርጊቶቹ፣ ቃላቶቹ፣ ግለሰቡ እውነተኛ ትህትና እንዳለው ይነግራሉ፣ እና አለባበሱን ከተገለጹት ፍሬዎች ጋር ያዛምዳሉ። ንጹሕ ምንጭ በተመሣሣይ ጣፋጭና መራራን ውሃ አያወጣም። ምንጩን አጽዱና ፈሳሾቹ ንጹህ ይሆናሉ፡፡ የእግዚአብሔር ቤት ብዙ ጊዜ በሰንበት ጠባቂዎች ልጆች ይረክሳል። ወላጆቻቸው አምላክን ለማገልገል በተሰበሰቡባቸው ስብሰባዎች ላይ በቤቱ ዉስጥ እንዲሯሯጡ፣ እንዲጫወቱ፣ እንዲነጋገሩ፣ የሰዎችን ትኩረት እንዲስቡና አምላክን ለማምለክ በተሰበሰቡበት ሥፍራ ክፉ ተጽዕኗቸውን እንዲያሳርፉ ይፈቅዳሉ። በቅዱሳን ማኅበር ጸጥታ መንገሥ እነደሚገባዉ አይቻለሁ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰዎች የሚሰበሰቡበት ቤት ብዙውን ጊዜ ፍጹም ባቢሎን ፣ የግራ መጋባትና የሥርዓት አልበኝነት ቦታ ይሆናል። ይህ እግዚአብሔርን ያሳዝነዋል። ወላጆች በልጆቻቸዉ ላይ ሥልጣን ከሌላቸው፣ እና ልጆቻቸውን በስብሰባ ላይ መቆጣጠር ካልቻሉ፣ ከማይታዘዙ ልጆቻቸው ጋር በቤታቸው ቢቆዩ እግዚአብሔር ደስ ይለዋል። ብዙ ሰዎችን ከማናደድና ስብሰባዎቻቸውን ከማበላሸት ይልቅ ከስብሰባዉና ከበረከቱ ብቀሩ ይሻላቸዋል። ወላጆች ልጆቻቸውን ከቁጥጥር ውጭ እንዲሆኑ አድርገዉ አሳድገዉ፣ ቤት ውስጥ ሳይቆጣጠሯቸዉ ከቀሩ፣ በስብሰባ ቦታ ላይ እንደፈለጉ ሊያዟቸዉ አይችሉም። በዚህ ጉዳይ የሚጎዱት ማን መሆን አለባቸው? በእርግጠኝነት፣ ወላጆች፡፡ አምላክን ለማምለክ በሚሰበሰቡበት ጊዜ ሌሎች ሰላማቸው እንዲረበሽ የማይፈልጉ ከሆነ ወላጆች ይሄ ሸክም ሊሰማቸው ይገባል።“ወላጆች፣ በዚህ ጉዳይ የተነሳ እናንተ ልትሰቃዩ (ሊሰማችሁ) ይገባል፣ ምክንያቱም የተዘነጋችሁትን ግዴታ እንድትመለከቱና እንድትወጡ ያደርጋችኋልና። ልጆቻችሁን ተሸክማችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከወሰዳችሁ፣ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የሚገናኝባቸው ቦታዎች መሆናቸውን እንዲረዱ ማድረግ አለባችሁ። በዚህ ረገድ በስማዊ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ እንዳለ በሰንበት ጠባቂዎች ዘንድ እንዲህ ዓይነት ሥርዓት አልተፈጠረም። ወላጆች ሆይ፣ የምትሠሩት ሥራ አለላችሁ። ልጆቻችሁን በቤታችሁ አስገዙ፤ ከዚያም በአምላክ ቤት ውስጥ ልታስተዳድሩአቸው ትችላላችሁና።”—Spiritual Gifts, vol. 2, pp. 288, 289.

5. ጥበብና እውቀትን መላበስ ሐሙስ ህዳር 12
ሀ. እያንዳንዳችን የራሳችንን አመለካከት ከውስጥ ወደ ውጭ ማለትም በልባችን፣ በቃላችንና በድርጊት መመርመር ያለብን ለምንድን ነው? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5 “በእምነት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ። ራሳችሁን ፈትኑ” (2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5)፡፡ ቁጣችሁን፣ አቋማችሁን፣ ሃሳባችሁን፣ ቃላታችሁን፣ ዝንባሌዎቻችሁን፣ ዓላማዎቻችሁን እና ድርጊቶቻችሁን በቅርበት ተቹ። የመንፈሳዊ ጤንነታችንን በቅዱሳን ጽሑፎች እስካልተረጋገጠ ድረስ የሚያስፈልገንን ነገር በጥበብ መጠየቅ የምንችለው እንዴት ነው?”—Selected Messages, bk. 1, p. 89“ወንድሞቼና እህቶቼ፣ የንግግር መክሊትን እንዴት ነው የምትጠቀሙት? አንደበት ለበራ ህሊናና ለቅዱስ የፍቅር መመሪያዎች እንዲታዘዝ መቆጣጠርን አስተምረሃልን? ንግግርህ ከዝሙት፣ ከኩራትና ከክፋት፣ ከተንኮልና ከርኩሰት የጸዳ ነውን? በእግዚአብሔር ፊት ተንኰል የሌለብህ ነህን? ቃላቶች የመናገር ኃይል አላቸው፡፡ ሰይጣን ከተቻለ አንደበት ለራሱ ለአገልግሎቱ ንቁ እንዲሆን ያደርጋል። በራሳችን የማይታዘዝ ብልትን መቆጣጠር አንችልም። መለኮታዊ ጸጋ ብቸኛው ተስፋችን ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 175.“ራሱን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት ያደረገ ሰዉ፣ አእምሮው እየሰፋና እየዳበረ ይሄዳል። እግዚአብሔርን የሚያገለግል ሰዉ የምማረዉ ትምህርት አንድ ወገን የሆነና ሚዛናዊነት የጎደለው፣ የአንድ ወገን ባሕርይን ብቻ የሚያዳብር ሳይሆን ነገር ግን የተመጣጠነና የተሟላ የሚያድርግ ትምህርት ያገኛል። በልፍስፍስ ፈቃድና አቅም በሌለው ባህሪይ ውስጥ የተገለጡ ድክመቶች ይሸነፋሉ፣ ምክንያቱም ቀጣይነት ያለው አምልኮ እና እግዚአብሔርን መምሰል ሰውን ከክርስቶስ ጋር ያለውን ቅርርብ በመያዝ የክርስቶስ አስተሳሰብ እንዲኖረው ያደርጋልና። ነገረ ሥራዉና የመርህ ጥንካሬዉ ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆናል። የእሱ ግንዛቤ ግልጽ ነው፣ እናም ከአምላክ የሚገኘውን ጥበብ ይገልጣል።”—Selected Messages, bk. 1, p. 338.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ህዳር 13
1. መርዛማ የሆነ ንግግር ሲያጋጥመኝ ምላሽ መስጠት ያለብኝ እንዴት ነዉ? 2. ሰዎች ነገሮችን በሚናገሩበት ጊዜ፣ የሚናገሩት ነገር ስለእነሱ ምን ያመለክታል? 3. በሰው አእምሮ ውስጥ ያለውን ጦርነት እና እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል አብራራ። 4. በውስጣችን ያለውን የተበከለዉን ውሃ የሚያንፀባርቁ ልማዶቼ/ዝንባሌዎቼ የትኞቹ ናቸው? 5. የአነጋገር ልማዴን መቀየር ያለብኝ እንዴትና ለምንድነዉ?
 <<    >>