ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ << >> ሰንበት፣ ጥቅምት 09፣ 2017 3ኛ ትምህርት ፈተናን መጋፈጥ “በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።” (ያዕቆብ 1፡12)። ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡ Testimonies for the Church, vol. 3, pp. 477–492. “ከጸሎታችሁ ጋር በሚስማማ መንገድ ተናገሩ። ፈተና እምነታችሁ እውነተኛ መሆኑን ካረጋገጠ ወይም ጸሎታችሁ መልክ (ቅርጽ) ብቻ እንደሆነ የሚያሳዩ ከሆነ በአናንተ ላይ የሰማይና የምድርን ያህል ርቀት ያለዉ ለውጥ ያመጣባችኋል።”—Christ’s Object Lessons, p. 146. 1. የመንፈሳዊ እድገት ምክንያቶች እሁድ ጥቅምት 03 ሀ. ያዕቆብ 1:2 በሕይወታችን እንዴት እንደሚፈጸም ምሥጢሩን ግለጽ። ነህምያ 8:10 “እንደ አስተማሪ የምንቀበላቸዉ ፈተናዎች ሁሉ ደስታን ይፈጥራሉ። መላው ሃይማኖታዊ ሕይወት የሚያንጽ፣ ከፍ የሚያደርግ፣ የሚያስደስት፣ በመልካም ቃላትና ሥራዎች መዓዛ ያላቸው ይሆናሉ። ጠላት በተስፋ መቁረጥ፣ በጭንቀት፣ በሐዘን እና በመቃተት ላይ ያሉ ነፍሳትን በማግኘቱ ይደሰታል። የእምነታችንን ውጤት በተመለከተ እንዲህ ዓይነት አመለካከት እንዲኖረን ይፈልጋል። ነገር ግን አስተሳሰባችን አሽቆልቁሎ አእምሯችን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንዳይደርስ እግዚአብሔር ይሻል። እያንዳንዱ ነፍስ በቤዛው ኃይል አሸናፊ እንዲሆን ይፈልጋል።”— Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 365, 366 ለ. አምላክ ፈተናዎች እንዲደርሱብን የሚፈቅደው ለምንድን ነው? ያዕቆብ 1:3፤ ሮሜ 5፡3 “የሚገጥሙንን ውጣ ውረዶች ተቋቁመን በሰይጣን ፈተና ላይ ድል የምንጎናጸፍ ከሆነ በእምነታችን ዙሪያ የሚመጡትንም ፈተናዎች እንዲሁ በማለፍ ከወርቅ ይልቅ የከበርን—ቀጣዩን ፈተና ለመቋቋም ጠንካራና የተሻለ ዝግጅት ያለን እንሆናለን፡፡ ነገር ግን ቁልቁል የምንሰጥምና ለሰይጣን ፈተናዎች መንገድ የምንከፍት ከሆነ እየተዳከምን በመሄድ በፈተናው ድል አንቀዳጅም፡፡… ለቀጣዩም ፈተና በቂ ዝግጅት አይኖረንም፡፡ በዚህ መልኩ የሰይጣን ፈቃድ ምርኮኛ እስክንሆን እየቀጨጭን እንሄዳለን፡፡ መላውን የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ዕቃ ለብሰን በማንኛውም ወቅት ከጨለማው ኃይል ሊነሳ ለሚችል ተጋድሎ ዝግጁ ልንሆን የግድ ነው፡፡”—Early Writings, p. 46. 2. ካሰብነው የተሻለ ውጤት ሰኞ ጥቅምት 04 ሀ. ትዕግስትን በመለማመድ ያለውን ጥቅም ግለጽ። ያእቆብ 1:4፤ ሉቃስ 21፡19 “እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ጸሎታችንን በምንፈልገው መንገድና ሰዓት ሊመልስልን ይችላል፣ ነገር ግን እርሱ ከዚያ በላይ ጥበበኛና መልካም ነው። ምኞታችንን ሁሉ ከማሳካት የበለጠና የተሻለ ነገር ያደርግልናል። በጥበቡና በፍቅሩ ስለምንታመን፣ በፈቃዳችን እንዲሸነፍ ልንጠይቀው አይገባም፣ ነገር ግን በእርሱ አላማ ዉስጥ ለመግባትና አላማውን ለመፈጸም መፈለግ አለብን። ምኞታችንና ፍላጎታችን በእርሱ ፈቃድ ዉስጥ መስጠም አለበት። እምነትን የሚፈትኑ እነዚህ ተሞክሮዎች ለእኛ ጥቅም ናቸው። በእነሱ አማካኝነት እምነታችን እውነት እና ቅን፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ብቻ የተመሠረተ፣ ወይም እንደሁኔታው የማይቀያየርና የማይለዋወጥ እንደሆነ ይገለጣል። እምነት የሚጠናከረው በተግባር ነው። በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ጌታን ለታጋሾች የተገቡላቸዉ ውድ ተስፋዎች እንዳሉ በማስታወስ ትዕግሥት ፍጹም ሥራውን በሕይወታችን እንድሠራ ልንፈቅድለት ይገባል።”—The Ministry of Healing, p. 231. ለ. ያዕቆብ እንዴት እና ለምን በዚህ ብልሹ ዓለም ውስጥ ስላለው የሥልጣንና የብልጽግና ጊዜያዊ አመለካከት የበለጠ ትልቅ ሥዕል ያሳየናል? ያዕቆብ 1፡9-11 “በዚህ ጊዜ፣ ከታላቁ የመጨረሻ ተጋድሎ በፊት፣ ልክ ከዓለም የመጀመሪያው ጥፋት በፊት እንደሆነዉ፣ ሰዎች በተድላና በገዛ ፍላጎቶች ይጠመዳሉ። በሚታዩትና አላፊ ነገሮች የተጠመዱ ሁሉ፣ የማይታየውንና ዘላለማዊውን እይታ ያጣሉ። አሁን ተጠቅመዉ ለሚጨርሱት ነገሮች የማይጠፋዉን ሀብት እየሠዉ ነው። አእምሯቸው ከፍ ሊል፣ የሕይወት አመለካከታቸው ሊሰፋ ይገባል። ከዓለማዊ ህልም ግድየለሽነት መንቃት ያስፈልጋቸዋል።“በቅዱስ ጽሑፍ ገጾች ላይ በግልጽ እንደተገለጸው የመንግሥታት መነሳትና መውደቅ፣ ውጫዊና ዓለማዊ ክብር ምን ያህል ዋጋ እንደሌለው መማር ያስፈልጋቸዋል። ባቢሎን፣ በሙሉ ኃይሏና በታላቅነቷ፣ ዓለማችን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አይታ የማታውቀው፣ በዚያን ጊዜ ለነበሩት ሰዎች በጣም የተረጋጋና ዘላቂ የሚመስለው ኃይልና ግርማ የነበራት፣ እንዴት ባለ መንገድ ሙሉ በሙሉ አለፈች! እንደ ‘የሣር አበባ’ ጠፋች። ስለዚህ መሠረቱ እግዚአብሔር ያልሆነበት ሁሉ ይጠፋል። ከዓላማው ጋር የተሳሰረና ባህሪውን የሚገልጽ ብቻ ነው የሚጸናው። ዓለማችን የምታውቃቸው ብቸኛ ነገሮች የእርሱ መሠረታዊ ሥርዓቶች ናቸው።”—Education, p. 183.“ዓለማዊ ውድ ሀብት ሁሉ ጊዜያዊ ነው። ዘላለማዊ ሀብት ማግኘት የምንችለው በክርስቶስ በኩል ብቻ ነው።”—The Review and Herald, December 10, 1901. 3. በጦርነቱ ሙቀት ውስጥ ማክሰኞ ጥቅምት 05 ሀ. ፈተና ሲደርስብን በጸሎት ምን ማድረግ አለብን? ለምንስ? ያእቆብ 1:12 “ማስመሰልንና ስሜትን ሁሉ አስወግድ። ቀላልና ተፈጥሯዊ እራስህን ሁን። በማንኛውም ሐሳብ፣ በቃልም ሆነ በሥራ እውነተኛ ሁን፤ እንዲሁም ‘እያንዳንዱ ለሌላው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር።’ መቼም ቢሆን ሥነ ምግባራዊ ተፈጥሮ በቋሚ ንቃትና ጸሎት መደገፍ እንዳለበት አስታውስ። ወደ ክርስቶስ እስከተመለከትክ ድረስ ደህና ነህ፤ ነገር ግን መሥዋዕትነቶችህንና ችግሮችህን ባሰብክበት ጊዜ፣ እንዲሁም ለራስህን ማዘን በጀመርክ ጊዜ፣ በአምላክ ላይ ያለህን እምነት ታጣለህ እናም ትልቅ አደጋ ላይ ትወድቃለህ።”—Testimonies for the Church, vol. 4, p. 522.“ከመልካም ሥራ ልባችን ሳናዞር ወይም ተስፋ ሳንቆርጥ፣ በመንገዳችን ላይ የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ምክንያት ምንም ዓይነት የሞራል ጨለማ ሊሸፍነን ቢሞክር እንኳ፣ በጸጥታ ወደ ፊት መሄድ አለብን። ትዕግስት፣ እምነትና ሥራችን መውደድ ልንማርባቸው የሚገቡ ትምህርቶች ናቸው። ራስን መግዛትና የሱስን መመልከት የዕለት ተዕለት ሥራ ነው። ጌታ በእርሱ የታመነችውንና የእርሱን እርዳታ የምትፈልግ ነፍስን ፈጽሞ አይተወውም፡፡ የሕይወት አክሊል የሚቀመጠው በአሸናፊው ራስ ላይ ብቻ ነው።”—Ibid., vol. 5, pp. 70, 71 ለ. እግዚአብሔር መከራዎችንና ፈተናዎችን ይልካል ማለት ስህተት የሆነዉ ለምንድነው? ያእቆብ 1:13 “ለኃጢአት ሰበብ በማቅረብ በደላችንን ለመቀነስ መሞከር የለብንም። እግዚአብሔር ለኃጢአት ያወጣዉን ዋጋ ተመን (ግምት) መቀበል አለብን፣ ያ ደግሞ በእውነተም ከባድ ነው። የኃጢያትን አስከፊነት መግለጥ የምችለዉ ቀራንዮ ብቻ ነዉ። . . .“ፈተና ኃጢአትን እንድናደርግ የሚገፋፋ ማታለያ ነው፣ ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር አይደለም፣ ከሰይጣንና ከልባችን ክፋት እንጂ። “እግዚአብሔር በክፉ አይፈትነንም፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።” ያዕቆብ 1:13“ሰይጣን እኛን ወደ ፈተና ሊያገባን ይፈልጋል፣ የባህሪያችን ክፋት በሰውና በመላእክት ፊት ይገለጥ ዘንድ፣ እኛን የራሱ አድርጎ ለመያዝ ሲል ይህንን ያደርጋል። . . . ጠላት ወደ ኃጢአት ይመራናል፤ ከዚያም ለአምላክ ፍቅር የማይገባን አድርጎ በመለኮታዊ ዓለማት ፊት ከሰሰ።”—Thoughts From the Mount of Blessing, pp. 116, 117. ሐ. ከሳሹ የቆሸሸዉን ባህሪያችንን እያሳዬ ሲከስ፣ ጌታ እንዴት ይቆምልናል? ዘካርያስ 3:1-4፤ 1ኛ ዮሐንስ 1:9–2:1 4. በድካማችን ላይ የእግዚአብሔር ጥንካሬ ረቡዕ ጥቅምት 06 ሀ. በጌታ ጸሎት ውስጥ “ወደ ፈተና አታግባን” የሚለውን ሐረግ አብራራ ። ማቴዎስ 6:13 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ ት. ኢሳ 30፡21 “[እግዚአብሔር] እንቅፋትን፣ ስደትን፣ እና ችግሮችን እንድንጋፈጥ የፈቀደልን እንደ እርግማን ሳይሆን እንደ የህይወታችን ታላቅ በረከት ነው። በጀግንነት ተቋቁመን የምናሳልፈዉ እያንዳንዱ ፈተና ፣ አዲስ ልምድ ይሰጠናልና በባህሪይ ግንባታ ስራችን ላይ እድገት ያመጣልናል። በመለኮታዊ ኃይል ፈተናን የምትቃወም ነፍስ የክርስቶስን ጸጋ ብቁነት ለዓለምና ለመለኮታዊ ዓለማት ትገልጣለች።“ነገር ግን ምንም እንኳን መራራ ቢሆንም ፈተናን ባንፈራም፣ እግዚአብሔር በገዛ ክፉ ልባችን ፍላጎት ወደምንወሰድበት ገደል እንድንወስድ እንዳይፈቅድ መጸለይ አለብን። ክርስቶስ የሰጠውን ጸሎት በማቅረብ፣ በመልካም ጎዳና እንዲመራን በመጠየቅ፣ እራሳችንን ለእግዚአብሔር መሪነት እናቀርባለን። ይህንን ጸሎት በቅንነት ማቅረብ ካልቻልን፣ በመረጥነው በማንኛውም መንገድ ለመራመድ እንወስን ይሆናል። እጁ እንዲመራን ብንጠብቅ መልካም ነዉ። . . .“ለሰይጣን ጥቆማዎች በመገዛት የምናገኘውን ጥቅም በማሰብ ዉሳኔ ለመሰጠት መዘግየታችን ትልቅ ችግር አለው። ኃጢአት ማለት ውርደትና ጥፋት ማለት ነዉ፣ ይህም ወደ ኃጢአት ለሚቀርብ ነፍስ ሁሉ ነው። ነገር ግን ኃጢአት በባህሪው የሚያሳውርና አታላይ ነው፣ እንዲሁም በሚያማምሩ አቀራረቦች ቀርቦ ያታልለናል፡፡ በሰይጣን ግዛት ላይ ራሳችን ካስቀመጥን ከኃይሉ እንደምንጠበቅ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ኃጢአት ሁል ጊዜ በዙሪያችን ስላለ፣ ፈታኙ እኛን ሊያገኝ የሚችልበትን መንገዶች ሁሉ መዝጋት ይኖርብናል።“‘ወደ ፈተና አታግባን’ የሚለው ጸሎት ራሱ የተስፋ ቃል ነው።”—Thoughts From the Mount of Blessing, pp. 117, 118. ለ. ፈተናን በተመለከተ አምላክ ምን ተማጽኖና ማረጋገጫ ሰጥቶናል? ያዕቆብ 1:14–16፤ 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:13 “ፈተና ምንድን ነው? የእግዚአብሔር ልጆች ነን የሚሉ ሁሉ የሚፈተሹበትና የሚፈተኑበት መንገድ ነው። እግዚአብሔር አብርሃምን እንደፈተነ፣ የእስራኤልን ልጆች እንደፈተነ እናነባለን። ይህ ማለት እምነታቸውን ለመፈተሽና እርዳታ ለማግኘት ወደ እርሱ እንዲመለከቱ ለመምራት ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ፈቅዷል ማለት ነዉ። እግዚአብሔር ዛሬ ረዳታቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ፈተናን ወደ ህዝቡ እንዲመጣ ፈቅዷል። በሚፈተኑበት ጊዜ ወደ እሱ ከቀረቡ፣ ፈተናውን እንዲቋቋሙ ያበረታቸዋል።”—In Heavenly Places, p. 251. 5. ፈተናዎችን የምንመለከትበት በእይታ ሐሙስ ጥቅምት 07 ሀ. በክርስቶስ ለመኖርና ከፈተናዎች ለመዳን ሁል ጊዜ ምን መምረጥ አለብን? ሉቃስ 4:8፤ ፊልጵስዩስ 1፡21 “ፈታኙ ክፉ ነገር እንድናደርግ ሊያስገድደን አይችልም። በራስ ፈቃድ ካልተገዙለት በቀር ሰይጣን አእምሮን መቆጣጠር አይችልም። ሰይጣን በእኛ ላይ ኃይሉን ለማሳየት የሚችለው ፈቃደኞች ስንሆንና የሃይማኖት እጃችን ክርስቶስን ሲለቅ ብቻ ነው። መለኮት ከእኛ የሚፈልገውን ለማሟላት ባፈገፈግን ቁጥር ሰይጣን ሊፈትነንና ሊያጠፋን መግቢያ በር ያገኛል። የእኛ ውድቀት ወይም ሽንፈት ክርስቶስን ለመንቀፍ ለሰይጣን ጥሩ አጋጣሚ ይሆንለታል።”—The Desire of Ages, p. 125. ለ. በክርስቶስ ወደ ድል እንድንገሰግስ የሚያነሳሳን ምንድን ነው? ፊልጵስዩስ 4:13፤ ራእይ 2:10 (የመጨረሻው ክፍል)፤ 3፡21። “የክርስቶስን መንፈስ የተላበሰ ሁሉ በክርስቶስ ይኖራል። በእሱ ላይ ያነጣጠረው የትኛዉም ምት ሁሉ ዙሪያዉን በከበበዉ በአዳኙ ላይ ያርፋል። ወደ እርሱ የሚመጣው ማንኛዉም ነገር ከክርስቶስ ዘንድ ነው። ክፋትን መቃወም አያስፈልገውም፣ ምክንያቱም ክርስቶስ መከላከያው ነውና፡፡ በጌታችን ፈቃድ ካልሆነ በቀር ምንም ሊነካው አይችልም፣ እና ‘የተፈቀደው ሁሉ’ ‘እግዚአብሔርን ለሚወዱት ለበጎ ነዉ። ሮሜ 8:28።”—Thoughts From the Mount of Blessing, p. 71.“የሕይወት ዘውድ የሚደረገዉ በአሸናፊው ራስ ላይ ብቻ ነዉ። በሕይወት ሲንኖር ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጠ ለእግዚአብሔር የምሠሩት ልባዊ ሥራ አለ።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 71. የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ጥቅምት 08 1. በሚቀጥለው ጊዜ አስቸጋሪ ፈተና ሲመጣብኝ ምን ማስታወስ አለብኝ? 2. አምላክ ለጸሎት መልስ ስለሚሰጥበት መንገድ ምን ማወቅ አለብኝ? 3. ፈተናዎችና መከራዎች የሚመጡት ከየት ነው? ለምንስ? 4. ፈተናን በምንቋቋምበት ጊዜ ምን እንሆናለን? 5. በክርስቶስ ሙሉ በሙሉ እንዴት ልኑር? << >>