ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ << >> ሰንበት ታህሳስ 05፣ 2017 11ኛ ትምህርት ትሁት አመለካከትን ማዳበር የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል” (ያዕቆብ 4፡10)። ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡ Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 41–44, 678–686 “በመታዘዝ የትህትና ጎዳና ስንራመድ ሌሎችም ይራመዱበት ዘንድ ወደ ሰማይ የሚያቀና ብሩህ ጎዳና እናመቻቻለን፡፡ በእግዚአብሔር ዓላማዎች ላይ ጥልቅ ተሞክሮ ይኖረን ዘንድ ለእኛ መታደል ነው፡፡”— The Science of the Times, March 17, 1890. 1. የሐሰት ማስተዋልን ማስወገድ እሁድ ህዳር 29 ሀ. ወንድሞቻችንን እንወዳለን ከሚሉት ከሁሉም ዘንድ ምን በጣም ጎጂ ልማድ ነው ጨርሶ መወገድ ያለበት¬¬— ለምን? ያዕቆብ 4፡-11.12 “ በሌሎች ላይ ክፉ መናገር ወይም በእነርሱ ዓላማ ወይም ድርጊት ላይ ራሳችንን ፈራጅ ማድረግ እንደ ቀላል ነገር ተደርጎ መቆጠር የለበትም፡፡”—Patriarchs and Prophets, p. 385.“የግብረ ገብነት (የሞራል) እውነተኛ ዋጋ ክፉ በማሰብም ሆነ በመናገር፣ ሌሎችንም በማቃለል ለራሱ ቅድሚያ አይወስድም፡፡ እያንዳንዱ ምቀኝነት፣ ቅንዓት፣ ክፉ ንግግር (ሀሜት) ከማንኛውም ዓይነት አለማመን ጋር ተጠራርጎ ከእግዚአብሔር ልጆች ዘንድ መወገድ ይኖርበታል።”—Our High calling, p. 234“በቤተክርስቲያናት ላይ አደገኛ ክፋትን በማስከተሉ ረገድ ውጤታማ ከሆኑት ኃጢአቶች መካከል በመሆናቸው፣ ሀሜትና የትችት መንፈስን ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ በእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን እልህ አስጨራሽ ጥረት መካሄድ ይኖርበታል፡፡ ግትርነትና አቃቂረኛነት (እንከን ፈላጊነት) ሰይጣን እንደሚሰራባቸው መሳሪያዎች ተደርገው ሊወገዙ ይገባል፡፡ የጋራ ፍቅር እና መተማመን በቤተክርስቲያን አባላት መካከል መበረታታትና መጠናከር ይገባቸዋል፡፡ ሁሉም፣ በፈሪሃ እግዚአብሔር እና ለወንድሞቻቸው ባላቸው ፍቅር ለሀሜት እና ለትችት ጀሮቻቸውን ይዝጉ፡፡ ሀሜተኛውን ሰው ወደ ቃለ እግዚአብሔር ትምህርት በቀጥታ አመላክቱት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲታዘዝ በመጠየቅ አለኝ የሚለውን ቅሬታ ተሳስተዋል ብሎ ላሰባቸው ሰዎች በቀጥታ አቅርብ ብላችሁ ሞግቱት፡፡ ይህ የተባበረ ተግባር በቤተክርስቲያን ላይ የብርሃን ጎርፍ እንዲጎርፍ ሲያደርግ በአንፃሩ የክፋትን ጎርፍ ይገድባል፡፡ ይህ ሲሆን እግዚአብሔር ይከብራል ፤ በጣም ብዙ ነፍሳትም ይድናሉ፡፡”—Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 609–610 2. ብርሃንን በአንክሮ መውሰድ ሰኞ ህዳር 30 ሀ. እቅድ ስናቅድ ሁልጊዜም ቢሆን በልባችን መያዝ ያለብን ነገር ምንድን ነው? መዝ 16:8; ያዕ 4፡- 10፣ 13-16 “በማለዳ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችሁ አስረክቡ ፤ ይህ የመጀመሪያ ተግባራችሁ እንዲሆን አድርጉ፡፡ ፀሎታችሁ፡- “ኦ ! ጌታ ሆይ ውሰደኝ ሙሉ በሙሉ የራስህ አድርገኝ እቅዶቼን ሁሉ በእግርህ ሥር አስቀምጣለሁ። ዛሬ ለአገልግሎትህ ተጠቀምብኝ፡፡ ከእኔ ጋር ሁንና የማደርገውን ነገር ሁሉ በአንተ እንዳደርገው እርዳኝ” የሚል ይሁን፡፡ በየማለዳ ለዚያ ቀን ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችሁ ስጡ፡፡ የእርሱ ምሪት በሚያሳችሁ መሰረት ወይ እንዲከናወኑ አልያም እንዲከሽፉ እቅዶቻችሁን ሁሉ ለእርሱ ስጡ፡፡ በዚህም መሰረት ዕለት በዕለት ሕይወታችሁን ለእግዚአብሔር እጆች ትሰጣላችሁ ፤ ሕይወታችሁም ክርስቶስን ወደ መምሰል እየተለወጠ ይሄዳል፡፡”— Steps to Christ, p. 70. ለ. በሁሉም የሕይወት ጉዳዮች ለተሰጠን ሰማያዊ ብርሃን እያንዳንዳችን ያለብንን የከበረ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ይግለፁ? ያዕቆብ 4፡-17 ፤ ማቴዎስ 12፡- 31፣32 “የሰዎችን ዓይን የሚያሳውርና ልባቸውንም የሚያደነድን እግዚአብሄር አይደለም፡፡ ይልቁንም በአስተማማኝ መንገድ እንዲሄዱና ስህተታቸውንም እንዲያርሙ ብርሃን ይልክላቸዋል፡፡ ይህን ብርሃን ችላ በማለት ነው ዓይን የሚታወረው ልብም የሚደነድነው፡፡ ሂደቱ ብዙውን ጊዜ አዝጋሚና ጎልቶ የማይታወቅ ነው፡፡ ብርሃን ወደ ነፍሳት የሚደርሰው በእግዚአብሄር ቃል፣ በአገልጋዮቹ ወይም በቀጥታ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ነው፡፡ ነገር ግን ከሚሰጠው ብርሃን አንዲት ጨረር እንኳን ችላ ከተባለች፣ መንፈሳዊ ነገርን የማስተዋል ችሎታ በከፊል ስለሚቀንስ ለሁለተኛ ጊዜ የሚገለፀው ብርሃን የደበዘዘ ይሆናል፡፡ በዚህ አኳኋን ጨለማው እየጨመረ ሲሄድ ነፍስ ጥቅጥቅ ጨለማ ውስጥ ትሆናለች፡፡”—The Desire of Ages, p. 322.“የጥርጣሬ ቃል መናገር፣ ስለ መለኮታዊ ብርሃን ጥያቄ ማንሳት ወይም ያን ብርሃን መንቀፍ አደገኛ ነው፡፡ በግድየለሽነትና አክብሮት በጎደለው መንፈስ የሚደረግ የትችት ልምድ ንቀትና አለማመን ሥር እንዲሰዱ በማድረግ በጠባይ ላይ ለውጥ ያስከትላል፡፡ ለዚህ ዓይነት ልምድ ተገዥ የሆነ ሰው ያለበትን አደገኛ ሁኔታ ባለመገንዘብ የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ለመተቸትና ችላ ለማለት የተዘጋጀ ይሆናል፡፡” —Ibid, p. 323.“ሰዎች ስለ ጤና ርዕሰ ጉዳይ ሲናገሩ ብዙ ጊዜ 'ማወቅ ካለብን ነገር የበለጠ ብዙ እናውቃለን' ይላሉ። አካላዊ ደህንነታቸውን በተመለከተ ለእያንዳንዱ የብርሃን ጨረሮች ተጠያቂ መሆናቸውን እና እያንዳንዱ ልማዳቸው ለእግዚአብሔር ምርመራ በግልጽ የሚታይ መሆኑን አይገነዘቡም።”—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 372 3. ከሚገባው በላይ የተጋነነ ኃብት (RICHES OVERESTIMATED) ማክሰኞ ታህሳስ 01 ሀ. ከሌሎች በላይ በቁሳዊ ኃብት የተባረኩ ሰዎች የከበቧቸውን ፈተናዎች አስመልክቶ ምን ማስጠንቀቂያ ተሰጠ ? ያዕቆብ 5፡-1 “ አገልጋዮች (ሚነስተሮች) የሙገሳ ቃላትን የሚያጎርፉ ወይም ፊትን አይተው የሚያዳሉ መሆን የለባቸውም፡፡ ለሀብታሞች በትንሹም ቢሆን ልዩነት የመፍጠር ካልሆም እነርሱን በቃል ደረጃ የማድነቅ አደጋ ድሮም፣ እስካሁን ድረስ የመሳሳት ከፍተኛ አደጋ እዚህ ላይ ተደቅኖአል፡፡ ለጥቅም ሲባል ‘ለሰዎች አድናቆት የማጉረፍ’ አደጋ አለ ፤ ዳሩ ግን ይህን በማድረግ ዘላለማዊ ፍላጎታቸው (ሕይወታቸው) አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ አንድ አገልጋይ (ሚኒስቴር) ምናልባት ከተወሰኑ ባለጸጋ ሰዎች የተለየ ሞገስ በማግኘት ልግስና ተችሮት ሊሆን ይችላል ፤ በዚህም አገልጋዩ የልቡ ደርሶ ሊደሰትና፣ በፋንታው ደግሞ ላደረገለት በጎ አድራጎት ለሰጪው (ለዶነሩ) የውዳሴ ቃል እንዲያጎርፍ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ምናልባት የሰጪው ስም በህትመት ውጤቶች ሊወጣ ይችላል ፤ ይሁን እንጂ ያ በልግስና የለገሰው ሰው ለጎረፈለት ምስጋናና ለተሰጠው መልካም ስም ጨርሾ ያልተገባ ሊሆን ይችላል፡፡ ልግስናው የተበረከተው፣ በገንዘቡ (በንብረቱ) መልካም ነገር ለማድረግ ወይም፣ አድናቆት ስላለው የእግዚአብሔርንም ዓላማ ለማስፋፋት ከሚል እጅግ ጥልቅና ህያው መርህ የመነጨ አይደለም ነገር ግን ከአንድ ከሆነ የራስ ወዳድነት ስሜት፣ ለጋስ ነው የሚል ስም ለማግኘት ካለው ጽኑ መሻት ተነስቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባት በስሜት ተነሳስቶ ሊለግስና በመርህ ደረጃ ልግስናው ጥልቀት የሌለው የታይታ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባት ስጥ ስጥ የሚያሰኝ ልብን የሚያላውሰውን እውነት በመስማት በወቅቱ የገንዘብ ቦርሳውን ከፍቶ ሊሆን ይችላል ፤ ይሁን እንጂ፣ ከዚህ ሁሉ በኋላ፣ ልግስናው ጥልቅ ዓላማ የለውም፡፡ በድንገት ይሰጣል ፤ ቦርሳውም እንዲሁ ድንገት ይከፈታል ከዚያም በጥንቃቄ ክርችም ብሎ ይዘጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ሰው አንዳች የምስጋና ቃል አይገባውም ፤ ምክንያቱም በማንኛውም የቃሉ መረዳት ቢታይ ገብጋባ (ስስታም) ነውና ፤ በመሆኑም በገንዘቡም ይሁን በሁሉም ነገር ሙሉ በሙሉ ካልተለወጠ በቁሙ የሚያደርቀውን (የሚያጠወልገውን) ውግዘት ተገዶ ይሰማል፡- ‘እንግዲህ እናንተ ባለ ጠጎች ስሙ፥ ስለሚደርስባችሁ መከራ ዋይ ዋይ እያላችሁ አልቅሱ፤ ሀብታችሁ ሻግቶአል ፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል’፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች በስተመጨረሻ እግጅ ዘግናኝ ከሆነው መታለል የሚነቁ ይሆናል፡፡ አልፎ አልፎ የሚለግሱ ሰዎችን የሚያሞግሱ ሰዎች ይሸነግላቸው (ያታልላቸው) ዘንድ ሰይጣንን ያግዙታል ፤ እንዲሁም የልግስናን ወይም መስዋዕት የመክፈልን የመጀመሪያ መርሆዎች ምንም የማያውቁ ሆነው ሳሉ፣ ነገር ግን በጣም ለጋሶች፣ ከፍተኛ መስዋእት ከፋዮች እንደሆኑ አድርገው ራሳቸውን እንዲቆጥሩ ያደርጓቸዋል፡፡ ”—Testimonies for the Church, vol. 1, pp. 475, 476. ለ. ገንዘብን በበተመለከተ በቅድሚያ የሚያሻንን ነገር እንዴት ነው ማሻሻል የምንችለው ? ምሳሌ 11:4. “የበጎ አድራጎት ልግስናን መለማመድ፣ (የሕይወት) መርህ እስኪሆንና የነፍስንም ዙፋን እስኪቆጣጠር ድረስ ዘወትር እየጎለበተና እየጠናከረ ይሄዳል፡፡ በልብ ውስጥ ራስ-ወዳድነትና ስግብግብነት ትንሽ ሥፍራም እንዲያገኝ መፍቀድ ለመንፈሳዊ ሕይወት እጅግ በጣም አደገኛ ነገር ነው፡፡ ”—Ibid., vol. 3, pp. 548, 549. 4. ጣኦትን ጨርሶ ማስወገድ ረቡዕ ታህሳስ 02 ሀ. ሰዎች ኃብትን የሚያገኙት በአብዛኛው በምን ምክንያት ነው? ያዕቆብ 5:-2 (የመጀመሪያው ክፍል) “የዚህ ዘመን ትውልድ ሃብት በማፍራት ጥልቅ ፍቅር ውስጥ ወድቋል፡፡ ብዙ ጊዜ ሀብት የሚገኘውም በማጭበርበር ነው፡፡ ለትንሽ ደመወዝ ላባቸውን ጠብ አድርገው ለመሥራት የተገደዱ፣ መሰረታዊ የኑሮ ፍላጎትን እንኳ ማሟላት አዳግቷቸው በድህነት እየተቆራመዱ የሚኖሩ ሥፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ በእጦት ተቸግረው፣ በጥረት ግረት እየለፉ ተስፋ በማጣታቸው ቀንበራቸውን አክብዶባቸዋል፡፡ በኑሮ አሳብ ተጨንቀውና ተጨቁነው እፎይታ ለማግኘት አቤት ለማለት ወደ ማን እንደሚዞሩ ግራ ገብቷቸዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ታዲያ ሃብታሞች በምቾትና በመንፈላሰስ ያላቸውን ማካበት ብቻ !“ገንዘብን መውደድና ሃብትን ማካበት ይህችን ዓለም የሌቦችና የቀማኞች ዋሻ አድርጓታል፡፡ ከክርስቶስ ዳግም ምፃት በፊት የሚሆነውን ስግብግብነት (ሆዳምነት) እና ጭቆና መጽሐፍ ቅዱስ ቁልጭ አድርጎ ገልፆታል።”— Prophets and Kings, p, 650,651 (ነቢያትና ነገሥታት ገጽ 650,651) ለ. ዛሬ ዓለምን በአብዛኛው የሚያነሳሳቸው ምንድን ነው? በገንዘብ ፍቅር ለሚነዱ ሰዎች ምን ተማጽኖ ነው መቅረብ ያለበት ? 1ኛ ጢሞ 6:- 9፣10 ፤ ዘዳ 8: 18፣19 “ኃብቱን በሀቅ እስካገኘው ድረስ አንድ ሰው ሃብታም ስለሆነ ብቻ መጽሐፍ ቅዱስ አይዘልፈውም፡፡ የክፋት ሁሉ ሥር የሆነው ገንዘብ ሳይሆን ለገንዘብ ያለው ፍቅር ነው፡፡ ሀብት እንዲያገኝ ለሰው ጉልበትን የሰጠ እግዚአብሄር ነው ፤ በመሆኑም ሀብቱን እየተጠቀመ ገንዘቡን እንደ የእግዚአብሄር መጋቢነት ለሚሰራ ሰው ለባለ ገንዘቡም ሆነ ለዓለምም ጭምር በረከት ነው፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ዓለማዊ ሀብት በማግኘት ፍቅር ተመስጠው እግዚአብሔር ለሚጠይቃቸው መጠየቅና የባልንጀሮቻቸውንም ፍላጎት ለማሟላት ህሊናቸው ደንዝዟል፡፡ ገንዘባቸውን ራሳቸው ለማስከበሪያነት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ነገር አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ቤቶቻቸውን በቅንጦት እቃዎች ይሞላሉ ፤ ነገር ግን በዙሪያቸው ሰብዓዊ ዘር በሰቆቃ፣ በወንጀልና በበሽታ እየማቀቁ በሞት እየተቀጠፉ እነርሱ ግን በቤት ላይ ቤት፣ በመሬት ላይ መሬት ይጨምራሉ፡፡ እነዚህ በዚህ መልኩ ራሳቸውን ለማገልገል ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ሰዎች በህይወታቸው ላይ የእግዚአብሔር ባህርይ ሳይሆን ነገር ግን የእርጉሙን ባህርይ ይገነባሉ፡፡“ ለእነዚህ ወንጌል በጣም ያሻቸዋል፡፡ አይኖቻቸውን ከንቱ ከሆነው አላፊ ጠፊ ቁስ አንስተው እጅግ ክቡር ወደሆነው ዘላለማዊ ሃብት ማዞር አለባቸው፡፡ …“ አንዳንዶች ከፍ ላለው የሕብረተሰብ ክፍል ለመሥራት የሚያስችል የተለየ ብቃት አላቸው፡፡ እነዚህ ወገኖች ወደ ታለሙት አባላት እንዴት መድረስ እንዳለባቸው እንዲያውቁ እግዚአብሄር ጥበብ ይሰጣቸው ዘንድ እርሱን መጠየቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ከእነርሱ ጋር የሚፈጥሩት ትውውቅ ተራ መሆን የለበትም ፤ ይልቁንም በየሱስ ወዳለው የእውነት እውቀት የሚመራውንና ግላዊ ጥረት የታከለበትን ሕያው እምነት ተጠቅመው ለነፍሳቸው የሚያስፈልገውን እንዲያውቁ ካንቀላፉበት መቀስቀስ ይኖርባቸዋል፡፡”—The Ministry of Healing., pp. 212,213. 5. ከቁሳዊው ዓለም ባሻገር መመልከት / LOOKING BEYOND MATERIALISM ሐሙስ ታህሳስ 03 ሀ. በወንጀል የተገኘ ሀብት የሚያመጣውን መዘዝ ይግለፁ፡፡ ያዕቆ 5፡- 2 (የመጨረሻው ክፍል) “ሀብት በማጭበርበር ማግኘት፣ በንግድ ማጭርበር፣ መበለቶችና አባት የሌላቸውን መጨቆን፣ ወይም ለራስ ማከማቸትና የተቸገሩ ድሆችን ችላ ማለት የኋላ ኋላ በመንፈስ በተነሳሳው ሐዋሪያ የተገለፀው ፍትሃዊ ፍርድ እንዲወርድ ያደርጋል፡፡”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 682. ለ. ሃብትን በተመለከተ የእግዚአብሔር ልዩ መልዕክት ምንድን ነው ? 1ኛ ጢሞቴዎስ 6:17–19. “እጅግ ትሁትና ድሆች የሆኑ፣ በመልካም ሥራ ግን የበለፀጉ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት፣ ባላቸው ታላቅ ሀብት ከሚኩራሩ ሰዎች ይልቅ በእግዚአብሔር እይታ እጅግ የተባረኩና የከበሩ (ክቡር ዋጋ ያላቸው) ናቸው፡፡ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለፀጋ ካልሆኑት እጅግ ከተከበሩት ነገሥታት ይልቅ፣ እነርሱ በሰማይ አደባባ እጅግ የተከበሩ ናቸው፡፡. . .“እነዚያ የቤተሰባቸው ማግኘት ያለባቸውን ደስታና ምቾት አራቁተው (ነፍገው) ገንዘብን የሚያከማቹ ወይም በመሬት ግዥ ላይ በስፋት እያፈሰሱ ያሉ ሰዎች እብዶች እንደሚያደርጉት እያደረጉ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር በብልጽግና አትረፍርፎ የሰጣቸውን በረከት ቤተሰቡ ይደሰቱበት ዘንድ አይፈቅዱላቸውም፡፡ ምንም እንኳ በጣም ብዙ ሀብት ቢኖራቸውም፣ የቤተሰቡ አባላት ብዙ ንብረት ያከማቹ ዘንድ፣ አሁንም ገና ብዙ ገንዘብ ለመቆጠብ አቅማቸው ከሚፈቅደው በላይ አዘውትረው ለመስራት ይገደዳሉ፡፡ ሀብት ለማካበት፣ አዕምሮ፣ አጥንት፣ እንዲሁም ጡንቻ እስከ መጨረሻው በሥራ ብዛት ይወጠራሉ ፤ በአንፃሩ ኃይማኖት ክርስቲያናዊ ግዴታዎች ተረስተዋል፡፡ ከጠዋት እስከ ማታ የነፍሳቸው ምኞት ሥራ፣ ሥራ፣ ሥራ የሚል ነው፡፡“ብዙዎቹ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመማር እና ከእነርሱ የሚሻውንም ነገር ለማስተዋል ቅን ፍላጎት እያሳዩ አይደለም፡፡ እውነትን ለሌሎች ለማስተማር እየጣሩ ያሉ አንዳንዶቹ የጌታን ቃል ራሳቸው አይታዘዙትም፡፡ እንደነዚህ ያሉ አስተማሪዎች ተጽዕኖ በእግዚአብሔር ዓላማ ላይ ባረፈ ቁጥር፣ የሚገኘው ውጤትም እጅግ ያነሰ ይሆናል፡፡”— Ibid., pp. 682, 683 የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ታህሳስ 04 1. በሌሎች ስህተት ላይ በማተኩርበት ጊዜ ምን እያደረኩኝ ነው ? 2. ሰማይ የላከውን ብርሃን ችላ ስል፣ መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደሚያዝን ግለፁ ? 3. ሀብታሞች እና ሚኒስተሮች (ፓስተሮች) ወደ ወጥመድ እንዴት ሊወድቁ ይችላሉ ? 4. ስስታምነት ለምንድነው እየጨመረ ያለው፣ ከመቼውም ይልቅ አሁን ማስወገድ ያለብን ለምድን ነው? 5. በክርስቶስ ራስን ማዋረድ (ትህትና) የተላበሰውን ውበትና ጥቅም ይግለፁ፡፡ << >>