Back to top

Sabbath Bible Lessons

ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ

 <<    >> 
ሰንበት፣ ጥቅምት 02፣ 2017 2ኛ ትምህርት
የመቋቋም ጥበብ “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።” (ያዕቆብ 1፡5)።
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Testimonies for the Church, vol. 1, pp. 120, 121; vol. 2, pp. 232–235
“እግዚአብሔር ቅርብ ነውና ጥበብን ፍለጋ ወደ ምድር ዳርቻዎች መሄድ አያስፈልግም። ስኬትን የሚሰጣችሁ አሁን ያላችሁ ወይም የሚኖራችሁ ችሎታዎች አይደሉም። ጌታ ለእናንተ ሊያደርግ የሚፈልገው ይህ ነው። . . . በጊዜአዊ (በሥጋዊ) እና በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ማስተዋልን ሊሰጣችሁ ይናፍቃል። እሱ የማሰብ ችሎታችሁን ማጎልበት ይችላል። ብርታትና ብልሃትን መስጠት ይችላል። መክሊትህን በሥራ ላይ አውል፣ ጥበብ እንዲሰጥህ አምላክን ጠይቅ፣ እሱም ይሰጣሃል።”—Christ’s Object Lessons, p. 146.

1. ጥበብን ለማግኘት መጸለይ እሁድ መስከረም 26
ሀ. በሕይወታችን ውስጥ ከሰበአዊ ጥበብ በላይ የምንፈልገው ለምንድን ነው? እንዴትስ ማግኘት ይቻላል? ያእቆብ 1:5 “ሰው ማድረግ በሚችለው ነገር ላይ መተማመን በመተዉ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ አማኝ ነፍስ ሊያደርግ በሚችለው ነገር ላይ የበለጠ መተማመን አለብን። እርሱ ከኋላዉ በእምነት እንድትከተል ይፈልጋልና። ከእርሱ ታላቅ ነገርን ለማግኘት እንድትጠብቅ ይናፍቃል።”—Christ’s Object Lessons, p. 146“በየሰንበት ቀኑ ስብከቶችን መስማት ብቻ፣ መጽሐፍ ቅዱስን እየገለጥን ማንበብ፣ ወይም በቁጥር በቁጥር ማብራሪያ መስጠታችን ብቻ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ወደ ግል ልምዳችን ካላመጣን በስተቀር ለእኛም ሆነ ለሚሰሙን አይጠቅምም። ማሰተዋላችን፣ ፈቃዳችን፣ ፍቅራችን፣ ለእግዚአብሔር ቃል ቁጥጥር መሰጠት አለበት። ያኔ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ የቃሉ ሕግጋቶች የሕይወት መርሆዋችን ይሆናሉ።“ጌታ እንዲረዳህ ስትለምን በረከቱን እንደምትቀበል በማመን አዳኝህን አክብር። ኃይል ሁሉ ጥበብ ሁሉ በእኛ ቁጥጥር ሥር ነው። ማድረግ ያለብን መጠየቅ ብቻ ነው።”—The Ministry of Healing, p. 514.

2. በመተማመን የተጠናከረ ሰኞ መስከረም 27
ሀ. የአምላክን ጥበብ ከራሳችን አልፎ ተርፎም በሕይወታችን ውስጥ ካሉት የተለመዱ ነገሮች የላቀ እንደሆነ አድርገን የምንመለከተው ከሆነ ምን ጥቅም እናገኛለን? ምሳሌ 3፡3-8 “ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ይሰጠዋልም። እንዲህ ዓይነቱ የተስፋ ቃል ከወርቅ ወይም ከብር የበለጠ ዋጋ አለው፡፡ በትሑት ልብ በእያንዳንዱ ችግር እና ግራ መጋባት ውስጥ መለኮታዊ መመሪያን ከፈለግክ፣ የጸጋ መልስ እንደሚሰጥህ በቃሉ ቃል ገብቷል። ቃሉም ፈጽሞ ሊወድቅ አይችልም። ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሉ ግን አያልፍም። በጌታ ታመኑ፣ ከቶ አታፍሩም። “በሰው ከመታመን በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል። በአለቆች ከመታመን በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።”“በሕይወት ውስጥ ምንም ዓይነት የሥልጣን ቦታ ብንይዝ፣ ሥራችን ምንም ይሁን ምን እርዳታ እንደሚያስፈልገን እንዲሰማን ትሑት መሆን አለብን። በእግዚአብሔር ቃል በመደገፍ፣ ሁሉንም ነገር እርሱ እንደሰጠን እውቅና በመስጠትና ነፍሳችንን በጸሎት በፊቱ በማፍሰስ ታማኝ መሆን አለብን። በራሳችን ማስተዋል ከተደገፍን፣ ውድ ወንድሞቼ፣ በአለም ውስጥ ስንጓዝ፣ ሀዘንና ብስጭት እናጭዳለንና። በፍጹም ልብህ በጌታ ታመን፣ እርሱ እርምጃህንም በጥበብ ይመራል፣ የሚያስፈልጉህ ነገሮች ሁሉ በዚህም ሆነ ለቀጣዩ ሕይወት የተሟሉ ይሆናሉ። ብርሃንና እውቀት ያስፈልግሃል፡፡ ከእግዚአብሔር ካልሆነ ደግሞ ከራስህ ልብ ትመካከራለህ፤ ከልብህ ጋር ከሆነ የተመካከርከዉ በራስህ ጭስ ውስጥ ትባዝናለህ፣ ከአምላክ ጋር ከሆነ ደግሞ መለኮታዊ ብርሃንን ከጽድቅ ፀሐይ ወደ ራስህ ትሰበስባለህ።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 427. ለ. መመሪያ ለማግኘት በሌሎች ሰዎች ላይ ከመደገፍ ራሳችንን ማላቀቅ ለምን ያስፈልገናል? ኤርምያስ 17:5-8 “ግራ መጋባት ሲፈጠርና ችግሮች ሲያጋጥሙህ ከሰው ልጅ ዘንድ እርዳታ አትፈልግ። ሁሉንም ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ። ችግሮቻችንን ለሌሎች የመንገር ልምዳችን ደካሞች ያደርገናል እንጂ ጥንካሬን አያመጣልንም። የመንፈሳዊ ድክመቶቻችንን ሸክም በእነርሱ ላይ ይጭንባቸዋል፣ እነሱም ሊያስወግዱት አይችሉም። የማይሳሳት፣ ወሰን የሌለው አምላክ ብርታት ማግኘት እየቻልን ለምን ተሳሳችና ሟች የሆነዉን የሰዉን ልጅ እርዳታ ለምን እንሻለን።”—Christ’s Object Lessons, p. 146

3. የላቀ መረጋጋትን ማዳበር ማክሰኞ መስከረም 28
ሀ. ጌታ ልመናችንን ከመመለሱ በፊት ምን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት አለብን? ያዕቆብ 1:6 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ ማርቆስ 11፡24። በዚህ ረገድ ጥንካሬን ለማዳበር እንዴት መወሰን እንደምንችል የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ግለጽ። 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡3–5 “በዚህ ጉዳይ ላይ ሸክሙን በሚሸከሙት ጥቂት አገልጋዮች ላይ ያለውን ሃላፊነት የሚገነዘቡት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። ወንድሞች እነዚህን ሰዎች፣ በራሳቸዉ ሊፈቷቸዉ በምችሏቸዉ በጥቃቅን ጉዳዮቻቸውን እነሱ እንዲፈቷቸዉ ወይም አንዳንድ የቤተ ክርስቲያንን ፈተናዎች ለመፍታት ከሥራቸው ላይ ደጋግመው ይጠሯቸዋል። “ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፣ እርሱም ይሰጠዋል፡፡” ነገር ግን በጸሎት ትጉና ታታሪ መሆን አለበት። ቆራጥ ካልሆነ፣ ጌታ የገባውን ቃል እንደሚፈጽም ያለማቋረጥ የሚጠራጠር ከሆነ ምንም አያገኝም።“ብዙዎች ለራሳቸው ወደ እግዚአብሔር ከመሄድ ይልቅ ይህን ርካሽ መንገድ በማሰብ አገልጋዮቻቸውን ከእግዚአብሔር ብርሃን እንዲያመጡላቸው ይፈልጋሉ። እንደዚህ ሲያደርጉ ብዙ ነገርን ያጣሉ፡፡ ክርስቶስን በየቀኑ ከተከተሉና እርሱን መሪና አማካሪ ካደረጉት፣ ስለ ፈቃዱ ግልጽ እውቀት ሊያገኙና በዚህም ጠቃሚ ልምድ እያገኙ ይሄዳሉ። እውነትን የሚያምኑ አንዳንድ ወንድሞች ይህን ልምድ በማጣታቸዉ በሌሎች ሰዎች ብርሃን ይመላለሳሉ። ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ምንም አይተዋወቁም እንዲሁም ስለ ፈቃዱ ምንም እውቀት የላቸውም፣ ስለዚህም በቀላሉ እምነታቸው ይሸረሸራል፡፡ እነሱ ያልተረጋጉ ናቸው፣ ምክንያቱም ለራሳቸዉ ልምድ ለማግኘት በሌሎች ላይ የመመርኮዝ እምነት ነበራቸውና።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 643, 644. ለ. ክርስቲያን ነኝ የሚል ግን እምነቱ የሚዋልል ከሆነ ከምን ጋር ይነጻጸራል? ያዕቆብ 1:6 (የመጨረሻው ክፍል)፤ ዘፍጥረት 49:4 (የመጀመሪያ ክፍል) ይህን እንዴት ማስወገድ እንችላለን? “የአብዛኞቹ ክርስቲያኖች ለጉባኤና ለጸሎት አንድ ላይ መሰብሰባቸውን በማቋረጥ ለጥቅት ቸል ቢሉ እምነታቸው ይናወጣል።”—Ibid., vol. 4, p. 106“የክርስቶስን ቃል እንደ ማረጋገጫ ያዙ። ወደርሱ እንድትመጡ አልጠራችሁምን? ተስፋ በሌለውና ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ መንገድ በፍጹም እንዳትናገር። ይህን ካደረግክ ብዙ ታጣለህ። ይህም ከላይ ላዩን በመመልከት ብቻ ችግሮችና ጫናዎች ሲደርሱ ማጉረምረምህ፣ መናኛና ደካማ እምነት እንዳለህ ያሳያል። ስትናገርም ሆነ ስትሠራ፣ እምነትህ የማይበገር ይመስል።”—Christ’s Object Lessons, pp. 146, 147

4. የተከፋፈለ ልብን ማስወገድ ረቡዕ መስከረም 29
ሀ. ጥበብ ለማግኘት የምናቀርበው ጸሎት ምላሽ እንደሚያገኝ እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? ሉቃስ 18:1፤ ያእቆብ 1:6፣ 7 “[ጥበብን ለማግኘት የሚደረግ] ልመና ከአእምሮ የወጣ፣ ትርጉም የለሽ ጸሎት መሆን አይደለም። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመወሰን ከጥበብ ጉድለት የሚመነጨው ጠንካራ የልብ ፍላጎትን የሚገልጽ ጸሎት ነው።“ከጸሎቱ በኋላ፣ መልሱ ወዲያውኑ ካልመጣ ለመጠበቅ አይታክቱና የተረጋጋችሁ ሁኑ፤ አትጠራጠሩም። የጠራችሁ የታመነ ነው እርሱም ደግሞ ያደርጋል የሚለውን የተስፋ ቃል ያዙ። እንደ መበለትዋ ሴት፣ ለዓላማችሁ ጽኑ። ነገሩ ለእርስዎ ጠቃሚና ትልቅ ውጤት ያለዉ ነውን? በእርግጥ አዎ፡፡ እምነታችሁ ሊፈተን ይችላልና አትጠራጠሩ። የምትመኙት ነገር ዋጋ ያለው ከሆነ ለጠንካራ፣ ልባዊ ጥረት ይገባዋልና። የተስፋው ቃል አለላችሁ፤ ትጉና ጸልዩ፡፡ ጽኑ ሁኑ፣ ጸሎቱ ምላሽ ያገኛል፤ ተስፋ የሰጠውስ አምላክ አይደለምን? እሱን ለማግኘት አንድ መስዋዕትነት የሚያስከፍልዎት ከሆነ ሲያገኙት የበለጠ ያመሰግናሉና። የምትጠራጠሩ ከሆነ ከጌታ አንዳች ነገር እንደምትቀበሉ እንዳታስቡ በግልፅ ተነግሯችኋል። እንዳትዝሉ፣ ነገር ግን በተስፋው ላይ ጸንተን እንድትኖሩ ማስጠንቀቂያ እዚህ ተሰጥቷል። ጤቁም አብዝቶም ይሰጣችኋል፡፡ብዙዎች የሚሳሳቱበት ቦታ እዚህጋ ነዉ። ከዓላማቸው ይርቃሉ፣ እምነታቸውም ይወድቃል። የብርታታችን ምንጭ ከሆነው ከጌታ ምንም የማያገኙት በዚህ ምክንያት ነው። እንደ ዕውርም እየተሰናከሉ በጨለማ መሄድ አያስፈልግም። ጌታ ብርሃንን ሰጥቷቸዋልና እነርሱም እሱ ባዘዘው መንገድ ቢሄዱና የራሳቸውን መንገድ ባይመረጡ ሁሉም ይከናዉንላቸዉ ነበር። የዕለት ተዕለት ሥራዎችን በትጋት መፈጸምን ይጠይቃቸዋል።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 130, 131. ለ. ለምንድነው ከተከፋፈለ ሀሳብ መራቅ ያለብን? ያዕቆብ 1:8፤ መዝሙረ ዳዊት 86:11 “ክርስቲያን ነን እያሉ ብዙዎች የዓለምን ቅርጽ አላቸው፣ እናም ፍቅራቸው በአምላክ ላይ የተመሠረተ አይደለም። በአንድ ጊዜ እግዚአብሔርንና ጣኦትን ለማገልገል እየሞከሩ ያሉ ባለ ሁለት አስተሳሰብ ናቸው። . . . ሁለት ጌቶችን ለማገልገል በመሞከር፣ በመንገዳቸው ሁሉ ያልተረጋጉ ስለሆኑ በየትኛዉም ሊመኩ አይችሉም። . . .“የሰይጣን ሥራ አጸያፊ እነደሆነ የሚያሳዩ ቃላቶችን መናገር፣ ነገር ግን በተግባር ወደ እርሱ አሳብ ሁሉ ሰተት ብሎ መግባት፣ ምን ይጠቅማል? ይህ ባለሁለት ዓይነት አስተሳሰብ ባለቤት መሆን ነው።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 7, p. 938.

5. ያዕቆብን ማስታወስ ሐሙስ መስከረም 30
ሀ. የሱስ የአምላክን ፈቃድ ለመፈጸም የሚያስችል ጥንካሬ ለማግኘት ልመናችንን ማቅረብ ያለብን እንዴት ባለ ብርታት እንደሆነ የገለጸው እንዴት ነው? ማቴዎስ 11፡12 “የሰማዩ መንግሥት ግፍ ተፈጸመባት ፥ ግፈኞችም ያዙአት። ይህ ጥቃት በሙሉ ልብ ውስጥ ይይዛል፡፡ ሁለት አስተሳሰብ መያዝ ማለት አለመረጋጋት ማለት ነው። ለዝግጅት ስራ ቆራጥነት፣ ራስን መካድና የተቀደሰ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ማስተዋልና ኅሊና አንድ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ፈቃዱ ለሥራ ካልበረ ውድቀት ይከተለናል። ሁሉም ሀሳቦችና ስሜቶች በሥራዉ ላይ መሳተፍ አለባቸው፡፡ ቅንዓትና ልባዊ ጸሎት የግድየለሽነትንና የቸልተኝነትን ቦታ መውሰድ አለባቸው። በትጋት፣ በቁርጠኝነት እና በክርስቶስ ትሩፋቶች ላይ በማመን ብቻ ማሸነፍና ሰማን ማግኘት እንችላለን። የስራ ጊዜያችን አጭር ነው። ክርስቶስ በቅርቡ ዳግም ይመጣል።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 1, p. 1096.“የመቀበል እድል ባገኘነዉ በታላቅ እውነት እና በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ስር ህያው የብርሃን መስመሮች መሆን እንችላለን። ከዚያም ወደ ምሕረት መክደኛው መቅረብ እንችላለን፤ የተስፋውንም ጨረር በማየት በተሰበረ ልብ በመንበርከክ ሽልማትን በሚያስገኝ መንፈሳዊ ወጊያ መንግሥተ ሰማያትን እንፈልግ። ያዕቆብም እንዳደረገዉ ታግለን በጉልበት እናገኘዋለንና። ያኔ መልእክታችን የሚያድን የእግዚአብሔር ኃይል ያለዉ ይሆናል። ልመናችን በትጋትና በታላቅ ፍላጎት ስሜት የተሞላ ይሆናል። እኛም የጠየቅነዉን ነገር አንከለከልም። የያዝነዉም እውነት የሚገለጸው በህይወታችንና በባህርያችን፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ባለው ሕያው ፍም በተነካው ከንፈራችን ነው።“ይህ ልምዳችን የኛ ሲሆን፣ በጣም ከልብ ከምንከባከበው ከምስክኑና ርካሹ ማንነታችን እንወጣለን። ከሚያበስበሰዉ ከራስ ወዳድነት ኃይል ልባችንን ባዶ እናደርጋለን፣ ለእግዚአብሔርም በምስጋናና በዉዳሴ እንሞላለን። ክርስቶስን ያከበረ የጸጋ ሁሉ አምላክ የሆነውን ጌታን እናከብራለን። ኃይሉንም በእኛ ይገልጣል፥ በመከሩም እርሻ እንደስለታም ማጭድ ያደርገናል። አምላክ ሕዝቡን የጠራዉ እርሱን ለሌሎች እንዲገለጡ ነዉ።”—Reflecting Christ, p. 217.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ጥቅምት 01
1. ከሰማይ የላቀ ጥበብ ለማግኘት አንዳንድ አስፈላጊ ቁልፎችን ግለጽ። 2. በሰዎች እውቀት ላይ በመታመን ስንረካ ምን ይሆናል? 3. አገልጋዮችን ነጻ በማውጣት በአዲስ ነፍሳት ላይ እንዲያተኩሩ የበኩሌን ማድረግ የምችለው እንዴት ነው? 4. ከማስበው በላይ በየትኞቹ የሕይወት ዘርፎች የበለጠ ባለሁለት አሳብ ልሆን የምችለዉ? 5. በመጨረሻው ቀን የያዕቆብን ተጋድሎ ኃይልና አስፈላጊነት ግለጽ።
 <<    >>