ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ << >> ሰንበት፣ ህዳር 28፣ 2017 10ኛ ትምህርት የአመለካከት ችግሮቻችንን ማሸነፍ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፡፡” ያዕቆብ 4፡7 ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡ Testimonies for the Church, vol. 3, pp. 39–47. “ንጹሕ፣ የሚቀድስ እውነትንና ውዱ ቤዛችንን መውደድ፣ የአሸናፊነት ጉዟችንን ያቀልልናል።”—Testimonies for the Church, vol. 4, p. 38. 1. ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍትሃዊነት እሁድ ህዳር 22 ሀ. የሰማይ ጥበብ ዝርዝር ውስጥ የተጠቀሱትን የመጨረሻዎቹን ሁለት ባሕርያት ጥቀስ። ያዕቆብ 3፡17 (የመጨረሻው ክፍል)። “ሐዋርያው ይሁዳ ‘ከአንዳንዶች ርኅሩኆች ኑሩ’ ብሏል። ይህ ልዩነት በአድሎአዊነት መንፈስ መተግበር የለበትም። 'ከደገፈከኝ እደግፍሃለሁ' ለሚል መንፈስ ምንም ዓይነት ቦታ መስጠት የለብንም። ይህ እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ያልተቀደሰ፣ ዓለማዊ አካሄድ ነው። ለጥቅም ሲባል ሞገስንና አድናቆትን መክፈል (መስጠት) ነው፡፡ በእነሱ በኩል ጥቅማጥቅሞችን እንደምናገኝ በማሰብ ለተወሰኑ ሰዎች አድልዎ ማሳየት ነዉ። ከሌሎች ይልቅ እኛን የተሻልን ብቁ አድርገዉ እንዲመለከቱን በትጋት በመመላለስ የእነርሱን በጎ ፈቃድ መፈለግ ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 4, pp. 221, 222.“እግዚአብሔር በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በሚደረገው ስንፍና ሥራ ደስ አይለውም። ተግሣጽና እርማት ለመስጠት የእርሱ መጋቢዎች እውነተኛና ታማኝ እንዲሆኑ ይጠብቃል። ስህተትን ማስወገድ ያለባቸው እግዚአብሔር በቃሉ በሰጠው አካሄድ መሠረት ነው እንጂ እንደራሳቸው ሃሳብና ስሜት አይደለም። ጠንከር ያለ መንገድ መጠቀም የለባቸዉም፣ ፍትሃዊ ያልሆነ፣ በጥድፊያ፣ በስሜት ስራ መሠራት የለበትም። ቤተ ክርስቲያንን ከሥነ ምግባር ርኩሰት ለማንጻት የሚደረገው ጥረት በእግዚአብሔር መንገድ መከናወን አለበት። ወገንተኝነት፣ ግብዝነት መኖር የለበትም። ኃጢአታቸው ከሌሎች ሰዎች ኃጢአት ያነሰ ኃጢአት ተደርጎ የሚቆጠርላቸዉ ተወዳጆች ሊኖሩ አይገባም፡፡ ኦ፣ ሁላችንም የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ምን ያህል ያስፈልገናል? ያን ጊዜ በክርስቶስ አእምሮ፣ በደግነት፣ በርኅራኄና በሀዘኔታ፣ ኃጢአትን ፍጹም በሆነ ጥላቻ እየጠላን ለኃጢአተኛው ፍቅር በማሳየት እንሠራለን።”—The Ellen G. White 1888 Materials, p. 144. 2. ክርስቶስን በትክክል መወከል ሰኞ ህዳር 23 ሀ. በንግግራችን ውስጥ ክርስቶስ ብቻ በትክክል መወከል የምንችለው እንዴት ነው? ያእቆብ 3፡18 “በከንፈራችን ክርስቶስን መመስከርና በስራችን ደግሞ እርሱን መካድ ይቻላል። በሕይወታችን የሚገለጡ የመንፈስ ፍሬዎች ስለክርስቶስ ይናገራሉ። ሁሉን ለክርስቶስ የተውን ከሆነ ሕይወታችን ትሑት፣ ንግግራችን ሰማያዊ፣ ምግባራችንም ነውር የለሽ ይሆናል። በነፍስ ውስጥ ያለው ኃይለኛ፣ የሚያነጻው የእውነት ተጽእኖ፣ እና የህይወት ውስጥ ምሳሌ የሆነው ክርስቶስ ባህሪይ፣ ስለእርሱ ይናገራሉ። የዘላለም ሕይወት ቃል በልባችን ውስጥ ከተዘራ ፍሬው ጽድቅና ሰላም ነው። ምቾትን ወይም ራስን በመውደድ፣ በማሾፍና በመቀለድ፣ እንዲሁም የአለምን ክብር በመሻት ክርስቶስን በህይወታችን ልንክደው እንችላለን። ከዓለም ጋር በመስማማት፣ በኩራት መልክ ወይም ውድ ልብስ በመልበስ በውጫዊ መልካችን ልንክደው እንችላለን። በሕይወታችን ውስጥ የክርስቶስን ባሕርይ ወይም የእውነትን የመቀደስ ተጽዕኖ ማሳየት የምንችለው በማያቋርጥ ነቅቶ በመጽናትና በማያቋርጥ ጸሎት ብቻ ነው። ብዙዎች ክርስቶስን ከቤተሰቦቻቸው ያባረሩት ትዕግስት በሌለው፣ በጋለ መንፈሳቸዉ ምክንያት ነው። በዚህ ረገድ እንዲህ ያሉት ነገሮች ሊያሸንፉት የሚገባቸዉ አሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 1, pp. 303, 304. ለ. በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚረጩትን፣ የትኞቹን የተለመዱ የሰዉ ልጅ ዝንባሌዎችን ነዉ በእርግጥ ማሸነፍ ያለብን—ለምን? ያእቆብ 4:1-3 “በዙሪያችን ወይም ተግባሮቻችን ተራና አስፈላጊ ያልሆኑ ወደሚመስሉበት ሁኔታ ላይ ባደረሱን ሁኔታዎች መበሳጨት በጣም አሳዛኝ ነገር ነው። የግልና ተራ (ዝቅ ያሉ) ተግባራት ለአንተ አስጸያፊ ሆነዉ ይታዩሃል፤ በዚህም እረፍት የለሽ፣ የተቸገርክና እርካታ አልባ ሆነሃል። ይህ ሁሉ የሚመለጨዉ ከራስ ወዳድነትህ ነው። . . .“ያለማቋረጥ የሚያለቅሱና የሚያጉረመርሙ፣ ደስተኛነትና የደስታ ፊት ማሳየት እንደ ኃጢአት የሚሰማቸው ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች እውነተኛ የሃይማኖት ርዕስ (ልብ) የላቸውም።”—Ibid., vol. 3, p. 334.“ስለሚጣፍጥ አሁንም በኋላም እጥፍ ድርብ (ከመጠን በላይ) እየበላሁ፣ ስለ ሆዳምነቴ ግንዛቤ ማግኘት ባልቻልኩበት ሁኔታ ዉሥጥ ሆኘ፣ በጽሑፍ ሥራዬ እንዲረዳኝ እንዴት ተንበርክኬ እግዚአብሔርን ልለምን እችላለሁ? በሆዴ ዉስጥ የወጠኩትን ምክንያታዊ ያልሆነ ሸክም እንዲንከባከበልኝ እግዚአብሔርን መጠየቅ እችላለሁን? ይህ እርሱን ማዋረድ ነው። ያ በገዛ ራሴን ባለመግዛት ኃጢአቴ እርሱ እንድተባበረኝ መጠየቅ ነው። አሁን ያሻኝን ያህል ግብስብስ በልቼ፤ ከዚያም እሱ እንድሠራው የሰጠኝን ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ኃይል እንዲሰጠኝ መጠየቅ ትክክል አይደለም።”—Ibid., vol. 2, pp. 373, 374“የክርስቶስ ሃይማኖት ልብን ሲገዛ ሕሊናችንም ይፈቅዳል፣ ሰላምና ደስታም ይነግሣል። ግራ መጋባትና ችግር ሊከብቡ ይችላሉ፣ ነገር ግን በነፍስ ውስጥ ሁል ጊዜ ብርሃን አለ።”—Ibid., vol. 4, p. 47. 3. የተለመዱ ወጥመዶችን ማምለጥ ማክሰኞ ህዳር 24 ሀ. በስም ብቻ ካለው እምነት በተቃራኒ ከክርስቶስ ጋር ባለው እውነተኛ ግንኙነት ውስጥ የትኛው ቁልፍ መሠረታዊ ሥርዓት አስፈላጊ ነው? ያእቆብ 4፡4። “ክርስቲያናዊ ሕይወታቸውን በግማሽ ተኩል የሚጀምሩት፣ መጀመሪያ ዓላማቸው ምንም ይሁን ምን በመጨረሻ ከጠላት ጎን ተሰልፈው ይገኛሉ። ከሃዲ፣ ከአእግዚአብሔር መንገድ ተቃራኒ መሆን ከሞት የበለጠ ከባድ ነው። የዘላለም ሕይወት ማጣት ማለት ነውና።“ሁለት አስተሳሰብ ያላቸው ወንዶችና ሴቶች የሰይጣን ምርጥ አጋሮች ናቸው። ለራሳቸው ምንም ዓይነት ጥሩ አስተያየት ቢኖራቸውም፣ ተቃዋሚዎች ናቸው፡፡ ለእግዚአብሔርና ለእውነት ታማኝ የሆኑ ሁሉ ለጽድቅ መቆም አለባቸው ምክንያቱም ትክክል ነውና። ካልተቀደሱ ጋር መቀላቀልና ለእውነት ታማኝ መሆን፣ በቀላሉ የማይቻል ነገር ነው። ራሳቸዉን ከሚያገለግሉት፣ ዓለማዊ እቅዶችን ከሚተገብሩት ጋር አንድነትን በመፍጠር፣ ከሰማያዊው መካሪ ጋር ያለንን ኅብረት ማጣት የለብንም። ከጠላት ወጥመድ እናመልጥ ይሆናል፣ ነገር ግን ተጎድተናል፣ ቆስለናል፣ እንዲሁም ልምዳችን ድንክዬ ወይም የደከመ ይሆናል።”—The Review and Herald, April 19, 1898. ለ. እያንዳንዱን የቅናት ዝንባሌ አጥብቀን ነቅለን ማስወገድ ያለብን ለምንድን ነው? ያእቆብ 4:5፣ 6 “በሳኦል ባህሪይ ውስጥ አንድ ትልቅ ጉድለት የመወደድ ወይም ጭብጨባ የመፈለግ ፍቅሩ ነው። ይህ ባህሪ በድርጊቶቹና በአስተሳሰቦቹ ላይ ሥልጣን ነበረው፤ ሁሉም ነገር ለመወደስና ራስን ከፍ ከፍ ለማድረግ ባለው ፍላጎት ያደርግ ነበር። ትክክል ወይም ስህተት የሚለውን ነገር የሚለካው በህዝብ ጭብጨባ መሠረት ነበር። ሰውን ደስ ያሰኘ ዘንድ በሕይወት የሚኖር ማንም ሰው አይድንም፤ አስቀድሞ የአምላክን ሞገስ ለማግኘት አልፈለገምና።”—Patriarchs and Prophets, p. 650“ሳኦልን ያዳከመዉ እና ዙፋኑን አደጋ ላይ የጣለው ምቀኝነቱ ነው። ይህ ክፉ ባህሪይ በዓለማችን ላይ ምን ያህል ያልተነገረ ጥፋት ሰርቷል! የቃየንን ልብ በወንድሙ በአቤል ላይ የቀሰቀሰው ዐይነት በሳኦል ልብ ውስጥም ተመሳሳይ ጠላትነት ነበረ፣ ምክንያቱም የአቤል ሥራዉ ጻድቅ ነበር፣ እግዚአብሔርም አክብሮታል፣ ቃየን የገዛ ሥራው ክፉ ነበር፣ እግዚአብሔርም ሊባርከው አልቻለም። ምቀኝነት የኩራት ዘር ነው፤ በልብ ውስጥ ከተንከባከቡት ደግሞ ወደ ጥላቻ፣ በመጨረሻም ወደ በቀልና ወደ መገዳደል ይመራል።”—Ibid., p. 651“ለእግዚአብሔር መገዛት፣ ፍቅርና ምስጋና፣ ቀኑ ምንም ያህል በጣም ደመናማ ቢሆንም በልብ ውስጥ ብርሃንን ያፈነጥቃሉ። ራስን መካድና የክርስቶስ መስቀል በፊትህ ናቸውና። መስቀሉንስ ታነሳለህን?”—Testimonies for the Church, vol. 4, p. 47. 4. ትኩረት እና መገዛት ረቡዕ ህዳር 25 ሀ. በክርስቶስ እውነተኛና ዘላቂ የሆነ ድል እንድናገኝ የሚረዳን የትኛው አስፈላጊ ነገር ነው? ያእቆብ 4፡7 “አንዳንዶች የኃጢያት ክፍያ እንደሚያስፈልጋቸው ይሰማቸዋል፣ ይህን ፍላጎት ሲያስተዉሉና የልብ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ሲያዉቁ፣ ትግሉ ይጀምራል። የራሳቸውን ፈቃድ ለመካድ ጥረትን ይጠይቃል፣ እዚህጋ ሲደርሱ ብዙዎች ያመነቱና ይወድቃሉ ወይም ወደ ኋላ ይመለሳሉ፡፡ ሆኖም ይህ ጦርነት በእውነት በተለወጠ ልብ ሁሉ ዉስጥ መኖር አለበት። ከውጪም ከውስጥም ፈተናዎችን መዋጋት አለብን። በራሳችን ላይ ድልን ማግኘት አለብን፣ ሰበአዊ መሻቶችንና ምኞቶችን መስቀል አለብን፤ በዚያን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር የነፍስ አንድነት ይጀምራል፡፡ የጠወለገውና ህይወት የሌለው የሚመስለው ቅርንጫፍ በህያው ዛፍ ግንድ ላይ ተሰክቶ ሕይወትን እንደሚያገኝ ሁሉ፤ እኛም የእውነተኛው ወይን ህያው ቅርንጫፎች እንሆናለን። ክርስቶስ ያፈራው ፍሬም በሁሉም ተከታዮቹ ይፈራል። ይህ አንድነት ከተመሰረተ በኋላ ሊጠበቅ የሚችለው ቀጣይነት ባለው፣ በትጋትና በቅን ጥረት ብቻ ነው። ክርስቶስ ይህን የተቀደሰ ትስስር ለማቆየትና ለመጠበቅ ኃይሉን ይጠቀማል፤ ረዳተ አልባና አቅመ ቢስ የሆነዉ ኃጢአተኛ በትጋት የድርሻውን መወጣት አለበት፣ አለዚያ ሰይጣን በጨካኙና ተንኮለኛ ኃይሉ ከክርስቶስ ይለየዋል።“እያንዳንዱ ክርስቲያን ሰይጣን የሚደርስበትን የነፍስን መንገድ ለመጠበቅ ያለማቋረጥ ነቅቶ መቆም አለበት። ለመለኮታዊ እርዳታ መጸለይ እና በተመሳሳይ ጊዜ ማንኛውንም የኃጢአት ዝንባሌ በቆራጥነት መቃወም አለበት። በድፍረት፣ በእምነት፣ በጽናት በመታገል ማሸነፍ ይችላል። ነገር ግን ድልን ለማግኘት ክርስቶስ በእርሱና እርሱም በክርስቶስ መኖር እንዳለበት አስታውስ።”— Testimonies for the Church, vol. 5, p. 47. ለ. ጳውሎስ በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ መንፈሳዊ ጥንካሬን በተመለከተ ያዕቆብ የሰጠውን ማብራሪያ የሚያስተጋባው እንዴት ነው? ሮሜ 6፡6-11 “ዓለማዊ አስተሳሰብ፣ ራስ ወዳድነትና መጎምጀት የአምላክን ሕዝቦች መንፈሳዊነትና ሕይወት እየበሉ ናቸዉ።”—Ibid., vol. 1, p. 141.“በጣም የጠነከረ እምነትና የበለጠ ቅን አምልኮ ያስፈልገናል። እናም በአእምሯችንና በልባችን ለአዳኛችን ያለውን ፍቅር ለመንከባከብ፣ ለራሳችን መሞት (ራስ ወዳድነትን መግደል) አለብን። ጌታን በሙሉ ልብ ስንፈልግ እሱን እናገኘዋለን፣ እንዲሁም ልባችን በፍቅሩ ይቃጠላል። እራስ ወደ ኢምንትነት ይወርዳል፣ የሱስ በነፍሳችን ሁሉ በሁሉ ይሆናል። . . .“ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለብን። ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ መሆን አለብን፣ ካልሆነ ግን በምናደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ ድክመትና ስህተቶች ይታያሉ።”—Ibid., vol. 6, p. 51. 5. ለሶበር ጸሎት ቆም ማለት ሐሙስ ህዳር 26 ሀ. ከክፉ ዝንባሌዎቻችን ጋር በምናደርገው ውጊያ ለእያንዳንዳችን የሚያስተጋባ ምን ማረጋገጫና ተማጽኖ አለን? ቆላስይስ 3:1-3፤ ያእቆብ 4:8፣ 9 “የዓለም ፍቅር ያለበት ማንም ሰው እውነትን ሊያውቅ አይችልም። ዓለም በእነርሱና በእግዚአብሔር መካከል ይገባል፣ እይታቸዉ እየደበዘዘና ቅዱሳን ነገሮችን ለመለየት እስከማይችሉ ድረስ ስሜቶቹ እያደነዘዘ ይሄዳል። እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሯል፡- “እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ። ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አንጹ። ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።” በአለም ብክለት እጆቻቸውን ያረከሱ ሰዎች እራሳቸውን ከቆሻሻው ማጽዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ዓለምን እያገለግሉ እግዚአብሔርን እንወዳለን የሚሉ ሁሉ ሁለት አሳብ ያላቸው ናቸው። ነገር ግን እግዚአብሔርንና ገንዘብን (mammon) ማገልገል አይችሉም። ዓለምን የሚወዱ ከዚህም የተነሳ ለእግዚአብሔር ያላቸውን ግዴታ የዘነጉ፣ ነገር ግን የክርስቶስ ተከታዮች እንደሆኑ የሚናገሩ ሁሉ ሁለት ሀሳብ ያላቸው ሰዎች ናቸው። የሁለቱም አይደሉምና። ንጹሕ የእውነት መሠረታዊ ሥርዓቶችን በመታዘዝ እጃቸውን ካላጸዱና ልባቸውን ካላጸዱ በስተቀር ሁለቱንም ዓለም ያጣሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 1, pp. 530, 531. ለ. በትሕትና በእግዚአብሔር ፊት ስንሰግድ ምን ይሆናል? መዝሙረ ዳዊት 34:18፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5:6፣ 7 “አሁን ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ካዋረድክ፣ በደልህን ከተናዘዝክና በሙሉ ልብህ ወደ እሱ ከተመለስክ፣ የደስተኛ (የእግዚአብሔር) ቤተሰብ አካል መሆን ትችላለህ። ይህን ካላደረግክ ግን የራስህ መንገድ ከመረጥክ በደስታህ ፍጻሜ (መጨረሻ) ላይ ነህ።”—Ibid., vol. 2, p. 304. የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ህዳር 27 1. ውስጣዊ ስሜቴን በጥልቀት ሲመረምር፣ በየትኞቹ አካባቢዎች ነዉ ግብዝ ሊሆን የምችለዉ? 2. ቃሎቻችን ብዙ ጊዜ ክርስቶስን በተሳሳተ መንገድ የሚገልጹባቸውን አንዳንድ መንገዶች ጥቀስ። 3. ምቀኝነት እምነትን መካድና አምላክን መሳደብ ነዉ የሚባለው ከምን አንጻር ነው? 4. በክርስቶስ ሕያው ለመሆን ለራሴ መሞት ለምን አስፈለገኝ? 5. ይህ ትምህርት ማሸነፍ ያለብኝ አንዳንድ እውነተኛ ጉዳዮችን እንዴት ያጠቃልላል? << >>