Back to top

Sabbath Bible Lessons

ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ

 <<    >> 
ሰንበት ታህሳስ 12/ 2017 12ኛ ትምህርት
በሰማይ ላይ ማተኮር የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “እናንተ ደግሞ ታገሡ፤ ልባችሁን አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና” (ያዕቆብ 5፡-8)።
ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Early Writings, p 72,73 
“ዘወትር ያለማቋረጥ በክርስቶስ ጽድቅ መጎናፀፍ ይኖርባችኋል፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችሁና ሩህሩህ፣ ደግና ትዕግስተኛ መንፈስ መያዝ (ማካበት) እንዳለባችሁ በልቦናችሁ መያዝ ያስፈልጋችኋል፡፡ ራስ ወዳድነትና ስግብግብነት በነፍሳችሁ ላይ ጨርሶ ማደር እንደማይገባው ይወታችሁን በጥልቀት መርምሩ፡፡”— Manuscript Release, Volume 13, p 288

1. ጊዜው እንደገና ህይወትን በጥልቀት የመመርመር ነው እሁድ ታህሳስ 06
ሀ. ከጥንት ጀምሮ እጅግ በጣም የላቀ ዋጋ ከተሰጣቸው አልፎም እንደጣኦት በተቆጠሩ ዕቃዎች ላይ በቅርቡ ምን ይፈጠራል—ይህስ ምን ያስታውሰናል (ያስገነዝበናል ? ኢሳ 31፡-6፣7 “የክፋት ሁሉ ሥር የሆነው በማይሆን (በተሳሳተ) አጠቃቀም ላይ የዋለው የገንዘብ ፍቅር ነው፡፡ በምስጋና ተቀብለን ለሰጪውም በአመስጋኝነት መልሰን መስጠት ያለብን የጌታ ንብረት አድርገን ከቆጠርነው ሀብት በረከት መሆኑ በተግባር ያረጋግጣል፡፡ ነገር ግን ይህ ሀብት እጅግ ወድ (ቅንጡ) ቤቶችን ለመገንባት ወይም ለባንክ አክሲዮን (ሽርክና) ግዥ ቢከማች ምን ዋጋ ይኖረዋል ? የወሰን የለሹ ልጅ ከሞተለት (ከሞተላት) አንድ ነፍስ መዳን ጋር ሲመዛዘን ይህ የተከማቸ ገንዘብ ምን ያህል ሊተመን ነው ?”—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 453.“እነዚያ ሰበብ ማብዛትን የሚመርጡ፣ ከኃጢአታቸው እና ከዓለም ጋር በመስማማት የሚቀጥሉ ለጣኦቶቻቸው ተላልፈው ይተዋሉ፡፡ . . . ክርስቶስ በራሱ ክብርና በአባቱም ክብር ከሰማይ ሲወርድ፣ የሰማይ ሰራዊት በሙሉ በድል ነሽነት ዜማ እያጀቡት ሲወርዱ፣ ተወዳዳሪ የሌለው የሙዚቃ ድምጽ ለጀሮ ሲሰማ በዚያኔ ሁሉም ፍላጎት ይኖረዋል፡፡ በዚያኔ አንድ ግድየለሽ ተመልካች እንኳ አይኖርም፡፡ በዚያኔ መላምት (ጭፍን ሃሳብ) ነፍስን የሚቆጣጠር አይሆንም፡፡ የአይን አዋጅ ሆኖበት የነበረው የወርቅ ክምር ለንፉጉ (ለስግብግቡ) ሰው ከዚያ በኋላ ሊያጓጓው አይችልም፡፡ የምድር ኩሩ ሰዎች የገነቧቸው ጣዖቶቻቸው ሆነው የኖሩት ቤተ-መንግስታት በጥልቻና በአስቀያሚነት ችላ ይባላሉ፡፡ ”—Ibid., vol. 2, p. 41.

2. ጊዜው ከመርፈዱ በፊት ሰኞ ታህሳስ 07
ሀ. ዛሬ ነገ በማለት ንብረት ያላቸው ሰዎች በገንዘባቸው እግዚአብሔርን ማስከበር የሚችሉበትን እድል እንደሚያጡ እንዴት ነው መጽሐፍ ቅዱሳት በጥልቀት የገለፁት ? ሆሴዕ 4:17ማቴዎስ 25:11፣ 12. ለ. የወቅቱን እውነት እናምናለን የሚሉትን ጨምሮ በራስ ወዳድነት ከምድራዊ ቁስ ሃብታቸው ጋር የተጣበቁትን ሁሉ በመጨረሻ የሚገጥማቸውን ውጤት ይግለፁ፡፡ ያዕቆብ 5:3. “[ያዕቆብ 5:1–3 የተጠቀሰ]፡፡ እነዚህ አስፈሪ ቃላት በተለይም የወቅቱን እውነት የሚያምኑ ሀብታሞችን እንደሚመለከቱ ተመልክቻለሁ፡፡ በንብረታቸው (በገንዘባቸው) የእርሱን ዓላማ ወደፊት እንዲገሰግስ ለማድረግ ጌታ ጥሪ ያቀርብላቸዋል፡፡ አጋጣሚው ቀርቦላቸው ነበር ፤ ነገር ግን በዓላማው ላይ ዓይናቸውን ጨፈኑ ፤ ከምድራዊ ኃብታቸው ጋር በፍጥነት ተጣበቁ፡፡ ለዓለም ያላቸው ፍቅር፣ ለእውነት ካላቸው ፍቅር ወይም ለባልንጀሮቻቸው ካላቸው ፍቅር ወይም ደግሞ ለእግዚአብሔር ካላቸው ፍቅር ይበልጣል፡፡ ንብረታቸውን (ገንዘባቸውን) እንዲለግሱ የጥሪ ግብዣ አደረገላቸው ፤ ሆኖም ግን በራስ ወዳድነትና በስግብግብነት ያላቸውን ሁሉ አንለቅም አሉ፡፡ የህሊና ወቀሳቸውን ፀጥ ለማድረግ አለፍ ቀደም እያሉ ትንሽ ትንሽ ጠብ ያደርጋሉ ፤ ነገር ግን ለዚህ ዓለም ያላቸውን ፍቅር ማሸነፍ አልቻሉም፡፡ ስለ እግዚአብሔር ብለው መስዋዕት አይከፍሉም፡፡ ለዘላለማዊ ሕይወት ከፍ ያለ ዋጋ የሚሰጡ፣ ነፍስ ሊኖራት ስለሚችለው ዋጋ ሃሳብና ግንዛቤ ያላቸውን፣ የእግዚአብሔርን ዓላማ ወደፊት እንዲገሰግስ ለማድረግ ገንዘባቸውን በሙሉ ፈቃዳቸው ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑትን ሌሎችን በምትካቸው ጌታ አስነሳ፡፡ ሥራው በፍጥነት እየተዘጋ ነው ፤ በመሆኑም በቅርቡ ገንዘባቸውን፣ ግዙፍ የእርሻ ማሳቸውን፣ ከብቶቻቸውን እና ሌላም ንብረታቸውን ሁሉ ሙጭጭ አድርገው የያዙ ሰዎች ገንዘብ ጨርሶ የማይፈለግ ይሆናል፡፡ ጌታም ወደ እነዚህ ንፉጋን ፊቱን በቁጣ በማዞር፡- ‘‘እናንተ ባለጠጎች ዘወር በሉ (ከፊቴ ጥፉ)’’ ሲላቸው ተመለከትኩ፡፡ እርሱ ጠርቶአችኋል ፤ ነገር ግን ማዳመጥ አልፈለጋችሁም፡፡ ለዚህ ዓለም ያላችሁ ፍቅር ድምፁን አፍኖ አስቀርቶባችኋል፡፡ ስለዚህ አሁን አትጠቅሙትም (ከእናንተ የሚሻው ነገር የለም)፡፡ ስለዚህ ገለል በሉ እንዲህ ሲል ያዛችኋል፡- ‘እናንተ ባለፀጎች ከፊቴ ጥፉ’፡፡“ኦህ፣ በዚህ ሁኔታ በጌታ መተፋት በጣም አስፈሪ መሆኑን አይቻለሁ፡፡—ንብረታችንን ሽጠን ስጦታ ብንሰጥ ኖሮ፣ በሰማይ መዝገብ ማከማቸት እንደምንችል እርሱ ነግሮን እያለ፣ ነገር ግን አላፊ ጠፊውን ምድራዊ ቁስ አለቅም ብሎ መያዝ በጣም አስፈሪ ነገር ነው፡፡ ሥራው እያበቃ ሲሄድ፣ እውነትም በታላቅ ኃይል ወደፊት እየተፋጠነ ሲሄድ፣ እነዚህ ሀብታሞች ገንዘባቸውን ወደ ጌታ አገልጋዮች እግር ስር በማስቀመጥ ይቀበሏቸው ዘንድ ሲማፀኗቸው አየሁ፡፡ የጌታ አገልጋዮች መልስ እንዲህ የሚል ነው፡- ‘ሂዱ እናንተ ባለፀገጎች፡፡ ገንዘባችሁ በቃ አይፈለግም፡፡ የእግዚአብሔርን ዓላማ ለማስፋፋት በገንዘባችሁ መልካም ነገር ማድረግ ስትችሉ ይዛችሁ አስቀራችሁት፡፡ ድሆች በጣም ተሰቃዩ፡፡ በገንዘባችሁ ሊባረኩ አልቻሉም፡፡ አሁን እግዚአብሔር ገንዘባችሁን አይቀበላችሁም፡፡ ስለዚህ ሂዱ እናንተ ባለፀጎች ዘወር በሉ’ ”—Testimonies for the Church, vol. 1, pp. 174, 175.

3. ወርቃማውን ሕግ (መመሪያ) መማር ማክሰኞ ታህሳስ 08
ሀ. ሀብታሞች (በሀብት የበለፀጉ ሰዎች) የቀጠሯቸውን ወይም ከእነርሱ የሚገዟቸውን ሰዎች ብዙ ጊዜ እንዴት ነው የሚመለከቷቸው—እኛስ ሁልጊዜ በልባችን መያዝ ያለብን ነገር ምንድን ነው ? ያዕቆብ 5፡-4–6 ፤ ማቴዎስ 7፡-12. “ በተከማቸው ሀብት ሁሉ እግዚአብሔር አለበት ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ሰይጣን ከእግዚአብሔር ይልቅ ገንዘብ በማከማቸት ብዙ ነገር ያደርጋል፡፡ ከተከማቸው ሀብት መካከል አብዛኛው ሊገኝ የቻለው የሰራተኞችን ደመወዝ በመጨቆን ነው፡፡ በተፈጥሮው ስግብግብ የሆነው ሀብታሙ ሰው የሰራተኛውን ዋጋ እንዳይነሳ አድርጎ በማድቀቅ እንዲሁም አጋጣሚውን ተጠቅሞ ግለሰቦችን በልጦ የበላይነቱን በመውሰድ በእሳት እንደሚበላ እንዲሁ ስጋውን የሚበላውን ሀብት ያከማቻል፡፡“ በአንዳንዶች ዘንድ ጥብቅ ሐቀኝነትና የተከበረ መንገድ እየተተገበረ አይደለም፡፡ እንደነዚህ ያሉት ከዚህ የተለየውን መንገድ መከተልና ጊዜውን ለመዋጀት በፍጥነት ሊሰሩ ይገባል፡፡ ብዙዎቹ ሰንበት ጠባቂዎች እዚህ ላይ ይስታሉ፡፡ በድሀ ወንድሞቻቸው ላይ እንኳ ያገኙትን አጋጣሚ ይጠቀሙባቸዋል ፤ እነዚህ ወንድሞቻቸው ገንዘብ በማጣት በሀፍረት ተሳቀው፣ በእጦትም ተጨንቀው ሳሉ፣ እነርሱ ግን አንድ እቃ (ንብረት) ሊያወጣ ከሚችለው ትክክለኛ ዋጋው የበለጠ ይጭኑባቸዋል፡፡ እነርሱ ለመክፈል ከሚችሉት የበለጠ ይጠይቋቸዋል፡፡ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ሁሉ ያውቃቸዋል፡፡ እያንዳንዱ የራስ ወዳድነት ተግባር፣ እያንዳንዱ በስግብግብነት ዋጋ አንሮ የማስከፈል ተግባር የዘራውን የራሱን ዋጋ ያጭዳል፡፡“ አንድ ወንድም ያለበትን የችግር ሁኔታ አለማሰብ ጭካኔና መጥፎ ተግባር መሆኑን ተመልክቻለሁ፡፡ በጭንቀት ከተወጠረ፣ ድኃም ከሆነ፣ ሆኖም የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ከሆነ፣ የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል ፤ እንዲያውም ከሀብታሞች የሚገዛቸው እቃዎች ላይ ሙሉ ዋጋ ሊተመንበት አይገባም ፤ ነገር ግን ለእርሱ ልባቸው በርህራሄ ሊሞላ (አንጀታቸው ሊንሰፈሰፍለት) ይገባል፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ አይነቱን የደግነት ተግባር እውቅና ይሰጠዋል ፤ አድራጊውም የተዘጋጀለትን ሽልማት አያጣም፡፡ ዳሩ ግን በብዙዎቹ ሰንበት ጠባቂዎች ላይ ጥብቅና የስስታምነት ድርጊታቸው ላይ በጣም አስፈሪ መዝገብ (ሂሳብ) ለምስክር ይቆምባቸዋል፡፡”—Testimonies for the Church, vol. 1, pp. 175, 176 ለ. በጥንት ጊዜያት አማኞች ያላቸውን ገንዘብ እንዴት ነበር በነጻ ይካፈሉ የነበሩት? 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡-1፣ 2 “ እውነትን ከልባቸው በማዳመጥ የተቀበሉ በጣም ጥቂት ምእመናን ወደነበሩበት ጊዜ ተጠቁሜ ነበር፡፡ እነርሱ የዚህ ዓለም ንብረት ያን ያህል አልነበራቸውም፡፡ ዓላማው (ወንጌሉ) የሚያስፈልገው ነገር በጥቂቶች መካከል ተከፋፍሎ ነበር፡፡ በዚህም ሀብታቸው በነፃነት በልግስና ለጌታ ለመስጠት፣ እውነትንም ለማሳተም፣ ካልሆነም በሌላ መንገድ የጌታን ዓላማ እንዲስፋፋ ለማድረግ ቤቶቻቸውንና መሬቶቻቸውን መሸጥና እንደ መጠለያ ሊገለገሉበት የሚችሉትን ረከስ ያለ ዋጋ ያላቸውን ቤቶች መግዛት ለአንዳንዶች አስፈላጊ ሆኖ ነበር፡፡ ራሳቸውን የሰውትን እነዚህን አማኞች ስመለከት፣ ለዓላማው ጥቅም (መስፋፋት) ሲሉ ማጣትንና ችግርን ችለው ማለፋቸውን ተመልክቻለሁ፡፡ መልዓክ በጎናቸው ቆሞ፣ ወደላይ ወደሰማይ በማመላከት ፡- ‘እናንተ በሰማይ ግምጃቤት (ቦርሳ) አላችሁ ! ሊያረጅ የማይችል የገንዘብ ካዝና (ቦርሳ) በሰማይ አላችሁ ! እስከመጨረሻ ፀንታችሁ ቆሙ፣ ሽልማታችሁም ታላቅ ይሆናል፡፡’ ”—Ibid., p. 176

5. ለዛሬ አስፈላጊ የሆነው መልካም ባህርይ ረቡዕ ታህሳስ 09
ሀ. ባህርያችንን ለማዳበር ትዕግስት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምድን ነው ? ያዕቆብ 5:7. “ ‘ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እየታገዘ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል’ [ያዕቆብ 5፡-7]፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር በሕይወቱ ለፍሬ እንዲደርስ ክርስቲያን መታገስና መጽናት አለበት፡፡ በተደጋጋሚ ሲሆን እንደሚታየው የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ ለመቀበል ስንፀልይ እግዚአብሔር ደግሞ እነዚህን ፍሬዎች ለማፍራት በምንችልበት ሁኔታ ውስጥ እኛን በማስገባት ለፀሎታችን ምላሽ በመስጠት ይሰራል፡፡ እኛ ግን የእርሱን ዓላማና ሃሳብ ስለማናስተውል ግራ በመጋባት ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ ነገር ግን ማንም ቢሆን በማደግና ፍሬ በማፍራት ውስጥ ካላለፈ በስተቀር እነዚህን የፀጋ (ስጦታዎች) ማዳበር አይችልም፡፡ ስለዚህ የእኛ ድርሻ እግዚአብሔርን ቃል መቀበልና በእርሱም መጽናት ነው ፤ ሕወይታችንን እንዲቆጣጠር ስንፈቅድለት የቃሉ ዓላማ በእኛ ውስጥ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡“ ‘የሚወደኝ ቢኖር’ አለ ክርስቶስ ሲናገር ‘ቃሌን ይጠብቃል ፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን’ ዮሐንስ 14:23፡፡ ኃይልን በሚሰጠን ሁሉን ቻይ ከሆነው ጋር ህያው ግንኙነት ሲኖረን ፍፁም፣ የበረታና የላቀ አሳብ (አዕምሮ) የእኛ ስብዕና ይሆናል፡፡ በመለኮት ሕይወት ስንሆን ለየሱስ ክርስቶስ እንማረካለን፡፡ በመሆኑም ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ከዚህ በፊት የኖርነውን ተራና የራስወዳድነት ኑሮ አንኖረውም፡፡ የእርሱ ባህርይ በእኛ ተፈጥሮ ውስጥ እንደገና ይፈጠራል (ይወለዳል)፡፡ ይህ ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ እናፈራለን —‘አንዱ መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ’ ይሆናል፡፡”—Christ’s Object Lessons, p. 61 (አማርኛው ገጽ 29) ለ. በምኖርባት በዚች ፕላኔት በክፉው መባባስ (ማየል) የተነሳ ፍርሃትና ተስፋ መቁረጥ ሲፈትነን ሳለ፣ መታመንና ትግስት በጣም ጠቃሚ የሆነው ለምድን ነው ? ያዕቆብ 5፡- 8 ፤ ሉቃስ 21፡- 19 “ዓለም የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ ደፋር ሆናለች። ከረጅም ትዕግሥቱ የተነሳ ሰዎች የእግዚአብሄርን ሥልጣን ረግጠዋል። ‘እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልም ዘንድ እውቀት አለን? (መዝሙረ ዳዊት 73:11) በማለት የእርሱ ርስት (ቅርስ) በሆኑት ላይ ግፍና ጭካኔን በማሳየት አንዱ አንዱን አበርትተዋል፡፡ ነገር ግን ማለፍ የማይችሉበት መስመር አለ። የተወሰነው ገደብ ላይ የሚደርሱበት ጊዜ ቅርብ ነው። አሁን እንኳን የእግዚአብሔርን ትግስት፣ የጸጋውን ገደብ፣ የምሕረቱን ወሰን ሊያልፉ ምንም አልቀራቸውም። ክብሩን በግልጽ ያሳይ ዘንድ፣ ሕዝቡንም ያድንና የዓመፅንም ጎርፍ ይገታ ዘንድ ጌታ ጣልቃ ይገባል፡፡”—Christ’s Object Lessons, p. 177, 178

5. ሊያበረታን የሚችል ምሳሌ ሐሙስ ታህሳስ 10
ሀ. በቤተክርስቲያን አጠቃላይ አባላት በአብዛኛው የምናተኩረው በምን ላይ ነው—ነገር ግን በዚህ ምትክ ምንድን ነው በልቦናችን መያዝ ያለብን? ዘለዋዊያን 19፡-18 ፤ ያዕቆብ 5፡-9፣ 10. “ከአዳም ልጆች መካከል የመጀመሪያ ክርስቲያን የነበረው አቤል የሰማዕትነት ሞት ሞተ፡፡ ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር ተራመደ ፤ ዓለም ግን አላወቀውም፡፡ ኖህ እንደ አክራሪና አስደንጋጭ ተቆጥሮ መሳቂያ መሳለቂያ ሆነ፡፡ ‘ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በውኅኒ ተፈተኑ’ ፤ ‘ሌሎችም ነፃ ሳይወጡ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ’ [ዕብራዊያን 11፡- 36፣35]፡፡ በእያንዳንዱ ዘመን የተመረጡ የእግዚአብሔር መልዕክተኞች መዘባበቻ ሆነዋል፣ ተሳደዋል፣ ተጨፍጭፈዋልም ፤ ሆኖም በስቃያቸውና በመከራቸው የእግዚአብሔር እውቀት ወደ ውጭ ሀገራት ተዳርሷል፡፡ የእርሱ ጠላቶች ስለ እውነት እንጂ በእውነት ላይ አንዳች ነገር ማድረግ እንደማይችሉ በማወቅ እያንዳንዱ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ወደ ሰራዊቱ ተመልምሎ (ምልምል ወታደር ሆኖ) መግባት እና ተመሳሳዩን ሥራ ወደ ፊት ማስፋፋት ይኖርበታል፡፡ እውነት ምንም እንኳ ጥላቻ ቢለጠፍበትም፣ በይፋ ወደ አደባባይ (ወደ ሰዎች ፊት ቀርቦ) የምርመራና የውይይት ርዕሰ ጉዳይ እንዲሆን እግዚአብሔር ወስኗል፡፡ የሰዎች አዕምሮ መናወጥና መነሳሳት አለበት ፤ እያንዳንዱ ውዝግብ (ጥል)፣ እያንዳንዱ የስም ማጥፋት ነቀፋ ፣ የህሊና ነፃነትን ለመገደብ የሚደረግ እያንዳንዱ ጥረት ሁሉ፣ በሌላ በምንም መንገድ ሳይነቃ ተኝቶ ይቀር የነበረውን አዕምሮ የሚያነቃበት የእግዚአብሔር መሳሪያዎች ናቸው፡፡“ይህ ውጤት በእግዚአብሔር መልዕክተኞች ታሪክ ውስጥ መታየት የቻለው ምን ያህል ነው ! እጅግ የከበረውና በአንደበተ ርቱዕነት የታወቀው እስጢፋኖስ በአይሁድ መማክርት ሸንጎ አነሳሽነት በድንጋይ ተወግሮ በሞተ ጊዜ በወንጌሉ ዓላማ ላይ አንዳች ኪሳራ አልደረሰም፡፡ ፊቱን በክብር የሞላው የሰማይ ብርሐን፣ በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሲፀልይ የተነፈሰው መለኮታዊ ርህራሔ፣ በጎን ቆሞ ለነበረው አክራሪና አሳዳጅ ፈሪሳዊ ለነበረው ለሳዑል በስቶ እንደሚወጋ ስለታም ቀስት ነበረ ፤ አሳዳጁ ፈሪሳዊ የክርስቶስን ስም በአህዛብ፣ በነገሥታት እንዲሁም በእስራኤል ልጆች ፊት ለመሸከም የተመረጠ እቃ ሆነ፡፡”—Thoughts From the Mount of Blessing, pp. 33, 34.

የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ታህሳስ 11
1. የራሴ ገንዘብ ስላለው ዋጋ ምንድን ነው መገንዘብ ያለብኝ ? 2. በያዕቆብ 5፡-1 ላይ ክርስቶስ ያቀረበው መፈተኛ ማለት ምን ማለት ነው? 3. በገንዘብ የሚከናወን ግዥና ሽያጭን በተመለከተ በምን ደካማ ጎን ነው ጥፋተኛ ልሆን የምችለው? 4. በመጨረሻ ትግስት መልካም ባህርይ ሆኖ በጌታ ሕዝቦች መካከል ማብራት የሚችለው እንዴት ነው ? 5. በታሪክ ዘመናት ሁሉ ክርስቲያን ሰማዕታት በትኩረታቸው ላይ ማነጣጠር የቻሉት እንዴት ነው ?
 <<    >>