ጥናቶች ከያዕቆብ መልእክት ውስጥ << >> የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ በረድንግ፣ ፔንስልቬንያ፣ ዩኤስኤ ውስጥ ለሚገኝ የጸሎት ቤት መሥሪያ ይዉላል ሰንበት፣ መስከረም 25፣ 2017 የምስራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ፊልድ (EUSF) ከፔንስልቬንያ፣ ኒው ዮርክ፣ ኮነክቲከት፣ ሮድ አይላንድ፣ ማሳቹሴትስ፣ ሜይን፣ ቨርሞንት፣ ኒው ሃምፕሻየር ግዛቶችን ያቀፈ በስምንት መልክዓ ምድራዊ አካባቢዎች የተከፋፈለ ነው። በፔንስልቬንያ ያለው ሥራ በአሁኑ ጊዜ ፈጣን እድገት እያሳየ ነው። በዚህ ግዛት ውስጥ ከ 53% በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሃይማኖተኛ እንደሆኑ ይገመታል - ሜቶዲስቶች ፣ ሉተራኖች ፣ ባፕቲስቶች፣ ጴንጤቆስጤዎች እና ሌሎችም ያቀፈ ሲሆን 28.3% ካቶሊኮች። በቅኝ ግዛት ዘመን መጀመሪያ ፔንስልቬንያ በአውሮፓ ከሚደርስባቸው ስደት ለማምለጥ የሃይማኖት ነፃነት ለሚፈልጉ ምዕመናን መሸሸጊያ ቦታ ነበረች። ይህ ታሪክ አሁንም በላንካስተር አውራጃ ውስጥ በሚገኙ ትላልቅ የአርሶ አደር ማህበረሰቦች ውስጥ ጨዋ የሆነ አለባበስ ለብሰው፣ በፈረስና በቡጊ ጋሪ እየተጓዙ በሚኖሩ በርካታ ባህላዊ የአሚሽ አማኞች ምስክር ናቸዉ። ባለፉት አመታት፣ ጥቂት SDARM አባላት በፔንስልቬንያ ኖረዋል እናም እዚህም የሚስዮናዊ ስልጠና ተሰጥቷል። ነገር ግን የወቅቱ እውነት ፍላጎት መነቃቃት የጀመረው በ2016 በረድንግ ከተማ ሁለት አባላት ከኒውዮርክ ሄደዉ መስራት ከጀመሩ በኋላ ነው። ቁጥራቸዉ እየጨመረ በመሄድበ በጋ ወቅት በየሰንበት ቀን ከሰአት በኋላ በአንድ መናፈሻ ውስጥ በመሰብሰብና በክረምት በአንድት እህት ቤት ውስጥ መሰብሰብ ተጀመረ። ከብዙ ወራት ጥናት በኋላ ብዙዎች በተሃድሶ እምነት ተጠመቁ። ረድንግ ከ95,000 በላይ ህዝብ ያለው አከባቢ ሲሆን የኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫዎች፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ የሃይል ማከማቻ ቴክኖሎጂዎችና ሌሎችም ቁሶች የማምረቻ ማዕከል ነው። እዚህ ያለው ቤተክርስቲያናችን አሁን በምስራቅ ዩኤስ መስክ ውስጥ ትልቁ ነዉ። ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ ለመቀላቀል ተጨማሪ አዳዲስ ነፍሳት እየተዘጋጁ ነው። በአሁኑ ጊዜ፣ በተከራየነው ተቋም ውስጥ እናመልካለን እናም መገኘታችንን ማረጋገጥና ለበለጠ አገልግሎት ማስፋት እንፈልጋለን። “የምእመናን ማኅበር ባለበት ቦታ ሁሉ የአምልኮ ቤት መገንባት አለበት። . . . መልእክቱ በተሰበከባቸውና ነፍሳት መልዕክቱን በተቀበሉባቸው ብዙ ቦታዎች፣ በማይመች ሁኔታዎች ውስጥ ናቸው፣ በዚህም ለሥራዉ የሚሆኑ ጥቅሞችን ለማግኘት ምንም ማድረግ አይችሉም። ብዙውን ጊዜ ይህ ሥራውን ወደፊት ለማስኬድ አስቸጋሪ ያደርገዋል።”—Evangelism, p. 376. በአካባቢዉ የአምልኮ ቤት እንድንሰራ፣ ብዙ ነፍሳት ወደ መንጋው እንዲገቡ እንዲረዱን እንጠይቃለን። ስለቸር ልግስናዎ በጣም እናመሰግናለን፣ ጌታ በበረከቱ ይባርካችሁ። ወንድሞቻችሁ ከምስራቃዊ ዩናይትድ ስቴትስ ፊልድ << >>