ከየሱስ ጋር መራመድ << >> ሰንበት፣ ሰኔ 27፣ 2018 1ኛ ትምህርት የእግዚአብሔር ፍቅር ለሰው ልጅ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።” (1ኛ ዮሐንስ 3፡1)። ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ ፡ Steps to Christ, chapter 1፣ pp. 9–15። “እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ልክ ከፀሐይ እንደሚወጣ የብርሃን ጨረሮች፣ ፍቅር፣ ብርሃንና ደስታ ከእርሱ ወደ ፍጥረታቱ ሁሉ ይፈስሳሉ።”—Thoughts from the Mount of Blessing, p. 77። 1. እግዚአብሔር ፍቅር ነው እሁድ ፣ ሰኔ 21 ሀ. እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር የሚያሳየው የተሰጠው ማስረጃ ምንድነው? ዘጸአት 34:-6፣ 7፤ ዮናስ 4:-2 (የመጨረሻው ክፍል)፤ ኤርምያስ 31:-3። “የእግዚአብሔር ቃል አምላካዊውን ባህሪ ይገልጻል፡፡ ወሰን ስለሌለው ፍቅሩና ሀዘኔታው ያወጀው እራሱ ይኸው አምላክ ነው፡፡ ሙሴ “ክብርህን አሳየኝ” ብሎ በጸለየ ጊዜ “መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ” (ዘጸ. 33፡-18-19) በማለት ነበር እግዚአብሔር የመለሰለት። ይህ የእርሱ ክብር ነው፡፡ ጌታ በሙሴ ፊት እያለፈ እንዲህ ሲል ዐወጀ፦ “እግዚአብሔር ርኅሩኅ ቸር አምላክ፣ እግዚአብሔር ለቁጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ፣ ፍቅርን ለሺህዎች የሚጠብቅ፣ ክፋትን ዐመጽንና ኃጢአትን ይቅር የሚል” (ዘጸ. 34፡-6-7)። እርሱ “ቸርና ርኅሩኅ፣ ከቁጣ የራቀ“፤ “ምህረት በማድረግ ደስ” የሚለው ነው (ዮናስ 4፡20፣ ሚክያስ 7፡-18)።”—Steps to Christ, p. 10። ለ. እግዚአብሔር ልጁን የላከበት ዓላማ ምን ነበር? ማቴዎስ 11፡-27፤ ዮሐንስ 14፡-8፣ 9። “እግዚአብሔር አለልክ ጥብቅ ፣ ከባድ ፍርድ የሚሰጥ እንዲሁም ጨካኝ ፈራጅና ርህራሄ ቢስ ዓይነተኛ ባህሪይው እንደሆነ አድርጎ ሰይጣን በአእምሮአቸው ውስጥ በመሳል አሳታቸው፡፡ እግዚአብሔር በሰዎች ላይ ለመፍረድ ሲል በቅናት ዓይን ስህተታቸውን ብቻ የሚፈልግ አምላክ ተደርጎ ተሳለ፡፡ ይህን በጽልመት የተሞላ ጥላ ለመግፈፍ እና ዘላለማዊውን አምላካዊ ፍቅር ለማሳየት ሲል የሱስ ከስዎች ጋር ሊኖር ወደዚህ ምድር መጣ።”—ibid, p 11። 2. የየሱስ ተልዕኮ ሰኞ ፣ ሰኔ 22 ሀ. የሱስ የራሱን ምድራዊ ተልእኮውን እንዴት ገለጸው? ሉቃስ 4:- 16-18። “[ሉቃስ 4:-18] ይህ እንግዲህ [የየሱስ] ሥራ ነበር። እርሱ መልካም እያደረገና በሰይጣን ግዞት ስር ወድቀው የነበሩትን እየፈወሰ በየስፍራው ተንቀሳቀስ። በመኃላቸው እየፈወሰ ያልፍ ስለነበረ፣ የህመምና የማቃሰት ድምፅ የሚሰማበት አንድም መንደር አልተገኘም ነበር፡፡ ሥራዎቹ በመለኮት ለመቀባቱ ማረጋገጫ በመሆን ፍቅር፣ ምህረትና ርኅራኄ በእያንዳንዱ የህይወቱ እንቅስቃሴ ተገልጾ ይታይ ነበር፡፡ ልቡ ለሰዎች ልጆች በፍቅርና በርኅራኄ ይፈስ ነበር፡፡ የሰዎችን ፍላጎት ለመድረስ ይችል ዘንድ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ ወሰደ፡፡ እጅግ ድኾችና ራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ እርሱን ቀርቦ ለማናገር ፍርሃት አልነበራቸውም፡፡ እንዲያውም ትናንሽ ብላቴናዎች ሳይቀሩ በእርሱ ዙሪያ ተስበው ነበር፡፡ ህጻናት እንኳን ሳይቀሩ በጭኖቹ ላይ በመውጣት፣ በፍቅር የተሞላ ቸርና ርኍሩኅ እንዲሁም አስተዋይ የሆነውን የፊቱን ገጽታ ለመመልከት ችለው ነበር፡፡”—Steps to Christ, p. 11፣ 12“የሱስ ለሰው ሁሉ በነፍስ ወከፍ የመንግሥቱ ጥሪ ሊደርሰው እንደሚገባ ተገነዘበ። ለእነርሱ በጐውን ሁሉ በመመኘት በመካከላቸው በመገኘቱ ልባቸውን ነካው። በአውራ መንገዶች ላይ፣ በየግል ቤቶቻቸው፣ በጀልባዎች ላይ፤ በምኩራብ፤ በሐይቅ ዳርቻዎችና በሠርግ ድግሥ ሥፍራ ፈለጋቸው። በየዕለት ተግባራቸው ተገናኛቸው፤ ስለ ዓለማዊ ጉዳያቸው ጭምር እንደሚጨነቅላቸው ተገለጸ። የመለኮትን በጐ ተጽዕኖ በየቤቱ እንዲኖር ለማድረግ ትምህርቱን በየቤተሰቡ አዳረሰ። የግል ትልቅ ርኅራኄው ልቦችን ለመሳብ እረዳ። ብዙ ጊዜ ለግል ጸሎት ወደ ተራራ ይሔድ ነበር፣ ይህን የሚያደርገው ግን በሕይወት ሒደት ውስጥ ለሚያካሒደው ሥራ ለመዘጋጀት ነበር። ከጸሎት ተመለሶ ሕሙማንን ፈወሰ፣ መሐይማንን አስተማረ፣ የሰይጣን ምርኮኞችን ሰንሰለት ሰበረ።”—The Desire of Ages, p. 151። ለ. በፍቅርና በርኅራኄ የተሞላ ቢሆንም፣ ክርስቶስ በታማኝነት በደልን በመገሠጽ ያሳየው ምሳሌ ምንድን ነው? ዮሐንስ 9:39 - 41፤ ማቴዎስ 21:12፣ 13። “የሱስ የእውነትን ቃል ሁልጊዜ በፍቅር ይናገር ነበር፡፡ እርሱ ከሰዎች ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ትኩረት የሚሰጥ፣ ደግ፣ አሳቢና አስተዋይ ነበር። የሱስ ግትር አልነበረም፣ ለሆደ ባሻው አላስፈላጊ ጠንካራ ቃላትን በመሰንዘር እንዲታወክ አድርጎ አያውቅም፣ ሰብዓዊውን ደካማነትም አልተቸም፡፡ እውነትን በግልጽ ይናገር ነበር! ይህንን ያደርግ የነበረው ግን ሁልጊዜ በፍቅር ነበር። ግብዝነትን፣ አለማመንን እንዲሁም ታማኝ አለመሆንን ቢያወግዝም፣ ግሳጼ ሲያደርግ ሳለ ግን በድምፁ ላይ ሳግ ይሰማ ነበር። . . . እያንዳንዱ ነፍስ በእርሱ ዘንድ የከበረ ነበር፡፡ መለኮታዊውን ክብር ከምንም ሳይቆጥር ነገር ግን ከፍ ባለ ፍቅር እራሱን ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ዝቅ ያደረገው አዳኝ፤ እንዳንዱን ሰው ሊያድነው ዓላማው የሆነውን የወደቀ ነፍስ በመመልከት ነበር፡፡”—Steps to Christ, p. 12 3. ራስን የመካድ ሕይወት ማክሰኞ ፣ ሰኔ 23 ሀ. አዳኛችን በሕይወቱ ዘመን ምን ከባድ ሸክም ተሸክሞ ነበር? ኢሳይያስ 53:5–7 ፤ ሉቃስ 2:48፣ 49። “የሱስ ለሰዎች መዳን የሚያስፈልገውን እጅግ ታላቅ የኃላፊነት ክብደት ተሸክሞ ኖረ። በሰው ልጅ መርሆዎችና ዓላማዎች ላይ ቁርጥ ለውጥ ካልተደረገ በስተቀር ሁሉም እንደሚጠፉ ያውቅ ነበር። ይህ የነፍሱ ሸክም ነበር፣ እና ማንም በእርሱ ላይ የወደቀውን ሸክም ሊያደንቅ አይችልም። በልጅነት፣ በወጣትነትና በጉልምስና ዘመን፣ በብቸኝነት ይመላለስ ነበር። ሆኖም ግን እሱ ባለበት ቦታ መገኘት በሰማይ እንደመገኘት ነበር። በየቀኑ መከራዎችንና ፈተናዎችን ተጋፍጧል፤ በየቀኑ ከክፉ ጋር ይገናኝ ነበር፣ በዚህም ሊባርካቸውና ሊያድናቸው በሚፈልጋቸው በሰው ልጆች ላይ ክፉው ምን ያህል ኃይል እንዳለው አይቷል። ሆኖም ግን አልተሸነፈም ወይም ተስፋ አልቆረጠም።“በሁሉም ነገር ምኞቱን ለተልእኮው በጥብቅ አስገዛ። ሁለንተናውን ለአባቱ ፈቃድ በማስገዛት ሕይወቱን አከበረ። በወጣትነቱ እናቱ በረቢዎች (በኃይማኖት መምህራን) ትምህርት ቤት አግኝታ “ ልጄ፣ ለምን እንዲህ አደረግህብን? “ አለችው ። እርሱም መለሰ - መልሱም የሕይወት ዘመኑ ሥራው ዋና ነገር ነበር - ለምን ትፈልጉኛላችሁ? በአባቴ ቤት መሆን እንዳለብኝ አታውቁምን? ““ሕይወቱ የማያቋርጥ የራስን ጥቅም መሥዋዕት የማድረግ ሕይወት ነበረ። ወዳጆቹ ደግነት እንደ መንገደኛ ሰው የሚያርፍበትን ቦታ ከሚሰጡት በስተቀር በዚህ ዓለም ውስጥ ምንም ቤት አልነበረውም። ለእኛ ሲል የችግረኞችና የድሆችን ሕይወት ለመኖር፣ በመከራ መካከል ለመመላለስና ለመሥራት መጣ። ያለምንም ጭብጨባ፣ ሳይታወቅና ሳይከበር፣ ብዙ ነገር ባደረገላቸው ሰዎች መካከል ተመላልሶ ሄደ።”—Gospel Workers, pp. 42፣ 43። ለ. የእግዚአብሔር የተትረፈረፈ ፍቅር መፍሰስ ስለ ሰማያዊ አባታችን ምን ያስተምረናል? ዮሐንስ 3:16፤ 1ኛ ዮሐንስ 4:9፣ 10። “ይህ ታላቅ መስዋዕትነት የተከፈለበት ምክንያት በአብ ልብ ውስጥ ሰውን የመውደድ ስሜት በመፍጠር እኛን ለማዳን ፈቃደኛ ለማድረግ አልነበረም። በጭራሽ! “እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና“ (ዮሐ. 3:16)። አብ እኛን የወደደበት ምክንያት ቁጣውን ለማብረድ መስዋዕት በመከፈሉ አይደለም። ነገር ግን እርሱ ራሱ ስለሚወደን የሚክፈለውን መስዋዕት አዘጋጀ። ክርስቶስ አማላጅ በመሆን ዘላለማዊ ፍቅሩን በኃጢአት ለወደቀው ዓለም አፈሰሰ “እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር አስታረቀ“ (2ኛ ቆሮ. 5:19)። እግዚአብሔር ከልጁ ጋር ሥቃይ ተቀበለ፡፡ በጌተሰማኔ ህማም እንዲሁም በቀራኒዮ መስቀል ሞት ዘላለማዊው አፍቃሪ ልብ የመዋጀታችንን ዋጋ ከፈለ፡፡” —Steps to Christ, p. 13። 4. የእኛ ምትክ እና ዋስትና ረቡዕ ፣ ሰኔ 24 ሀ. የነፍሳችን መዳን መሠረት ምንድን ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 1:30፤ የሐዋርያት ሥራ 16:31። “ ኦህ፣ ክርስቶስ የጠፋውን የሰውን ልጅ ለማዳን ምንኛ የነፍስ ረሃብና ናፍቆት ነበረው! በመስቀል ላይ በመሞት፣ የግል አዳኙ አድርጎ በእርሱ ለሚያምን ኃጢአተኛ ሁሉ ኃጢአቱን ወደ መለኮታዊ ምትክ ወደራሱ አዛወረ። የበደለኛው ዓለም ኃጢአቶች፣ በቃሉ ላይ ‘እንደ አለላ የቀሉ’ ተብለው የተገለጹት፣ ወድ መለኮታዊ ዋስትና ተሸጋግረዋል። “—This Day With God, p. 236. ለ. መዳናችንን በተመለከተ ክርስቶስ ከሰው ልጅ ጥረት ወይም ጥበብ በላይ የሆነውን ምን አደረገ? ዮሐንስ 10:17፤ ሮሜ 5:6-8 ። “አባቴ ይወዳችኋል፣ እኔ ደግሞ እናንተን ለመዋጀት ህይወቴን አሳልፌ በመስጠቴ አብልጦ ይወደኛል። በእናንተ ምትክ በመሞቴ፤ የደኅንነታችሁ ዋስትና በመሆኔ፣ ህይወቴን በመስጠቴ፤ ዕዳችሁንና መተላለፋችሁን በመውስዴ በእርግጥም እኔ የአባቴ ነኝ። በእኔ መስዋዕትነት እግዚአብሔር ጻድቅ ይሆናል፣ በእርግጥም እርሱ በየሱስ የሚያምነውን ሁሉ ያጸድቃል።““ከእግዚአብሔር ልጅ በቀር ደኅንነት ሊያስገኝልን የሚችል አንዳችም ሌላ የለም። በአባቱ እቅፍ ያለው እርሱ ብቻ ነው እግዚአብሔርን መተረክ የሚችለው። የእግዚአብሔርን ፍቅር ከፍታና ጥልቀት የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው ሊገልጽልን የሚችል፡፡ የአብን ፍቅር በክርስቶስ ከተፈጸመው ዘላለማዊ መስዋዕት ውጪ በኃጢአት ለወደቀውና ለጠፋው ሰብዓዊ ፍጡርሌላ ማንም ሊገልጽ አይችልም።”—Steps to Christ, p. 14። ሐ. ዮሐንስ በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ስለነበረው ጠበቃችን ምን መሰከረ ? 1ኛ ዮሐንስ 1 ፡1–3። “ የኃጢአትን አስከፊ ባህሪ የሚያውቁ እና በእግዚአብሔር ሕግ መተላለፍ ምክንያት የሚመጣውን ውድመት ታላቅነት የሚረዱ ጥቂቶች ብቻ ናቸው። ኃጢአተኛውን ወደ እግዚአብሔር የሞራል ምስል ለመመለስ አስደናቂውን የመቤዠት እቅድ ስንመረምር፣ የሰውን ልጅ ነፃ ለማውጣት ብቸኛው መንገድ የተገኘው በእግዚአብሔር ልጅ ራስን መስዋዕት የማድረግ እና ወደር በሌለው ትሕትና እንዲሁም በእርሱ ታላቅ ፍቅር መሆኑን እናያለን። ከእግዚአብሔር እና ከሰው ልጅ ጠላት ጋር ለመዋጋት ጥንካሬ የነበረው እርሱ ብቻ ነበር፣ በዚህም ምትክ እና ዋስትና በመሆን፣ በእምነት እሱን ለሚጨብጡት፣ በስሙ እና በመልካምነቱ ድል አድራጊዎች እንዲሆኑ ኃይል ሰጣቸው።”—Christian Education, p. 112. 5. የሱስ ዋጋውን ከፈለልን ሐሙስ ፣ ሰኔ 25 ሀ. ክርስቶስ የመቤዠታችንን ዋጋ እንድከፍል ምን ብቁ አደረገው? 1ኛ ጴጥሮስ 1:18፣ 19፤ ዕብራውያን 5:8፣ 9። “የደኅንነታችንን ዋጋ በመክፈል ዘላለማዊው አባት ልጁ ይሞት ዘንድ በመስጠት የከፈለው ዘላለማዊ መስዋዕት: እኛ በክርስቶስ ምን ልንሆን እንደምንችል ከፍ ያለ ግንዛቤ ሊያስጨብጠን ይገባል። በመንፈስ የተነካው ሐዋርያው ዮሐንስ እግዚአብሔር አብ ለጠፋው ዘር ያለውን ፍቅር ከፍታ፣ ጥልቀትና ስፋት ባስተዋለ ጊዜ፣ በታላቅ አምልኮና አክብሮት ተሞልቶ ነበር። የዚህን ፍቅር ታላቅነትና ርኅሩኅነት ያስተዋለው ዮሐንስ፤ ይህን እንዴት እንደሚገልጸው ተስማሚ የሆነ ቋንቋ በማጣት፦ «የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው» (1ኛ ዮሐ. 3:1) በማለት ይናገራል። ይህ ለሰዎች የተሰጠው ዋጋ እንዴት ያለ የከበረ ነው! የሰው ልጆች በመተላለፋቸው ጠንቅ የሰይጣን ተገዢዎች ለመሆን በቁ። በክርስቶስ መስዋዕትነት ላይ በሚኖር እምነት ግን የአዳም ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን ቻሉ። ክርስቶስ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ በመውሰድ በኃጢአት የወደቀውን ሰብዓዊ ፍጡር ከፍ ከፍ አደረገው። ኃጢአተኞችም ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት በመፍጠራቸው ምክንያት በእርግጥ «የእግዚአብሔር ልጆች» ለመባል የሚገባቸው ሆኑ።”—Steps to Christ, p. 15 ለ. ሐዋርያው ዮሐንስ የእግዚአብሔርን ፍቅር ታላቅነት ለመግለጽ ምን ቃላት ተጠቅሟል? 1ኛ ዮሐንስ 3:1፣ 2. “እንዲህ ያለው ፍቅር አቻ የለውም። የስማያዊው ንጉሥ ልጆች! የከበረ ተስፋ! ይህ ሁልጊዜ ልናሰላስለው የሚገባን ተስፋ ነው! እርሱን ላልወደደው ዓለም የተበረከተ አቻ የሌለው ፍቅር! ይህ ሐቅ ነፍሳችንን በሐሴት የመሙላት ኃይል ያለው ሲሆን፤ ደግሞም ራሳችንን ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንድናስገዛ የሚያደርግ ነው። መለኮታዊውን ባህሪ በመስቀሉ ብርሃን ባጠናን ቁጥር፤ ምህረት፣ አፍቃሪነትና ይቅር ባይነት ከፍትሕና ከአድልዎ ነፃ ከመሆን ጋር ሕብረት ሲፈጥሩ እንመለከታለን። እንዲሁም እናት መንገዱን ለሳተው ልጇ ካላት ናፍቆትና ርኅራኄ ጋር ሲነጻጸር እጅግ የላቁትን ሊቆጠሩ የማይችሉትን ዘላለማዊ የፍቅሩን መረጃዎች አብልጠንና ለይተን እናያለን።”—ibid የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ፣ ሰኔ 26 1. ከእግዚአብሔር ባህሪ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ባህሪያት ግለጽ። 2. የሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ባሕርይ የገለጠው እንዴት ነው? 3. የክርስቶስ ተልዕኮ በምርጫዎቹ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው? 4. የሱስ የእኛ ምትክ በመሆኑ ምን ትምህርቶችን ያስተምረናል? 5. በእኛ ምትክ ክርስቶስ የሰጠው ታላቁን ስጦታ ግለጽ። << >>