Back to top

Sabbath Bible Lessons

ከየሱስ ጋር መራመድ

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሐምሌ 18፣ 2018 4ኛ ትምህርት
ኃጢአትን መናዘዝ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል። (ምሳሌ 28፡13)።
ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ ፡   Steps to Christ, chapter 4፣ pp. 37-41. 
“ከልብ የሚደረግ ንስሐ ርኅራኄው ወደ ማያልቅበት አምላክ በቀጥታ ያመራል።”—Steps to Christ, p. 38

1. የእግዚአብሔር ምሕረት እሁድ ፣ ሐምሌ 12
ሀ. በኃጢአታችንን ስናውቅ ምን ማድረግ አለብን? ምሳሌ 28:13ያዕቆብ 5:16 “ከእግዚአብሔር ምህረትን የማግኛው መንገድ ቀላልና ቀና ብቻ ሳይሆን ለማገናዘብም አስቸጋሪ አይደለም። ለኃጢአታችን ይቅርታ እናገኝ ዘንድ ከባድና አሳዛኝ ነገር እንድናደርግ ጌታ አይፈልግብንም። መተላለፋችን እንዲደመስስና ነፍሳችንን ለሰማይ አምላክ አደራ ለመስጠት ረጅምና አድካሚ የምናኔ ጉዞ ማድረግ ወይም ህመም ያለው የንስሐ ቅጣት መቀበል አያሻንም። ነገር ግን ኃጢአቱን የተናዘዘ የተዋትም ምህረትን ያገኛል።”—Steps to Christ, p. 37 ለ. ይህ በእኛ ውስጥ ምን ዓይነት አመለካከት ይጠይቃል? ምሳሌ 15:33፤ 19:23፤ መዝሙር 34:18. “መተላለፋቸውን በማሳወቅ ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት በትህትና ዝቅ አድርገው ያላቀረቡት፣ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት ለማግኘት ገና ይቀራቸዋል። ንስሓ መግባት ስላለብን ነገር፣ ንስሓ መግባት ካልተለማመድን፣ በእውነተኛው መንገድ ነፍሳችንን ካላዋረድንና በተሰበረ መንፈስ ኃጢአታችንን ካልተናዘዝን መተላለፋችን በእውነት ይቅር ይባል ዘንድ አንፈልግም ማለት ነው። እንዲህ ከሆነ ደግሞ የእግዚአብሔርን ሰላም ለማግኘት ፈጽሞ እንችልም። የኃጢአት ይቅርታ ለማግኘት ያልቻልንበት ብቸኛው ምክንያት ልባችንን በትህትና ለእግዚአብሔር ዝቅ ለማድረግ ፈቃደኞች አለመሆናችንና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር መስማማት አለመቻላችን ነው። እርሱ ይህን አስመልከቶ ግልጽ መመሪያ ሰጥቷል። በግልም ሆነ በሕብረት ኃጢአታችንን ስንናዘዝ ሳለ ከልብ በመነጨ እና በነፃነት መንፈስ ልናደርገው ይገባል እንጂ በግፊት መሆን የለበትም።”—ibid, p 37፣ 38

2. መናዘዝ እና ይቅር ማለት ሰኞ ፣ ሐምሌ 13
ሀ. አንድን ሰውን ስናስቀይም ከእሱ በተጨማሪ ደግሞ ሌላ ማንን አስቀይመናል? መዝሙር 51:4 “በዚህ ዙሪያ ሐዋርያው «ስለዚህ ኃጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ» (ያዕ. 5፡16) በማለት ይናገራል። ኃጢአታችሁን ሁሉ ይቅር ሊል ለሚችለው ለእግዚአብሔር ብቻ ተናዘዙ፤ ስህተታችሁንም እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ። ጓደኛችሁን ወይም ጎረቤ ታችሁን ቅር ብታሰኙ ጥፋታችሁን አምናችሁ ተቀበሉ። የበደላችሁትም ሰው በነጻ ይቅር ሊላችሁ ይገባዋል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ይቅር ይላችሁ ዘንድ ለምኑት። ምክንያቱም ያ ያቆሰላችሁት ወንድም የእግዚአብሔር ንብረት በመሆኑ እርሱን በመጉዳታችሁ ፈጣሪ እና አዳኝ የሆነው ጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርታችኋል።”—Steps to Christ, p. 37 ለ. ሌሎችን ይቅር ማለት ያለብን ለምንድን ነው? ማቴዎስ 6:14፣ 15፤ ኤፌሶን 4:32 “ ይቅር የማይል ሰው ከእግዚአብሔር ምሕረት የሚያገኝበትን ብቸኛውን መንገድ ይቆርጣል። የጎዱን ሰዎች ጥፋታችንን እስካልተናዘዙ ድረስ ይቅርታችንን በመከልከል ትክክለኛ ነገር እንዳደረግን ማሰብ የለብንም። ያለምንም ጥርጥር ልባቸውን በንስሐና በኑዛዜ ማዋረድ የእነሱ ድርሻ ነው፤ ነገር ግን በደላቸውን ቢናዘዙም ባይናዘዙም እኛ ለእነሱ የርኅራኄ መንፈስ ማሳየት ይገባናል። ምንም ያህል ቢጎዱንም፣ ቅሬታችንን ከፍ አድርገን ልንመለከተውና በጉዳታችን ምክንያት ለራሳችንን በማሰብ ማዘን አይገባንም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ለፈጸምነው በደል ይቅርታ ለማግኘት ተስፋ ስለምናደርግ፣ ክፉ የሠሩብንን ሁሉ ይቅር ማለት አለብን።”—Thoughts from the Mount of Blessing, pp. 113፣ 114. ሐ. ለሰው ልጅ ያለንን ግዴታ ምን ሊያስተምረን ይገባል? 1ኛ ጴጥሮስ 4:8፤ ሮሜ 13:8 “መለኮታዊው ሕይወት ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ይኑር፤ በዚህም ተስፋ በሌለው ነገር ውስጥ ተስፋን የሚያለመልም እና በኃጢአት በተሰበረ ልብ ውስጥ የሰማይን ሰላም የሚያመጣውን የሰማይ ፍቅር በእናንተ በኩል ይግለጽ። ወደ እግዚአብሔር ስንመጣ፣ ይህ በመግቢያችን ላይ የሚገጥመን ሁኔታ ነው፣ ከእርሱ ምሕረትን በመቀበል፣ ለሌሎች የእርሱን ጸጋ ለመግለጥ እራሳችንን እናስገዛለን።”—ibid, p 114፣ 115።“ሰው ለሰው የሚያሳየው ኢሰብአዊነት ትልቁ ኃጢአት ነው። ብዙዎች የእግዚአብሔርን ፍትህ እንደሚወክሉ ያስባሉ፤ ርህራሄውንና ታላቅ ፍቅሩንም መወከልን ግን ሙሉ በሙሉ ይረሱታል። እነዚህ ሰዎች በሸካራነትና በጭካኔ የሚከሷቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከመጀመሪያውም በፈተና ውጥረት ውስጥ ያሉ ናቸው። ሰይጣን ከእነዚህ ነፍሳት ጋር እየተዋጋ ነው፣ እና ሻካራ፣ ርህራሄ የሌላቸው ቃላት ተስፋ ያስቆርጧቸዋል እንዲሁም በፈታኙ ኃይል ምርኮ ሆነው እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል።”—The Ministry of Healing, p. 163

3. በዝርዝር እና ከልብ በመነጨ መንፈስ ማክሰኞ ፣ ሐምሌ 14
ሀ. ሌሎችን ኃጢአቶች ለእግዚአብሔር ብቻ ስንናዘዝ ነገር ግን በሕዝብ ፊት መናዘዝ ያለብን ምን ዓይነት ኃጢአቶች ናቸው? መዝሙር 32፡-5፤ ማቴዎስ 5፡-23፣ 24። “እውነተኛ ኑዛዜ ሁል ጊዜ ጠቅለል ተደርጎ የሚቀርብ ሳይሆን እያንዳንዷን ኃጢአት በዝርዝር ማውሳትን ይጠይቃል። ምናልባትም የሠራነው ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ብቻ መቅረብ ያለበት ሊሆን ይችላል። ሰውን ጎድተን ከሆነ ወደዚያ ሰው ቀርበን ድርጊታችንን ማመን ተገቢ ነው። በሕዝብ ፊት መናዘዝ የሚያስፈልገው ኃጢአት ሠርተንም ከሆነ መድረክ ላይ መናዘዝ ይጠበቅብናል። ይሁን እንጂ የትኛውም አይነት ኑዛዜ ግልጽና ቀጥተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ በደለኛ የሆንበት ጥፋት የቱ እንደሆነ የሚገልጽ መሆን አለበት።”—Steps to Christ, p. 38“የግል ኃጢአቶችን በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል ብቸኛው አስታራቂ ለሆነው ለክርስቶስ መናዘዝ አለብን።… እያንዳንዱ ኃጢአት በእግዚአብሔር ላይ የሚፈጸም በደል ነው፣ እናም በክርስቶስ በኩል ለእርሱ መናዘዝ አለብን። እያንዳንዱን ግልጽ ኃጢአት ደግሞ በግልጽ መናዘዝ አለብን።”— Gospel Workers፣ pp. 216። ለ. የእውነተኛ ኑዛዜ ዓላማ ምንድን ነው? 1ኛ ሳሙኤል 12፡-19። “በሳሙኤል ዘመን የእስራኤል ልጆች ከእግዚአብሔር መንገድ ተቅበዝብዘው በመውጣታቸው በእርሱ ላይ የነበራቸውን እምነት አጡ። ይህን ተከትሎም ኃጢአት ባመጣው መዘዝ ይሰቃዩ ጀመር። ክፉና ደጉን ለመለየት የሚያስችላቸውን የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ያጡት እነዚህ ሕዝቦች ከታላቁ የዩኒቨርስ ገዢ ፊታቸውን በማዞር በአካባቢያቸው እንደነበሩት አሕዛብ ሊገዙ ተመኙ። እስራኤላውያኑ ስላም ከማግኘታቸው አስቀድሞ “ንጉሥ እንዲነግሥልን በመጠየቃችን ተጨማሪ ጥፋት አደረግን” (1ኛ ሳሙ. 12:-19)። በማለት በግልፅ ኃጢያታቸውን ተናዘዘ። የስሩትን ኃጢያት ስሙን በመጥቀስ መናዘዝ ነበረባቸው።”—Steps to Christ, p. 38፣ 39። ሐ. ኑዛዜን ተከትሎ ምን ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ አለበት? ኢሳይያስ 1:-16፣ 17 ፤ ሕዝቅኤል 33:-15። “ ኃጢአትን መናዘዝ ከልብ የመነጨ መጸጸትና መለወጥ ከሌለው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም። በሕይወት ውስጥ ለውጦች እንዲመጡ በመወስን እያንዳንዱ ለእግዚአብሔር አጸያፊ የሆነው ነገር መወገድ ይኖርበታል። ይህም በእውነት ስለ ኃጢታችን የማዘናችን ውጤት ይሆናል።”—ibid, p 39።“ እንደ ዘኬዎስ ሁሉ፣ የተለወጠ ነፍስ ክርስቶስን ወደ ልቡ የመግባቱ ምልክት እንዲሆን በሕይወቱ ያደርጋቸውን የነበሩትን ዓመፀኛ ድርጊቶችን በመተው ያሳያል። እንደ ቀራጩ አለቃ፣ ካሳ በመስጠት ቅንነቱንም ያረጋግጣል።”—The Desire of Ages, p. 556

4. የራስን ትክክለኛነት የማረጋገጥ አደጋ ረቡዕ ፣ ሐምሌ 15
ሀ. ጌታ አዳምና ሔዋንን ስለ ኃጢአታቸው ሲጠይቃቸው፣ በእርግጥ የእነሱ ጥፋት እንዳልሆነ እንዴት አመላክተዋል? ዘፍጥረት 3:12፣ 13. “አዳም ኃጢአቱን ሊክድም ሆነ ሊያስተባብል አልቻለም፤ ነገር ግን በድርጊቱ መጸጸቱን ከመግለጽ ይልቅ ጥፋቱን በሚስቱ ላይ፣ ብሎም በእግዚአብሔር ላይ ለማሳበብ ሞከረ፡፡ “ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ” አለው”—Patriarchs and Prophets, p. 57“አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ ከበሉ በኋላ በፍርሃትና በሐፍረት ስሜት ተዋጡ። በመጀመሪያ ወደ አዕምሮአቸው የመጣው ሃሳብ፣ ለሠሩት ኃጢአት ምክንያት በማቅረብ ከአስከፊው የሞት ቅጣት ማምለጥ የሚችሉበትን መንገድ መቀየስ ነበር። የሠሩትን ኃጢአት አስመልከቶ እግዚአብሔር ጥያቄ ባቀረበላቸው ጊዜ አዳም ሲመልስ ለኃጢአቱ በከፊል ተጠያቂ ያደረገው እራሱን እግዚአብሔርን በከፊል ደግሞ ረዳቱን ነበር «ይህች ከእኔ ጋር እንድትኖር የሰጠኸኝ ሴት፣ እርሷ ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝና በላሁ (ዘፍ. 3:12)። ሴቲቱ ደግሞ በእባቡ በማመካኘት «እባብ አሳተኝና በላሁ (ዘፍ. 3:13) ስትል መልስ ሰጠች። ሔዋን ለኃጢአቷ የሰጠችው ምክንያት «እባቡን ለምን ፈጠርክ? ለምንስ ወደ ገነት ይመጣ ዘንድ ፈቀድክለት?» የሚል ጥያቄ ያዘለ ሲሆን በዚህም በኃጢአት ለመውደቃቸው እግዚአብሔርን ተጠያቂ ሲያደርጉት ይስተዋላሉ።”—Steps to Christ, p. 40 ለ. ራስን የማጽደቅ ኑዛዜ ውጤታማ ያልሆነው ለምንድን ነው? ኢዮብ 9:20ሉቃስ 16:15 “ራስን የማጽደቅ መንፈስ የመጣው ከውሸት አባት ሲሆን በአዳም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ሁሉ ላይ ታይቷል። እንደዚህ ዓይነት መናዘዝ በመለኮታዊ መንፈስ የተነሳሳ አይደለም እናም በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የለውም። እውነተኛ ንስሐ አንድ ሰው ጥፋቱን እንዲሸከም እና ያለ ማታለል ወይም ግብዝነት እንዲቀበል ይመራዋል።”— ibid, p 40።“ለኃጢአታችን ሰበብ በማቅረብ ጥፋታችንን ለመቀነስ መሞከር የለብንም። የእግዚአብሔርን የኃጢአት ተመን መቀበል አለብን፣ ያ በእርግጥም ከባድ ነው። የኃጢአትን አስከፊነት ሊገልጽ የሚችለው ቀራንዮ ብቻ ነው። የራሳችንን ጥፋት መሸከም ቢኖርብን ያደቅቀን ነበር። ኃጢአት የሌለበት ግን በእኛ ቦታ ተተካ፤ ምንም እንኳን የማይገባው ቢሆንም፣ በደላችንን ተሸክሟል። ‘ኃጢአታችንን ብንናዘዝ’፣ እግዚአብሔር ‘ታማኝና ጻድቅ ነው፤ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን ይችላል’ 1ኛ ዮሐንስ 1፡-9። ይህ ክቡር እውነት ነው!— ሕጉንም፣ በየሱስም የሚያምኑትን ሁሉ የሚያጸድቅ እውነት ነው። ‘ክፋትን ይቅር የሚል፣ የርስቱንም ቅሬታ በደል የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም፣ ምክንያቱም በምሕረት ደስ ይለዋል።’ ሚክያስ 7፡-18።”—Thoughts from the Mount of Blessing, p. 116

5. ግልጽ ኑዛዜ ሐሙስ ፣ ሐምሌ 16
ሀ. ጳውሎስ ኃጢአቱን በትህትና እና በዝርዝር እንዴት አምኖ ተቀበለ? የሐዋርያት ሥራ 26:10፣ 11። “ በእግዚአብሔር ቃል ላይ በምሳሌ የቀረበው ከልብ የመነጨ ንስሐና እራስን ማዋረድ ለኃጢአት አንዳችም ምክንያት ለመስጠት የማይሞክሩበትን ወይም እራስን ጻድቅ የማያደርጉበትን የኑዛዜ መንፈስ ይገልጽልናል። ጳውሎስ ላደረገው ጥፋት ምክንያት በመደርደር እራሱን ለመከላከል አልፈለገም፤ ነገርግን መተላለፉን ሳያሳንስ እንዳለ በጥቁር ቀለም አሰፈረው። [ሐዋርያት ሥራ 26:10፣ 11 የተጠቀሰ]”—Steps to Christ, p. 41 ለ. ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈው የመጀመሪያ መልእክቱ ስለራሱ ምን አለ? 1ኛ ጢሞቴዎስ 1:15። “በራሳችን ውስጥ ድክመትን ብቻ እንጂ፣ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን ነገር ማየት አንችልም፣ ሰይጣንም የባህሪ ጉድለቶቻችንን ማስተካከል እንደማንችልና ምንም ጥቅም እንደሌለን ይነግረናል። ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት ስንሞክር፣ ጠላት በሹክሹክታ “መጸለይ ምንም ፋይዳ የለውም፤ ባለፈው ያንን ክፉ ነገር አላደረግክምን? በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት አልሠራህምን? ይለናል። ነገር ግን ለጠላታችን፡- “የልጁ የየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” ብለን ልንነግረው እንችላለን። 1ኛ ዮሐንስ 1፡-7። ኃጢአት እንደሠራን እና መጸለይ እንደማንችል ሲሰማን ያኔ ለመጸለይ ትክክለኛ ጊዜ ነው። ያፈርን እና በጣም የተዋረድን ልንሆን እንችላለን፣ ነገር ግን መጸለይ እና ማመን አለብን።” [1ኛ ጢሞቴዎስ 1:-15 ተጠቅሷል።] ይቅርታ... በክርስቶስ ነቁጣ አልባ ጽድቅ መሠረት የተሰጠን ነጻ ስጦታ ነው።”—Thoughts from the Mount of Blessing, p. 115፣ 116. ሐ. ኃጢአታችንን ብንናዘዝ እግዚአብሔር ምን ተስፋ ሰጠን? 1ኛ ዮሐንስ 1፡9። “በእውነተኛ ንስሐ ስር የሚገዛው ትህትናን የተላበሰውና የተሰበረው ልብ፣ ለእግዚአብሔር ፍቅር እና ለከበረው ቀራኒዮ ያለውን አድናቆት ይቸራል። ልጅ ለአፍቃሪው ወላጅ አባቱ ስህተቱን እንደሚያስታውቅ ሁሉ በእውነት ንስሐ የሚገባውም ሰው ኃጢአቱን በሙሉ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል ‘ኃጢአታችንን ብንናዘዝ፤ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን፤ ከዐመጻ ሁሉ ሊያነፃን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።’ (1ኛ ዮሐ. 1:9)።”—Steps to Christ, p. 41

የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ፣ ሐምሌ 17
1. ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር በታማኝነት ስንናዘዝ፣ በእርሱ ፊት እንዴት እንቆማለን? 2. ለሌሎች ሰዎች አንዳንድ ኑዛዜዎች መደረግ ያለባቸው በምን ሁኔታዎች ውስጥ ነው፣ እና ለምን? 3. ኑዛዜን በግልጽ መግለጽ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? 4. ራስን ማጽደቅ ያለውን አደጋ ግለጽ። 5. የትህትና መናዘዝ ውጤት ምንድን ነው?
 <<    >>