Back to top

Sabbath Bible Lessons

ከየሱስ ጋር መራመድ

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሐምሌ 25፣ 2018 5ኛ ትምህርት
ቅድስና የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።“ (ኤርምያስ 29፡13)።
ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ ፡   Steps to Christ, chapter 5፣ pp. 43–48። 
“ ግጭቱን (ውዝግቡን) በራሳችን ኃይል ማሸነፍ ለእኛ የማይቻል ነው፤ አእምሮን ከእግዚአብሔር የሚመልስ (የሚያዘናጋን) ማንኛውም ነገር፣ ራስን ከፍ ከፍ ወደማድረግ ወይም በራስ ላይ ወደመመካት የሚመራን ማንኛውም ነገር፣ በእርግጠኛነት የመውደቂያ መንገዳችን እያዘጋጀልን ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ዋና ዓላማ በሰው ኃይል ላይ አለመታመንን ማሳደግ እና በመለኮታዊ ኃይል ላይ እምነትን ማበረታታት ነው።”—Patriarchs and Prophets, p. 717

1. ከራስ ጋር የሚደረግ ተጋድሎ (ውጊያ) እሁድ ፣ ሐምሌ 19
ሀ. ጳውሎስ የክርስቲያናዊ ጦርነትንና ለጦርነቱ (ተጋድሎንና ለተጋድሎው) የሚያስፈልገውን መሣሪያ እንዴት አድርጎ ገለጸው? ኤፌሶን 6: 12-18። “እጅግ በከረረና ተወዳዳሪ በሌለው ብልጣ ብልጥ ፈተናዎቹ ሰይጣን በክርስቶስ ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ ሆኖም በእያንዳንዱ ግጭት ተገፈተረ። እነዚያ ጦርነቶች ስለእኛ የተደረጉ ናቸው፤ እነዚያ ድሎች፣ እኛ ድል እናደርግ ዘንድ የሚቻለን እንዲሆን ያደርጉናል። ለሚሹት ሁሉ ክርስቶስ ብርታትን ይሰጣል። ያለ ራሱ እሽታ በስተቀር ማንም ሰው በሰይጣን አይሸነፍም። ፈታኙ ፈቃድን የመቆጣጠር ወይም ነፍስን አስገድዶ ኃጢአት የማሰራት ኃይል የለውም። ማስጨነቅ ይችል ይሆናል፤ ሆኖም መበከል አይቻለውም። ሰቆቃን እንጂ መርከስን አያስከትልም። ክርስቶስ ድል የመንሳቱ እውነት ሰይጣንንና ኃጢአትን በቆራጥነት ይዋጉት ዘንድ ተከታዮቹን ሊያበረታታቸው ይገባል።”—The Great Controversy, p. 510 ለ. ሰይጣን ሙሉ የበላይነትን ለማግኘት የሚሞክረው የት ነው? ምሳሌ 4:23 “ሰው በልቡ እንደሚያስብ፣ እንዲሁ ነው።” ምሳሌ 23:7። ልብ በመለኮታዊ ጸጋ መታደስ አለበት፣ አለበለዚያ የሕይወትን ንጽሕና መፈለግ ከንቱ ይሆናል። ከክርስቶስ ጸጋ ነፃ በሆነ፣ ክቡርና ደግ ባህሪ ለመገንባት የሚሞክር ሰው ቤቱን በተንሰራታች አሸዋ ላይ ይገነባል። በኃይለኛ የፈተና አውሎ ነፋሶች ሲመጡ በእርግጥም ይወድቃልና።”—Patriarchs and Prophets, p. 460.

2. መለኮታዊ ግብዣ ሰኞ ፣ ሐምሌ 20
ሀ. የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን ምን መተው አለብን? ሉቃስ 14:33ማቴዎስ 6:24 “ራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ስንሰጥ፤ ከእርሱ የሚለዩንን ነገሮች ሁሉ ፍጹም መተው ይኖርብናል። ይህን አስመልከቶ አዳኙ እንዲህ ይላል “እንደዚሁም ከእናንተ ማንም ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም” (ሉቃስ 14:-33)። ልባችንን ከእግዚአብሔር የሚያርቀውን ነገር ሁሉ መተው ይገባናል። ለሐብት ቅድሚያ መስጠት የብዙዎች ጣዖት ነው። የንዋይ ፍቅርና የተትረፈረፈ ሐብት የማግኘት አባዜ ለሰይጣን ጠፍንጎ የሚስጥ የወርቅ ስንስለት ነው። መልካም ስም ማግኘትና ዓለማዊ ክብርን መጎናጸፍ የብዙዎች ጣኦት ሲሆን፤ በንፉግነት የታጠረ የምቾት ኑሮ እየኖሩ ሌሎችን በመርዳት የሚገባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ አለመወጣት እንዲሁ ሌላው ጣዖት ነው። በመሆኑም ሙሉ በሙሉ ካልሆነ በስተቀር በከፊል የእግዚአብሔር ልጆች መሆን አንችልም።”—Steps to Christ, p. 44. ለ. እግዚአብሔር የልብና የሕይወት መታደስ ለሚፈልጉ ሁሉ ምን ዓይነት መለኮታዊ ግብዣ ያቀርባል? ኢሳይያስ 1:18ኤርምያስ 29:13ያዕቆብ 4:7–10 “የእግዚአብሔር መንግሥት ሰይጣን አስመስሎ ሊያቀርብ እንደሚሞክረው በጭፍን መገዛት እና ምክንያት አልባ የባርነት ሥርዓት አይደለም፡፡ በተቃራኒው እግዚአብሔር “ኑና እንዋቀስ” (ኢሳ. 1:-18) በማለት ለአዕምሮአችንና ለህሊናችን የፍቅር ግብዣውን ያቀርባል፡፡ እግዚአብሔር የፍጡራኑን ፈቃድ በግድ አያስገድድም ፤ በመሆኑም በፈቃደኝነትና በማስተዋል ላይ ያልተመሰረተን አምልኮ መቀበል አይችልም፡፡ በግዳጅነት የተመሰረተ ራስን መስጠት እውነተኛውን የአዕምሮአዊ ዕድገትና የባህሪ መጎልበት በማገድ ሰብዓዊውን ፍጡር ከአንድ ግዑዝ ማሽን ያልተለየ ያደርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ የፈጣሪ ዓላማ አይደለም፡፡ እርሱ የሚመኘው የፍጥረት ሥራው አክሊል የሆነው ሰብዓዊው ፍጡር ዘወትር እያደገ በመሄድ ሊደርስ ወደ ሚችለው ከፍ ያለ ማዕረግ ላይ እንዲደርስ ነው፡፡ እርሱ በጸጋው ወደ ራሱ ሊያመጣን በመመኘት የተትረፈረፈ ባርኮቱን ከፊት ለፊታችን በመዘርጋት ሥራውን በእኛ ውስጥ መሥራት ይቻለው ዘንድ ራሳችንን ለእርሱ እንድናስረክብ ይጋብዘናል፡፡ ከኃጢአት እሥራት ተፈትተን የእግዚአብሔር ልጆች የሚያገኙትን በክብር የተሞላ ነጻነት እንካፈል ዘንድ እነሆ ምርጫውን ለእኛ ትቶልናል፡፡ ”—ibid, p 43፣ 44“ክርስቶስ የሰው ዘር አዳኝ ሆኖ ተገለጠ። ሕዝቡ በራሳቸው ሥራ፣ በራሳቸው ጽድቅ ወይም በራሳቸው በምንም መንገድ መተማመን የለባቸውም፤ ነገር ግን የዓለምን ኃጢአት በሚያስወግደው በእግዚአብሔር በግ ላይ እንጂ። በእርሱ ከአብ ጋር ያለው ጠበቃ ተገለጠ። በእርሱ በኩል ‘ኑና አብረን እንወያይ’ ይላል ጌታ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አመዳይ ቢሆን እንደ በረዶ ነጭ ይሆናል፤ እንደ ደምም ቢቀላም እንደ ባዘቶ ይሆናል።’ ይህ ግብዣ ዛሬ ለእኛ ያው ነው። የተስፋውን ቃል ያገኝ ዘንድ፣ ኩራት፣ ራስን ከፍ አድርጎ መመልከት ወይም ራስን ማጽደቅ ማንም ሰው ኃጢአቱን ከመናዘዝ አያግደው።”—Fundamentals of Christian Education, p. 239.

3. ክርስቶስ ሁሉንም ሰጠ ማክሰኞ ፣ ሐምሌ 21
ሀ. ለክርስቶስ ልጆቹን ወደ ሰማይ የመውሰድ መብት የሰጠው ምንድን ነው? ቆላስይስ 1:14፤ ዕብራውያን 7:25 “በእግዚአብሔር ፈጽሞ ችላ የተባለ በመሰለበት በዚያ አስከፊ የጨለማ ወቅት ክርስቶስ የመጨረሻውን ሰብአዊ የወዮታ ጽዋ ጠጣ። በዚያ እጅግ አስጨናቂ ጊዜ የሱስ የተማመነው ከዚያ በፊት በአባቱ ዘንድ ተቀባይነት እንደነበረው ባየው ማረጋገጫ ነው። የአባቱን ባሕርይ፣ ፍርዱ ፍትሃዊ መሆኑን፣ መሐሪነቱንና ታላቅ ፍቅሩን ያውቅ ነበር። የሱስ የአባቱን ትእዛዝ ለመፈጸም ምንጊዜም ደስተኛ ስለነበር እምነቱን በዚህ አባቱ ላይ አደረገ። ራሱን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ስላስገዛ አባቱ እንደተለየው ይሰማው የነበረው ስጋት ለቀቀው። ስለዚህ ክርስቶስ በኃይማኖት አሸናፊ ሆነ።”—The Desire of Ages, p. 756“እግዚእብሔር የሱስን እንደ ስጦታ ባቀረበ ጊዜ መላ ሰማይን ሰጠ። እንደ ሰው አስተሳሰብ ከሆነ ይህ መስዋዕት ፍጹም ብኩንነት ነው። እንደ ሰብአዊ ፍጡር የአስተሳሰብ ሥልት ከሆነ መላው የማዳን ዕቅድ የመሐሪነትና የንብረት ብኩንነት ነው። ራስን ችላ ማለትና ከልብ የመነጨ መስዋዕትነት በየቦታው ያጋጥሙናል። ሰውን ከወደቀበት ለመነሳትና በክርስቶስ አማካይነት በተገለጸው ወሰን የሌለው ፍቅር ለመባረክ አሻፈረኝ ሲል የሰማይ ሠራዊት በመገረም ይመለከታሉ። ይህን በመመልከት ይህ ሁሉ ብኩንነት ለምንድን ነው? ማለት ይችላሉ።”“ነገር ግን የጠፋውን ዓለም የማዳን ሥራ የተሟላ፣ የተትረፈረፈና እንከን የሌለው መሆን ነበረበት። የክርስቶስ ስጦታ እያንዳንዱን እግዚአብሔር የፈጠረውን ነፍስ ለማዳረስ ሲባል እጅግ የተትረፈረፈ ሆነ። ይህን ትልቅ ስጦታ ለመቀበል ፈቃደኛ ለሆኑት ብቻ እንዲበቃ ተደርጐ አልተወሰነም። ሁሉ ሰው ባይድንም በሰፊ ችሮታ የተቀየሰለትን ሁሉ ስላላከናወነ የማዳን ዕቅድ ባክኖአል ሊባል አይችልም። በቅቶ መትረፍ አለበት።”—ibid, pp 565፣ 566 ለ. የሱስ ልጆቹ ለመሆን ከሚፈልጉና መንፈሱን ለመቀበል ከሚፈልጉ ሁሉ ምን ይፈልጋል? ምሳሌ 23:26 “[የሱስ] የኃጢአተኞችን ኑዛዜ ለመስማት እና ንስሐቸውን ለመቀበል በርኅራኄ እየጠበቀ ነው። እናትየው ከምትወደው ሕፃን ልጇ ፈገግታን ለማየት እንደምትጓጓ እሱም ከእነርሱ የምስጋና ምላሽ ይጠብቃል። ታላቁ አምላክ እርሱን አባ አባት ብለን እንድንጠራው ያስተምረናል። ልቡ በፈተናዎቻችንና በመከራዎቻችን ሁሉ ምን ያህል በቅንነትና በርኅራኄ እንደሚናፍቅ እንድንገነዘብ ይፈልጋል።”—Gospel Workers, pp. 210.“ሁሉን ለእርሱ ስናስረክብ የትኛውን ነው ለራሳችን የምናስቀረው? የሱስ በኃጢአት የተበከለውን ልብ በደሙ ሲያነጻ፤ ሲያጠራና ወደር በሌለው ፍቅሩ ሲያድን፣ ሰብአዊ ፍጡር ግን ሁለንተናውን ለእርሱ ማስረከቡ አስቸጋሪ እንደሆነ አድርጎ ሲያስብ ይስተዋላል። ይህ ሲነገር ስሰማም ሆነ ስጽፈው ያሳፍረኛል!”—Steps to Christ, p. 46.

4. ሙሉ በሙሉ ራስን መስጠት ረቡዕ ፣ ሐምሌ 22
ሀ. ጳውሎስ ለአማኞች የነበረው ልባዊ ፍላጎት ምን ነበር? ሮሜ 12:1፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 5:23። “ ምንም እንኳን ለጥንቷ እስራኤል የተነገረ ቢሆንም፣ እነዚህ ቃላት ዛሬ ላሉት የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሆን ትምህርትን ይዘዋል። ሐዋርያው ወንድሞቹን ሰውነታቸውን “ሕያው፣ ቅዱስ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት” አድርገው እንዲያቀርቡ ሲማጸን፣ የእውነተኛ ቅድስና መርሆችን ያስቀምጣል። ይህ ንድፈ ሐሳብ፣ ስሜት ወይም የቃላት ብቻ ሳይሆን፣ ወደ ዕለታዊ ሕይወት የሚገባ ሕያው፣ ንቁ መርህ ነው። የመብላት፣ የመጠጣት እና የአለባበስ ልማዶቻችን አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ መሆን አለባቸው፤ ሰውነታችንን ለጌታ ስናቀርብ፣ በተሳሳተ ልማድ የተበላሸ መሥዋዕት ሳይሆን “ሕያው፣ ቅዱስ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት” መሆን አለበት።”—The Sanctified Life, pp. 27፣ 28“ ራሳችንን ለእግዚአብሔር አገልግሎት መስጠት አለብን፣ እናም መስዋዕቱን በተቻለ መጠን ፍጹም ለማድረግ መጣር አለብን። እግዚአብሔር ከምንሰጠው ነገር ለራሳችን ምርጥ ከሆነው ነገር ያነሰ ከሆነ አይደሰትም። በሙሉ ልባቸው የሚወዱት፣ ለእርሱ በሕይወታቸው ውስጥ ምርጡን አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋሉ፣ እናም ፍቃዱን ለማድረግ ከሚያስችላቸው ከእርሱ ሕጎች ጋር ራሳቸውን ለማስማማት ዘወትር ይጥራሉ።”—Patriarchs and Prophets, p. 352፣ 353 ለ. ሕዝቡ በጴንጤቆስጤ ቀን የጴጥሮስን ንግግር ሲሰሙ፣ በልባቸው ላይ የነበረው ሸክም ምን ነበር? የሐዋርያት ሥራ 2:37፣ 38። “[ሕዝቡም] ደቀ መዛሙርቱ የተሰቀለው የእግዚአብሔር ልጅ ነው እያሉ ሲናገሩ ሰሙ። ካህናትና ገዢዎችም ተንቀጠቀጡ። ሕዝቡም የተነገረውን ነገር ከማመናቸው የተነሳ ጭንቀት ያዛቸው። ልባቸውም ተነካና ጴጥሮስንና ሌሎችንም ሐዋርያትን፦ ‘ወንድሞች ሆይ፥ ምን እናድርግ?’ አሉአቸው። የደቀ መዛሙርቱን መልእክት ካደመጡት መካከል በእምነታቸው ቅን የሆኑ ቀናተኛ አይሁዶች ነበሩ። ከተናጋሪው ቃል ጋር የተያያዘው ኃይል የሱስ በእርግጥ መሲሕ መሆኑን አሳመናቸው። …“በካህናትና በገዢዎች በመታለል ክርስቶስን የካዱ መሆናቸውን ጴጥሮስ ላመኑት ሰዎች በታላቅ አፅንዖት ተናገረ፤ እናም ምክርን ለማግኘት ወደእነዚህ ሰዎች መመልከታውን የሚቀጥሉ ከሆነ፣ እንዲሁም እነርሱ ደፍረው ከማድረጋቸው በፊት፣ መሪዎቻቸው ለክርስቶስ እውቅና እስኪሰጡ ድረስ የሚጠብቁ ከሆነ፣ ክርስቶስን መቼም እንደማይቀበሉ ተናገረ። እነዚህ ኃያላን ሰዎች እግዚአብሔርን እንደሚፈሩ ቢናገሩም (የቅድስና መልክ ቢላበሱም) ለምድራዊ ሀብትና ክብር ከፍተኛ ጉጉት ነበራቸው። ብርሃንን ለመቀበል ወደ ክርስቶስ ለመምጣት ፈቃደኛ አልነበሩም።”—The Acts of the Apostles, pp. 43፣ 44

5. ራስን መስጠትን መጠበቅ ሐሙስ ፣ ሐምሌ 23
ሀ. ሙሉ በሙሉ ለጌታ ራሳችንን ሰጥተን የክርስቶስን መልክ መምሰል እንደምንችል እምነት የሚያመጣው ምንድን ነው? ፊልጵስዩስ 2:12፣ 13. “እግዚአብሔር ቃል ኪዳኖቹን (ተስፋዎቹን) ሳይፈጸም ይቀራል፣ ትዕግስቱም ይሟጠጣል፣ ርኅራኄውም ያልቃል ብለህ እንድትፈራ አላዘዘህም። ይልቁንም ፈቃድህን ለክርስቶስ ፈቃድ ማስገዛት ተስኖህ፣ በትውልድ (በውርስ) የመጡና በልምምድ የዳበሩ የባህሪ ዝንባሌዎች ህይወትህን እንዳይቆጣጠሩት ልትፈራ ይገባሃል። ‘በመልካም ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።’ ራስ ወዳድነትህ በነፍስህና በታላቁ ዋና ሠራተኛ መካከል ጣልቃ እንዳይገባ ፍራ። እግዚአብሔር በአንተ በኩል ሊያሳካው የሚፈልገውን ከፍተኛ ዓላማ በገዛ ራስህ ፈቃድ እንዳታበላሽ ፍራ። በራስህ ኃይል መታመን፣ እጅህን ከክርስቶስ እጅ ማስለቀቅ እና ያለ እርሱ ሕያው መገኘት የሕይወትን መንገድ ለመጓዝ መሞከርን ፍራ።”—Christ’s Object Lessons, p. 161 ለ. የእምነት ጽናት እና ለትክክለኛ መርሆዎች ሙሉ በሙሉ መገዛት እንዴት ሊጠበቅ ይችላል? ገላትያ 2:20ማቴዎስ 16:24፣ 25። “የቅድስና በረከትን ለማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች በመጀመሪያ ራስን መስዋዕት የማድረግን ትርጉም መማር አለባቸው። የክርስቶስ መስቀል ‘እጅግ የላቀና ዘላለማዊ የክብር ክብደት’ የተሰቀለበት ማዕከላዊ አምድ (ምሰሶ) ነው።”—The Acts of the Apostles, pp. 560“ልብዎን ሊለውጡም ሆነ በልብዎ ውስጥ ያለውን ፍቅር ለእግዚአብሔር መስጠት አይችሉም። ነገር ግን እርሱን ለማገልገል ምርጫዎ በማድረግ ፈቃድዎን ለእርሱ ማስገዛት ይችላሉ። ይህን ሲያደርጉ ሳለ ፈቃዱን በእርስዎ ውስጥ የሚያደርገው አምላክ እርሱ እንደሚወድና እንደሚፈቅድ መሥራት ይጀምራል። . . .“በጎውን ፈቃድ በመለማመድ በሕይወት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለውጥ ማምጣት ይቻላል። ፈቃድዎን ለክርስቶስ በማስገዛት ከአለቆችና ከኃይላት በላይ ከሆነው ኃያል ጋር ራስዎን ተባባሪ ያድርጉ። ታማኝና የማይለወጥ ሆነው ሲቆሙ ፤ ብርታትን ከላይ ያገኛሉ። ያለማቋረጥ ራስዎን ለእግዚአብሔር አሳልፈው ሲሰጡ አዲስ ሕይወት መኖር ይጀምራሉ ያውም የእምነት ህይወት።”—Steps to Christ, p. 47፣ 48

የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ፣ ሐምሌ 24
1. ከነፍሳችን ጠላት ጋር በሚደረገው ውጊያ ስኬታማ ለመሆን ምን ያስፈልጋል? 2. አስቀድሞ የተሸነፈ ጠላትን ለማሸነፍ የሚደረገው እውነተኛ ውጊያ ምንድን ነው? 3. ክርስቶስ ለድነታችን ከሰጠው ስጦታ ምን እንማራለን? 4. እግዚአብሔር ዓላማ ለአማኞች፣ በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ ምንድን ነው? 5. ፈቃዳችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የሚስማማ ከሆነ፣ በየቀኑ ምን ይገጥመናል?
 <<    >>