Back to top

Sabbath Bible Lessons

ከየሱስ ጋር መራመድ

 <<    >> 
ሰንበት፣ ነሐሴ 09፣ 2018 7ኛ ትምህርት
የደቀመዝሙርነት መፈተኛ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።“ (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17)።
ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ ፡   Steps to Christ, chapter 7፣ pp. 57–65 
“ባህርይ የሚገለጸው አልፎ አልፎ በሚደረጉ ጥሩ ወይም መጥፎ ሥራዎች ሳይሆን አዘውትረው በሚነገሩ ቃላትና ድርጊቶች ነው።”—Steps to Christ, p. 57፣ 58

1. የመንፈስ ሥራ እሁድ ፣ ነሐሴ 03
ሀ. ክርስቶስ የመለወጥን ሥራ ሲገልጽ ምን ትምህርት አስተምሯል? ዮሐንስ 3:5-8 “ አንድ ሰው የተለወጠበትን ትክክለኛ ጊዜ ወይም ቦታ ወይም በመለወጡ ሂደት ውስጥ የነበሩ አጠቃላይ ሁናቴዎችን አያይዞ አንድ በአንድ መናገር አይችል ይሆናል። ይሁን እንጂ መናገር አልቻለም ማለት አለመለወጡን ያሳያል ማለት አይደለም። … ልክ እንደ ንፋሱ የእግዚአብሔር መንፈስም በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚሠራው ሥራ በጉልህ ከመታየቱና ከመሰማቱ ውጭ መንፈሱ በዓይን አይታይም። ያ የሰው ዓይን የማያየው ውስጣችንን ዳግም የሚያድሰው ኃይል በነፍሳችን ውስጥ አዲስ ሕይወትን ይዘራል፤ በእግዚአብሔር አምሳል የሆነውን አዲስ ማንነትን ይፈጥራል።”—Steps to Christ, p. 57 ለ. በእውነት በተለወጠ ሰው ሕይወት ውስጥ ምን ለውጦች ይታያሉ? ሮሜ 12:9–18 ፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5:17። “በራሳችን ልባችንን መለወጥም ሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ራሳችንን ማስማማት አንችልም። በመሆኑም በራሳችንም ሆነ በመልካም ሥራችን ላይ ሙሉ ለሙሉ መታመናችንን ስናቆም፤ ያኔ የእግዚአብሔር ጸጋ በውስጣችን ማደሩን ህይወታችን ይገልጻል። ይህን ተከትሎ በባህሪያችንና በልማዳዊ ድርጊቶቻችን ለውጥ መስተዋል ይጀምራል። በእነዚህ በሁለት የተለያዩ ነገሮች መካከል ያለው ልዩነት ግልጽ ስለሚሆን በቀድሞው ሁናቴና በአሁኑ መሃል ያለው ልዩነት ምን እንደ ሆነ ለይቶ ለማወቅና ለመወእሁድ ይቻላል። ...“እርግጥ ነው ያለ ክርስቶስ ለዋጭ ኃይል ውጫዊ የባህርይ መልካምነት ሊኖር እንደሚችል አይካድም። በሌሎች ለመታየትና ለመወደስ ያለን ፍላጎት የተስተካከለ ሕይወት የምንለውን እንድንቀዳጅ ሊያተጋን ይችላል። ለራሳችን ያለን አክብሮት የክፋት መገለጫ እንዳንሆን ሊያግዘን ይችል ይሆናል፡ ምናልባትም እራስ-ወዳዱ ልብ ለሌሎች መልካምን ነገር ሊያደርግ ይችል ይሆናል። ታዲያ ከማን ወገን እንደሆንን የሚወስነው በምን መንገድ ነው?“አዕምሯችንን የተቆጣጠረው ማን ነው? ሃሳባችን ከማን ጋር ነው?”—ibid., 57፣ 58

2. አዲስ ፍጥረት መሆን ሰኞ ፣ ነሐሴ 04
ሀ. በመንፈስ የተሞሉ ሰዎች የሚያፈሩት ፍሬ ምንድን ነው? ገላትያ 5:22፣ 23። “ በክርስቶስ የሱስ አዲስ ፍጥረት የሆኑ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ ያፈራሉ። … ቀድሞ ይጠሏቸው የነበሩ ነገሮችን አሁን ይወዳሉ፤ ቀድሞ ይወዷቸው የነበሩ ነገሮችን አሁን ይጠላሉ። በራሳቸው ብቻ የሚታመኑ ልበ ደንዳኖች የነበሩት ትሁትና የተሰበረ ልብ ባለቤት ይሆናሉ። ግብዝነትና ልታይ ባይነት በእውነተኛነት እና በጭምትነት ይተካል። የመጠጥ ሱሰኛው ከነበረበት የመጠጥ ሱስ ይላቀቃል፤ አባካኞች ከማባከን ይታቀባሉ። የዓለም የግብዝነት ልማዶች እና ፋሽኖች ወልቀው ይጣላሉ። ክርስቲያን «ውጫዊ ጌጥን› መፈለግ በማቆም «ነገር ግን የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሆን ዘንድ (1ኛ ጴጥ. 3:3-4) ይፈልጋል።”—Steps to Christ, p. 58፣ 59“ የመንፈስ ቅዱስ ተጽእኖ (ውጤት) የክርስቶስ ሕይወት በነፍስ ውስጥ መኖሩ ነው። ክርስቶስን በአይናችን አናየውም አናነጋግረውም ፤ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በአንድም ይሁን በሁሉም ቦታ ለእኛ ቅርብ ነው። ክርስቶስን በሚቀበል ውስጥም ሆነ በእሱ በኩል ይሰራል። መንፈስ በሕይወታቸው ውስጥ መኖሩን የሚውቁ ሰዎች የመንፈስ ፍሬዎችን ይገልጣሉ —ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ገርነት፣ ቸርነት፣ እምነት።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 6, p. 1112 ለ. እውነተኛ ንስሐ ማስረጃው ምንድን ነው? ሕዝቅኤል 33:14፣ 15 “በሕይወት ላይ የሚታይ ተሐድሶን (ለውጥን) የማያመጣ ንስሃ እውነተኛ ንስሃ አይደለም። አንድ ሰው ቃል ኪዳኑን ካፀና፣ ዘርፎ የነበረውን ሲመልስ፤ ኃጢአቱን ከተናዘዘ እንዲሁም እግዚአብሔርንና በአጠገቡ ያሉ ሰዎችን ከወደደ ይህ ኃጢአተኛ የነበረ ሰው ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገሩን እርግጠኛ ሊሆን ይችላል።“በደለኞችና በኃጢአት የረከስን መሆናችንን አምነን ወደ ክርስቶስ በመቅረብ የፀጋ ምህረቱ ተቋዳሾች ስንሆን ፍቅር ከልባችን ይፈልቃል። የክርስቶስ ቀንበር ቀላል ከመሆኑ የተነሳ አንድ ስው በእርሱ ሲሆን ሸክሙ ሁሉ ይቀለዋል። በጨለማ የተዋጠ ይመስል የነበረው መንገድ በጽድቅ ብርሃን ወገግታ ፍንትው ብሎ ይበራል።“የክርስቶስ የአፍቃሪነት ባሕርይ በተከታዮቹ ላይም ይታያል። የእርሱ ደስታ የእግዚአብሔር አብን ፈቃድ ማድረግ ነበር። የአዳኛችንን ሕይወት የተቆጣጠረው ኃይል የአብ ፍቅርና ለአብ ክብር ማምጣት ነበር። የክርስቶስ ሥራዎች ሁሉ ያማሩና የከበሩ የሆኑት በፍቅር ስለተሠሩ ነው። እግዚአብሔር ፍቅርነው፣ ፍቅርም ከእግዚአብሔር ነው። በንስሓ ያልታደስ ልብ ንፁሕ ፍቅር ሊያፈልቅ አይችልም። ይህ ንፁሕ ፍቅር ሊገኝ የሚችለው የሱስ ከነገሠበት ልብ ብቻ ነው። “አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንዋደዳለን።” (1ኛ ዮሐ. 4:19)። ልባችን በመለኮታዊ ፀጋ ከታደስ፤ የድርጊቶች ሁሉ መሠረት የሆነው ፍቅር ባህርያችንን ይለውጣል፤ አስተሳሰባችንን ይመራል፤ ምኞታችንን ይቆጣጠራል፤ ጥላቻችንን ያስወግዳል፤ መንፈሳችንን ይቀድሳል። ይህንን ፍቅር ዘወትር ስንለማመደው፧ ሕይወታችን ይጣፍጣል እንዲሁም በአካባቢያችን ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እናሳድራለን።”—Steps to Christ, p. 59.

3. ሁለት ስህተቶች ማክሰኞ ፣ ነሐሴ 05
ሀ. በብዙ ክርስቲያን ነን በሚሉ ሰዎች ዘንድ ምን አደገኛ ስህተቶች ተቀባይነት አግኝቷል? ፊልጵስዩስ 3:9ሮሜ 10:3ያዕቆብ 2:17 “የእግዚአብሔር ልጆች በተለይም ጌታን በቅርቡ የግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ ሊርቋቸው የሚገቡ ሁለት ስህተቶች አሉ። የመጀመሪያው እና ከዚህ በፊት የጠቀስነው «በራሳችን መልካም ስራና ተግባር ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት እንችላለን» የሚለው እምነት ነው። ይሁን እንጂ፣ በራሱ ጥረት ሕግን በመጠበቅ ቅዱስ ለመሆን የሚጥር ማንኛውም ስው የማይቻል ነገር እየሞከረ ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው ከክርስቶስ ውጪ የሚያደርገው ነገር ሁሉ በእራስ ወዳድነትና በኃጢአት በተበከለ ማንነት የሚያደርገው ነው። ቅዱስ የሚያደርገን በእምነት የምንቀበለው የክርስቶስ ፀጋ ብቻ ነው።“ከዚህ ተቀራኒውና ቀላል የማይባለው አደገኛ ስህተት ደግሞ «የክርስቶስ ጸጋ ተካፋዮች የምንሆነው በእምነት በመሆኑና የእኛ መልካም ሥራዎች ከመዳናችን ጋር ምንም ግንኙነት ስለሌላቸው ክርስቶስ ሰዎችን የእግዚአብሔርን ሕግ ከመጠበቅ ነጻ አውጥቶአቸዋል» የሚለው እምነት ነው።”—Steps to Christ, pp. 59፣ 60. ለ. የክርስቶስ ጸጋ ለእግዚአብሔር ሕግ ከመታዘዝ ነፃ እንደማያደርገን የአዲስ ኪዳን ተስፋ እንዴት ግልጽ ያደርገዋል? ዕብራውያን 8:10፤ 10:16። “የእግዚአብሔር ሕግ የራሱ የእግዚአብሔር፣ የማንነቱ መገለጫ ነው፤ ሕጉ የፍቅርን ባሕርይ ያቀፈ ከመሆኑ የተነሳ በሰማይና በምድር የመንግሥቱ መሠረት ነው። ሕይወታችን በእግዚአብሔር _ አምሳል ከተለወጠ፤ መለኮታዊው ፍቅርም በልባችን ውስጥ ከሰረጸ የእግዚአብሔርን ሕግ ተግባራዊ እናደርጋለን። የፍቅር መርሆ በልባችን ውስጥ ሲስርጽ እኛም የፈጠረንን አምላክ አምሳል ስንይዝ «ሕጌን:- ”ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ” (ዕብ. 10:16) የሚለው የአዲሱ ኪዳን ተስፋ ቃል ይፈጸማል። ሕግም በልባችን ውስጥ ሲጻፍ ሕይወታችን በእርሱ ይመራል። በፍቅር እና ታማኝ አገልግሎት የተመሰረተው ታዛዥነት እውነተኛ የደቀ መዝሙርነት ምልክት ነው።”—ibid, p 60.“እግዚአብሔር፣ ከኤደን ይኖሩ ከነበሩት ቅዱሳን ጥንዶች ይፈልግ የነበረውን መስፈርት በዚህ ጊዜም ይፈልጋል ይኸውም ለእርሱ መስፈርቶች ፍጹም ታዛዥነት ነው። ሕጉ በሁሉም ዘመናት አንድ ነው። በብሉይ ኪዳን የቀረበው ታላቅ የጽድቅ መለኪያ በአዲስ ኪዳን ዝቅ አይልም። የእግዚአብሔርን ቅዱስ ሕግ የይገባኛል ጥያቄዎች ማዳከም የወንጌል ሥራ አይደለም፣ ነገር ግን ሰዎች ትእዛዛቱን መጠበቅ ወደሚችሉበት ሁኔታ ማሳደግ ነው እንጂ።”“ነፍስን የሚያድነው በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት በዚህ ዘመን ብዙዎች እንደምናገሩት አይደለም። ‘እመኑ፣ እመኑ፣’ የሚለው ጩኸታቸው ነው፤ ‘በክርስቶስ ብቻ እመኑ፣ ትድናላችሁ። ማድረግ ያለባችሁ ይህ ብቻ ነው’ ይላሉ። እውነተኛ እምነት ለመዳን በክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ታምኖ እያለ፣ ደግሞም ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ፍጹም ወደ መስማማት ይመራል።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 6, p. 1073

4. መዳን ነፃ ስጦታ ነው ረቡዕ ፣ ነሐሴ 06
ሀ. ከዘላለም ሕይወት እጩዎች ምን ይጠበቃል? 1ኛ ዮሐንስ 5:2፣ 3፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 7:19 “ራሳችሁን ለእርሱ ብትሰጡና እንደ አዳኛችሁ ብትቀበሉት የፈለገውን ያህል ኃጢአተኛ የነበራችሁ ቢመስላችሁም፤ ነገር ግን ስለ ራሱ ሲል እንደ ጻድቅ ይቆጥራችኅል። የክርስቶስ ባሕርይ በእናንተ ምትክ ተቆጥሮ በእግዚአብሔር አብ ፊት ምንም ኃጢአት እንዳልሠራ ሰው ሆናችሁ እንድትታዩ ያደርጋችኋል።“ከዚህ በተጨማሪም ክርስቶስ ልባችሁን ይቀይራል፤ በእምነትም በልባችሁ ውስጥ ይኖራል። ታዲያ ይህንን ከክርስቶስ ጋር ያለ ግንኙነት በእምነት እየጠበቃችሁ ፈቃዳችሁን ያለ ማቋረጥ ለእርሱ እየሰጣችሁ እስከኖራችሁ ድረስ እርሱም መልካም ፈቃዱን የመፈለግ እና የማድረግን ነገር በእናንተ ውስጥ ይሠራል። ስለዚህ እናንተም፡- ‘ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም፣ ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝ እና ስለእኔ ራሱን በስጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው’ (ገላ. 2፡20) ትላላችሁ። ስለዚህ የሱስ ለደቀመዛሙርቱ፡- «በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና» (ማቴ. 10:20) ብሏቸዋል። ከዚያም በእናንተ ከሚሠራው ከክርስቶስ ጋር ሆናችሁ የእርሱን አይነት መንፈስ ትገልጻላችሁ፣ እንደ እርሱም መልካም ሥራን ታደርጋላችሁ። ሥራዎቹም የጽድቅና የመታዘዝ ናቸው።“ስለዚህ የምንኩራራበት የራሳችን የሆነ ምንም ነገር የለንም። ራሳችንን ከፍ አድርገን የምናይበት ምንም መሠረት የለንም። ብቸኛው የተስፋችን መሠረት ለእኛ የተቆጠረልን የክርስቶስ ጽድቅና በእኛ ውስጥ እንዲሁም በእኛ በኩል በመሥራት ለውጥ የሚያመጣው የእርሱ መንፈስ ብቻ ነው።”—Steps to Christ, p. 62፣ 63 ለ. ጌታ ሁሉም ሰው መዳንን እንዲያገኝ ዝግጅት ቢያደርግም፣ አንዳንዶች ለምን መንገዱን ይስታሉ? ኤፌሶን 2:8፣ 9፤ የሐዋርያት ሥራ 4:12፤ ሮሜ 9: 30-33። “እምነት እኛን ከታዛዥነት ነፃ ከማውጣት ይልቅ የክርስቶስ ጸጋ ተካፋይ እንድንሆንና እንድንታዘዝ የሚያደርገን ያው እምነት ብቻ ነው። ...“ «በክርስቶስ ማመን ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ነፃ ያወጣል» የሚለው አስተሳሰብ «እምነት» ሳይሆን እምነት የሚመስል ስህተት ነው። በርግጥ «ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና» (ኤፌ.2:8) ይላል። ነገር ግን «እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።» (ያዕ. 2:17) ይላል። የሱስ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት ለራሱ እንዲህ ብሎ ነበር፦ «አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ» (መዝ. 40:8)። ተመልሶ ወደ አባቱ ቀኝ ከማረጉም በፊት «እኔ የአባቴን ትዕዛዝ እንደጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፣ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ (ዮሐንስ 15:10)» በማለት ተናግሮአል። እንደዚሁ መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ ዮሐ. 2:3-6 እና በ1ኛ ጴጥ. 2:21 «ትዕዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን፡፡. . . በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል፡፡» «ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለእናንተ መከራን ተቀብሏልና» ይላል።”—ibid. pp. 60–62

5. በእምነት መኖር ሐሙስ ፣ ነሐሴ 07
ሀ. ሐዋርያው ጳውሎስ በድል አድራጊነት እንዴት ኖረ? 1ኛ ቆሮንቶስ 15:30፣ 31። “ይህንን ከክርስቶስ ጋር ያለ ግንኙነት በእምነት እየጠበቃችሁ ፈቃዳችሁን ያለ ማቋረጥ ለእርሱ እየሰጣችሁ እስከኖራችሁ ድረስ እርሱም መልካም ፈቃዱን የመፈለግ እና የማድረግን ነገር በእናንተ ውስጥ ይሠራል።”—Steps to Christ, p. 62፣ 63“ ክርስቶስ በሰብዓዊነቱ ፍጹም የሆነ ባሕርይ ፈጥሯል፣ እናም ይህ ባሕርይ ለእኛ ሊያካፍለን በፊታችን ያቀርባል። “ጽድቃችን ሁሉ የመርገም ጨርቅ ነው።” ኢሳይያስ 64:6። እኛ በራሳችን ልናደርገው የምንችለው ነገር ሁሉ በኃጢአት ረክሷል። “የእግዚአብሔር ልጅ ግን ኃጢአታችንን ለማስወገድ ተገለጠ፤ በእርሱም ኃጢአት የለም።“. . . ክርስቶስ የሕጉን መስፈርት ሁሉ በፍጽምና ታዝዟል። ስለ ራሱ እንዲህ ብሏል፡- “አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ማድረግ እወዳለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።” መዝሙር 40:8 . . . . ፍጹም በሆነ ታዛዥነቱ እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንዲታዘዝ አስችሎታል። ለክርስቶስ ስንገዛ፣ ልባችን ከልቡ ጋር፣ ፈቃዳችን ከፈቃዱ ጋር ይዋሃዳል፣ አእምሮአችን ከአእምሮው ጋር አንድ ይሆናል ፤ ሀሳቦቻችን በእርሱ ኃሳብ ይማረካሉ ፤ ያኔ የእርሱን ሕይወት እንኖራለን። የጽድቁን ልብስ መልበስ ማለት ይህ ነው። “—Christ’s Object Lessons, p 311፣ 312 ለ. መዝሙሬኛው በራሱ ሕይወት ምን ዓይነት ደስታን ገልጾ ነበር? መዝሙር 119:97 “ስለ እምነት በምንናገርበት ጊዜ መዘንጋት የሌለብን ነገር አለ። ከእውነተኛው እምነት ፍጹም የተለየ የእምነት አይነት አለ። የእግዚአብሔር ሕልውናና ኃያልነት እንዲሁም የቃሉ እውነትነት ሰይጣንና ጭፍሮቹ እንኳ በልባቸው ሊክዱት የማይችሉት ተጨባጭ እውነታ ነው። ለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ በያዕ. 2:19 ላይ ፡- «እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ አንተ ታምናለህ መልካም ታደርጋለህ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።» ይላል። ስለዚህ ይህ አይነት እምነት እውነተኛ እምነት አይደለም። እውነተኛ እምነት በእግዚአብሔር ቃል ማመን ብቻ ሳይሆን፣ ፈቃዳችንን ለእርሱ ማስገዛትንም ይጨምራል። አንድ ሰው ልቡን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሲያስገዛ፣ በዚያ ሰው ልብ ውስጥ ነፍስን የሚያነጻ በፍቅር የሚሠራ እምነት አለ ማለት ነው። በዚህም እምነት አማንኝነት ነው ልባችን በእግዚአብሔር አምሳል የሚታደሰው።”—Steps to Christ, p. 63

የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ፣ ነሐሴ 08
1. የለውጥ ማስረጃውን ይግለጹ። 2. በአሮጌው ሰው እና በአዲሱ ሰው መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? 3. በመንፈሳዊ ሕይወታችን ውስጥ ልንርቃቸው የሚገቡ ሁለት አደጋዎችን ግለጽ። 4. በጸጋ ሥር ስንኖር፣ የታዛዥነት ጥቅሙ ምንድን ነው? 5. ክርስቶስ በልብ ውስጥ ሲኖር የትኞቹን ሀሳቦች፣ ምኞቶች እና ዓላማዎች ከፍ አድርገው ይመለከቱታል?
 <<    >>