ከየሱስ ጋር መራመድ << >> ሰንበት፣ ነሐሴ 02፣ 2018 6ኛ ትምህርት እምነትና ተቀባይነት ማግኘት የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።“ (ሕዝቅኤል 36፡26)፡፡ ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ ፡ Steps to Christ, chapter 6፣ pp. 49–55። “ያለፉትን ኃጢአቶችህን ማስተሰረይ አትችልም፤ ልብህን መለወጥና ራስህን ቅዱስ ማድረግ አትችልም። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን ሁሉ በክርስቶስ በኩል እንደሚያደርግልህ ቃል ገብቷል።“—Steps to Christ, p. 51። 1. ይቅርታ እና ሰላም እሁድ ፣ ሐምሌ 26 ሀ. እግዚአብሔር የሰጠን የይቅርታና የሰላም ድንቅ ተስፋ ምንድን ነው? 1ኛ ዮሐንስ 1፡9። “ህይወትዎ በስስት (በራስ-ወዳድነት) እና በኃጢአት የተሞላ መሆኑን ይመለከታሉ። በመሆኑም ይቅር ለመባል፣ ከበደል ለመንጻት እንዲሁም ነጻ ለመውጣት ይናፍቃሉ። ታዲያ ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት የመፍጠርና ዳግም በአምሳሉ የመቀረጽ እድል ያገኙ ዘንድ ምን ማድረግ ይችላሉ?“አጥብቀው የሚሹት ነገር ቢኖር ሰላም ማለትም ሰማያዊውን ይቅርታና ሰላም እንዲሁም የነፍስ ውስጥ ፍቅርን ነው። ይህን ነገር ገንዘብ ሊገዛው፣ አእምሮ (እውቀት) በጥረቱ የግሉ ሊያደርገው ወይም ጥበብ ሊያገኘው አይችልም ፤ በግል ጥረትዎ የራስዎ ለማድረግ ተስፋ ማድረግ አይችሉም። እግዚአብሔር ግን እነዚህን ነገሮች ‘ያለ ገንዘብ ያለ ዋጋም’ (ኢሳ. 55:1) በስጦታ መልክ ያበረከትልዎታል። በመሆኑም እጆችዎን ዘርግተው መቀበል እስከ ቻሉ ድረስ በእርግጥም የእርስዎ ናቸው። “—Steps to Christ, p. 49 ለ. መላውን ፍጡር ከእግዚአብሔር ጋር በሚስማማ አዲስ ሰውነት የሚቀይር ሌላ አስፈላጊ ቃል ኪዳን ምንድን ነው? ሕዝቅኤል 36:26። “ ኃጢአትዎን ተናዝዘዋል፣ ከልብዎም አርቀውታል። ራስዎን ለእግዚአብሔር ለመስጠት ወስነዋል። ከዚህ በኋላ ወደ እርሱ በመሄድ ኃጢአትዎን እንዲያጥብልዎና አዲስ ልብ እንዲሰጥዎ ይጠይቁት። ከዚያም በገባው የተስፋ ቃል መሠረት የጠየቁትን እንደተቀበሉ ይመኑ። እግዚአብሔር ቃል የገባልንን ስጦታ የራሳችን ለማድረግ፣ እንደተቀበልነው መቁጠር እንዳለብን የሱስ በምድር ላይ ሳለ ያስተምር የነበረው ትምህርት ነበር።”—ibid, p 49፣ 50 [Author’s italics.] 2. በክርስቶስ የሚገኝ ሕይወት ሰኞ ፣ ሐምሌ 27 ሀ. የሱስ በቤተስዳ የነበረውን ሽባ ምን እንዲያደርግ ነገረው፣ እናም ከዚህ ተሞክሮ ምን መማር እንችላለን? ዮሐንስ 5:1-9 “በቤተሳይዳ ወደ ነበረው ሽባ ሰው ታሪክ እንመለስ። ይህ በሥቃይ ላይ የነበረ ምስኪን አንዳችም የሚረዳው ሰው አልነበረውም፤ እንዲሁም ላለፉት 38 ዓመታት አንዴም እንኳ እግሮቹን ተጠቅሞባቸው አያውቅም። ነገር ግን የሱስ ‘ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ’ ሲል ተናገረው። ምናልባትም ይህ ህመም የደቆሰው ሰው ‘ጌታ ሆይ የምታድነኝ ከሆነ ለቃልህ እታዘዛለሁ’ ማለት ይችል ነበር። ምስኪኑ ሰው በዚህ ፋንታ ከክርስቶስ አንደበት በወጡት ቃላት በማመን ወዲያውኑ ማድረግ ያለበትን አደረገ። ለመራመድ ፈቃደኛ ሆነ ተራመደም። ክርስቶስ የተናገረውን ቃል ተከትሎ ተንቀሳቀስ፤ እግዚአብሔርም ኃይል ሰጠው። ከህመሙም ተፈወሰ።”—Steps to Christ, p. 50 [Author’s italics.]“የሱስ ስለ መለኮታዊ እርዳታ የሰጠው ማረጋገጫ አልነበረም። ሰውየው በመጠራጠር የመፈወስ ዕድሉን ሊያጣ ይችል ነበር። ነገር ግን የክርስቶስን ቃል በማመንና እምነቱንም በተግባር በመግለጹ ብርታትን አገኘ።“በዚያው ዓይነት እምነት እኛም መንፈሳዊ ፈውስ ማግኘት እንችላለን፡፡ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ህይወት ተቋርጠናል፡፡ ነፍሳችን ሰሏል (ሽባ ሆኖአል)፡፡ ሽባው ሰው መራመድ እንዳልቻለ ሁሉ እኛም በራሳችን ኃይል የተቀደሰ ሕይወት መኖር አንችልም፡፡ አቅመ ቢስ መሆናቸውን የሚገነዘቡና ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስማማቸውን ዓይነት ሕይወት የሚናፍቁ ብዙ ናቸው ፤ ነገር ግን ይህን ፍላጐታቸውን ለማግኘት የሚያደርጉት መፍጨርጨር ሁሉ ከንቱ ነው። ተስፋ በመቁረጥ፡- ‘እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?’ [ሮሜ 7:24] በማለት ይጮኻሉ፡፡ እነዚህ ተስፋ የቆረጡ ተፍጨርጫሪዎች ወደ ላይ ቀና ብለው ይመልከት። አዳኛችን በደሙ በገዛቸው ላይ ጐንበስ ብሎ በአንደበት ሊገለጽ በማይቻል ርኅራኄ «መዳን ትፈልጋለህን?» ይላል፣ በጤናና በሰላም እንድትነሳ ያዝሃል።”—The Desire of Ages, p. 203 ለ. ለኃጢአተኛው በክርስቶስ በኩል የተገባለት የተስፋ ቃል ምንድን ነው? 2ኛ ዜና መዋዕል 7:14፤ ሆሴዕ 14:4። “ላለፈው ኃጢአትዎ ስርየት ማግኘት ወይም በራስዎ ብርታት ልብዎን ማንጻት አይችሉም። ነገር ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል እነዚህን ሁሉ ያደርግልዎ ዘንድ ቃል ገብቶአል። በዚህ ተስፋ በማመን ኃጢአትዎን ይናዘዙ፤ እራስዎንም ለእግዚአብሔር ያስረክቡ። እርሱንም ለማገልገል ፈቃደኛ ይሁኑ። እርስዎ ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ፣ እግዚአብሔርም ቃል የገባውን ለእርስዎ ይፈጽማል። ይቅር እንደተባሉና እንደነጹ በማመን የተስፋው ቃል በእርስዎ ሕይወት እንደተፈጸመ ቢያምኑ፣ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን እምነትዎን እውን ያደርገዋል። ልክ የሱስ ለሽባው ሰው እንደተፈወሰ ባመነ ጊዜ የሚራመድበትን ኃይል እንደሰጠው፣ እርስዎም ይድናሉ።”“እንደዳኑ እስኪሰማዎት ድረስ አይጠባበቁ፤ ይልቁንም «አምናለሁ፤ ድኛለሁ፤ ይህንንም የምለው ስሜቴ መስክሮልኝ ሳይሆን እግዚአብሔር ቃል ስለገባልኝ ነው።› ይበሉ።”—Steps to Christ, p. 51 3. በተወደደው (በክርስቶስ) ተቀባይነት ማግኘት ማክሰኞ ፣ ሐምሌ 28 ሀ. የሱስን አዳኛችን አድርገን ስንቀበለው፣ ያለፉ ኃጢአቶች ምን ይሆናሉ? ሮሜ 3:24፣ 25፤ 5:1፣ 9፣ 10። “የሱስ «ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደተቀበላችሁት አድርጋችሁ እመኑ፣ ይሆንላችሁማል» (ማር. 11፡24) በማለት ይናገራል። ይህን ተስፋ ለመቀበል የተቀመጠ ቅድመ ሁኔታ ያለ ሲሆን ይኼውም በጸሎት የምንለምነው ነገር ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የተስማማ እንደሆነ ነው። ነገር ግን ከኃጢአት አንጽቶ ልጆቹ ሊያደርገን፣ ቅዱስ ሕይወትም እንድንኖር ያስችለን ዘንድ ይህ እግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን በረከቶች መጠየቅና እንደተቀበልናቸው ማመን እንዲሁም ስለተደረገልን ነገር እግዚአብሔርን ማመስገን የእኛ ፋንታ ነው። ወደ የሱስ በመቅረብ ከኃጢአት እንድንነጻ እንዲሁም ያለ ጸጸት ወይም ሐዘን ከሕጉ ፊት እንቆም ዘንድ ዕድል ተሰጥቶናል።”—Steps to Christ, p. 51 [Author’s italics.] ለ. አማኙ በእግዚአብሔር ፊት ምን ዓይነት አቋም አለው? ሮሜ 8:1። “የክርስቲያን ሕይወት በባህርይው ትህትናን የተላበሰ ቢሆንም በሃዘንና ራስን በማቆርቆዝ የሚታወቅ መሆን የለበትም። እግዚአብሔር አዎንታ የሚሰጠውና የሚባርከው ሕይወት መኖር የሁሉም ሰው ዕድል ነው። በውግዘትና በጽልመት ውስጥ እንኖር ዘንድ የሰማዩ አባታችን ፈቃድ አይደለም። ጭንቅላቱን ዝቅ ከሚያደርግና (ከሚያቀረቅርና)፣ ልቡ በራስ ሃሳብ ከተሞላ ጋር እውነተኛ ትህትና አብሮ ስለመሄዱ የሚያረጋግጥ መረጃ የለም። ወደ የሱስ ሄደን እንነፃለን፣ በሕጉ ፊትም ያለ ሃፍረትና ያለ ፀፀት መቆም እንችላለን።”—The Great Controversy, p. 477“ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፈን ስንሰጥ እና በሙሉ ልባችን ስናምን የክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻል፡፡ ሕሊና ከኩነኔ ነጻ መሆን ይችላል፡፡ በደሙ በማመን፣ በክርስቶስ የሱስ ሁሉም ፍጹም መሆን ይችላሉ፡፡ እየተናገርን ያለነው ስለማይቻል ነገር ስላልሆነ እግዚአብሔር ይመስገን። ቅድስናን ልናገኝ እንችላለን፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ልናገኝ እንችላለን፡፡ ክርስቶስና እግዚአብሔር ስለ እኛ ምን እንደሚያስቡ ሊያሳስበን አይገባም፣ ነገር ግን ሊያሳስበን የሚገባ ነገር ቢኖር የእኛ ምትክ ስለሆነው ክርስቶስ እግዚአብሔር ምን ያስባል የሚለው ነው፡፡ በውድ ልጁ ሆናችሁ ተቀባይነት አግኝታችኋል።”—Selected Messages, bk. 2, pp. 32፣ 33 ሐ. ከእግዚአብሔር ጋር ወደዚህ የቃል ኪዳን ግንኙነት የገቡ ሁሉ ምን ዓይነት ለውጥ ሊያሳዩ ይገባል? 1ኛ ጴጥሮስ 1:18፣ 19፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6:19፣ 20፤ ገላትያ 3:26። “ስለዚህ እናንተ የራሳችሁ አይደላችሁም፤ በዋጋ ተገዝታችኋልና። (1ኛ ጴጥ. 18-19)። እንዲህ እግዚአብሔርን በማመን ብቻ፤ መንፈስ ቅዱስ በልብዎ ውስጥ አዲስ ሕይወት እንዲወለድ አድርጓል። በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እንደተወለደ አዲስ ሕጻን ይቆጠራሉ። እግዚአብሔርም አንድያ ልጁን በሚወድበት ፍቅር እርስዎንም ይወድዎታል።”—Steps to Christ, p. 51፣ 52 4. ከክርስቶስ ጋር መራመድ ረቡዕ ፣ ሐምሌ 29 ሀ. አማኝ ራሱን እንዴት መጠበቅ አለበት? ቆላስይስ 2፡6። “ራስዎን ለየሱስ ከሰጡ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ ወይም ራስዎን ከእርሱ መነጠል የለብዎትም። ይልቁንም በየቀኑ «እኔ የክርስቶስ ነኝ፤ ራሴን ለእርሱ አሳልፌ ሰጥቼዋለሁ» በማለት እርሱ መንፈሱን እንዲሰጥዎና በጸጋው ይጠብቅዎ ዘንድ ይጠይቁት። የእግዚአብሔር ልጅ የሆኑት ራስዎን ለእርሱ በመስጠትና በእርሱ በማመን እንደሆነ፣ በእርሱ መኖርንም መቀጠል ይኖርብዎታል። ሐዋርያው እንዲህ ይላል- «እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ የሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ» (ቆላ. 2፡6)።“አንዳንዶች «የእርሱን በረከት ከመጠየቃችን በፊት ሕይወታችን የተለወጠ መሆኑን ለእግዚአብሔር ለማሳየት ለተወሰነ ጊዜ ልንፈተሸ ይገባናል›› ብለው ያስባሉ። ነገር ግን የጌታን በረከት አሁኑኑ መጠየቅና የግላቸው ማድረግ ይችላሉ። ድካማቸውን ለማሸነፍ የእግዚአብሔር ጸጋና የክርስቶስም መንፈስ ያስፈልጋቸዋል። አልያ ግን ክፉን ማሸነፍ አይችሉም። የሱስ ከነኃጢአታችን፤ ረዳተቢስና ጥገኛ እንደሆንን፣ ባለንበት ሁኔታ ወደ እርሱ እንድንመጣ ይወዳል። ከነደካማነታችንና መተላለፋችን በንስሓ በእግሮቹ ሥር መውደቅ እንችላለን። እርሱም በፍቅር እጆቹ ያቅፈናል፤ ቁስላችንን ይጠርግልናል፤ ከእርኩስታችንም ሁሉ ያጠራናል፧ ይህንንም ማድረግ ለእርሱ ክብሩ ነው።”—Steps to Christ, p. 52. ለ. በመማር ሂደት ውስጥ ለሚፈጠሩ ስህተቶች ምን አይነት ዝግጅት (አቅርቦት) ተደርጓል? 1ኛ ዮሐንስ 2፡1፣ 2። “እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ለሌሎች እንጂ እርስዎን እንደማይጨምር አድርጎ የማስቡን ጥርጣሬ ያስወግዱ። ተስፋዎቹ የተሰጡት በንስሓ በፊቱ ለሚቀርቡ ተላላፊዎች (ኃጢአተኞች) ሁሉ ነውና! በክርስቶስ አማካኝነት ብርታትና ጸጋ በአገልጋይ መላእክቱ በኩል ለእያንዳንዱ አማኝ ነፍስ እንዲሰጡ ተደርጎአል። በመሆኑም በሞተለት በየሱስ በኩል ብርታትን፣ ንጽህናንና ጽድቅን ማግኘት የማይችል አንድም ኃጢአተኛ የለም። በኃጢአት የተበላሸውንና የተበከለውን ልብሳቸውን አውልቆ ነጩን የጽድቅ ሸማ ያለብሳቸው ዘንድ ይጠባበቃቸዋል። እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ ልመናውን የሚያቀርበው፡፡ ”—Ibid., pp. 52, 53. ሐ. በዚህ ጉዞ እንዴት እንደተጠናከርን አብራራ። 1ኛ ዮሐንስ 1:7፤ ገላትያ 5:16፣ 17፣ 25። “ በጥበብ መንገድ የሚሄዱ በመከራ ውስጥ እንኳን እጅግ ደስተኞች ናቸው፤ ምክንያቱም ነፍሳቸው የምትወደው እርሱ በዓይን ባይታይም ከጎናቸው ነውና። ወደ ላይ በሚወጡበት በእያንዳንዱ እርምጃ ደጋፊ እጁን በግልፅ ያስተውላሉ፤ በእያንዳንዱ እርምጃ፣ ከማይታየው (ሥፍራ) የክብር ብልጭታዎች (ብርሐናት) በመንገዳቸው ላይ ይታያሉ፤ የምስጋና መዝሙሮቻቸውም እጅግ ከፍ ወዳለው የጥዑመ-ዜማ ከፍታ በመውጣት፣ በዙፋኑ ፊት ከሚዘምሩት ከመላእክት መዝሙሮች ጋር ይቀላቀላሉ።”—Thoughts from the Mount of Blessing, p 140 5. የአባት የሚቤዥ ፍቅር ሐሙስ ፣ ሐምሌ 30 ሀ. በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው? ኢሳይያስ 55:7፤ 44:22። “ሰብአዊ ፍጡራን አንዳቸው ሌላቸውን በሚያስተናግዱበት አይነት መንገድ እግዚአብሔር እኛን አያስተናግደንም። የእርሱ አሳብ የምህረት፤ የፍቅርና በርህራሄ የተሞላ አሳብ ነው።”—Steps to Christ, p. 53.“እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ተግሣጽ ነፍሱን በኑዛዜና በንስሐ የሚያዋርድ ሁሉ፣ ተስፋ እንዳለው እርግጠኛ መሆን ይችላል። የእግዚአብሔርን ተስፋ በእምነት የሚቀበል ሁሉ ይቅርታን ያገኛል። ጌታ በእውነት የተጸጸተች ነፍስን ፈጽሞ አይጥልም።”—Patriarchs and Prophets, p. 726. ለ. ሰማያዊ አባታችን ስለጠፉት ሁሉ ያለው እውነተኛ አመለካከት ምንድን ነው? ሕዝቅኤል 18:32፤ ሉቃስ 15: 18–20። “ሰይጣን ከእግዚአብሔር የተሰጠንን የተረጋገጠ በረከት ለመስረቅ ዝግጁ ነው። እርሱ እያንዳንዱን የተስፋ ጭላንጭልና የብርሃን ጨረር ከነፍሳችን ሊወስድ ይመኛል። በመሆኑም ይህ ምኞቱ እውን ይሆን ዘንድ ልንፈቅድለት አይገባም። ጆሮችዎን ለፈታኙ በመስጠት ፋንታ እንዲህ ይበሉት «እኔ ህያው እሆን ዘንድ የሱስ ሞተልኝ! ይወደኛል፣ እንድጠፋ የእርሱ ምኞት አይደለም። . . . «ነገር ግን እርሱ ገና ሩቅ ሳለ፤ አባቱ አይቶት ራራለት ወደ እርሱም እየሮጠ ሄዶ አቅፎ ሳመው» [ሉቃስ. 15:18-20]። ይህ ተምሳሌት ተቅበዝብዞ የነበረው ልጅ እንዴት ተቀባይነት እንዳገኘ ያወሳል።“ይህ ልብ የሚነካ ምሳሌ እንኳ የሰማያዊውን አባት ወደር የለሽ ርኅራኄ ለመግለጽ ብቁ አይደለም። ጌታ በነቢያቱ አማካኝነት «በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህም በርኅራኄ ሳብሁሽ› (ኤር. 31:3) በማለት ይናገራል። የጠፋው ልጅ ከአባቱ ቤት ርቆ በባዕድ አገር የነበረውን ሁሉ ያባክን በነበ ረበት ጊዜ የአባቱ ልብ እርሱን ይናፍቅ ነበር። ይህ የአባቱ መናፈቅ ልጁ ወደ እግዚአብሔር ይመለስ ዘንድ ነፍሱን ያነቃ፣ ያባብል እንዲሁም በፍቅርወደ ተሞላው የአባቱ ልብ ይስበው ነበር።”—Steps to Christ, p. 53፣ 54 [Author’s italics.] የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ፣ ነሐሴ 01 1. ኃጢአቷ ይቅር የተባለላት ነፍስ ውስጥ የሚገባው ምንድን ነው? 2. በቤተሳይዳ የነበረው ሽባ በድንገት መራመድ የቻለው ለምንድን ነው? 3. ክርስቶስን እንደ አዳኛችን ስንቀበል፣ የእኛስ ተስፋ ምንድን ነው? 4. ከክርስቶስ ጋር የድል ጉዞ ምስጢር ምንድን ነው? 5. በሰይጣን ክፋትና በአብ ቤዛዊ ፍቅር መካከል ያለውን ልዩነት ግለጽ ። << >>