ከየሱስ ጋር መራመድ << >> ሰንበት፣ ነሐሴ 30፣ 2018 10ኛ ትምህርት እግዚአብሔርን ማወቅ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ጥበበኛ የሆነና ይህን የሚጠብቅ ማን ነው? እርሱ የእግዚአብሔርን ምሕረት ያስተውላል።“ (መዝሙር 107፡43)። ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ ፡ Steps to Christ, chapter 10 ፣ pp. 85–91። “የእውነተኛ እውቀትና የእውነተኛ እድገት ሁሉ ምንጭ እግዚአብሔርን በማውቅ ውስጥ አለ።”—Education, p. 14. 1. እግዚአብሔር ራሱን ይገልጣል እሁድ ፣ ነሐሴ 24 ሀ. ጌታ ሰዎችን ወደ ራሱ ለመሳብ የሚፈልገው በዚህ ዓለም ውስጥ ባሉ በምን ነገሮች በኩል ነው? መዝሙር 19:1-6 ፤ ምሳሌ 2:1-5 “ እግዚአብሔር ለእኛ ራሱን ለማስተዋወቅና ከእርሱ ጋር ሕብረት እንዲኖረን የሚጠቀምባቸው መንገዶች ብዙ ናቸው። ተፈጥሮ ያለማቋረጥ ለሕሊናችን እግዚአብሔር መኖሩን ይነግረናል። ልቡን ከፍቶ ያስተዋለ ሰው ሁሉ በእጁ ስራ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፍቅርና ክብር በማየት ይደነቃል። ጆሮውን ከፍቶ ያዳመጠ ሰው ሁሉ ደግሞ እግዚአብሔር በተፈጥሮ አማካኝነት ሊያስተላልፍ የፈለገውን መልዕክት ለመስማትና ለማስተዋል ይችላል። የለመለሙት መስኮች፣ ረዣዥም ዛፎች፣ ቡቃያዎች፣ አበቦች፣ የሰማይ ደመናዎች፣ የሚዘንቡት ዝናቦች፣ ፈሳሽ ውሃዎች እና በሰማይ ያሉ ፍጥረቶች ሁሉ ለልቦቻችን መልዕክትን ያስተላልፋሉ። እነዚህ ሁሉ እኛን ከፈጣሪ ጋር ለማስተዋወቅ ይጋብዙናል።”—Steps to Christ, p. 85። ለ. የሱስ እውነትን በአድማጮቹ አእምሮ ውስጥ ለማስቀመጥ ምን ተጠቀመ? ማቴዎስ 13:3፣ 34። “ አዳኛችን ጠቃሚና ክቡር ትምህርቶቹን በፈጠረው ፍጥረት ውስጥ አስቀመጠ። በሥራ ብዛት የተወጠረውን ማንኛውም ሰው እንኳን ቢሆን የእግዚአብሔርን ትምህርት ሁልጊዜ ማስታወስ እንዲችል ብሎ የእውነትን ቃል ከዛፎች፣ ከወፎች፣ በሸለቆ ውስጥ ካሉት አበባዎች፣ ከኮረብታዎች፣ ከባሕሮች፣ ከኩሬዎች፣ ከሚያምሩት ሰማያት እንዲሁም በዙሪያችን ካሉት በእግዚአብሔር ቃል ከተፈጠሩት ፍጥረቶች ሁሉ ጋር አያይዞታል።”“እግዚአብሔር ባማረ ውበት ያስጌጣትን ምድራዊ ቤታችንን በማየት ልጆቹ እንዲደሰቱና እንዲያደንቁ ይፈልጋል።”—ibid 2. የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራዎች ሰኞ ፣ ነሐሴ 25 ሀ. ከተፈጥሮ ምን ትምህርት ማግኘት ይቻላል - ለምሳሌ ከአበቦች፣ ከወፎችና ከከዋክብት? ሮሜ 1:20፤ የሐዋርያት ሥራ 14:17። “ በሳይንስ ጥናት… ስለ ፈጣሪ እውቀት ማግኘት አለብን። እውነተኛ ሳይንስ ሁሉ በቁሳዊው ዓለም ውስጥ የእግዚአብሔር የእጅ ጽሑፍ ትርጓሜ ብቻ ነው። ሳይንስ በጥናት የሚያመጣው የእግዚአብሔርን ጥበብና ኃይል የሚያሳዩ አዳዲስ ማስረጃዎችን ብቻ ነው። በትክክል ከተረዳነው የተፈጥሮ መጽሐፍም ሆነ የተጻፈው ቃል እርሱ የሚሠራባቸውን ጥበባዊና መልካም ሕጎችን በማስተማር ከእግዚአብሔር ጋር እንድንተዋወቅ ያደርጉናል።”—Patriarchs and Prophets, p. 599“በማስተዋል ካዳመጥን የእግዚአብሔር ፍጥረታት ስለመታዘዝና ስለመታመን ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶችን ይሰጡናል። ኮቴ በሌለው መንገዳቸው በሕዋው ውስጥ ከዘመናት እስከ ዘመናት በተመደበላቸው መንገድ ከሚጓዙት የሠማይ ከዋክብት ጀምሮ በጣም ትንሽ እስከሆነችው ነገር (አቶም) ድረስ ፍጥረት ለፈጣሪው ፈቃድ ይታዘዛል። እግዚአብሔር ለፈጠረው ሁሉ ያስባል፤ የሚያስፈልገውንም ሁሉ በሰዓቱ ይሰጠዋል።”—Steps to Christ, pp. 85፣ 86 ለ. ያልተበላሸውን የተፈጥሮ ውበትና ሰላም ስናስብ፣ ስለ ተስፋይቱ አዲስ ምድር ምን መታወስ አለበት? 1ኛ ቆሮንቶስ 2:9፤ ራዕይ 21:1። “በምናባችሁ የጻድቃንን መኖሪያ ሳሉት። ይህንን በምታደርጉበት ጊዜ የጻድቃን መኖሪያ ዓይነ-ህሊናችሁ ከሚገምተው (ምናባችሁ ከሚያስበው) በላይ እንደሆነ አስታውሱ። እግዚአብሔር በተፈጥሮ ውስጥ በሰጠን የተለያዩ ስጦታዎች ማየት የምንችለው እፁብ ድንቅ የሆነውን የክብሩን ብልጭታ ብቻ ነው።”— ibid, pp. 86፣ 87“ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የጅሆባ (የህያው እግዚአብሔር) ዘላለማዊ ዓላማ መገለጥ (ራዕይ) ተሰጥቷታል። የእርሱ ሕዝቦች ከአሁኑ ፈታኝ መከራዎች አሻግረው የወደፊቱን ድል እንዲመለከቱ ተፈቅዶላቸዋል ፤ ተጋድሎው (ጦርነቱ) ከተጠናቀቀ በኋላ የተዋጁት የተስፋይቱን ምድር ይወርሳሉ። እነዚህ የወደፊት ክብር ራእዮች፣ በእግዚአብሔር እጅ የተሳሉ ትዕይንቶች፣ ዛሬ ለቤተክርስቲያኑ እጅግ ውድ ህብቶች ሊሆኑ ይገባል።” —Prophets and Kings, p. 722.“የዳኑት ውርስ በመጽሐፍ ቅዱስ አገር ተብሎ ይጠራል [ዕብ 11÷14-16]። በዚያ ቦታ ሰማያዊው እረኛ መንጋውን ወደ ሕያው ምንጮች ይመራቸዋል። የሕይወት ዛፍ በየወሩ ፍሬ ትሰጣለች፤ ቅጠሎችዋም ለአሕዛብ አገልግሎት ይውላሉ። ሳያቋርጡ የሚፈሱ እንደ መስታወት ድንጋይ የነጹ ጅረቶች፣ ባጠገባቸው ቅጠላቸውን የሚያውለበልቡ ጥላቸውን ለዳኑት ባዘጋጀው መንገድ ላይ የሚያሳርፉ ዛፎችም አሉ። ወደ ውብ ኮረብታማ ስፍራዎች የሚለወጡ የተነጣጠሉ ሜዳዎች አሉበት፤ የእግዚአብሔር ተራራዎችም ግዙፍ ከፍታቸውን (ጫፎቻቸውን) አምጥቀው ገዝፈው ይታያሉ። በነዚያ ፀጥታ በሰፈነባቸው ሜዳዎች በሕያው ምንጮች አፋፍ ለረዥም ጊዜ ተጓዥና ተቅበዝባዥ የነበሩት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ቤታቸውን ያገኛሉ።”—The Great Controversy, p. 675 3. የሰጭነቱ ምስክርነት ማክሰኞ ፣ ነሐሴ 26 ሀ. በተስፋ መቁረጥና በፈተና ጊዜ ሊያበረታቱን የሚችሉ ምን ውድ ትምህርቶችን ከነቢያት መማር ይቻላል? ያዕቆብ 5:17፤ ሮሜ 8:28፤ 1ኛ ዮሐንስ 5:14። “ ልባችንን ከፍተን ማስተዋል ከቻልን በሚያጋጥሙን የየዕለቱ ገጠመኞችና በአካባቢያችን በሚከስቱት ክስተቶች ጠቃሚ ትምህርቶችን ማግኘት እንችላለን። . . . በቃሉ ውስጥ የአበው፤ የነብያት እንዲሁም የሌሎች ቀደምት ቅዱሳን ታሪክ ተፅፎ እናነባለን። እነርሱም “እንደኛው ሰው ነበሩ›› (ያዕ. 5፡17)። እንደኛ ከተስፋ መቁረጥ ጋር የታገሉ፤ በፈተናም ውስጥ የወደቁ ነበሩ! ቢሆንም እንደገና ድፍረትን በማግኘት በእግዚአብሔር ፀጋ አማካኝነት አሸናፊዎች ሆኑ። በእነርሱ ምሳሌነት እኛም በጽድቅ ጎዳና በምንሮጠው ሩጫ መበረታትን እናገኛለን።”—Steps to Christ, pp. 87፣ 88። ለ. እግዚአብሔር ለተፈጥሮ በሙሉ የሚያስፈልጋቸውን የሚሰጥ ከሆነ፣ ለልጆቹስ ምን ያህል የበለጠ ይሰጣል? መዝሙር 107:43፤ 145:15፣ 16። “ተፈጥሮ እና ራሱን ለፍጡራኑ የገለጠበት መለኮታዊ መንገድ የእግዚአብሔርን ፍቅር ይመሰክራሉ። በሰማይ ያለው አባታችን የህይወት፣ የጥበብና የደስታ ምንጭ ነው። እስቲ አስደናቂና ውብ ወደሆነው ተፈጥሮ ይመልከቱ። ይኸው ወደር የማይገኝለት ተፈጥሮ ለሰብዓዊው ፍጡር ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ህይወት ላላቸው ፍጡራን እጅግ የተስማማና የደስታ ምንጭም መሆኑን ያስቡ። ምድርን ደስ የሚያሰኘው የፀሐይ ብርሃን እና መሬቱን የሚያረሰርሰው ዝናብ፣ ኮረብታው፣ ባሕሩና መስኩ ሁሉም በአንድነት ስለ ፈጣሪ ፍቅር ይናገራሉ።”—Ibid., p. 9. ሐ. እግዚአብሔር እንደሚንከባከበን (እንደሚጠነቀቅልን) የገባልን የተስፋ ቃል በምን ላይ እንድናተኩር ሊያደርገን ይገባል? ማቴዎስ 6: 30-34። “ልንሰራቸው የሚገቡንን ነገሮችን የማስተዳደሩን (የመፈፀሙን) ኃላፊነት በገዛእጃችን ወስደን፣ ለስኬት በራሳችን ጥበብ በምንታመንበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ያልሰጠንን ሸክም በራሳችን ላይ እየተሸከመንና ያለእርሱ እርዳታም ለማከናወን እየጣርን ነው ማለት ነው፡፡ ይህን በማድረግ የእግዚአብሔር የሆነውን ኃላፊነት በራሳችን ላይ ተሸከምን ማለት ነው ፤ በዚህም ምክንያት ራሳችንን በእውነት በእርሱ ቦታ እያስቀመጥን ነው ማለት ነው። እንዲህ ስናደርግ ጭንቀት ይደርስብንና አደጋንና ኪሳራን ልንጠብቅ እንችላለን፣ ምክንያቱም ይህ እንደሚደርስብን የተረጋገጠ ነገር ነውና። ነገር ግን እግዚአብሔር እንደሚወደን እና (ለህይወታችን የሚያሻንን) መልካም እንደሚያደርግልን በእውነት ስናምን ስለወደፊቱ ጊዜ መጨነቅ ማቆም አለብን። ልጅ አፍቃሪ ወላጁን እንደሚታመን እኛም በእግዚአብሔር ላይ መተማመን ይኖርብናል። ከዚያም ጭቀቶቻችን (ችግሮቻችን) እና ስቃዮቻችን ይጠፋሉ ፤ ምክንያቱም ፈቃዳችን በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ይዋጣልና።”—Thoughts from the Mount of Blessing, pp. 100፣ 101 4. የእግዚአብሔር መገለጥ ረቡዕ ፣ ነሐሴ 27 ሀ. ክርስቶስ ስለሰዎች መዳንን በተመለከተ የእግዚአብሔርን ዕቅድ ግልጽ የሆኑ መገለጦችን ያስቀመጠው የት ነው? ዮሐንስ 5:39፤ ኢሳይያስ 34:16። “እግዚአብሔር በቃሉ አማካኝነትም ይናገረናል። ስለ ባሕርይውም፣ ለእኛ ስላለው ዓላማ እና የጠፋውን ሰው ለማዳን ስላላው እቅድ ቃሉ የበለጠ ግልፅ በሆነ መንገድ ይነግረናል።”—Steps to Christ, p. 87። ለ. በእግዚአብሔር ብርታትና ኃይል ለማደግ የሚፈልጉ ሁሉ በየቀኑ ምን ማድረግ አለባቸው? ዮሐንስ 6:53፣ 63፤ ቆላስይስ 3:1፣ 2። “ኃጢአተኛውን ሰው በመቤዠት እግዚአብሔር የሰራው ሥራ መላእክት በጥልቅ ሊመረምሩት የሚመኙት ርዕስ ነው። ይህ የድነት ሚስጢር የዳኑት ፃድቃን ለዘለዓለም የሚመረምሩት ሳይንስ እንዲሁም የውዳሴ መዝሙራቸው ዋና ርዕስ ይሆናል። ታዲያ ይህንን ጠቃሚ ርዕስ ዛሬውኑ በሰፊው ልናጠናው አይገባምን? ወደር የለሹ የየሱስ ምህረትና ፍቅሩ በእኛ ፈንታ የከፈለው መስዋትነት፣ ስለዚህ አስፈላጊ ጉዳይ በደንብ እንድናስብበት ጥሪ ያቀርቡልናል። አዕምሮአችንና ኃሳባችን ሁሉ ስለአዳኞችን እና ስለአማላጃችን ባሕርይ እንዲሁም ሕዝቡን ከኃጢአት ለማዳን ስለመምጣቱ ዓላማ ማሰብና ማሰላሰል አለበት።”—ibid, pp. 88፣ 89 ሐ. የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ልባችን እንዴት ማስገባት አለብን? ማቴዎስ 4:4፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2:15። “ትምህርቱን በአድናቆት የሚቀበል መንፈስ ያለው ማናቸውም ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚያነብበት ጊዜ አንዲት ገጽ እንኳ ብትሆን ጠቃሚ ሀሳቦች ሳያገኝ አያልፍም፡፡ ነገር ግን ዋናው ጥቅም የሚገኘው አልፎ አልፎ በሚደረግና ባልተያያዘ ጥናት አይደለም፡፡ ታላቁ የእውነት ሥርዓት ችኩልና ግዴየለሽ በሆነ አንባቢ አማካይነት የሚሰጥ አይደለም፡፡ ብዙዎቹ የወርቅ መዝገቦች ከላይኛው የመሬት ልባስ ሥር በጣም ጠለቅ ብለው ነው የሚገኙት። ሊደርስባቸው የሚችሉትም ትጋት በተሞላበት ምርምርና ባልተቋረጠ ጥረት ነው፡፡ በታላቁ ጥቅል ውስጥ የሚካተቱ እውነቶች ተፈልገው መሰብሰብ አለባቸው፡፡ «ከዚህም ጥቂት ከዚያም ጥቂት፡፡» ኢሳ 28፡10“እንግዲህና እንዲያ እየተፈለጉ ሲሰበሰቡ፣ አንደኛው ከሌላው ጋር በትክክል ተስማምቶ ግጥምጥም ይላል፡፡ እያንዳንዱ ወንጌል የሌሎቹ ደጋፊ፣ እያንዳንዱ ትንቢት የሌላው መግለጫና ማብራሪያ፣ እያንዳንዱ እውነት ለሌሎች እውነቶች እድገት መነሻ (መግለጫ) ይሆናል፡፡ የአይሁዶች የኢኮኖሚ ጥላው (ዓይነቱ) በወንጌል ውስጥ ተብራርቷል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እያንዳንዱ መሠታዊ ሀሳብ የራሷ ቦታ አላት፡፡ እያንዳንዷ እውቀትም የራሷ የሆነ ፍሬ አላት፡፡ በንድፍና በአፈፃፀም ላይ ያለው የተሟላ ቅርጽ ባለቤት ለሆነው ደራሲ ምስክርነት ይሰጣሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ግሩም ድንቅ ቅርጽ ፈልፍሎ ሊያንጸው የሚችለው የሰው አእምሮ ሳይሆን ወሰን የሌለበት አምላክ ብቻ ነው።”—Education, pp. 123፣ 124 5. የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሐሙስ ፣ ነሐሴ 28 ሀ. በከባድ የጭንቅ ጊዜው፣ ለኤርምያስ መጽናኛና እርዳታ ያመጣለት ነገር ምንድን ነው? ኤርምያስ 15:16። “መጽሐፍ ቅዱስን እንደማጥናት የአእምሮን የማገናዘብ ችሎታ የሚያጠነክር ሌላ ነገር የለም። አሳባችንን ከፍ የሚያደርግ እንደ እግዚአብሔር ቃል ያለ ሰፊና የከበሩ እውነቶችን የያዘ ሌላ መጽሐፍ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚገባ ተጠንቶ ቢሆን ኖሮ በዚህ ዘመን ብርቅ የሆኑትን የአእምሮ መስፋት፣ የባሕርይ ክቡርነትንና የዓላማ ጽናትን ሰዎች መቀዳጀት በቻሉ ነበር።”—Steps to Christ, p. 90“ቅዱሳት መጻሕፍትን በጸሎት በታላቅ ትኩረት የሚያነብ ሰው፣ ወደ እግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ እንዳገኘ ያህል ግልጽ የሆነ ግንዛቤና ትክክለኛ ፍርድ ያገኛል።”—Mind, Character, and Personality, vol. 1, p. 95. ለ. ቅዱሳት ጽሑፎችን እንዴት ማጥናት አለብን እና እንደዚህ አይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከመጀመሩ በፊት ምን መቅደም አለበት? መዝሙር 119:9፣ 11፣ 16። “ የእግዚአብሔር እውነት፣ ልክ እንደ ወርቅ፣ ሁልጊዜም በግልጽ ቦታ የተቀመጠ አይደለም፤ የሚገኘው ከልብ በማሰብና በማጥናት ብቻ ነው።”—Gospel Workers, pp. 76“ልክ አንድ ማዕድን ቆፋሪ በከርስ ምድር ውስጥ የሚገኘውን የከበረ ድንጋይ በጥልቀት ቆፍሮ እንደሚያወጣ፣ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተደበቁትን እንቁዎች ለማግኘት ተግቶ የሚፈልግ ማንም ሰው ለሕይወቱ እጅግ ጠቃሚ እውነቶችን ያገኛል። ላይ ላዩን ለሚያነብ ሰው ግን እነዚህ እውነቶች አይታዩትም። ወደ ልባችን የምናስገባቸውና የምናስቀምጣቸው የእግዚአብሔር ቃሎች ከሕይወት ፏፏቴ እንደሚፈስ ምንጭ ይሆኑልናል።”“ መጽሐፍ ቅዱስን በምንም ዓይነት ያለፀሎት ማጥናት የለብንም። ገፆቹን ከመግለጣችንና ከማንበባችን በፊት መንፈስ ቅዱስ ቃሉን እንዲገልጥልንና እንድናስተውል እንዲረዳን ልንጠይቀው ይገባል። ይገልጥልናል። … ዛሬም የሱስ የእውነትን ብርሃን ለማግኘት በስውር ሆነን ወደ እርሱ ስንፀልይ እያንዳንዳችንን ያየናል። ቅዱሳን መላዕክት እራሳቸውን ዝቅ አድርገው በትህትና የእግዚአብሔርን አመራር ከሚሹ ሁሉ ጋር ይሆናሉ።”—Steps to Christ, p. 91 የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ፣ ነሐሴ 29 1. አዳኛችን ሕዝብን ለመድረስ ምን ዓይነት የማስተማሪያ ዘዴ ተጠቅሟል? 2. እግዚአብሔር ራሱን ለሁሉም - ቃሉን ማግኘት ለማይችሉ ሰዎች ጭምር - ለመግለጥ ምን ዝግጅት አድርጓል? 3. ከእግዚአብሔር መለኮታዊ መመሪያ ምን መማር ይቻላል? 4. መጽሐፍ ቅዱስን እንደ እግዚአብሔር መገለጥ አድርገን ልንይዘው የሚገባንን አመለካከት ግለጽ። 5. ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር በተያያዘ መድገም ያለብን የኤርምያስ ተሞክሮ የትኛው ነው? << >>