Back to top

Sabbath Bible Lessons

ከየሱስ ጋር መራመድ

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሐምሌ 04፣ 2018 2ኛ ትምህርት
የሱስ ለኃጢአተኛው ስለማስፈለጉ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “የሱስም መልሶ። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።“ (ዮሐንስ 3፡3)።
ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ ፡   Steps to Christ, chapter 2፣ pp. 17–22 
“ ለወደቀው ለሰው ዘር የመዳን ተስፋ በክርስቶስ ብቻ ነው።”—The Desire of Ages, p. 147

1. የመጀመሪያው የሰው ሁኔታ እሁድ ፣ ሰኔ 28
ሀ. የሰው ልጅ በኤደን የነበረውን የመጀመሪያ ሁኔታ ግለጽ። ዘፍጥረት 1:26፣ 27፣ 31፤ መዝሙር 8:4–6 “ሰው በመጀመሪያ ከፍ ያለ ማዕረግና ችሎታ እንዲሁም ሚዛኑን የጠበቶ አስተሳስባዊ ውበት ነበረው። ሰው በፍጡርነቱም ሆነ ከእግዚአብሔርጋር በነበረው ኅብረት ፍጹም ነበር።”—Steps to Christ, p. 17“ሰው በመልኩና በጸባዩ በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጠረ፡፡ ክርስቶስ ብቻ “የእግዚአብሔር ነጸብራቅ” ነው (ዕብ. 1፡3)፡፡ ሰው ግን በእግዚአብሔር አምሳያ ተፈጠረ፡፡ ተፈጥሮውም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ስምሙ ነው፡፡ አእምሮው መለኮታዊ ነገሮችን ለመረዳት ይችላል፡፡ ስሜቶቹ ንጹህ ነበሩ ፍላጎቱም በዓላማው ቁጥጥር ስር ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን አምሳል በመልበሱ ቅዱስና ደስተኛ፣ለአምላካዊውም ፈቃድ ፍጹም ታዛዥ ነበር።”—Patriarchs and Prophets, p. 45 ለ. በሰው ልጅ አፈጣጠር ውስጥ የነበረውን መለኮታዊ ዕቅድን ለማክሸፍ ሰይጣን እንዴት ሠራ? ዘፍጥረት 3:1 - 7፤ ሮሜ 6:16፤ 1ኛ ዮሐንስ 2:16 “በአለመታዘዝ ጥንት የነበረውን ችሎታ አጣ፣ እራስ ወዳድነት በፍቅር ቦታ ተተካ። ሰብዓዊው ተፈጥሮ የተስጠውን ትእዛዝ በመተላለፉ ደካማ ሆነ። ይህን ተከትሎም በራሱ ብርታትና ጥንካሬ ክፉውን መቋቋም የማይችል ሆነ። ሰው በሰይጣን ግዞት ስር ወደቀ። እግዚአብሔር በተለየ መልኩ ጣልቃ ባይገባ ኖሮ ለዘላለም በዚህ ሁኔታ በቀጠለ ነበር። ፈጣሪ ለሰዎች የነበረውን መለኮታዊ ዕቅድ ማሰናከል፣ ምድርን በሥቃይና መከራ መሙላት የፈታኙ ዓላማ ነበር። ይህ ሥቃይና መከራ እግዚአብሔር ሰው መፍጠሩን ተከትሎ የመጣ ውጤት እንደሆነም አድርጎ ያቀርባል።”—Steps to Christ, p. 17

2. ከእግዚአብሔር መገኘት መሸሽ ሰኞ ፣ ሰኔ 29
ሀ. አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሠሩ በኋላ የእግዚአብሔርን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ምን ምላሽ ሰጡ? ዘፍጥረት 3:8-10 ለ. ኃጢአተኛ የሰው ልጆች፣ በወሰን አልባው አምላክ ፊት መቆም የማይችሉት ለምንድን ነው? ዘጸአት 33:20፤ ዘዳግም 4:23፣ 24 “ሰው በኃጢአት ከመውደቁ አስቀድሞ «የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት ሐብት ሁሉ… በእርሱ ዘንድ... ” (ቆላስያስ. 2:-3) ከሆነው ከአምላኩ ጋር በደስታ የተሞላ ግንኙነት ነበረው። ነገር ግን ኃጢአት ከሠራ በኋላ በቅድስናው ያገኝ የነበረውን ደስታ አጣ፤ ይህን ተከትሎም ከእግዚአብሔር ፊት መደበቅ ፍላጎቱ ሆነ። ይህ ሁናቴ ዛሬም ዳግም ባልተወለደ ልብ ውስጥ ይስተዋላል። እንዲህ ዓይነቱ ልብ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ስለሌለው ከእርሱ ጋር አንድነት በመፍጠር ደስታ አያገኝም። ኃጢአተኛው እግዚአብሔር ባለበት ቦታ በመገኘቱ አይደሰትም፤ ከቅዱሳን ጋር ሕብረት ከማድረግ ይሸሻል። ይህ ሰው ሰማይ እንዲገባ ቢፈቀድለት እንኳ ሰማይ አስደሳች ስፍራ ሊሆንለት አይችልም። ከክርስቶስ ጋር በሰማይ የሚነግሠው እያንዳንዱ እራስ ወዳድነት ያልተጠናወተው አፍቃሪ ልብ ፍጹም ከሆነው አምላክ ጋር ልብ ለልብ የተሳሰረ አንድነት ሲፈጥር፣ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የሌላት ልብ ግን ከፈጣሪዋ ጋር የሚያገናኛት መስመር በመበጠሱ ምላሽ መስጠትም ሆነ መቀበል አትችልም። የግለሰቡ አስተሳሰብም ሆነ ፍላጎት በዚያ ስፍራ ከሚኖሩ ጻድቃን ጋር የሚጻረር ይሆናል። ግሩም ጣዕም በተላበሰው በሰማያዊው ዜማ መሃል እርሱ ግን ምላሽ የማይሰጥ የተበጠስ የሙዚቃ ክር ይሆናል። ለእንዲህ ያለው ሰው ሰማይ የሥቃይ ስፍራ ይሆንበታል።”—Steps to Christ, p. 17፣ 18። ሐ. ለሰው ልጅ ከኃጢአት ቅጣት ማምለጥ የማይቻለው ለምንድን ነው? ኢዮብ 14:4ሮሜ 8:7፣ 8፤ ኢሳይያስ 64:6 “ከሰመጥንበት የኃጢአት አረንቋ በራሳችን አምልጠን መውጣት አንችልም። ልባችን በክፋት ተሞልቶአል ልንለውጠውም አንችልም። ለመሆኑ ”ከርኩስ ነገር ውስጥ ንጹህን ማን ሊያወጣ ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም!” (ኢዮብ. 14:4)።. . . ትምህርት፣ ባህል፣ መልካም ውሳኔ መወሰን ፣ የአእምሮን አቅም አሟጦ መጠቀም እንዲሁም ሰብዓዊው ጥረት እኚህ ሁሉ የራሳቸው አግባብና ጠቀሜታ ያላቸው ቢሆኑም ነገር ግን እዚህ ላይ አቅመቢስ ሆነው እናገኛቸዋለን። እነዚህ ነገሮች ምናልባት የታረመ ውጫዊ ባህሪ ማፍራት ቢችሉም ልብን መቀየር ግን አይሆንላቸውም፤ የህይወትን ምንጮች ሊያነጹ አይችሉም። ሰዎች ከኃጢአተኝነት ወደ ቅድስና ከመለወጣቸው አስቀድሞ፣ አዲስ ህይወት ሊሰጣቸው የሚችል ከላይ የተላከ ኃይል በውስጣቸው ሊሠራ የግድ ነው። ያ ኃይል ደግሞ ክርስቶስ ነው። የእርሱ ጸጋ ብቻውን ለደ ረቀችው ነፍስ የለመለመ ህይወት በመስጠት በቅድስና ወደ እግዚአብሔር ሊስባት ይችላል።”—Ibid., p. 18.

3. የአዳኝ አስፈላጊነት ማክሰኞ ፣ ሰኔ 30
ሀ. ስለ ሰው ልብ ምን መገንዘብ አለብን? መዝሙር 14:1-3ሮሜ 3:9-11 “እግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፣ ‘ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል’ (ሮሜ 3:23)። ‘መልካም የሚያደርግ የለም፤ አንድም እንኳ’ (ሮሜ 3:12)። ብዙዎች በልባቸው ሁኔታ ተታልለዋል። የተፈጥሮ ልብ ከሁሉ ይልቅ አታላይና ክፉ እንደሆነ አያውቁም። በራሳቸው ጽድቅ ተጀቡነው፤ ራሳቸው ባወጡት ሰብዓዊ የባሕርይ ደረጃ ላይ በመድረስ ይረካሉ፤ ነገር ግን መለኮታዊውን ደረጃ ሳይደርሱ ሲቀሩና የእግዚአብሔርንም መስፈርቶች በራሳቸው ማሟላት ሲሳናቸው ምን ያህል የወደቁ እንደሆኑ አያስተውሉም።”—Selected Messages, bk. 1, p. 320 ለ. እኛ በሰባአዊነታችን መንፈሳዊውን ዓለም መለየትና እግዚአብሔርን መንግሥት ማየት የማንችለው ለምንድን ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 2:14፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 4:4። “ማንም ከላይ «ካልተወለደ›፤ አዲስ ልብ፤ አዲስ መሻት፤ አዲስ ዓላማ ወይም አዲስ ተነሳሽነት ካልተቀበለ «በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም» (ዮሐ. 3:3) በማለት አዳኙ ተናግሮአል። «ሰው በተ ፈጥሮው የተላበሰውን መልካም ነገር ማጎልበት ብቻውን በቂ ነው» የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ለሞት የሚያደርስ ማታለያ መንገድ ነው። «መንፈሳዊ ያልሆነ ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የሆነውን ነገር ሊቀበል አይችልም፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ነገር ለእርሱ ሞኝነት ነው፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊረዳው አይችልም› (1ኛ ቆሮ. 2፡14)። “ዳግመኛ መወለድ አለባችሁ ስላልሁህ አትገረም“ (ዮሐ. 3:7)። ስለ ክርስቶስ እንደሚከተለው ተ ጽፎአል “ህይወት በእርሱ ነበረች፤ ይህች ህይወት የሰው ብርሃን ነበረች“ (ዮሒ. 1፡4)። “እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ አዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና“ (የሐዋሪያት ሥራ 4፡-12)።”—Steps to Christ, p. 18፣ 19። ሐ. ራሳችንን ማዳን ባንችልም፣ ምን ማድረግ እንችላለን? ማቴዎስ 11: 28–30፤ ዮሐንስ 3:3 “እግዚአብሔር ‹‹ዓለምን ከራሱ ጋ ሊያስታርቅ“ (2ኛ ቆሮ. 5፡19) በክርስቶስ ውስጥ መገለጽ ነበረበት፡፡ ሰው በኃጢአት እጅግ በመውረዱ ተፈጥሮው ቅዱስና መልካም ከሆነው አምላክ ጋር በራሱ ህብረት ለመፍጠር የሚቻለው አልነበረም፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ሰብዓዊውን ፍጡር ከሕጉ ኩነኔ ከዋጀው በኋላ መለኮታዊው ኃይል ከሰብዓዊው ፍጥረት ጋር ግንኙነት መፍጠር ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ በኃጢአት የወደቁት የአዳም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት በንስሐ በመቅረብና በክርስቶስ ላይ በሚኖራቸው እምነት ዳግመኛ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› (1ኛ ዮሐ. 3፡2) ይሆናሉ።”—Patriarchs and Prophets, p. 64

4. የኃጢአተኛው ተማጽዕኖ (ልመና) ረቡዕ ፣ ሐምሌ 01
ሀ. ሐዋርያው ጳውሎስ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኛ መሆኑን ሙሉ በሙሉ ሲያውቅ የነበረው ችግር ምን ነበር? ሮሜ 7:12፣ 14፣ 24. “የእግዚአብሔርን አፍቃሪነትና ደግነቱን፤ ርኅራኄውንና አባታዊ ጥንቃቄውን መገንዘብ ብቻውን በቂ አይደለም። እንዲሁም በዘላለማዊው የፍቅር መርኀ ላይ የተመሰረተውን አምላካዊውን ጥበብና የሕጉን ፍትሐዊነት መረዳት ብቻውን የትም አያደርስም። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን በማወቁ ነበር እንዲህ የተናገረው- “ሕጉ በጎ እንደሆነ እመሰክራለሁ» “ስለዚህ ሕጉ በራሱ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዙም ቅዱስ፣ ጻድቅና መልካም ነው“ (ሮሜ 7፡12)። ሐዋርያው ነፍሱን ዘልቆ ይሰማው ከነበረ ታላቅ ሥቃይና ተስፋ መቁረጥ በመነሳት «እኔ ግን ለኃጢአት እንደ ባሪያ የተሸጥኩ ሥጋዊ ነኝ› (ሮሜ 7:16፣ 12፣ 14) በማለት ጨምሮ ይናገራል። ሐዋርያው ሊደርስበት ያልቻለውን ንጽህናና ጽድቅ በመናፈቅ “እኔ ምን ዓይነት ጎስቋላ ሰው ነኝ! ከዚህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ሊያድነኝ ይችላል?“ (ሮሜ 7:24) በማለት ሲጮኽ ይደመጣል። እንዲህ ያለው ለቅሶ በዘመናት ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ኃጢአት ከተጫናቸው ልቦች ወደ ሰማይ ሲተም ኖሮአል። ለእነዚህ ወገኖች መልሱ አንድ ሲሆን ይኸውም “እነሆ! የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ“ (ዮሐ. 1:29) የተሰኘ ነው።”—Steps to Christ, p. 19“እቅመ ቢስ መሆናቸውን የሚገነዘቡና ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስማማቸውን ዓይነት ሕይወት የሚናፍቁ ብዙ ሲሆኑ ይህን ፍላጐታቸውን ለማግኘት ግን የሚያደርጉት መፍጨርጨርሁሉ ከንቱ ነው። . . . አዳኛችን በደሙ በገዛቸው ላይ ጐንበስ ብሎ በአንደበት ሊገለጽ በማይቻል ርኅራኄ “መዳን ትፈልጋለህን?“ ይላል፣ በጤናና በሰላም እንድትነሳ ያዝሃል።”—The Desire of Ages, p. 203 ለ. ያዕቆብ ከወንድሙ ከዔሳው በሸሸ ጊዜ እግዚአብሔር እንደማይተወው በምን መንገድ አረጋግጦለታል? ዘፍጥረት 28: 10-13። “[ያዕቆብ] ከሌሎች የተገለለ ዓይነት ስሜት ሲሰማው ይህ ሁሉ ችግር ሊደርስበት የቻለው እራሱ በተከለተው የተሳሳተ መንገድ እንደሆነ ያውቅ ነበር፡፡ የተስፋ መቁረጥ ጨለማ በነፍሱ ላይ ሲያንዣብብ ለመፀለይ እንኳን ድፍረት አልነበረውም። ብቸኝነቱ እጅግ ስለበረታበት ከዚህ በፊት ተሰምቶት የማያውቅ የእግዚአብሔር ጥበቃ አስፈለገው፡፡ በልቅሶ እና በጥልቅ ኃፍረት ተሞልቶ ኃጢአቱን ተናዘዘ፣ ለዘላለሙ ያልተተወ ለመሆኑ ምልክት እንዲያሳየው እግዚአብሔርን ለመነ፡፡ ነገር ግን ሸክም የበዛባት ልቡ ምንም እረፍት አላገኘችም፡፡ በራሱ ላይ እምነት አጥቷል፡፡ የአባቶቹ አምላክ እግዚአብሔር ደግሞ እንዳገለለው ፍርሃት ተሰምቶታል፡፡ እግዚአብሔር ግን ያዕቆብን አልተወውም፡፡ ምኅረቱ ስህተት ለፈጸመው እና ታማኝ ላልሆነው አገልጋዩ ደረሰው፡፡ ጌታ ለያዕቆብ በትክክል ምን እንደሚያስፈልገው የገለጸለት ሲሆን ይኸውም --አዳኙን ነበር፡፡ ኃጢአት የሠራ ቢሆንም ዳግመኛ በአምላካዊው ምኅረት መከለሉ ሲገለጽለት ልቡ በምስጋና ተሞላ።”—Patriarchs and Prophets, p. 183

5. ሰማይንና ምድርን ማገናኘት ሐሙስ ፣ ሐምሌ 02
ሀ. ያዕቆብ በምድረ በዳ ካየው መሰላል ምን ትምህርት ማግኘት ይቻላል? ዘፍጥረት 28:16፣ 17፤ ዮሐንስ 1:51 “ ለያዕቆብ የደኅንነት እቅድ የተገለጸለት ሲሆን ይህም ሙሉ ለሙሉ ሳይሆን ነገር ግን በወቅቱ ለእርሱ አስፈላጊ የሆነውን ያህል ነበር፡፡ በህልሙ ያየው ምስጢራዊ መሰላል ክርስቶስ ከናትናኤል ጋር ሲነጋገር የጠቀሰው ዓይነት ነበር “ሰማይ ተከፍቶ፣ የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ” (ዮሐ.1፡51)፡፡ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ እስካመጸበት ጊዜ ድረስ በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል ነፃ የሆነ የሃሳብ እና የስሜት መጋራት ነበር፡፡ ነገር ግን አዳም እና ሔዋን የፈጸሙት ኃጢአት ምድርን ከሰማይ የነጠለው በመሆኑ የሰው ልጅ ከፈጣሪው ጋር የሚጋራው ነገር እንዳይኖር አድርጓል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ዓለም በተስፋ መቁረጥ ስሜት አልተተወችም፡፡ መሰላሉ የሱስን የሚወክል ሲሆን እርሱም የግንኙነቱ አመቻች ነበር፡፡ ኃጢአት የፈጠረውን ባህር በራሱ ድልድይ አማካኝነት ባያገናኘው ኖሮ አገልጋይ መላዕክቱ በኃጢአት ከወደቁ ሰዎች ጋር ምንም ዓይነት ነገር ባልተካፈሉ ነበር።”—Patriarchs and Prophets, p. 184 ለ. የክርስቶስ መካከለኛነት የመሠረተውን ግንኙነት ግለጽ። ሮሜ 3:23 - 26፤ ዕብራውያን 1:14 “ሰው በአምላኩ ላይ ክህደት በመፈጸም እራሱን ከእግዚአብሔር ነጠለ፤ ይህን ተከትሎም ምድርከሰማይ ተለያየች። በሰማይና በምድር መሃል ግዙፍ ሸለቆ ቢከሰትም ነገርግን በክርስቶስ አማካኝነት ምድር ዳግመኛ ከሰማይ ጋር ተገናኘች። ኃጢአት የፈጠረውን ሸለቆ ክርስቶስ አገናኘው። አገልጋዮች መላእክትም ከስዎች ጋርዳግመኛ ግንኙነት ሊኖራቸው ቻለ። ደካማና ረዳተቢስ የሆነውንና በኃጢአት የወደቀውን ሰው ክርስቶስ ከዘላለማዊው የኃይል ምንጭ ጋር አገናኘው። . . . ““በምድር ያሉትን ልጆቹን እግዚአብሔር የሚወድበት ፍቅር ከሞት የበረታ ፍቅር ነው። ልጁን ለእኛ መስዋእት እንዲሆን በመስጠት መላውን ሰማይ በአንድ ስጦታ አጠቃልሎ ሰጥቶናል። የአዳኙ ህይወት፣ ሞት፣ ትንሳኤና አማላጅነት፣ እንዲሁም የመላእክት አገልግሎት፣ የመንፈስ ቅዱስ ተማጽኖ፣ አብ ከላይ ሆኖ መሥራቱ እነዚህ ሁሉ የማያቋርጡ ሰማያዊ ጥረቶች በኃጢአት ለወደቀው ለሰው ልጅ ደኅንነት በአንድነት የሚሠሩ ናቸው።”—Steps to Christ, p. 20፣ 21።

የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ፣ ሐምሌ 03
1. ከውድቀት በፊት እና በኋላ የሰው ልጅን ሁኔታ አነጻጽር። 2. ከውድቀት በኋላ፣ ሰው ምን አደረገ እና ለምን? 3. ለኃጢአት ችግር ብቸኛው መልስ ምን ነበር? 4. ለያዕቆብ በሕልሙ የተሰጠውን ድንቅ ምልክት ትርጉምን አብራራ። 5. እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ምን አይነት የመገናኛ መንገድ ይጠቀማል?
 <<    >>