Back to top

Sabbath Bible Lessons

ከየሱስ ጋር መራመድ

 <<    >> 
ሰንበት፣ መስከረም 09፣ 2019 12ኛ ትምህርት
ጥርጣሬን ማሸነፍ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና።“ (ያዕቆብ 1፡6)።
ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ ፡   Steps to Christ, chapter 12 ፣ pp. 105–113 
“እግዚአብሔር እምነታችንን ለመመስረት የሚያስችል በቂ ማስረጃ ሳይሰጠን እንድናምን ፈጽሞ አይጠይቀንም።”—Steps to Christ, p. 105

1. ጥርጣሬ ምንድን ነው? እሁድ ፣ መስከረም 03
ሀ. በእምነትና በጥርጣሬ መካከል ለመወላወል ስንፈተን ምን ማስታወስ አለብን? ያዕቆብ 1:5-7 “ [የአዳኛችን] ቃልኪዳን የጌታን ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ለመከተል ፈቃደኛ ለሆኑ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ማንንም አያስገድድም፤ ስለዚህ ለመማር ክብራቸው የማይፈቅድላቸውን፣ እንዲሁም የራሳቸውን መንገድ በመፈለግ የሚባዝኑትን ሊመራቸው አይችልም። ሁለት አሳብ ያለው ሰው - እግዚአብሔርን ፈቃድ እንደሚፈጽም እየተናገረ፣ ግን የራሱን ፈቃድ ለመከተል የሚፈልግ - ‘ያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች ነገር እንደሚያገኝ አይምሰለው' ተብሎ ተጽፎአል። ’ ያዕቆብ 1፡7፡፡ ”—Patriarchs and Prophets, p. 384 ለ. ጥርጣሬን ለማሸነፍ ጌታ ምን ሰጥቷል? መዝሙር 119:105ዕብራውያን 11:1፣ 3፣ 6። “በዓይን የሚታይ ማረጋገጫ ባናገኝም እምነታችን በማስረጃዎች ላይ መመስረት አለበት። መጠራጠር የሚፈልጉ ሰዎች ሁልጊዜ አጋጣሚውን ያገኛሉ። በአንጻሩ ደግሞ እውነትን ለማወቅ ከልባቸው የሚመኙ ሰዎችም እምነታቸውን ለመመስረት በቂ ማስረጃ ያገኛሉ።”—Steps to Christ, p. 105.“ቃሉ መለኮታዊ ባህርይ ያለው ለመሆኑ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ በቂ ማስረጃ ሰጥቷል። ድነታችን የሚመለከቱት ታላላቅ እውነቶች በግልጽ ቀርበዋል። በእውነት ለሚፈልጉት ሁሉ እንደሚሰጥ ቃል በተገባው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እያንዳንዱ ሰው እነዚህን እውነቶች ለራሱ መረዳት ይችላል። እምነታቸውን ያሳርፉበት ዘንድ ጠንካራ መሰረት እግዚአብሔር ለሰዎች ሰጥቷቸዋል።”— The Great Controversy, p. 526፣ 527.

2. መለኮታዊ ምስጢሮች ሰኞ ፣ መስከረም 04
ሀ. እግዚአብሔር ያላብራራቸውን (ያልገለጣቸውን) ምስጢሮች እንዴት ልንይዛቸው ይገባል? ዘዳግም 29:29ኢዮብ 38:4–11 “ በመለኮታዊው ደራሲ የተጻፈው የእግዚአብሔር ቃል፣ ልክ እንደ ራሱ እንደ አምላክ ባህርይ፣ ውስን በሆኑት ፍጥረታት በሙላት ሊስተዋሉ የማይችሉ ሚስጢሮችን ይዞአል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት፤ የኃጢአት ወደ ዓለም መግባት፣ የክርስቶስ ስጋ መልበስ፣ የዳግም መወለድ፣ የትንሳኤ፣ እንዲሁም ሌሎች ብዙ ርእሶች ለሰብአዊ ፍጡር አእምሮ ለማስረዳትም ሆነ በሙላት ለማስተዋል የሚያዳግቱ ምስጢራት ናቸው። ሆኖም ግን የአሰራሩን ምስጢር ማስተዋል ስላልቻልን፤ የእግዚአብሔርን ቃል የምንጠራጠርበት ምክንያት ሊሆነን አይችልም።”—Steps to Christ, p. 106.“እግዚአብሔር ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ ለማድረግ አያስገድድም። በፊታቸው ብርሃንና ጨለማ፣ እውነትና ሐሰት ስላለላቸው የትኛውን እንደሚቀበሉ ውሳኔው የራሳቸው ነው። ሰብአዊ አእምሮ ትክክለኛውን ከስሕተቱ የመለየት ኃይል ተሰጥቶታል። ሰዎች በግብታዊ ስሜት ሳይሆን ከቅዱሳት መጻሕፍች አንዱን ጥቅስ ከሌላው ጋር በማመዛዘን በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲወስኑ የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው። አይሁዶች « ጥላቻቸውን አስወግደው ትንቢቶችን ከየሱስ ሕይወት ጋር ቢያመዛዝኑ ኖሮ ትንቢቶቹ በትሑቱ ገለሏዊ ሕይወትና አገልግሎት እንዴት በትክክል እንደተፈጸሙ ለመረዳት በቻሉ ነበር።”“ዛሬም ብዙ ሰዎች አይሁዶች በተሳሳቱበት አኳኋን ይሳሳታሉ። የኃይማኖት መምህራን በራሳቸው ባሕልና የመረዳት ስልት መጽሐፍ ቅዱስን ያነባሉ፣ ሕዝቡም ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብበው ስለ እውነት ራሳቸው ከመወሰን ፈንታ ነፍሳቸውን ለመሪዎቻቸው ያስረክባሉ። እግዚአብሔር እውነት በስብከትና በማስተማር እንዲሰራጭ ፈቅዶአል፣ ነገር ግን የእያንዳንዱን ሰው ትምህርት በቅዱሳት መጻሕፍት መፈተን እለብን።”—The Desire of Ages, p. 458, 459 ለ. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመረዳት የሚከብዱ ነገሮች እንዳሉ እንዴት ይታወቃል? 2ኛ ጴጥሮስ 3:16። “በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ለማስተዋል የሚቸግሩ ጥቅሶች፤ ቃሉን የማያምኑት መጽሐፍ ቅዱስን ለማጣጣል የሚጠቀሙባቸው ቢሆንም እነርሱ ግን የበለጠ በቃሉ ላይ መታመንን የሚጨምሩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር በቀላሉ የሚስተዋሉ ነገሮችን ብቻ ይዞ ቢሆን ኖሮ፤ የእግዚአብሔር ታላቅነት ግርማ ውስን በሆነው አእምሮአችን በቀላሉ ቢስተዋል ኖሮ፣ መጽሐፍ ቅዱስ መለኮታዊ ምንጭ ባልኖረው ነበር። የምስጢራት መኖር በራሱ በእግዚአብሔር ቃል ላይ እምነትን ሊጭርልን ይገባል።”—Steps to Christ, p. 107.

3. የማያምን ልብ ያለበት አደጋ ማክሰኞ ፣ መስከረም 05
ሀ. በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ለሚገኙ አማኞች ምን የተለየ አደጋ አለ? ዕብራውያን 3:122 ጢሞቴዎስ 4:3፣ 4። “እጅግ አስፈላጊ ከመሆናቸው የተነሳ በሰማይ መካከል በሚበሩ ቅዱሳን መላእክት እንዲወከሉ ያደረጋቸውን ማስጠንቀቂያዎች እግዚአብሔር ወደ ሰዎች ሲልክ የማመዛዘን ኃይል የተቸረው እያንዳንዱ ሰው መልእክቱን እንዲሰማ ይጠብቅበታል። ለአውሬውና ለምስሉ በሚሰግዱ ላይ የተነገሩት አስፈሪ ቅጣቶች [ራዕይ 14÷9-11] የአውሬው ምልክት ምን እንደሆነ ይማሩ ዘንድ፣ እርሱንም ላለመቀበል ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይገነዘቡ ዘንድ ሁሉንም ሰው ትንቢታትን በትጋት ወደ ማጥናት ሊመሩአቸው ይገባቸዋል። አብዛኛው ሕዝብ ግን እውነትን ከመስማት ጆሮውን ይመልሳል፣ ወደ ተረትም ዘወር ይላል። ወደ መጨረሻዎቹ ቀናት ሐዋርያው ጳውሎስ አቆልቁሎ ሲያይ እንዲህ ይላል፦ “ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣልና” [2ኛ ጢሞ 4÷3] እነሆ ያ ጊዜ ሙሉ በሙሉ ደርሶአል። የኃጢአተኛውን፣ የዓለም አፍቃሪውን ልብ መሻቶች ስለሚያውክ፣ እልፍ አዕላፋት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነቶች አይፈልጉም፤ ሰይጣንም የሚያፈቅሯቸውን ማታለያዎች ያቀርብላቸዋል።”—The Great Controversy, p. 594, 595. ለ. በመጨረሻው ዘመን ስለሚኖሩት የሁለቱ ክፍሎች አመለካከት ምን ትንቢት ተነግሯል? ዳንኤል 12:10፤ ራዕይ 22:11። “ነገር ግን የተሐድሶዎች ሁሉ መሰረት፣ የአስተምህሮዎች ሁሉ ደረጃ መለኪያ አድርጎ መጽሐፍ ቅዱስንና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ የሚጠብቅ ሕዝብ እግዚአብሔር በምድር ይኖረዋል። የምሁራን አስተያየቶች፣ የሳይንስ ድምዳሜዎች፣ እንደሚወክሏቸው አብያተ ክርስቲያናት በቁጥር በርካታ የሆኑትና የሚጋጩት የመንፈሳዊ ጉባኤ እምነቶችና ውሳኔዎች፣ የአብላጫ ድምጽ – እነዚህ ሁሉ፣ ማንኛቸውም ቢሆኑ አንድን ኃይማኖታዊ ጉዳይ ለመቀበልም ሆነ ላለመቀበል እንደመረጃ ሆነው ሊወሰዱ አይገባቸውም። ማንኛውንም አስተምህሮ ወይም መመሪያ ከመቀበላችን በፊት፣ ድጋፍ የሚሆነው፣ ግልጽ የሆነ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚል [ቃል] መጠየቅ ይገባናል።”—ibid, p 595.“ከጽድቅ ፀሐይ ጋር ህያው ግንኙነት ላለው ለዚያ ሰው፣ ከእግዚአብሔር ቃል አዲስ ብርሃን ሁልጊዜም ይገለጥለታል። ሊገለጥ የሚችል እውነት (ከእንግዲህ) የለም ብሎ ማንም ሰው መደምደሚያ ላይ አይድረስ። ተግቶ በመጸለይ እውነትን ለሚፈልግ ሰው ከእግዚአብሔር ቃል የሚያበሩትን የከበሩ የብርሃን ጨረሮችን ያገኛል። ለእግዚአብሔር ቅሬታ ሕዝብ ንብረት ይሆኑ ዘንድ መሰብሰብ ያለባቸው ብዙ እንቁዎች አሁንም በየቦታው ተበታትነዋል። ነገር ግን ብርሃን የሚሰጠው ለቤተክርስቲያን ብርታት እንዲሆን ብቻ ሳይሆን በጨለማ ውስጥ ላሉም እንዲፈነጥቅ ነው።”—Counsels on Sabbath School Work, p. 34.

4. የጥርጣሬ እውነተኛ መንስኤ ረቡዕ ፣ መስከረም 06
ሀ. አስፈላጊ እና አስፈላጊ ያልሆኑትን እንዴት መለየት እንችላለን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13:5፤ ቲቶ 3:9–11 “እግዚአብሔር ለእምነት በቂ ማስረጃ የሰጠ ቢሆንም ላለማመን ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን በሙሉ ግን ፈጽሞ አያስወግድም። ጥርጥሮቻቸውን ለመስቀል ማንጠልጠያዎች የሚፈልጉ ሁሉ ያገኟቸዋል። እያንዳንዱዋ ተቃውሞ እስክትወገድ፣ ለመጠራጠርም ምንም ዕድል እንዳይኖር እስኪሆን ድረስ የእግዚአብሔርን ቃል ለመቀበልና ለመታዘዝ እምቢ የሚሉ እነርሱ ፈጽመው ወደ ብርሐኑ አይመጡም።”— The Great Controversy, p. 527 ለ. ለትሑታን ምን በረከቶች ይመጣሉ? ያዕቆብ 4:6፣ 10፤ 1ኛ ጴጥሮስ 5:6፣ 7 “ፍላጎቶቼን ሁሉ አሟላልኝ። የነፍሴ ረሐብ በጥጋብ ተተካ። ለእኔ መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስ ማንነት የተገለጠበት መጽሐፍ ነው። ለምን በክርስቶስ ታምናለህ? ብትሉኝ እርሱ ለእኔ መለኮታዊ አዳኜ ስለሆነ ነው። ለምን መጽሐፍ ቅዱስን ታምናለህ? ብትሉኝ ለነፍሴ የእግዚአብሔር ድምጽ ሆኖ ስላገኘሁት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንደሆነና ክርስቶስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ለራሳችን ምስክርነቱን ልናገኝ እንችላለን። በጥበብ የተቀነባበረ ውሽት እንደማናምንም እናውቃለን።”—Steps to Christ, p. 112. ሐ. ሐዋርያው ጳውሎስ አሁን ያለውንና የወደፊት የአማኙን ተሞክሮ እንዴት ይገልጸዋል? 1ኛ ቆሮንቶስ 13:12 “በዚህ ሕይወት መረዳት የምንጀምረው ግሩም የሆነውን የመዳንን ርዕሰ-ጉዳይ ብቻ ነው። በውስኑ ማስተዋላችን መስቀል ላይ የሚገናኙትን ውርደትንና ክብርን፣ ሕይወትንና ሞትን ፍርድንና ምሕረትን ከልብ እናሰላስል ይሆናል፤ ሆኖም የአዕምሯችን ኃይላት እስከ ጥግ ቢለጠጡ እንኳ አስፈላጊነቱን ሙሉ ለሙሉ መረዳት ይሳነናል። የማዳንን ፍቅር ወርዱንና ስፋቱን፣ ጥልቀቱንና ቁመቱን መረዳት ያገኘነው በድንግዝግዝ ነው። በዋጋ የተገዙት፣ እንደታዩ በሚያዩበት፣ እንደታወቁም በሚያውቁበት ጊዜም ቢሆን የማዳን እቅድ ሙሉ ለሙሉ መረዳት አያገኝም፤ ነገር ግን ማብቂያ በሌላቸው ዘመናት ውስጥ፣ ለሚደነቅና ሐሴት ለሚያደርግ አዕምሮ አዳዲስ እውነቶች በቀጣይነት ይገለጣሉ።”—The Great Controversy, p. 651.“ወደፊት የምንወርሳትን ምድር በእምነት አሻገርን በማየት ከእውነት ምንጭ ጋር በመቆራኘት ልናገኝ የምንችለውን የማስተዋል እድገት በተስፋ እንጠብቅ። ዛሬ ግራ ያጋባን ነገር ሁሉ ያን ጊዜ በእግዚአብሔር እርዳታ ግልጽ ስለሚሆንልን ልባችን በደስታ ይሞላል። አሁን ለውስኑ አእምሯችን መረዳት ያስቸገሩን ነገሮች ያን ጊዜ ፍፁም መግለጫ እናገኝላቸዋለን።” 1ኛ ቆሮንቶስ 13:12 የተጠቀሰ፡፡ አሁን ለውስኑ አዕምሯችን ይረዳው ዘንድ ግራ-መጋባትና የዓላማዎች መክሸፍ ብቻ የሆኑ ነገሮች ያን ጊዜ [ለምን እንደዚያ እንደሆኑ] እጅግ ፍፁምናን የተላበሰና የተዋበ ውህደት (ስምምነት) ያለው ሆኖ እንመለከተዋለን [1ኛ ቆሮንቶስ 13:12 የተጠቀሰ]”—፡፡ ፡፡”—Steps to Christ, p. 112፣ 113.

5. የእግዚአብሔር ዓላማ ለሕዝቡ ሐሙስ ፣ መስከረም 07
ሀ. በዚህ ዘመን መጨረሻው እየተቃረበ ባለበት ወቅት ጌታ ቃሉን በምን አስደናቂ መንገድ እየገለጸ ነው? ራዕይ 10:2፣ 6፣ 7። “የታተመው መጽሐፍ የራዕይ መጽሐፍ ሳይሆን ነገር ግን ከመጨረሻው ዘመን ጋር የተገናኘው የዳንኤል ትንቢት የተወሰነ ክፍል ነው፡፡ . . . [ ዳን. 12፡ 4 የተጠቀሰ]፡፡ መጽሐፉ በተከፈተ ጊዜ «ወደ ፊት አይዘገይም (ከእንግዲህ ጊዜ የለም)» ተብሎ ታውጇል (ራዕይ 10፡-6ን ይመልከቱ)፡፡ አሁን የዳንኤል መጽሐፍ ማህተሙ ስለተፈታ ክርስቶስ ለዮሐንስ ያሳየው ራዕይ ለምድር ኗሪዎች ሁሉ መምጣት (መድረስ) አለበት፡፡ እውቀት ከመብዛቱ የተነሳ ሕዝብ በኋለኛው ዘመን ለመቆም ሊዘጋጅ ነው።”—Selected Messages, bk. 2, p. 105.“ብዙዎች የራዕይ መጽሐፍ የተዘጋ መጽሐፍ ነው በማለት ምስጢሮቹን ለማጥናት ጊዜ ማጥፋት እንደሌለባቸው ያስባሉ። የመዳንን ክብር መመልከት እንዳለባቸው እና በፍጥሞ ደሴት ለዮሐንስ የተገለጡት ምስጢሮች ከእነዚህ ያነሰ ግምት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ይናገራሉ። ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን መጽሐፍ እንደዚህ አይመለከተውም። . . .“የራዕይ መጽሐፍ ስለዓለም የነበረውን፣ ያለውንና የሚመጣውን ይከፍታል፤ መልእክቱ የተሰጠው የዓለም ፍጻሜ ለደረሰብን ለእኛ መመሪያና ትምህርት ይሆን ዘንድ ነው። ስለዚህ በአክብሮትና በፍርሃት ማጥናት አለብን። . . .“ጌታ ራሱ ለባሪያው ለዮሐንስ የራዕይ መጽሐፍ ምስጢሮችን ገለጠለት፣ እናም ሁሉም ያጠናቸው ዘንድ ክፍት እንዲሆኑ አደረገ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያለፉ ትዕይንቶች እና አሁን በዙሪያችን እየተከናወኑ ያሉ ለዘላለማዊ ሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ተገልጸዋል፤ በተጨማሪም በጨለማ ኃይሎች እና በሰማይ ልዑል መካከል የመጨረሻው ታላቁ ተጋድሎ (ጦርነት) እስኪከሰት እስከ ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ሌሎቹ ሙሉ በሙሉ ፍጻሜያቸውን የማያገኙ ትንቢቶችንም ይዟል።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 7, p. 954. ለ. አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ረገድ ምን ማድረግ አለባቸው? 2ኛ ጢሞቴዎስ 2:15፤ ዮሐንስ 7:17

የግል ክለሳና የመወያያ ጥያቄዎች አርብ ፣ መስከረም 08
1. እውነት ምን እንደሆነ ለመረዳት ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? 2. አንዳንድ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ሊረዱ የማይችሉበትን ምክንያት አብራራ። 3. ብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መቀበል የማይፈልጉት ለምንድን ነው? 4. በእርግጥ መጠራጠር የሚፈልጉ ሰዎች ሁልጊዜ ምን ያገኛሉ? 5. እውነትን ለመረዳት፣ ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
 <<    >>