Back to top

Sabbath Bible Lessons

ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (II)

 <<    >> 
11ኛ ትምህርት ሰንበት፣ መስከረም 04፣ 2017

ለታላቅ ዓላማ ተጨማሪ ጊዜ

የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም። ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እኛ ይታገሣል።” (2ኛ ጴጥሮስ 3፡9)።

“እኛ፣ ከተቤዡት ቅዱሳን ሁሉ ጋር፣ የወርቅ በገናና የክብር ዘውድ ጭነን በብርጭቆ ባሕር ላይ በምንቆምበትና በፊታችንም የዘላለማዊ ህይወት ግዝፈት ተዘርግቶ በምንመለከትበት ጊዜ፣ የአማክሮው የጥበቃ ጊዜ ምን ያህል አጭር እንደነበረ በዚያን ጊዜ ማስተዋል እንችላለን።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 485.

ለጥናት የተመረጠው መጽሐፍ፡   Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 183–199. 

እሁድ ጳጉሜ 03

1. ምን እያየን ነው?

ሀ. ፌዘኞች ለጥርጣሬያቸው ሰበብ አድርገው የሚጠቅሱት ምንድን ነው—ይህስ አመለካከት ጌታን በመጠባበቅ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ሊጎዳቸው የሚችለው እንዴት ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 3:4 ፤ ኢሳይያስ 56:1

“የዓለም ፍቅር ሃሳባችንን ሁሉ ስለዋጠ፣ ዓይኖቻችን ወደ ላይ ወደ ሰማይ ማተኮራቸውን ትተው ወደ ታች ወደ ምድር አተኩረዋል። በተለያዩ የገቢ ማግኛ የሥራ ዘርፎች በቅንዓት እና በታላቅ ትጋት እንጣደፋለን ፤ ዳሩ ግን እግዚአብሔር ተረስቷል፣ ሰማያዊው ሀብትም ዋጋ ተነፍጎታል። በመጠበቅና በመመልከት አቋም ላይ አይደለንም። የዓለም ፍቅር እና የባለጠግነት አታላይነት እምነታችንን ጋርደውታል፣ በመሆኑም የአዳኛችን መገለጥ በናፍቆትና በፍቅር እየተጠባበቅነው አይደለንም። ስለራሳችን ለማሰብና ለመንከባከብ የቻልነውን ሁሉ እንጥራለን። የመረጋጋት እና በእግዚአብሔር ላይ የመታመን ከፍተኛ እጦት አለብን። ብዙዎቹ ማጣትና መቸገር ይደርስብናል ብለው በመስጋት ይጨነቃሉ፣ ያቅዳሉ፣ ይሠራሉ፣ ያወጣሉ ያወርዳሉ፡፡ ለመጸለይም ሆነ በሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ላይ ለመሳተፍ ጊዜያቸውን መሰዋት አይፈልጉም፤ እንዲሁም ስለራሳቸው ባላቸው ሃሳብ፣ እግዚአብሔር ስለእነርሱ ያስብላቸው ዘንድ አንዳች እድል አይሰጡትም፡፡ ከዚህ የተነሳ አምላክ ብዙ ነገር አያደርግላቸውም ፤ ምክንያቱም እድል አልሰጡትምና፡፡ ለራሳቸው ብዙ ነገር ያደርጋሉ ፤ በእግዚአብሄር ላይ ያላቸው እምነትና መታመን ግን በጣም ትንሽ ነው።

“ ጌታ በድንገት ሲመጣ ተኝተው እንዳያገኛቸው፣ ዘወትር እንዲፀልዩና ነቅተው እንዲጠብቁ ባዘዛቸው ህዝቦች ላይ የዓለም ፍቅር ያለው አፍዛዥ አደንዛዥነት እጅግ አስፈሪ ነው፡፡ ”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 195, 196.


ሰኞ ጳጉሜ 04

2. በመጨረሻ . . . ወይስ በጣም በቅርቡ?

ሀ. በዳግም ምጽዓቱ እናምናለን በሚሉ አማኞች መካከል እንኳን ሳይቀር ዘባችነት (መላገጥ) እንዴት እየበዛ እንደሚሄድ ይግለፁ። ማቴዎስ 24:48–51; ምሳሌ 26:20–22; ሮሜ 1፡29-32

“ክፉ አገልጋይ በልቡ፡- ‘ጌታዬ አሁን አይመጣም ይዘገያል’ ይላል። ክርስቶስ አይመጣም አይልም። ስለ ክርስቶስ መምጣትም አያፌዝም። ነገር ግን በልቡ፣ በተግባሩ እና በቃላቱ ጌታ ይዘገያል የሚል የሚል መልዕክት ያስተላልፋል። ጌታ በቶሎ ይመጣል የሚለውን እምነት ከሌሎች አእምሮ እንዲጠፋ ያደርጋል። የተጽእኖው አርያነት ሰዎችን ማን አለብኝ ባይና ግድየለሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ሰዎች በአለማዊነት ተውጠው ስሜታቸው የደነዘ እንዲሆኑ ያደርጋል። አዕምሯቸው የዓለማዊ ስሜት (ፍትወት)፣ የተበላሹ አስተሳሰብ ተገዥ ይሆናል፡፡ ክፉው አገልጋይ ከሰካራሞች ጋር ይበላል ፤ ይጠጣል፤ ደስታ ለማግኘትም ከዓለም ጋር ይዋሃዳል። ለጌታቸው ታማኝ የሆኑትን አገልጋዮች በመክሰስና በማውገዝ ያሰቃያቸዋል። ”—The Desire of Ages, p. 635. [የዘመናት ምኞት አማርኛው ገጽ 665].

ለ. የክርስቶስን ዳግመኛ ዳግመኛ ዳግመኛ ዳግመኛ መምጣት ሩቅ እንደሆነ ከሚቆጥሩት ሰዎች በተቃራኒ መቆም ያለብን እንዴት ነው? ቆላስይስ 3፡1-4

“የዓለማዊያን ትኩረት ወደ ተለያዩ የገንዘብ ማተረፊያ ሥራዎች ቢወሰወሱም፣ የእኛ ትኩረት ግን ወደ ሰማያት መሆን አለበት። ልክ በየሱስ ፊት ላይ ያበሩ እንደነበረ በልባችን ላይ ያበሩ ዘንድ የከበሩትን መለኮታዊ የብርሃን ጮራዎች ከቤተመቅደሱ በመሳብ ኃይማኖታችን ወደ ሰማያዊው መዛግብት እፁብ ድንቅ ምስጥራት ዘልቆ መግባት ይኖርበታል፡፡ ፌዘኞች በሚጠባበቁትና በሚመለከቱት ላይ በመሳለቅ ‘የመምጣቱ የተስፋ ቃል የት አለ? በማለት ይጠይቃሉ፡፡ ተስፋችሁ ከንቱ ሆኖ ታዝናላችሁ፡፡ ስለዚህ አሁን ከእኛ ጋር ተሰለፉ ፤ በአለማዊ ሃብትም ትበለጽጋላችሁ። ሀብት አካብቱ፣ ገንዘብም አከማቹ በዓለምም የተከበራችሁ ሁኑ’ ይሏቸዋል፡፡ [መገለጡን] በመጠባበቅ ላይ የሚገኙት ወደ ላይ እያዩ 'እየጠበቅን ነው' ብለው መለሱ። እናም ከምድራዊ ደስታ እና ከዓለማዊ ዝና፣ እንዲሁም አታላይ ከሆነው ዓለማዊ ሃብት ፊታቸውን በማዞር በታማኝነት በቦታቸው ላይ መቆማቸውን ያሳያሉ። በመመልከት (በመጠበቅ) ጠንካራሮች ሆኑ ፤ ስንፍናን፣ ራስ ወዳድነትን እና ችግር አልባ የምቾት ፍቅርን ያሸንፋሉ፡፡ የመከራ እሳት በላያቸው ይነዳል፣ የጥበቃ ጊዜውም የረዘመ ይመስላል። እነርሱ አንዳንዴ ያዝናሉ ፤ እምነታቸውም ይዝላል ፤ ነገር ግን ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ በማንጋጠጥ፣ ፍርሃታቸውን እና ጥርጣሬያቸውን በማሸነፍ እንደገና በጋራ ይሰለፋሉ ፤ በመሆኑም ለባላንጣዎቻቸው እንዲህ ይሏቸዋል፡- ‘እየጠበቅሁ ነኝ ፤ የጌታዬን መገለጥ እየተጠባበሁ ነው። በመከራ፣ በስቃይና በችግር ሁሉ እከብራለሁ’።”— Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 194, 195


ማክሰኞ ጳጉሜ 05

3. የተፈጥሮ አካላትን በመጠቀም መፍረድ

ሀ. በአለም ታሪክ ውስጥ ምን በጣም አስፈላጊ ኹነት (ክስተት) ነው ብዙ ጊዜ ችላ ተብሎ የሚታለፈው? ዘፍጥረት 6:5–8; 7:23 ፤ 2ኛ ጴጥሮስ 3:5, 6

“አሮጌው ዓለም በጎርፍ ከመጥፋቱ በፊት፣ በስራ ክህሎት የተካኑ ሰፊ የእውቀት አድማስ ያላቸው የተሰጥኦ ሰዎች ነበሩ። ነገር ግን እግዚአብሔርን ከእቅዳቸውና ከምክራቸው ውጭ በማድረጋቸው በአዕምሯቸው ሃሳብ (አስተሳሰብ) ተበላሹ። እግዚአብሔር ፈጽሞ ያላዘዛቸውን ለማድረግ ጥበበኛ ነበሩ፤ ክፋትን ለማድረግ በጥበብ የተካኑ ነበሩ። ይህ ምሳሌ በኋላ ለሚወለዱ ልጆች አደገኛ ምሳሌ እንደሚሆን በመመልከቱ ጌታ ጉዳዩን በገዛ እጁ ወሰደው። ለአንድ መቶ ሀያ ዓመታት በባሪያው በኖህ በኩል ማስጠንቀቂያ ላከላቸው። ነገር ግን በታላቅ ፀጋው የተሰጣቸውን ይህን የአማክሮ ጊዜ በኖህ ላይ በመሳለቅ በከንቱ አባከኑት። ተላገጡበት አወገዙትም። እግዚአብሔር በእርግጥም ይፈጽመዋል ብሎ ባወጀው ፍርድ ላይ ባሳየው ያልተለመደ ትጋትና ጥልቅ ስሜት ሳቁበት። ስለ ሳይንስ እና ተፈጥሮን ስለሚቆጣጠሩ ህጎች ተናገሩ። ከዚያም በኖህ ቃላት ላይ ህዝባዊ ክብረ በዓላትን በማዘጋጀት እብድ አክራሪ ብለው ጠሩት። የአምላክ ትዕግስትም ተሟጠጠ።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 1, p. 1090.

ለ. ይህችን ዓለም በመጨረሻ የሚጠብቃት ምንድን ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 3:7 ፤ መዝሙረ ዳዊት 11:6; 59፡13።

“አሮጌውን ዓለም ለማጥፋት ጥቅም ላይ ያዋላቸውን መሳሪያዎች ያወጣ ዘንድ ከርሰ ምድሮች፣ የጌታ የጦር መሳሪያ ማከማቻዎች ነበሩ። የከርሰ ምድር ውኃ ወደ ላይ ፈነዳ ፤ የጥፋት ሥራውን ይፈጽም ዘንድ፣ ከሰማይ ከወረደው ዝናብ ጋር ተዋሃደ። የጥፋት ውኃ ከወረደ ጀምሮ አምላክ ክፉ ከተሞችን ለማጥፋት በምድር ላይ ውኃንና እሳትን ወኪሎቹ አድርጎ ተጠቅሟል።.”—Spiritual Gifts, vol. 3, p. 82.

“የሐሰት አባት ጠቅላላ ሥራው ሁሉ በሰማይ በህግ መጻሕፍት ተጽፎ ይገኛል ፤ እናም በመሪያም ይሁን በተግባር ተግባራዊ ለማድረግና ለሰዎች ለማቅረብ ራሳቸውን ለሰይጣን አገልግሎት አሳልፈው የሚሰጡ ሁሉ፣ እንደሥራቸው ይቀበላሉ። ሥሩና ቅርንጫፉ በመጨረሻው ቀን እሳት ይጠፋል። ታላቁ የክህደት ዋና ጄኔራል የሆነው ሰይጣን ሥሩ ሲሆን ፤ እንዲሁም ስለ እግዚአብሔር ሕግ ውሸትን የሚያስተምሩ የእርሱ ሰራተኞች በሙሉ ደግሞ ቅርንጫፎች ናቸው።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 4, p. 1184.


ረቡዕ መስከረም 01

4. አስፈሪው የዘላለም አምላክ

ሀ. የእግዚአብሔር ልጆች በተስፋዎቹ እንዲታመኑ እና ለዘላለማዊነትም ተስፋ እንዲያደርጉ፣ የፈጣሪያችን ወሰን የለሽነት ልኬት እንዴት ነው ጠቅለል ብሎ የተገለፀው? መዝሙረ ዳዊት 90:4 ፤ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡8

“እግዚአብሔር ለሕዝቡ የገባው ውርስ በዚህ ዓለም ላይ አይደለም። አብርሃም በምድር ላይ ምንም ርስት አልነበረውም ፤ ‘የእግር ጫማ ስንኳ የሚያህል ርስት አልሰጠውም’ (የሐዋርያት ሥራ 7፡5)፡፡ ብዙ ሀብት ነበረው፥ እናም ያለውን ሃብት ለእግዚአብሔርም ክብርና ለባልንጀሮቹ ጥቅም አውሎታል ፤ ነገር ግን ይህችን ዓለም እንደ ቤቱ አድርጎ አልተመለከተም። የከነዓን ምድር ለዘላለም ርስት አድርጎ እንደሚሰጠው የተስፋ ቃል በመግባት፣ ጣዖት አምላኪዎቹን የሀገሩን ሰዎች ትቶ ይወጣ ዘንድ ጌታ ጠራው ፤ ዳሩ ግን የተስፋ ቃሉን እርሱም ይሁን ልጁ ወይም የልጁ ልጁ አልተቀበሉም። አብርሃም ለሟቾቹ የመቃብር ቦታ በፈለገ ጊዜ ከከነዓናውያን በገንዘብ መግዛት ነበረበት። በተስፋይቱ ምድር ብቸኛ ይዞታው የነበረው በማክፌላ ዋሻ ውስጥ የሚገኘው በዓለት የተፈለፈ መቃብር ነበር።

“ የእግዚአብሔር ቃል ግን ሊወድቅ አይችልም ፤ እንዲሁም በአይሁድ ሕዝብ በከነዓን በመውረሳቸው የመጨረሻውን ስኬት ማሳካት አልቻለም። 'ለአብርሃምና ለዘሩ የተስፋው ቃል ተሰጠ።' ገላትያ 3፡16፡፡ አብርሃም ራሱ ርስቱን መካፈል ነበረበት። የአምላክ ተስፋ ፍጻሜው የዘገየ ሊመስል ይችላል ፤ ምክንያቱም ‘በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፣ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና’ (2 ጴጥሮስ 3:8)፡፡ የሚዘገይ ሊመስል ይችላል ፤ ነገር ግን በተወሰነው ጊዜ፣ ‘በእርግጥ ይመጣልና፣ አይዘገይምም’። ዕንባቆም 2:3። ”—Patriarchs and Prophets, pp. 169, 170.

ለ. የክርስቶስን መምጣት በተመለከተ ምን ማስተዋል አለብን? 2 ጴጥሮስ 3:9; ናሆም 1:3

“ የእግዚአብሔር ታጋሽነት አስገራሚ ነው። ምሕረት ለኃጢአተኛው ሲማጸን ፍትሕ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቅ ቆይቶአል። . . .

“ዓለም የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ ደፋር ሆኖአል። ከረጅም ትዕግሥቱ የተነሳ ሰዎች ሥልጣኑን ረግጠዋል። ‘እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለን?’ (መዝሙረ ዳዊት 73:11) እያሉ በእርሱ ውርስ (ቅርስ) ላይ ግፍና ጭካኔን በማሳየት አንዱ አንዱን አበርትተዋል፡፡ ነገር ግን ማለፍ የማይችሉበት መስመር አለ። የተወሰነው ገደብ ላይ የሚደርሱበት ጊዜ ቅርብ ነው። አሁን እንኳን የእግዚአብሔርን ትዕግስት፣ የጸጋውን ገደብ፣ የምሕረቱን ወሰን አልፈዋል። ክብሩን ግልጽ ያሳይ ዘንድ፣ ህዝቡንም ያድንና የዓመፅንም ጎርፍ ይገታ ዘንድ ጌታ ጣልቃ ይገባል።”—Christ’s Object Lessons, pp. 177, 178.


ሐሙስ መስከረም 02

5. ጥልቅ ንስሃ የመግባት እድል

ሀ. አምላክ ላሳየን ትዕግሥት በጣም አመስጋኞች መሆን ያለብን ለምንድን ነው?መዝሙረ

ዳዊት 86: 12-15

“ጌታ ሊረዳን፣ ሊያበረታን እና ሊባርከን ፈቃደኛ ነው ፤ ነገር ግን በባህሪያችን ውስጥ ያሉ ቆሻሻዎች በሙሉ ተቃጥለው እስኪወገዱ ድረስ በማጣራት ሂደት ውስጥ ማለፍ አለብን፡፡ እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ተቀጥለው እንዲወድሙ ሳይሆን ነገር ግን በሳቱ ነጽተው ይወጡ ዘንድ በማጣሪያ ምድጃው ውስጥ ማለፍ ይኖርባቸዋል። ”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 485.

“ የማይሳሳቱ እንደ ሆኑ በማሰብ ወደ ሰዎች አትመልከቱ፤ ተስፋችሁንም በእነርሱ ላይ አታድርጉ፡፡ ነገር ግን ዘወትር ወደ የሱስ ተመልከቱ። በእምነታችን ላይ ነቀፋ ሊያስከትል የሚችል አንዳች ነገር ትንፍሽ አትበሉ። ስውር ኃጢአታችሁን በአምላካችሁ ፊት ብቻ ተናዘዙ። ችግራችሁን እንዴት አድርጎ በትክክል ማከምና መፈወስ ለሚችለው ለእርሱ የልባችሁን መቅበዝበዝ አምናችሁ አቅርቡለት፡፡ በባልንጀራችሁ ላይ በደል አድርሳችሁ ከሆነ፣ ጥፋታችሁን አምናችሁ ተናዘዙላቸው ፤ ያጠፋችሁትን ሙሉ በሙሉ በመመለስ የመለወጥን ፍሬ አሳዩ፡፡ ከዚያም በረከቱን ጠይቁ። እንደሆናችሁት ሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ፤ እርሱም ህመማችሁን ሁሉ ይፈውሳል። ጉዳያችሁን (ልመናችሁን) ወደ ፀጋው ዙፋን አጥብቃችሁ አቅርቡ ፤ ሥራውም ጥልቅ ይሁን። ከእግዚአብሔር ጋር እና ከነፍሳችሁን ጉዳይ በተመለከተ ከምር ቆራጥ ሆኑ። በእውነት የተጸጸተ ልብ ይዛችሁ ወደ እርሱ ከመጣችሁ ድልን ይሰጣችኋል። ያኔ ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን ውዳሴ በማሳየት ስለነጻነት ጣፋጭ ምስክርነት ልትሰጡ ትችላላችሁ። አምላክ አላግባብ አይረዳችሁም ፤ አይፈርድባችሁምም። ባልንጀሮቻችሁ ስርየት ሊሰጧችሁም ሆነ ከኃጢአት ሊያነፁአችሁ አይችሉም። ሰላምን ሊሰጣችሁ የሚችለው የሱስ ብቻ ነው። እርሱ ይወዳችኋል ራሱንም አሳልፎ ሰጥቷችኋል። ታላቅ የፍቅር ልቡ ''በድካማችን ስሜት ተነክቷል ?''፡፡ ይቅር ለማለት ሊያዳግተው የሚችል ምን ታላቅ ኃጢአት አለና? እርሱ ሊያድናት ያልቻለው በጨለማና በኃጢአት የተደቆሰች ምን ዓይነት ነፍስ ልትኖር ትችላለች ? እርሱ ቸር ነው ፤ ከእኛ መልካም ሥራን በመሻት የሚመለከተ ሳይሆን ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ወሰን ከሌለው መልካምነቱ የተነሳ የክህደት በሽችንን ፈውሷል፣ በነጻም ወድዶናል፡፡ እርሱ 'ለቍጣ የዘገየ፣ ምሕረቱም የበዛ' ነው። ‘ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወድዶ ታገሶናል’። ”—Ibid., p. 649.


አርብ መስከረም 03

የግል ግምገማ ጥያቄዎች

1. ከአምላክ እንድርቅ የሚያደርጉኝ የትኞቹ የዓለም ገጽታዎች ናቸው?

2. በመንፈሳዊ አነጋገር አገልጋዮቼን በመምታት ጥፋተኛ መሆን የምችለው እንዴት ነው?

3. ስለ መጪው የእሳት ፍርድ ጥልቅ ግንዛቤ ማዳበር ያለብኝ ለምንድን ነው?

4. የአብርሃምንና የልጆቹን ውርስ (ርስት) ይግለፁ (ገላ 3፡29)።

5. ለዚህ ትንሽ ተጨማሪ ጊዜ አመስጋኝ መሆን ያለብኝ ለምንድን ነው? እንዴትስ ልጠቀምበት?

 <<    >>