የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ ለአንጎላ ዩኒየን ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ይውላል
የሰባተኛ ቀን ተሐድሶ የሰሜናዊ ምስራቅ አንጎላ— የሰሜን ክዋንዛ፣ ዩጂ እና ማላንጄ የሚባሉ ሶስት ግዛቶችን ያገለግል ዘንድ በ 2015 ዓ.ም በጀነራል ኮንፍራንስ ተደራጀ፡፡ የኋለኛው (ማላንጄ) የሚገኘው በሰሜን ማዕከላዊ የአንጎላ መስክ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ነው። ቀጠናው 181,110 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን 3,550,774 ነዋሪዎች እንደሚኖሩበት ይገመታል። የሰባተኛ ቀን ተሀድሶ መልዕክት ወደዚህ ክልል የመጣው በ1978 ቀስ በቀስ ነው። ነገር ግን በ1990 ዓ.ም በእግዚአብሔር ቸርነት ሥራው በክልላችን በጥልቀት በመመስረት ከዚያን ጊዜ ጀምሮ መገስገሱን አልቆመም። ጉልህ እድገት በማሳየት፣ የወቅቱ እውነት መልእክት በአካባቢው በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ሊደርስ በቅቷል።
አሁን የሚያስፈልገን ነገር ለአንጎላ ዩኒየን ሰራተኞች የሚሆኑ የስራ ክፍሎች፣ ቤተመፃህፍት እና የስብሰባ አዳራሽ ያለው ህንፃ መገንባት ነው።
በቀላሉ ተደራሽ የሆነ በከተማ ዳርቻ መሬት አግኝተናል። በዚህ ክልል የእግዚአብሔርን ቅዱስ ሥራ በትክክል ሊወክል የሚችል ሕንፃ መገንባት እንደምንችል ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ከፊታችን የሚጠብቀንን ታላቅ ተግባር በማሰብ፣ ሊከናወኑ የሚገባቸውን ሥራዎች እቅድና ቅንጅት በፍፁም ሥርዓት ለመፈፀም የሚያስችል ተቋማዊ ድርጅት ያስፈልገናል። ይህንም ስናደርግ የሚከተለውን በአእምሯችን መያዝ ይገባናል— “[እግዚአብሔር] የቤተክርስቲያንን ስራዎች ለማከናወን መመሪያና ስርዓት ይጠበቅ ዘንድ ከጥንት ጊዜ ያነሰ አይሻም፡፡ የራሱን የማረጋገጫ ማህተም ያሳርፍበት ዘንድ ሥራው በታላቅ ጥንቃቄና ትክክለኛነት ይከናወን ዘንድ ይሻል፡፡ ክርስቲያን ከክርስቲያን ጋር፣ ቤተ ክርስቲያን ከቤተክርስቲያን ጋር፣ ሰብዓዊ መሳሪያነት ከመለኮታዊው ጋር፣ እያንዳንዱ ወኪል ለመንፈስ ቅዱስ በመታዘዝ ሁሉም በአንድነት ሲተባበሩ የእግዚአብሔርን ጸጋ መልካሙን ምሥራች ለዓለም ይሰብካሉ።”—The Acts of the Apostles, p. 96.
የመዳን መልእክት ወደ ምድር ሁሉ መድረስ አለበት፣ ጌታም “በምድርም ላይ ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ አይታክትም ፤ አይሰበርም” የሚለው ቃል ለመፈፀሙ እርግጠኞች ነን፡፡ “ደሴቶችም ትምህርቱን ይጠባበቃሉ (ኢሳይያስ 42፡4)”።
ሰፊ በሆነው በዚህ የአንጎላ ግዛት ለሚገኙ ነፍሳት ወንጌልን ለማስፋፋት፣ ለዚህ ፕሮጀክት ስጦታችሁን በመለገስ ትረዱን ዘንድ በዓለም ዙሪያ የምትገኙ ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችነን እንማጸናችኋለን፡፡
ጌታ እግዚአብሔር አትረፍርፎ ይባርካችሁ።
- ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ ከሰሜን ምስራቅ የአንጎላ ዩኒየን