እሁድ
ሐምሌ 28
1. እዚህ እና አሁን ማደግ
ሀ. ሐዋርያው ጴጥሮስ ለአማኞች ምን አጽንዖት ሰጥቷል? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡12-15
“ለዚያ ጊዜ የተለየ አስፈላጊነት የነበረው ወቅታዊ እውነት በሉተር ዘመን ነበር፤ ለቤተ ክርስቲያንዋ ዛሬም ወቅታዊ እውነት አለ። ሁሉን ነገር እንደ ፈቃዱ ማድረግ የሚቻለው እርሱ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሰዎችን ለማስቀመጥ፣ እንዲያገለግሉ ለተቀመጡበት ሁኔታዎችና ለኖሩበት ዘመናቸው ገጣሚ የሚሆን የተለየ ኃላፊነት ለመስጠት እግዚአብሔር ፈቃደኛ ነው። ለሚሰጣቸው ብርሐን ዋጋ የሚሰጡ ከሆነ፣ ሰፊ እውነት በፊታቸው ይከፈታል።።”—The Great Controversy, pp. 143, 144.
ለ. ከሰማይ ስለመጣው ብርሃን ባለን ግንዛቤ እንዴት ማደግ እንዳለብን አስረዳ። ዕብራውያን 5:12-14፤ 6፡1–3።
“እያንዳንዱ የእምነት እና የታዛዥነት እርምጃ ነፍስ ‘ጨለማ በሌለበት’ ከዓለም ብርሃን ጋር የበለጠ ግንኙነት እንድትፈጥር ያደርጋታል።”—Ibid., p. 476.
ሰኞ
ሐምሌ 29
2. ተጠያቂነት
ሀ. ብዙ ከሰማይ የተላከ ብርሃን ስናገኝ ተግባራችንን መለወጥ የሚያስፈልገን ለምንና እንዴት ነው? ያእቆብ 4:17፤ ምሳሌ 4:18፤ ማቴዎስ 6፡23
“እግዚአብሔር እንደ ተሰጣቸው ጸጋና እውነት መሠረት ከሕዝቡ ምላሽ ይፈልጋል። ሁሉም የጽድቅ ጥያቄዎቹ ሙሉ በሙሉ መሟላት አለባቸው። ተጠያቂነት ያላቸው ፍጡራን በሚያበራላቸው ብርሃን መሄድ አለባቸው። ይህን ማድረግ ካልቻሉ ብርሃናቸው ጨለማ ይሆናል፣ ጨለማቸውም ብርሃናቸው የበዛበትን በሚያህል ደረጃ ታላቅ ይሆናል። የተከማቸ ብርሃን በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ በራ። ነገር ግን ብዙዎች ብርሃኑን መከተልን ቸል ብለዋል፣ እናም በዚህ ምክንያት በታላቅ መንፈሳዊ ድካም ውስጥ ናቸው።
“የእግዚአብሔር ሕዝብ አሁን እየጠፋ ያለው እውቀት ከማጣት የተነሳ አይደለም። መንገዱን፣ እውነትንና ሕይወትን ስለማያውቁ አይደለም አሁን የሚወቀሱት። ማስተዋላቸው ላይ የደረሰው እውነት፣ በነፍስ ላይ የበራ እና ተቀባይነትን የተነፈገው ወይም የተከለከለው ብርሃን፣ ይወቅሳቸዋል። ብርሃን ያልነበራላቸው ሰዎች የናቁት ብርሃን ስለሌ አይኮነኑም። ለእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ ካደረገው የበለጠ ሌላ ምን ሊደረግ ይችል ነበር? ብርሃን፣ ክቡር ብርሃን፣ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ያበራል፤ ነገር ግን በብርሃኑ ለመዳን ፈቃደኛ ካልሆኑ፣ ሙሉ በሙሉ በብርሃኑ መኖር ካልቻሉና በጨለማ ውስጥ ላሉት ለሌሎች ካላበሩ ይህ ብርሃን አያድናቸውም። እግዚአብሔር ሕዝቡን ይህን እንዲያደርጉ ጠርቷቸዋል። ኃጢአትን መናዘዝና መተው እንዲሁም ወደ ጌታ መመለስ የግለሰብ ሥራ ያስፈልጋል። አንድ ሰው ይህን ሥራ ለሌላው መሥራት አይችልም። ሃይማኖታዊ እውቀት እጅግ በዝቷል በዚህም ተጓዳኝ ግዴታዎቻችንም በዚያው ልክ ጨምሯል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ታላቅ ብርሃን እየበራ ነው፣ ነገር ግን በእርሱ ለመራመድ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተወግዘዋል። ዕውር ቢሆኑ ኃጢአት በሌለባቸው ነበር። ነገር ግን ብርሃን አይተዋ፥ ብዙ እውነትንም ሰምተዋል፣ ነገር ግን ጥበበኞችና ቅዱሳን አልሆኑም። ብዙዎች ለዓመታት በእውቀትና በእውነተኛ ቅድስና ምንም እድገት አላሳዩም። መንፈሳዊ ድንክዬዎች ናቸው። ወደ ፍጽምና ከመሄድ ይልቅ ወደ ጨለማውና ወደ ግብፅ ባርነት እየተመለሱ ነው። አእምሯቸው እግዚአብሔርን ለመምሰል እና ለእውነተኛ ቅድስና አልተለማመደም።
“የእግዚአብሔር እስራኤል ይነቃሉን? እግዚአብሔርን መምሰል የሚፈልጉ ሁሉ ኃጢአትን ሁሉ ለማስወገድ፣ ምስጢራዊ ኃጢአትን ሁሉ ለእግዚአብሔር ለመናዘዝ፣ ነፍሳቸውንም በፊቱ ያስጨንቁታልን? በታላቅ ትህትና የእያንዳንዱን ድርጊት መነሻዎች ይመረምራሉን? የእግዚአብሔር ዓይን ሁሉንም እንደሚያነብ፣ የተሰወረውንም ሁሉ እንደሚመረምር ያውቃሉን? ሥራው ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር በመቀደስ ይሠራ። እኛ እና ያለን ሁሉ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር እንድናስገዛ ጥሪ ያደርጋል። አገልጋዮችና ሰዎች አዲስ መለወጥ፣ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል፣ ያለዚያ ለሕይወት የሚሆኑ የሕይወት ሽታዎች ሳይሆኑ ለሞት የሚሆኑ የሞት ሽታዎች ይሆናሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 123, 124.
ማክሰኞ
ሐምሌ 30
3. የወቅቱ እውነት
ሀ. በነሱ ጥናት ላይ ትኩረት ከማድረግ መዘናጋት የሌለብን ርዕሰ ጉዳዮችን ምሳሌዎች ስጥ። ዳንኤል 7:9፣ 10፤ 8:14፤ መዝሙረ ዳዊት 119:33-35
“በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተካተቱ ብዙ ውድ እውነቶች አሉ፣ ነገር ግን መንጋው አሁን የሚያስፈልገው ' የወቅቱ እውነት ' ነው። መንጋውን አንድ ለማድረግ እና ነፍስን ለመቀደስ በማይጠቅሙ ጉዳዮች ላይ በማሰላሰል መልእክተኞች አሁን ከተሰጡን አስፈላጊ ነጥቦች የመራቅ አደጋ አይቻለሁ። ሰይጣን ሥራውን ለመጉዳት የሚቻለውን መንገደ ሁሉ ይጠቀማል።
ነገር ግን እንደ ቤተ መቅደሱ ያሉ ርዕሰ ጉዳዮች፣ ከ2300 ቀናት፣ ከእግዚአብሔር ትእዛዛት እና ከየሱስ እምነት ጋር በተገናኘ፣ ያለፈውን የአድቬንቲስት እንቅስቃሴን ለማብራራት እና አሁን ያለንበትን አቋም ለማሳየት፣ የተጠራጠሩትን እምነት ለመመስረት እና ለወደፊት ክብር እርግጠኛ እንዲሆኑ ማድረግ፣ እነዚህ፣ መልእክተኞቹ ሊያተኩሩባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች መሆናቸዉን ደጋግሜ አይቻለሁ።”—Early Writings, p. 63. [Author’s emphasis.]
ለ. ለ180 ዓመታት ያህል (በአጠቃላይ ዓለም ታሪክ አንጻር በቅርብ ጊዜ) የወቅቱ እውነት አስፈላጊ ገጽታ ምን ነበር? ራእይ 14:6-13
“የመጀመሪያው፣ የሁለተኛው እና የሶስተኛው የመላእክት መልእክት አዋጅ የተገኘው በአምላክ ቃል ነው። አንዲት ቅንጣት ወይም ጫፍ መቅረት የለበትም። የትኛውም ሰብዓዊ ባለሥልጣን አዲስ ኪዳንን በብሉይ ከመተካት በላይ የእነዚህን መልእክቶች ቦታ የመቀየር መብት የለውም። ብሉይ ኪዳን በምሳሌና በምልክት የተገለጸ ወንጌል ነው። አዲስ ኪዳን የሚያስተምረው ደግሞ በፍሬ ነገር ነው። አንዱ የሌላውን ያህል አስፈላጊ ነው። ብሉይ ኪዳን ከክርስቶስ ከንፈሮች ትምህርቶችን ያቀርባል፣ እናም እነዚህ ትምህርቶች በተለየ መልኩ ኃይላቸውን አላጡም። የመጀመሪያውና ሁለተኛው መልእክቶች በ1843 እና በ1844 የተሰጡ ሲሆን አሁን በሦስተኛው መለዓክት በማወጅ ላይ ነን፤ ነገር ግን ሦስቱም መልእክቶች አሁንም መታወጅ አለባቸው። እውነትን ለሚሹ ሰዎች እነዚህ መለዕክቶች መደጋገማቸው እንደበፊቱ ሁሉ አሁንም አስፈላጊ ነው። ወደ ሦስተኛው መልአክ መልእክት የሚያደርሱንን ትንቢቶች በተግባር እያሳይን በብዕርና በድምፅ አዋጁን እናሰማለን። ያለመጀመሪያው እና ሁለተኛው መለዕክት ሶስተኛው ሊኖር አይችልም። እነዚህን መልእክቶች በኅትመት፣ በንግግሮች፣ በትንቢታዊ ታሪክ መስመር ውስጥ ያሉትን ነገሮችና ወደፊት የሚፈጸሙትን ነገሮች በማሳየት ለዓለም ልናስተላልፍላቸው ይገባል።”—Counsels to Writers and Editors, pp. 26, 27.
ረቡዕ
ነሐሴ 01
4. ለማደግ መመኘት
ሀ. እውነት ሲገለጥ ሌሎች ባይቀበሉትም እንኳ እኛ እንድንቀበል የሚያስችለንን አመለካከት ግለጽ። ኤርምያስ 29:13፤ ማቴዎስ 18:3፤ ዮሐንስ 7፡17
“እንደ ትንሽ ልጅ ሆነህ ለመመራት ፈቃደኛ ስትሆን፣ ማስተዋልህ ሲቀደስ እና ፈቃድህና ጭፍን ጥላቻህ እጅ ስሰጡ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን የሚያበራልህና እውነትን በውበቱ የሚያሳይህ እንደዚህ ያለ ብርሃን በልብህ ውስጥ ይወጣል። ማያያዣው ፍፁም በሆነ መልኩ የተገናኘ ልክ እንደ ወርቃማ ሰንሰለት የመሰለ ብርሃን የወጣላሃል።”—Testimonies for the Church, vol. 3, p. 448.
ለ. ብዙውን ጊዜ ቸልተኝነት የወቅቱን እውነት ተጽዕኖ የሚያዳክመው እንዴት ነው—መድኃኒቱስ ምንድን ነው? ኢሳይያስ 56:9፣ 10፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 14:8፤ ራእይ 3፡17-19
“የሦስተኛውን መልአክ መልእክት ሕዝቡን በማይማርክበት መንገድ የማቅረብ አደጋ ላይ ነን። በኃይል ሊሰበክ የሚገባው መልእክት ተራና ድምፅ አልባ እስከሆነ ድረስ ሌሎች ብዙ የማይረቡ መሻቶች በዚሁ መለዕክት ውስጥ ቦታውን ይይዛሉ።”—Ibid., vol. 6, p. 60.
“የምንኖረው በዚህች ምድር ታሪክ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ነው። በዚህ ዘመን አስፈላጊ የሆነውን መንፈሳዊ እድገት እንድንለማመድ ለመንፈሳዊ ፍላጎቶቻችን ብዙ ጊዜ መስጠት አለብን። ቆራጥ ማሻሻያ ማድረግ አለብን። ድምፁ እንዲህ ይላል፡- ጠባቂዎቹ መንቃት አለባቸው፣ መለከትንም ድምጽ ያሰሙ። ማለዳ ይመጣል፤ ደግሞም ምሽት። ንቁ፣ የእኔ ጠባቂዎች። እውነትን ሲያቀርቡ አሁን መሰማት የነበረባቸው ድምፆች ዝም ብለዋልና። ነፍሳት በኃጢአታቸው እየጠፉ፣ አገልጋዮችና ሐኪሞች፣ አስተማሪዎች ተኝተዋል። ጠባቂዎቹን አናንቃቸው!”—The Pacific Union Recorder, February 20, 1908.
“እውነተኛው ምሥክር ባለጸጋ እንደሆንክ ስታስብ፣ ገና ምንም ነገር እንደለሌህና ሁሉም ነገር እንደሚያስፈልግህ ይናገራል። ሚኒስትሮች እውነትን በቃል ብቻ ማቅረባቸው በቂ አይደለም፤ በተግባርም ማሳየት አለባቸው። ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸውን ተግባራዊ ትምህርቶች በማጥናት ለነፍሶቻቸው እና ለሰዎች ይህንኑ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ክርስቶስ ይህን የተግሣጽ ምስክርነት ስለሰጠ፣ ለሕዝቡ ርኅራኄ የሌለው ፍቅር እንደሌለው እናስብን? በፍፁም! ሰውን ከሞት ለመቤዠት የሞተው፣ በመለኮታዊ ፍቅር የወደዳቸውን፣ የሚወዳቸውንም ይገስጻል።”—Testimonies for the Church, vol. 3, pp. 257, 258.
ሐሙስ
ነሐሴ 02
5. ምድር ከክብሩ የተነሳ በራች
ሀ. የሱስ ወደዚህ ምድር ከመመለሱ በፊት የወቅቱ እውነት እንዴት እንደሚሰፋ እና እንደሚፋጠን ግለጽ። ራእይ 18:1-5
“[ራእይ 18:1, 2, 4] ይህ ጥቅስ በራእይ 14 (ቁጥር 8) ሁለተኛው መልአክ የተናገረው የባቢሎን ውድቀት ማስጠንቀቂያ የሚደግምበት ጊዜ እንደሚመጣ ያሳያል። ይህ መልእክት ለመጀመሪያ ጊዜ ከተላለፈ በ1844 የበጋ ወቅት ባቢሎንን፣ ወደተዋቀሩት የተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ እየገቡ ያሉትን ጥፋቶችን በተመለከተ ተጨማሪ ነገር መጥቀስ ይቻላል።”—The Great Controversy, p. 603.
ለ. አብዛኛው አለም የወቅቱን የእውነት መልእክት የማይመች አድርጎ ከሚመለከተው አንጻር ምግባራችን ልሆን እንዴት ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡12-16
“በእያንዳንዱ ልምዳችን ከእግዚአብሔር መማር አለብን። እርሱን በቅን ልብ ስንፈልገው የባሕርይ ጉድለቶቻችንን ለእርሱ እንናዘዛለን።እርሱም ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ በትህትና ለመቀበል ቃል ገብቷል። ለእግዚአብሔር የይገባኛል ጥያቄዎች ራሱን የሚያስገዛ ሁሉ የክርስቶስ መገኘት ይኖረዋል፣ እና ይህ አንድነት ለእርሱ በጣም ውድ ነገር ይሆናል። መለኮታዊውን ጥበብ በመያዝ በፍትወትም በዓለም ላይ ካሉት ጥፋቶች ሁሉ ያመልጣል።”—Testimonies to Ministers, p. 483.
“ወደ ክርስቶስ ስትመጡ ‘እኔ ቅዱስ ነኝ’ ብላችሁ አትመኩ። አንተ የራስህን ልብ ስለማታውቀው እግዚአብሔር ብቻውን ስለ አንተ ይናገር። ይህ ትምክህት ቅዱሳት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል እንደማታውቁ የተረጋገጠ ማስረጃ ነው። አንተ ታዛዥ፣ በደስታም ሥርዓቱን የምትጠብቅ መሆንህን፣ እግዚአብሔር በመጻሕፍቱ ይጻፍ፣ መዝገቦቹም በመላእክትና በሰዎች ፊት በታላቁ ቀን ይገልጣሉ።—The Signs of the Times, December 22, 1887.
አርብ
ነሐሴ 03
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. የወቅቱ እውነት ካለፈው ጊዜ የሚለየው እንዴት ነው?
2. በወቅቱ እውነት በመኖሬ በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂ የምሆነው ለምንድን ነው?
3. የወቅቱን እውነት ለሌሎች ማካፈል አስፈላጊ እንዲሆን የማደርገው ለምንድን ነው?
4. ለደማቅ ብርሃን ያለኝ አመለካከት መንፈሳዊ እድገቴ ላይ ተጸዕኖ የሚኖረው እንዴት ነው?
5. ተቃውሞ ሲያጋጥመኝ ቁርጥ ያለ ውሳኔዬ ምን መሆን አለበት?