እሁድ
ሰኔ 30
1. አስፈላጊ የክርስትና ጥራት
ሀ. እምነታችንን በትጋት ስንገነባ ምን እርምጃ እንወስዳለን? (2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:5)
“የወንጌልን እምነት ከተቀበልን በኋላ፣ የእኛ የመጀመሪያ ስራ በጎ እና ንፁህ መርሆችን ለማወቅ መፈለግ ነው፣ በዚህም እውነተኛ እውቀትን ለመቀበል አእምሮንና ልብን ማጽዳት ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 1, p. 552.
“ክፉን ለመቋቋም ሁል ጊዜ ንቁ መሆን የማያቋርጥ ትግል ነው። ነገር ግን በራስ እና በጨለማ ኃይሎች ላይ አንድን ድል ከሌላው እያስከተልን ስናገኝ ዋጋውን እናገኛለን። . . .
“ንፁህ፣ ያልተበላሸ በጎነት ከለሌው፣ ማንም ሰው ወደየትኛውም ክብር ከፍ ሊል አይችልም። የከበረ ምኞትና የጽድቅ ፍቅር በውርስ የሚገኝ ነገር አይደለም። ባሕርይን መግዛት አይቻልም፤ ፈተናን ለመቋቋም በከባድ ጥረቶች መፈጠር አለበት። የትክክለኛ ባሕርይ መመስረት የህይወት ዘመን ሙሉ ስራ ነው፣ ከታላቅ አላማ ጋር የተዋሃደ የፀሎት ማሰላሰል እድገት ዉጤት ነው። ያለህበት የባህርይ ልቀት የራስህ ጥረት ውጤት መሆን አለበት። ጓደኞችህ ሊያበረታቱህ ይችላሉ፣ ነገር ግን ስራውን ለአንተ ሊሰሩልህ አይችሉም። መመኘት፣ ማቃሰት፣ ማለም፣ መቼም ታላቅ ወይም ጥሩ አያደርግህም። መሰላሉን መውጣት አለብህ። የአዕምሮህን ወገብ ታጠቅ፤ እንዲሁም በፈቃድህ ኃይሎች ሁሉ ለመሥራት ተነስ።”—Fundamentals of Christian Education, p. 87.
ሰኞ
ሐምሌ 01
2. ለመዳን አስፈላጊ እውቀት
ሀ. ጴጥሮስ ወደለው መሰላል በመውጣት እንድናገኝ የተጠራንበትን የእውቀት አይነት ግለጽ። 2ኛ የጴጥሮስ 1:5 (የመጨረሻው ክፍል)፤ ዮሐንስ 17፡3
“ሐዋርያው በአማኞች ፊት የክርስቲያናዊ የፍጽምና መሰላልን አቅርቧል፣እያንዳንዱ እርምጃ በእግዚአብሔር እውቀት ቀጣይነት ያለው እድገትን የሚወክል፣ እና መውጣትም የማይቆም (የማያበቃ) ነው። . . .
“የወንጌልን እምነት ከተቀበልን በኋላ፣ የአማኙ ቀጣይ ስራ በባህሪው ላይ በጎነትን መጨመር እና በዚህም ልብን በማንጻት እና አእምሮን ለእግዚአብሔር እውቀት መቀበያ ማዘጋጀት ነው። ይህ እውቀት የእውነተኛ ትምህርት እና የእውነተኛ አገልግሎት ሁሉ መሰረት ነው። ከፈተና የሚጠብቀው ብቸኛው ትክክለኛ መከላከያ ነው፤ እናም አንድን ሰው በባህሪው እግዚአብሔርን እንዲመስል የሚያደርገው ይህ ብቻ ነው። በእግዚአብሔርና በልጁ በየሱስ ክርስቶስ እውቀት ለአማኝ 'ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚያስችለው ሁሉ' ተሰጥቷቸዋል። የአምላክን ጽድቅ ለማግኘት ከልብ የሚፈልግ ምንም ዓይነት ጥሩ ስጦታ አይከለከልም።”—The Review and Herald, September 19, 1912.
“ስለ ክርስቶስ መማር አለብን። እርሱ ለቤዣቸው ሰዎች ምን እንደሆነ ማወቅ አለብን። በእርሱ በማመን የመለኮት ተፈጥሮ ተካፋዮች መሆናችን ዕድላችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባናል፤ ስለዚህም በዓለም ካለው ፍትወት ማምለጥ አለብን። ያኔ ከኃጢያት ሁሉ፣ ከባሕርይ ጉድለት ሁሉ እንነጻለን። አንድም የኃጢያት ዝንባሌ እንኳ ልንይዝ አይገባንም። . . .
“ከመለኮታዊ ተፈጥሮ ስንካፈል፣ በዘር የሚተላለፍና ያዳበርነው የኃጢአት ዝንባሌዎች ከባህሪያችን ይቆረጣሉ፣ እናም ለበጎ ነገር ሕያው ኃይል እንሆናለን። ስለ መለኮታዊው መምህር ስለተማርን፣ በየቀኑ ከተፈጥሮው ተካፋዮች ስንሆን፣ የሰይጣንን ፈተናዎች ለማሸነፍ ከእግዚአብሔር ጋር እንተባበራለን። ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ እንደ ሆነ ሰው ከክርስቶስ ጋር አንድ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ይሠራል፤ ሰውም ለዚህ ዓላማ ይሠራል።”— The SDA Bible Commentary [E. G. White Com- ments], vol. 7, p. 943.
ለ. ለክርስቲያናዊ እድገት አስፈላጊ የሆነውን ሁለተኛ የእውቀት ዓይነት ጥቀስ። —መዝሙር 77:6፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5
“ከክርስቶስ እርዳታ ለማግኘት፣ የሚያስፈልገንን ነገር መገንዘብ (ማወቅ) አለብን። ስለራሳችን ትክክለኛ እውቀት ሊኖረን ይገባል። ክርስቶስ ማዳን የሚችለው ኃጢአተኛ መሆኑን ራሱን የሚያውቅ ሰው ብቻ ነው። የኛን ፍጹም አቅመ ቢስ መሆናችንን ስንመለከትና በራስ መተማመናችን ስንተው ብቻ መለኮታዊ ኃይልን እንይዛለን።”—Testimonies for the Church, vol. 8, p. 316.
ማክሰኞ
ሐምሌ 02
3. ራስን የሚቆጣጠር፣ ከቁጥጥር ውጪ አይደለም።
ሀ. በመንፈስ አነሳሽነት የወንጌል አስተማሪዎች የሚያስተምሩት በምን ጉዳይ ላይ ነው? ሥራ 24:24፣ 25፤ ፊልጵስዩስ 4፡5
“ስምንት ደረጃዎችን ባቀፈው በጴጥሮስ የመቀደስ ሂደት መሰላል ላይ ለአንድ ሰዓት ተኩል ያህል ለሰዎች ተናገርኩ። በቁጣ እና በአእምሮ፣ በሥነ ምግባራዊ እና በአካላዊ ጥንካሬ ወላጆች ልጆቻቸውን ራስን መካድ እና ራስን መግዛትን፣ የምግብ ፍላጎትን እና ጣዕሙን በመጠበቅ ልጆቻቸውን ማስተማር አስፈላጊነት ላይ አስተማርኩ።
“ራስን ስለመግዛት እና ራስን ስለመካድ ያሉት ትምህርቶች በትምህርትነት ደረጃ፣ በልጅነትና በወጣትነት ዕድሜ መወሰድ አለባቸው። መሻቶቻችን ሊገደቡና ሊሰለጥኑ ይገባል፣ ይህም በወላጆች ላይ የሚያተኩር ሃላፊነት ያለው ስራ ነው። ባለፉት ትውልዶች ውስጥ ያሉ ወጣቶች የህብረተሰቡን ሁኔታ ጠቋሚዎች ናቸው።
“ወላጆች ጠረጴዛውን ጤናማ በሆነ ምግብ በማሰራጨት፣ የሚያበሳጩና የሚያነቃቁ ንጥረ ነገሮችን በማስወገድ ረገድ ኃላፊነታቸውን ቢወጡ፣ በተመሳሳይም ልጆቻቸው ራሳቸውን እንዲገዙና ባህሪያቸውን እንዲያዳብሩ ቢያስተምሩ ኖሮ አሁን እንደ አንበሳ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚል ባሕርይ ያለዉን ወጣት ልንቆጣጠረው ጥረት ማድረግ አይጠበቅብንም ነበር። የመሻት ልማዶች ከተፈጠሩ እና በእድገታቸው ጋር አብሮ ካደጉና በጥንካሬያቸውም ጋራብረው ከጠነከሩ በኋላ ፣ በወጣትነት ጊዜ በትክክል ያልሰለጠኑ ሰዎች መጥፎ ልማዶቻቸውን ለማፍረስ፣ እራሳቸውንና ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ የምግብ ፍላጎታቸውን ለመግታት በጣም ከባድ ይሆንባቸዋል። እንዲህ ያሉትን ሰዎች ወደ ጉልምስና ሲደርሱ ማስተማር እና የክርስቲያናዊ ራስን መግዛትን አስፈላጊነት እንዲሰማቸው ማድረግ እንዴት ያለ ከባድ ነው! ራስን የመግዛት ትምህርቶች መጀመር ያለባቸው ሕጻናት ገና በእቅፍ ውስጥ ሲበሳጩ (ሲናወጡ) ነው።”—The Review and Herald, May 11, 1876.
ለ. በመሰላሉ ላይ ቀጥሎ ያለው ምንድን ነው - እና ለምን? 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:6 (የመጀመሪያው ክፍል)
“እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ህጉን እንዲጥስ ፍቃድ አይሰጥም። ነገር ግን ሰው ለሰይጣን ፈተናዎች በመገዛት ለእንስሳዊ ፍላጎትና መሻት በመገዛት ከፍተኛ ችሎታዎችን ያጣል፣ እናም እነዚህ ወደ ላይ ሲያድጉ፣ ሰው ከመላእክት ትንሽ ዝቅ ብሎ የተፈጠረው፣ ከተንከባከቡት ለከፍተኛ ችሎታዎች ላይ መድረስ የምችል አቅም ያለው፣ ለሰይጣን ቁጥጥር እጅ ይሰጣል። በዚህም ሰይጣን መሻትን በአለመግዛት እስራት ውስጥ ያሉትን በቀላሉ ማግኘት ይችላል። መሻትን በአለመግዛት፣ አንዳንዶች ግማሹን፣ ሌሎች ሁለት ሶስተኛውን የአካል፣ የአዕምሮና የሞራል ኃይላቸውን መስዋዕት ያደርጋሉ። የሰይጣንን ዘዴዎች ለማወቅ ንፁህ አእምሮ ያላቸው፣ ሥጋዊ ፍላጎታቸው በምክንያትና በኅሊና ቁጥጥር ሥር መሆን አለባቸው። የከፍተኛ የአእምሮ ኃይሎች ሥነ ምግባራዊና ጠንካራ እርምጃ ለክርስቲያናዊ ባሕርይ ፍጹምነት አስፈላጊ ነው።”—The Health Reformer, March 1, 1878
ረቡዕ
ሐምሌ 03
4. ትዕግስት፣ ራስን መግዛት ከለሌ የማይቻል ነው
ሀ. ራስን መግዛት በመሰላሉ ላይ ወደ ቀጣዩ አስፈላጊ የጥራት ደረጃ እንዴት ይመራል? 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1: 6 (መካከለኛው ክፍል)፤ ሉቃስ 21፡19
“የነርቭን እና የአንጎልን ኃይል ወይም አካላዊ ጥንካሬን የሚያዳክም ማንኛውም ልማድ ወይም ልምምድ ራስን ከመግዛት በኋላ ለሚመጣው የሚቀጥለው ጸጋ ልምምድ - ለትግስት- ብቁ አያደርገንም። . . .
“መሻትን መግዛት የማይችል፣ ስሜቶችን የሚያነቃቁ ማለትም ቢራ፣ ወይን፣ ጠንካራ መጠጦችን፣ ሻይንና ቡናን፣ ኦፒየምን፣ ትምባሆን፣ ወይም ከእነዚህ ውስጥ አንዱንም ለጤና ጠንቅ የሆኑ ነገሮችን የሚጠቀም፤ ታጋሽ ሰው ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ራስን መግዛት የትዕግስትን ጸጋ ከመጨመራችን በፊት እግሮቻችንን ማውጣት ያለብን የመሰላሉ ደረጃ ነው። በምግብ፣ በልብስ፣ በሥራ፣ በመደበኛ (በእንቅልፍ) ሰዓት፣ ጤናማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በትጋትና በጥረት ራሳችንን ከሕይወትና ከጤና ጋር መልካም በሆነ ግንኙነት እንድናደርግ ዘንድ የማግኘት ግዴታችን በሆነው እውቀት መመራት አለብን።—Our High Calling, p. 69.
ለ. ራስን መግዛት፣ ትዕግሥትን እንዲዳብር የሚረዳው እንዴት ነው—በምድር ታሪክ የመጨረሻ ቀናት ሁለቱም በጣም አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ራእይ 14:12
“የምግብ ፍላጎት በማርካት በጨጓራችን ላይ የሚደርሰው በደል የብዙዎቹ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች ፍሬያማዉ ምንጭ ነው። ፍላጎትን ባለመግዛትና ያለምክንያት የሚበሉና የሚሰሩ፣ እነዚያ ያለምክንያት የሚያወሩና የሚተገብሩ ናቸው (ይሆናሉ)። ራሱን የማይገዛ ሰው ታጋሽ ሊሆን አይችልም። ራሳችን ለመግዛት እንችል ዘንድ የአልኮል መጠጦችን መጠጣት አስፈላጊ አይደለም። መሻትን ያልገዛ አመጋገብ፣ ያለጊዜ መመገብ፣ አብዝቶ መመገብና በቅመም የበለጸገ ጤናማ ያልሆነ ምግብ የመመገብ ኃጢአት የምግብ መፍጫ አካላትን ጤናማ ተግባር ያጠፋል፣ አንጎልን ይጎዳል እና ፍርድን ያዛባል፣ ምክንያታዊ፣ የተረጋጋ፣ ጤናማ አስተሳሰብ እና ተግባር እንዳይኖር ይከላከላል። ይህ ደግሞ የተዋጣለት የቤተ ክርስቲያን የፈተና ምንጭ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰዎች በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ባለው ሁኔታ ውስጥ እንዲሆኑ፣ እርሱን በሥጋቸውና በመንፈሳቸው እንዲያከብሩት፣ በፍላጎት እና በቅንዓት መሻታቸውንና በነገር ሁሉ ራሳቸውን መግዛት አለባቸው። ከዚያም እውነትን በውበቱና በንጽህና ተረድታችሁ በሕይወታችሁ እንድትፈጽሙት ይሁን፤ እንዲሁም ፍትሐዊ፣ ጥበበኛና ቅን ጎዳና በመከተል የእምነታችንን ጠላቶች የእውነትን መንገድ የሚነቅፉበት አጋጣሚ አትስጧቸው።”—Testimonies for the Church, vol. 1, pp. 618, 619.
ሐሙስ
ሐምሌ 04
5. የትዕግስት እጅግ ያማረው ውጤት
ሀ. በውስጣችን ለማደግ የሚገባው የትዕግስት ልምምድ ምንድን ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡6 (የመጨረሻው ክፍል)።
“ትዕግሥት ማጣት ጠብንና ክስን ሐዘንንም ያመጣል። ነገር ግን ትዕግሥት የሰላምንና የፍቅር ስሜትን በቤት ውስጥ ባለን የሕይወት ልምዶች ውስጥ ያፈሳል። ውድ የሆነውን የትዕግስት ጸጋ ለሌሎች ስናሳይ፣ እነርሱም መንፈሳችንን ያንጸባርቃሉ፣ እኛም ከክርስቶስ ጋር እንሰበሰባለን። ትዕግስት በቤተክርስቲያን፣ በቤተሰብና በማህበረሰብ ውስጥ አንድነት እንዲኖር ይፈልጋል። ይህ ጸጋ ከሕይወታችን ጋር መሸመን (ድርና ማግ ልሆን) ይገባል። እያንዳንዱ ሰው በዚህ እድገት ደረጃ (እርከን) ላይ ከፍ ማለትና በእምነት ፣ በበጎነትና ራስን በመግዛት ፣ የትዕግስት ጸጋን መጨመር አለበት።
“ ‘በትዕግስትም እግዚአብሔርን መምሰል።’ እግዚአብሔርን መምሰል የክርስቲያናዊ ባህሪይ ፍሬ ነው። በወይኑ ግንድ ብንኖር የመንፈስ ፍሬዎችን እናፈራለን። የወይኑ ህይወት በቅርንጫፎቹ በኩል ይገለጣል። እግዚአብሔርን የመምሰል ጸጋ ከተሸከምን ከሰማይ ጋር የቅርብ እና የጠበቀ ግንኙነት ሊኖረን ይገባል። የእርሱን መልክ ካንጸባረቅንና የልዑል ወንዶችና ሴቶች ልጆች መሆናችንን ካሳየን የሱስ በቤታችን እንግዳ፣ የቤተሰባችን አባል መሆን አለበት። ሃይማኖት በቤት ውስጥ እጅግ የሚያምር ነገር ነው። ጌታ ከእኛ ጋር የሚኖር ከሆነ በሰማይ ያለን የክርስቶስ ቤተሰብ አባላት እንደሆንን ይሰማናል። መላእክቶች እንደሚመለከቱን እንገነዘባለን እናም ምግባራችን የዋህና ታጋሽ ይሆናል። ጨዋነትንና እግዚአብሔርን መምሰልን በማዳበር ወደ ሰማይ አደባባይ ለመግባት እንዘጋጃለን። ንግግራችን ቅዱስ ይሆናል፣ ሀሳባችንም በሰማያዊ ነገሮች ላይ ይሆናል።
“ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ። በሁሉም የሕይወት ጉዳዮች እግዚአብሔርን አከበረ። በቤቱና በሥራው፣ ‘ይህ በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋልን?’ ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርን በማሰብና ምክሩን በመከተል በባህሪው ተለወጠ እና አምላካዊ ሰው ሆነ፤ መንገዱም ጌታን ደስ አሰኘ።”—The Review and Herald, February 21, 1888.
አርብ
ሐምሌ 05
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. ንቁ እና ቋሚ ክርስቲያናዊ በጎነቶችን ማዳበር ለምን አስፈለገኝ?
2. አምላክን የበለጠ ማወቅ የምችለው እንዴት ነው? ይህስ በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
3. በየትኞቹ የሕይወቴ ዘርፎች የበለጠ ራስን መግዛት አለብኝ?
4. ጠበኛና ተንኮለኛ በሆነው ኅብረተሰብ ውስጥ ትዕግሥት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
5. በሄኖክ ምሳሌ እንደተገለጸው እግዚአብሔርን መምሰል የትና እንዴት ነው የተገለጠው?