እሁድ
ነሐሴ 19
1. የአመለካከት ችግሮች
ሀ. ጴጥሮስ የሐሰተኛ አስተማሪዎችን እጣ ፈንታ የገለፀው እንዴት ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 2፡17፣20
“ከቤተ ክርስቲያን ለተነሱ፣ እና በብዙ የእምነት ወንድሞች እውነተኛ ተደርገው የተቆጠሩ ሐሰተኛ አስተማሪዎችን፣ ሐዋርያው ‘ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም ከተጠበቀላቸው፣ ውኃ ከሌለባቸው የምንጭ ጕድጓዶች፣ በዐውሎ ነፋስ ከተነዱ ደመናዎች ጋር አነፃጽሮ አቀረባቸው። 'ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ መጨረሻቸው የከፋ ነው' በማለት ገልጧል።”—The Acts of the Apostles, p. 535.
ለ. ሌሎች ዝቅ አድርገው ሲመለከቱን ወይሞ ትዕግስታችንን ሊያስጨርሱን ሲፈትኑን በሳል አመለካከት እንድንይዝ እና ጥበብ የተላበሰ ሞርጫ መወሰን እንችል ዘንድ ሊረዱን ዪችሉት ጊዜ የማይሽራቸው ቃላት የትኞቹ ናቸው? መክብብ 7፡8።
“ብዙዎች ሙገሳና አድናቆትን ይወዳሉ እናም ጥቃቅን እንከኖችን ወይም ችላ መባልን በአይነ ቁራኛ ይከታተላሉ። በዚህ ደረቅ የሆነ፣ ይቅር የማይል መንፈስ አለ። ምቀኝነት፣ ጥል፣ በልጦ ለመገኘት ፉክክር አለ። . . .
“የመጀመሪያ (አንደኛ) ለመሆን እጅግ በጣም በተጣጣርክ ቁጥር፣ የዋህ እና ትሑት መንፈስን መንከባከብ እስካልቻልክ ድረስ፣ በአምላክ ሞገስ የመጨረሻ እንደምትሆን አስታውስ። ብዙዎች ስኬታማ መሆን ሲችሉ የልብ ኩራት እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል። 'ከክብር በፊት ትሕትና ትቀድማለች' ፤ እናም 'በመንፈሱ ትዕግሥተኛ የሆነ ሰው በመንፈሱ ከታበየው (ኩሩ ከሆነው) ይበልጣል'።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 50.
ሰኞ
ነሐሴ 20
2. አንዳንድ አስደሳች ምሳሌዎች / ማሳያዎች
ሀ. ጴጥሮስ እኛን ለማንቃት እንደማጣቀሻ አድርጎ የገለፀው ምንድን ነበር ? ምሳሌ 26:11; 2ኛ ጴጥሮስ 2፡20-22
“ዓለም ለጥፋቷ ጎምርታለች። እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ታግሶ ሊቆይ የምችለው በጣም ለትንሽ ጊዜ ነው. . .። ከምህረት ጋር ሳይደባለቅ የተዘጋጀውን የቁጣውን ጽዋ መጠጣት አለባቸው። . . . በየሱስ የማያፍር፣ በጌታ ጎን የቆመው ማን እንደሆነ በቅርቡ ይታወቃል። የዓለምን ፋሽን ትተው ራሱን የካደውን የክርስቶስን ሕይወት ለመኮረጅ የሞራል ድፍረት የሌላቸው፣ በእርሱ ያፍራሉ እንዲሁም የእርሱን አርያነቱን ሊያፈቅሩት አይችሉም።”—Testimonies for the Church, vol. 1, p. 287.
ለ. በተመሳሳይም ከእርሱ ጋር ያለንን ትሑት እና ጥገኛ ትስስር አጥብቆ ከመያዝ እንዳንወድቅ ክርስቶስ ያስጠነቀቀን እንዴት ነው? ሉቃስ 11፡24-26
“የተጌጠው ቤት በራስ-ጽድቅ የተሞላውን ነፍስ ይወክላል። ሰይጣን በክርስቶስ ተባርሯል። ነገር ግን መግቢያ አገኛለው በሚል ተስፋ ተመለሰ። ሲመለስም ቤቱን ባዶ ሆኖ፣ ተጠርጎ እና አጊጦ አገኘው። እዚያ ቦታ ያለው የራስ-ጽድቅ ብቻ ነበር።
‘ከዚያም ሄዶ ከእርሱ የከፉትን ሌሎችን ሰባት አጋንንት ከእርሱ ጋር ይይዛል ፤ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል’።
“የራስ-ጽድቅ ሰይጣን ለክብሩ የሚጠቀምበት፣ የሰብዓዊነት ማስዋቢያ እርግማን ነው። ነፍስን በራሳቸው ክብርና ሽንገላ የሚያጌጡ ከፊተኛው ለበለጠ ለሰባቱ መናፍስት መግቢያ በሩን ያዘጋጃሉ። እውነትን ሲቀበሉ እነዚህ ነፍሳት ራሳቸውን ያታልላሉ። እነርሱ በራሳቸው የጽድቅ መሠረት ላይ እየገነቡ ናቸው። የጉባኤ ጸሎቶች ድግግሞሽ ባለው ሥርዓት ወደ እግዚአብሔር ሊቀርቡ ይችላሉ ፤ ነገር ግን በራስ ጽድቅ የሚቀርቡ ከሆነ እግዚአብሔር በእነርሱ አይከበርም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- ‘ ጽድቅህንና ሥራህን እናገራለሁ ፤ እነርሱ ለአንተ አይጠቅሙህምና’። ምንም እንኳ ያ ሁሉ ታይታና ድምቀት (ሽር ጉድ) ቢኖርም፣ በተጌጠው መኖሪያቸው፣ ሰይጣን ከነክፉ የመላዕክቱ ጭፍራው ጋር በመምጣት በማታለሉ ይረዳው ዘንድ በነፍስን ውስጥ ስፍራን ይወስዳል፡፡ ሐዋርያው እንዲህ ሲል ጽፏል፡- “በጌታና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ከሆኑ ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስባቸዋል። አውቀው ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት ይሻላቸው ነበርና’’።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 5, p. 1093.
ማክሰኞ
ነሐሴ 21
3. በእምነት መቀጠል
ሀ. በክርስቶስ "እንዲንቀጥል" በገልጽ የተነገረን ለምንድን ነው ? ቆላስይስ 1፡21-23
“በግዛቱ ሥር ለመግባት ሆን ብለን የጨለማውን መንግሥት አስተዳደር መምረጥ የለብንም። ከብርሃን መንግስት ጋር ያለንን ግንኙነት ለማቋረጥ አንዷን መርህ መጣስ ብቻ በቂ ነው። ከሰማያዊ ወኪሎች ጋር የማንተባበር ከሆነ ሰይጣን ልብን ይቆጣጠርና መኖሪያው ያደርገዋል። ከክፉ መከላከያ ብቸኛው መንገድ ክርስቶስ በልብ ላይ በሃይማኖት ማደሩ ነው። ከእግዚአብሄር ጋር ሙሉ በሙሉ እስካልተሳሰርን ድረስ፣ የራስ-ወዳድነትን፣ የራስ-ደስታን እና ያልተቀደሰ የኃጢአት ፈተና ተጽዕኖን መቋቋም አንችልም። ብዙ መጥፎ ልማዶችን ልንተው፣ ከሰይጣን ጋር ያለንን ህብረት ልናቆም እንችል ይሆናል። ነገር ግን ራሳችንን ለእርሱ አሳልፈን በመስጠት በእያንዳንዱ ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር ወሳኝ ግንኙነት ከሌለን፣ እንሸነፋለን። ከክርስቶስ ጋር የግል ትውውቅ እና ቀጣይነት ያለው ኅብረት ካልፈጠርን፣ በጠላት እጅ እንወድቃለን ፤ በመጨረሻም እርሱን ትዕዛዝ እንፈጽማለን።”—The Desire of Ages, p. 324.
ለ. መረዳት ያለብንን በየሱስ የምናገኘውን የጽድቅ በሃይማኖትን ሚዛናዊ ውህደት አስረዳ። ሮሜ 3፡24–26; ዕብራውያን 6:4–6; 10:26, 27
“በሰዎች መካከል በተመላለሰ ጊዜ ድውያንን የፈወሰ፣ አጋንንትን ያወጣ እርሱ፣ ዛሬም ያው ኃያል አዳኝ ነው። እምነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር ቃል ነው። ከዚያም 'ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ አላወጣውም' በማለት የገባውን የተስፋ ቃል አጥብቃችሁ ያዙ (ዮሐንስ ወንጌል 6፡37)፡፡ ‘ጌታ ሆይ፣ አምናለሁ፣ አለማመኔን እርዳኝ’ በማለት በለቅሶ በእግሩ ሥር ራሳችሁን ጣሉ። ይህን ካደረጋችሁ በፍፁም አትጠፉም—በፍጹም።”—Ibid., p. 429.
“ኃጢአተኛው ወደ ሕጉ ሲመለከት፣ የሰራው በደል ግልጽ ይሆንለታል፣ ወደ ህሌናውም ዘልቆ ይሰማዋል፣ ይፈረድበታል። የእርሱ ብቸኛ ሰላም እና ተስፋ ሊገኝ የሚችለው ወደ ቀራንዮ መስቀል በመመልከት ብቻ ነው። እግዚአብሔርን በቃሉ ይዞ የተስፋ ቃሉን ሲጨብጥ፣ እፎይታ እና ሰላም ወደ ነፍሱ ይመጣል። እንዲህ ሲል የለቅሶ ጩኸቱን ያሰማል፡-‘ጌታ ሆይ፣ በልጅህ ስም ወደ አንተ የሚመጡትን ሁሉ ለማዳን ቃል ገብተሃል። እኔ የጠፋሁ፣ ረዳተ ቢስና ተስፋ የለለኝ ሰው ነኝ። ጌታ ሆይ አድነኝ ፤ ያለዚያ በቃ መጥፋቴ ነው’። እምነቱ ክርስቶስን አጥብቆ ይይዛል፣ በእግዚአብሔርም ፊት ፃድቅ ሆኖ ይቆጠራል (ይጸድቋል)።
“ነገር ግን እግዚአብሔር ጻድቅና ኃጢአተኛውንም በክርስቶስ ቸርነት ሊያጸድቅ ቢችልም፣ ማንም ሰው የታወቁ ኃጢአቶችን እየሠራ ወይም የታወቁ ሥራዎችን ችላ እያለ ነፍሱን በክርስቶስ የጽድቅ ልብስ ሊሸፍን አይችልም። ጽድቅ ህይወት ከመከናወኑ (ተግባራዊ ከመደረጉ) በፊት ሙሉ በሙሉ ልባችንን እናስረክበው ዘንድ እግዚአብሔር ይጠይቃል። ሰው ጽድቅን የራሱ ማድረግ (መውረስ) ይችል ዘንድ፣ በፍቅር በሚሰራና ነፍስን በሚያነጻ ንቁና ሕያው እምነት አማካኝነት የማያቋርጥ መታዘዝ ሊኖር የግድ ነው። ”—Selected Messages, bk. 1, pp. 365, 366.
ረቡዕ
ነሐሴ 22
4. እስከ ብርሃን መኖር
ሀ. ከሰማይ በተላከልን በተትረፈረፈ ብርሃን የተባረክን እንደመሆናችን፣ ስለ መዳናችን ጉዳይ እጅግ በጣም ጥንቅቁዎች ከሆንን ሁልጊዜም ቢሆን ከአዕምሯች መያዝ ያለብን ነገር ምንድን ነው? ያእቆብ 4:17
“ሰዎች ስለ ጤና ጉዳይ ሲናገሩ ብዙ ጊዜ 'ማወቅ ካለብን ነገር የበለጠ ብዙ እናውቃለን' ይላሉ። በአካላዊ ደህንነታቸው ረገድ ለእያንዳንዱ የብርሃን ጨረሮች ተጠያቂ መሆናቸውን እና እያንዳንዱ ልማዳቸው ለእግዚአብሔር ምርመራ በግልጽ የሚታይ መሆኑን አይገነዘቡም፡፡ አካላዊ ሕይወት ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ እንደነገሩ ሊታከም አይገባም። እያንዳንዱ የአካል ክፍል፣ ማንኛውም የአካል ጥቃቅን ክፍሎች፣ ከጎጂ ልማዶች በታላቅ ጥንቃቄ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል።”—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 372
ለ. ተሐድሶ (ጤና አንድ ምሳሌ ሆኖ) እጅግ በጣም በሚያስፈልባቸው በበርካታ በወቅቱ እውነት በርካታ ዘርፎች (ገጽታዎች) ላይ የዕለት ተዕለት ውሳኔዎቻችን የሚያስከትሉት የውጤት አድሳቸው ምን ያህል ስፋት ይኖራቸው ይሆን? ሮሜ 14:21 ፤ ኤርምያስ 13:20
“የጤና ተሐድሶ ርዕሰ ጉዳይ በአብያተ ክርስቲያናት ቀርቧል ፤ ብርሃኑ ግን ከልብ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ የወንዶችና የሴቶች ራስ ወዳድነት፣ ጤናን የሚያበላሹ ድርጊቶች ሕዝቡን ለእግዚአብሔር ታላቅ ቀን ማዘጋጀት የሚለውን የመልእክቱን ተጽእኖ ተቋቁመዋል። አብያተ ክርስቲያናት ጥንካሬን የሚጠብቁ ከሆነ, እግዚአብሔር የሰጣቸውን እውነት መኖር አለባቸው. የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን ብርሃን ችላ ካሉ፣ በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ውድቀት ውስጥ ትክክለኛውን ውጤት ያጭዳሉ። እናም የእነዚህ አረጋውያን የቤተ ክርስቲያን አባላት ተጽዕኖ አዲስ ወደ እምነት የሚመጡትን ያቦካቸዋል። ጌታ አሁን ብዙ ነፍሳትን ወደ እውነት ለማምጣት አይሠራም ምክንያቱም በቤተክርስቲያኑ አባላት ምክንያት ያልተለወጡ እና አንድ ጊዜ የተለወጡ ነገር ግን ወደ ኋላ የተመለሱት. እነዚህ ያልተቀደሱ አባላት በአዲሶቹ አማኞች ላይ ምን ተጽእኖ ይኖራቸዋል? አምላክ ሕዝቡ ሊያስተላልፉት የሚገባውን መልእክት ከንቱ አያደርጉምን?”—ኢቢድ. ገጽ 370, 371
ሐ. በዛሬው ጊዜ ከሰማይ የተላከ ብርሃን በተሰጣቸው ሁሉ ላይ የሚደርሰውን ከባድ ኃላፊነት ግምት ውስጥ በማስገባት በአሁኑ ጊዜ ምን ልባዊ ጥሪ ይቀርብልናል? ኤርምያስ 3:12፣ 13፤ መዝሙረ ዳዊት 32:5
ሐሙስ
ነሐሴ 23
5. ወደ ፊት መበርታት
ሀ. በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ለምትኖረው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ ተገቢ የሆኑ ተማጽኖዎችን ግለጽ። ዕብራውያን 5:13፣ 14፤ 6:1፤ ፊልጵስዩስ 2:14፣ 15
“በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ሁሉ ለአገልግሎት መታደስና መቀደስ ሊኖር ይገባል። ለወደፊትም በስራችንና በምናካሂደው ስብሰባዎች ላይ አንድ ልብ መሆን አይገባምን? መንፈስ ቅዱስ ወደ ልብ ሁሉ እንዲገባ በመጠየቅ ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት አንታገልምን? በመካከላችን የተገለጠው የክርስቶስ መገኘት አገልግሎታችንን ደካማና ቅልጥፍና የጎደለው እንዲሆን ያደረገውን የአለማመንን ደዌ ይፈውሳል። የመለኮታዊ ህይወት እስትንፋስ ወደ እኛ እንዲተነፍስ እንፈልጋለን። ጌታ ብርሃንንና ጸጋን ለአለም የሚልክበት መስመር መሆን አለብን። ወደ ኋላ ተንሸራታቾች ሊመለሱ ይገባል። ኃጢያታችንን ማስወገድ ያለብን በመናዘዝ እና በንስሐ ኩራተኛዉን ልባችንን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ነው። ለመቀበል በተዘጋጁት ላይ የመንፈሳዊ ኃይል ዝናብ ይዘንባል።”—Testimonies for the Church, vol. 8, p. 46. [Author’s emphasis.]
“የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች፣ ሥራችሁ ምንም ይሁን ምን ለክርስቶስ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ። አሁን ያሉትን ወርቃማ እድሎች አትዘንጉ እንዲሁም እግዚአብሔር ገጣሚ ያላደረገህን ስራ በቀላሉ በምቾትና በስኬት አከንውነዋለሁ ብለህ እያሰብክ ተቀምጠህ ህይወትህ ውድቀትን እንዲያሳይ አታድርግ። በአቅራቢያህ ያለውን ሥራ ስራው። በሚስዮናዊነት መስክ ውስጥ በአደጋዎችና በችግር ውስጥ ቢሆንም፣ ሥራ፤ ነገር ግን ስለ መከራና ስለ መስዋዕትነት እንዳታጉረመርም እለምንሃለሁ። ዋልደንሶችን ተመልከት። የወንጌል ብርሃን ላልደረሳቸው አእምሮ እንዲበራ ምን ምን እቅድ እንዳዘጋጁ ተመልከት። በዚህ ህይወት ሽልማታችንን ለማግኘት ብለን መድከም የለብንም፣ ነገር ግን በሩጫው መጨረሻ ላይ ባለው ሽልማት ዓይኖቻችን በማትኮር መስራት አለብን። በአሁኑ ጊዜ የሚፈለጉ ወንዶችና ሴቶች ልክ የኮምፓስ መጠቆሚያ መርፌ ለምድር ዋልታ ታማኝ እንደሆነው ያህል ለሥራው ታማኝ የሆኑ ወንዶችና ሴቶች ናቸው፣ መንገዳቸው ሳይስተካከልና እንቅፋት ሁሉ ሳይወገድ የሚሠሩ ወንዶችና ሴቶች ናቸው።”—Colporteur Ministry, pp. 68, 69.
አርብ
ነሐሴ 24
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. አንድ ሰው እኔን የማያደንቅ መስሎ ከታየኝ በጣም መጥፎ ግምት እሰጠዋለሁኝን?
2. በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ራስን ማጽደቅ የሚገለጠው በምን መንገዶች ነው?
3. በክርስቶስ ደም በማመን መጽደቅን እንዴት ማግኘት እና በእርሱ መኖር እችላለሁ?
4. የማውቀውን በተሻለ ለማንፀባረቅ በየትኞቹ የሕይወት ዘርፎች መሥራት ያስፈልገኛል?
5. ቅሬታ ለማቅረብ (ለማማረር) ስፈተን ምን ማስታወስ አለብኝ?