Back to top

Sabbath Bible Lessons

ትምህርት ከጴጥሮስ መልእክቶች (II)

 <<    >> 
  ሰንበት፣ ሐምሌ 27፣ 2016

የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ ለጄነራል ኮንፈራንስ ትምህርት ክፍል

ትምህርት፣ ልክ እንደ መቀደስ፣ የህይወት ዘመን ስራ፣ የሰው ልጅ ልምድ ውስጣዊ አካል ነው። በዚህ ሰንበት ይህንን የቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ አካል ተደራሽነቱን ለማስፋት እንድትረዱን እንጠይቃለን።

ሚስዮናውያን መሆንን ከመጀመሪያዎቹ ዓመታት መማር አለብን። "እያንዳንዱ እውነተኛ ደቀ መዝሙር እንደ ሚስዮናዊ ሆኖ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ይወለዳል" (The Desire of Ages,p. 195) "ልጆችህንም አጥብቀህ አስተምራቸው፥ በቤትህም ስትቀመጥ ፥ በመንገድም ስትሄድ ፥ ስትተኛም ስትነሣም ተናገርአቸው" ( ዘዳ 6፡7)። እናም ድሉ ከተጠበቀ፣ እና ኃጢያት እና ኃጢአተኞች በማይኖሩበት ጊዜ፣ የትምህርት ስራ ይቀጥላል።

ቤተ ክርስቲያናችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አሁን ወላጆች ለልጆቻቸው ተገቢውን የትምህርት መሠረት ለመመሥረት፣ ወጣቶች በእግዚአብሔር ፈቃድ እውቀት ማደግ የሚችሉበት፣ አዋቂዎችም እየበለጸጉ የሚሄዱባቸውን ቁሳቁሶች ለማቅረብ ዝግጁ መሆን አለባት።

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ አብዛኞቹ የትምህርት ተቋማት መሰረታዊ ትምህርቶችን ከማስተማር ይልቅ የዓለማዊነት ማስተማሪያ ማዕከላት ሆነዋል። ብዙዎች፣ ትምህርት በልጆቻቸው ላይ ምን ያህል ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በመገንዘባቸው ለልጆቻቸው የአምላክን ክብር ለማስተማር የሚረዱ ቁሳቁሶችን ጠይቀዋል።

ስለዚህ የጂ.ሲ. ትምህርት መምሪያ ዓላማውና ትኩረቱ አድርጎ አጠቃላይ ሥርዓተ ትምህርት እያዘጋጀ ነው። ከአስተማሪዎቻችን እና ከተለያዩ ማህበራት እና የፊልድ ኮንፈረንሶች ጋር በመተባበር ይህንን ስርዓተ-ትምህርት የማዘጋጀት ስራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።

ሆኖም ፕሮጀክቱ አሁን ካለን አቅም በላይ ነው። ቁሳቁሶቹን ለማዘጋጀት፣ ለመተርጎምና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የእናንተን ለጋስ አስተዋጾ እንፈልጋለን። በየትምህርት ቤታችን እና በቤታችን ትምህርት ቤቶች የሚጠቀሙት ተማሪዎች “ለዚህ ህይወት ጠቃሚ እና ለዘለአለም ለእግዚአብሔር አገልግሎት ብቁ እንዲሆኑ” ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቁሳቁሶች እንድናዘጋጅ የእርስዎ ድጋፍ ያስችለናል።—Counsels to Parents, Teachers, and Students, p. 495.

ይህ ፕሮጀክት ትልቅ እንደሆነ እንገነዘባለን፣ ነገር ግን በጣም አስፈላጊ ነው። በእናንተ ድጋፍ የወንጌልን መልእክት ለአለም ሁሉ በብቃት ለማድረስ ከእኛ መካከል ታናናሾቹን ለማስታጠቅ ቁሳቁሶችን እናዘጋጃለን።

አስቀድሜን እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ስጦታዎችንና ሰጭዎችን ይባርክ!

ለጄነራል ኮንፈራንስ ትምህርት ክፍል

 <<    >>