እሁድ
መስከረም 05
1. የማይቀር፣ የማይነቃነቅ
ሀ. የመጨረሻው ማስፈፀሚያ የሚገለፀው እንዴት ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 3፡10
“በ1000 ዓመታት መጨረሻ ወቅት ኃጢአተኛ ሙታን በአካል ተነስተው ከመጥፋታቸው በፊት አዲሱ ሰማይና አዲስ ምድር፣ ( ራእይ 21: 1 ኢሳ 65: 17 ፤ 2 ጴጥ 3: 13) አይገለጡም። በ1000ዎቹ ዓመታት መጨረሻ ማለትም ክፉዎቹ ሙታን በሚነሱበት በዚያው ወቅት ‘ከእስራቱ መፈታቱን’ አየሁ ፤ ሰይጣን ቅድስቲቱን ከተማ ከቅዱሳን እጅ መንጠቅ እንደሚችሉ በማሳመን ሰይጣን ሸነገላቸው። ከዚያም ክፉዎች በሰይጣን መሪነት ‘በቅዱሳን ሰፈር’ ዙሪያ ገሰገሱ። እናም ከተማይቱንም ለመያዝ ጥረት ለማድረግ በተዘጋጁ ጊዜ ሁሉን ቻዩ አምላክ ከፍ ካለው ዙፋኑ፣ በከተማይቱ ላይ፣ የሚባላን የእሳት እስትንፋስ እፍ አለባቸው ፤ በላያቸውም ወርዶ ‘ሥርና ቅርንጫፍ’ ሳያስቀር ጨርሶ በላቸው።
“ ክርስቶስ የወይኑ ግንድ እንደ ሆነ ልጆቹም ቅርንጫፎች እንደ ሆኑ፣ እንዲሁም ሰይጣን 'ሥሩ' ልጆቹ ደግሞ 'ቅርንጫፎች' መሆናቸውን አየሁ፡፡ እናም ‘ጎግና ማጎግን’ በሚያጠፉው በመጨረሻው ጥፋት ወቅት መላው የክፉ ሠራዊት ‘ሥሩና ቅርንጫፍ’ ሳይቀርላቸው ይቃጠላሉ ፤ ከህልውናም ይፋቃሉ (ህልውናቸውም ያከትማል)።”— A Word to the Little Flock, pp. 11, 12.
ሰኞ
መስከረም 06
2. ምድር በእሳት ፀዳች (ትፀዳለች)
ሀ. የብሉይ ኪዳን ነቢያት የመጨረሻውን የክፋት ጥፋት እና የምድርን መንጻት አስቀድሞ የተመለከቱት እንዴት ነበር? ኢሳይያስ 34:8-10; ሕዝቅኤል 28:16-19
“እሳት ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወረደ። ምድር ተሰባበረች፤ በውስጥዋ የተደበቁት መሳሪያዎች ወደ ላይ ወጡ፡፡ ሚፋጁ ነበልባሎች ከእያንዳንዱ ከተከፈተ የምድር ገደል ወጡ፡፡ ቋጥኞች ራሳቸው ተቃጠሉ። እንደ ምድጃ እሳት የሚያቃጥለው ቀን መጥቶአል። የሰማይ ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ቀለጠ ፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ተቃጠለ (ሚልክያስ 4:1 ፤ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡10)፡፡ የምድር ፊት አንድ የቀለጠ ግዙፍ አካል መሰለ¬¬¬¬—ሰፊና የሚፈላ የእሳት ሐይቅ። የፍርድ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን የማይመስሉ ሰዎች መጥፊያ ሰዓት ነው— ‘የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን’ ነው። . . .
“ክፉዎች ፍዳቸውን (ዋጋቸውን) በምድር ተቀበሉ (ምሳሌ 11፡31)፡፡ 'ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር' (ሚልክያስ 4:1)፡፡ አንዳንዶች በቅጽበት ሲጠፉ፣ ሌሎች ደግሞ ለብዙ ቀናት ተሰቃዩ። ‘እንደ ሥራው’ መጠን ሁሉም ተቀጡ። የጻድቃን ኃጢአት ወደ ሰይጣን ተላለፈና ስለራሱ አመፅ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ሕዝቦች እንዲሠሩት ባደረገው ኃጢአት ሁሉ ልክ እንዲሰቃይ ተደረገ። የእርሱ ቅጣት፣ ካሳታቸው ይልቅ እጅግ የበዛ ነው። በተንኮል ያታለላቸው ሁሉ ከጠፋ በኋላ፣ እርሱ በህይወት ሆኖ ይሰቃይ ዘንድ የግድ ይለዋል፡፡ በስተመጨረሻ ኃጢአን ሥርና እና ቅርንጫፍ፣ በሚያፀዳው ነበልባል ጠፉ — ሥሩ ሰይጣን፣ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ተከታዮቹ፡፡የሕጉ ሙሉ ቅጣት ተሟልቷል ፤ የፍርድ ጥያቄም ተሟልተዋል ፤ ሰማይና ምድርም፣ እያዩ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አወጁ። ”—The Great Controversy, pp. 672, 673. (ታላቁ ተጋድሎ አማርኛው ገጽ 767፣ 768)
ለ. የእግዚአብሔርን ቀጣይ እርምጃ ውበት ግለጽ። ራእይ 20:7-10, 15; 21:1, 2።
“እግዚአብሔር በመጨረሻ ምድርን ሲያነጻ፣ ምድር ወሰን እንደሌለው የእሳት ባሕር ትመስላለች። እግዚአብሔር በጥፋት ውኃ ንውጠት መካከል ስምንት ጻድቃን ሰዎችን በመያዙ መርከቡን እንደጠበቀ ሁሉ፣ እንዲሁም ከጻድቁ አቤል ጀምሮ በህይወት እስከኖረው እስከመጨረሻው ቅዱስ ድረስ፣ በሁሉም ዘመናት የሚገኙ ታማኞ ቅዱሳንን የያዘችውን አዲሲቷን የሩሳሌምን ከእሳቱ ይጠብቃታል። ምንም እንኳን ከተማዋ ካረፈችበት ክፍል በስተቀር መላዋ ምድር በፈሳሽ እሳት ባህር ውስጥ ብትጠቀለልም፣ ከተማይቱ ግን ልክ እንደ ታቦቱ በሁሉን ቻይ ሃይል ተአምር ትጠበቃለች። በአውዳሚው የእሳት ሃይል መካከል ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ፀንታ ትቆማለች። ”— Spiritual Gifts, vol. 3, pp. 87, 88.
ማክሰኞ
መስከረም 07
3. አሳሳቢው እውነታ
ሀ. በምድር ነዋሪዎች ላይ የሚመጣው የመጨረሻውና የመጨረሻው እውነታ ምን እንድናስብ ሊያደርገን ይገባል? መዝሙር 139:23፣ 24 ፤ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡11
“እውነት በልባችን እና በህይወታችን ላይ ቀዳሽ ተጽእኖ ሲኖረው፣ ለእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው አገልግሎት ማቅረብ እንችላለን፣ እርሱንም በምድር ማስከበር እንችላለን፡፡ የመለኮታዊ ባህርይ ተካፋዮች በመሆን እና በምኞት የተነሳ ከተንሰራፋው በዓለም ካለው እርኩሰት አምልጠን በምድር ላይ እሱን ማክበር እንችላለን።
“ኦህ፣ ጌታቸው ባሪያዎቹን ሊቆጣጠር በመጣ ጊዜ፣ ሳይዘጋጁ የሚያገኛቸው ስንቶች ይሆኑ! ብዙዎች ክርስቲያንነት ምን ማለት እንደሆነ ያላቸው ሃሳብ ቁንጽል ነው። በዚያኔ የራስ-ጽድቅ አንዳች ዋጋ አይኖረውም፡፡ የክርስቶስን ፅድቅ ተጎናጽፈው የተገኙ፣ በመንፈሱም የተሞሉ እና በልብ እና በህይወት ንፅህና እርሱ እንደተመላለሰ መመላለስ የቻሉ ብቻ ፈተናውን መቋቋም ይችላሉ፡፡ ንግግራችን የተቀደሰ መሆን አለበት፣ በዚያኔ ቃላቶቻችን በጸጋ ይቀመማሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 317, 318
ለ. በአስቸኳይ የሚያስፈልገንን ጥልቅ ቅድስና ያብራሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡6
“እውነትን በእውነት የምታምን ነፍስ ሁሉ ተዛማጅ ስራዎች ይኖራታል። ሁሉም ትጉ እና የተከበሩ ይሆናሉ እንዲሁም ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ ለማሸነፍ በሚያደርጉት ጥረት የማይታክቱ ይሆናሉ። እውነት በመጀመሪያ በነፍሳቸው በጥልቅ ከተተከለ፣ ይኸውን እውነት በሌሎች ልብ ለመትከል ይፈልጋሉ፡፡ እውነት በውጫዊ ክፍል በይበልጥ ተጠብቆ ቆይቷል። ይህን እውነት ወደ ውስጠኛው የነፍስ ውስጣዊው መቅደስ አስገቡት፣ በልብ ዙፋንም ላይ አስቀምጡት ፤ ከዚያም ህይወትን ይቆጣጠር ዘንድ ፍቀዱለት። የእግዚአብሔር ቃል ሊጠና እና ልታዘዙት ይገባል ፤ ከዚያም ልብ እረፍትን፣ ሰላምን እና ደስታን ያገኛል ፤ ይህም ሲሆን ምኞት ወደ ሰማይ ያተኮረ ይሆናል ፤ ነገር ግን እውነት ከሕይወት ተለይታ በውጫዊው ላይ ብቻ ከሆነ፣ ልብ በሚንበለበለው በእግዚአብሔር የመልካምነት እሳት ላይ መሞቅ አይችልም።
“ በብዙዎች ዘንድ የየሱስ ሃይማኖት ለተወሰኑ ቀናት ወይም ለተወሰኑ አጋጣሚዎች የሚጠበቅ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ ችላ ተብሎ ወደ ጎን የሚገፈተር ነው። ሁልጊዜም የሚኖረው የእውነት መርህ ለሰንበት ቀን ጥቂት ሰዓታት ወይም ለጥቂት የበጎ አድራጎት ተግባራት ብቻ የሚውል ሳይሆን ነገር ግን ባህርይን እንዲያነጻና እንዲቀድስ ወደ ልብ ውስጥ ዘልቆ መግባት አለበት፡፡ የሰው ልጅ ከሰማይ ያለዚህ ልዩ ብርሃንና ብርታት ሳይላክለት የኖርበት እንዲት አፍታ እንኳ ካለች፣ የእግዚአብሔርን እውነት አያስፈልገውም ማለት ነው። የእግዚአብሔር ንጹሕና ቅዱስ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ፣ አማካሪውና መመሪያው፣ የሕይወቱ ዋና ተቆጣጣሪ ኃይል መሆን አለበት። በልባችን አጥብን ከያዝናቸው ዬዛቸውነህ ትምህርቶች ይሰጠናል። ”—Ibid., vol. 5, p. 547.
ረቡዕ
መስከረም 08
4. መከልከል የለበትም
ሀ. እግዚአብሔር ለህዝቡ ያለውን እቅድ እና በዚህ ዓለም ላይ የሚያተኩሩ ግማሽ ልብ ያላቸው ሰዎች ለዛ እቅድ እና በእሱ ለመኖር የሚፈልጉ ሰዎች ምን ምላሽ እንደሚሰጡ ይግለፁ። ቲቶ 2፡11–14; ዘዳግም 26፡18።
“በአንድ ወቅት በቅርብ እውን የሚሆነውን የጌታን ዳግም ምጽዓት በመልከት በደስታ ፈንድቀውና ድምፆቻቸውን ከፍ አድርገው የጮኹ ወገኖች አሁን የቤተክርስቲያን መሰረት የሚሆኑበት ጊዜ መጥቶአል፡፡ እነዚህ ሰዎች በየሱስ ዳግም ምጽዓት በማመናቸው ዓለም በእነርሱ ላይ እንዲሳለቅ ለማድረግና ተጽእኖአቸውን ለማጥፋት ሁሉንም ዓይነት የሐሰት ተግባራት ተነዝቶባቸዋል፡፡ ነገር ግን አሁን ማንም ሕያው አምላክን በመናፈቅ ጽድቅን ቢራብና ቢጠማ እግዚአብሔር ፍቅሩን በልቡ ውስጥ በማፍሰስ ኃይሉን ያድስለታል ፤ የነፍሱን መናፈቅ ያረካለታል፡፡ ደግሞም ለእግዚአብሔር ምስጋና በማቅረብ ክብርን ለእርሱ ቢሰጥ በእነዚህ በክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ላይ በተሳለቁ አስመሳይ አማኞች ከመስመር የወጣ ክፉ መንፈስ ያለበት አማኝ ተደርጎ በመፈረጅ ማላገጫቸው ይሆናል፡፡
“ክርስቲያኖች ነን ከሚሉት ከእነዚህ ሰዎች መካከል ብዙዎቹ አለባበሳቸው፣ አነጋገራቸውና ድርጊታቸው እንደ ዓለም በመሆኑ አማኝ መሆናቸው በብቸኝነት ሊታወቅ የሚችልበት መንገድ መሆኑ ነው፡፡ ምንም እንኳ የክርስቶስን መገለጥ እየተጠባበቅን ብለው ሲናገሩ ቢደመጡም ነገር ግን አነጋገራቸው በዓለማዊው ነገሮች እንጂ በሰማይ የሉም። ታዲያ ‘እንዴት ዓይነት ሰዎች ሊሆኑ ይገባል?’ ‘በቅዱስ ኑሮና እግዚአብሔርን በመምሰል’ ‘የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት ሊጠብቁና ሊያፋጥኑ’ ይገባል። (2ኛ ጴጥ 3:11፣ 12)፡፡ ‘በእርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻ' (1ኛ ዮሐንስ 3፡3)፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ የአድቬንቲስትን ስም የያዙ ሰዎች ጊዜያቸውን የሚያባክኑት የሚእግዚአብሔርን ቃል በማጥናትና በፊቱ ድጋፍ ለማግኘት በመጣር ሳይሆን ነገር ግን አካላቸውን በማስጌጥና በዓለም አይን መልካም ሆነው ለመታየት ጥረት በማድረግ መሆኑ በማስረጃ የተደገፈ ነው፡፡ ”—Early Writings, p. 108. (ቀደምት ጽሁፎች ገጽ 80)
ለ. በተቃራኒው የእኛ ትኩረት ምን መሆን አለበት? 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡18
“ በዚህ የድህነት ምስኪን ህይወት ላይ ያላችሁን ማጉረምረም አቁሙ ፤ ነገር ግን የነፍሳችሁ ሸክም ከዚህ የተሻለውን ሕይወት፣ እስከመጨረሻ እውነተኛ እና ታማኝ ሆነው ለፀኑት የተዘጋጀውን ዘላለማዊ ቤት እንዴት ማግኘት ይቻላል ሊሆን ይገባል። በዚህ ህይወት ከተሳሳትክ ሁሉም ነገር አከተመ (ጠፋ ማለት ነው)፡፡ እድሜህን ሁሉ (መላ ህይወትህን) ምድራዊ ሀብትን ለማካበት ካዋልከው እና ሰማያዊውን ካጣህ፣ እጅግ አስከፊ ስህተት መስራትህን ታገኘዋለህ። ሁለቱም ዓለም ሊኖሩህ አይችሉም። ”— Testimonies for the Church, vol. 1, p. 706.
ሐሙስ
መስከረም 09
5. ወደ ላይ ከፍ ያለውን መመልከት
ሀ. ሊሳሳቱ በሚችሉ መሪዎች እና ሌሎች የቅርብ አጋሮቻቸው ደካማውን ሰብዓዊ ሰው በጭፍን መታመንን አስመልክቶ ምን ማስጠንቀቂያ ተሰጠን? ኢሳይያስ 3:11, 12; አሞጽ 2:4; 4፡12።
“እግዚአብሔርን እንደሚያገለግሉ ቢያስቡም ነገር ግን በፍጥነት እንደ ቀበቶ በፍጥነት እታጠቁ ያሉ ሰዎች አሉ። ለእነርሱ ጠማማው መንገድ ቅን ይመስላቸዋል ፤ ዘወትር የእግዚአብሔርን እውነት በመጣስ እየኖሩ ናቸው። ብልሹ መርሆዎች ከሕይወት ልምምዳቸው ጋር ተጠላልፈው ተሳስረዋል፡፡ በመሆኑም የትም ቢሄዱ የክፋት ዘርን ይዘራሉ። ሌሎችን ወደ ክርስቶስ መምራት በሚገባቸው ቦታ፣ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ በጥያቄ እንዲሞሉና እንዲጠራጠሩ ያደርጋቸዋል። .”—Testimonies to Ministers, p. 281.
“የሕይወትን ቃል ለሌሎች እየሰበኩ ነገር ግን መልዕክቱ በውስጡ የያዛቸውን የትሕትና እና ራስን የመካድ መንፈስን ከማያሳዩ ሰባኪዎች ተጠንቀቁ። እንደነዚህ ያሉ ሰዎች በነውጥ ጊዜ ሊቆሙ አይችሉም፡፡ ልክ እንደ ሳኦል የአምላክን ድምፅ ችላ ይላሉ ፤ እንደ እርሱም ብዙዎች የገዛራሳቸውን አካሄድ ለማጽደቅ በተጠንቀቅ ይቆማሉ። በጌታ ነቢይ በኩል በተገሰጸ ጊዜ፣ ሳኦል የእግዚአብሔርን ቃል እንደታዘዘ በጽኑ ተናግሯል። ነገር ግን የበጎች ጩኸት እና የበሬዎች ግሳት እግዚአብሔርን አለመታዘዙን ይመሰክራል። በተመሳሳይ ሁኔታም ዛሬ ብዙዎች ለእግዚአብሔር ታማኞች መሆናቸውን አስረግጠው ይናገራሉ ፤ ነገር ግን የኮንሰርቶች ዝግጅት እና ሌሎች የደስታ መቦረቂያ ስብሰባዎቻቸው፣ ዓለማዊ ጓደኞቻቸው፣ ራሳቸውን ማክበራቸው፣ እንዲሁም ለእውቅና ያላቸው ጉጉት ሁሉም የእርሱን ድምጽ እንዳልታዘዙ ይመሰክራሉ። 'ሕዝቤ ግን ልጆች አስጨናቂዎቻቸው ናቸው፥ ሴቶችም ይገዙአቸዋል።'
“ወንጌል በፊታችን ያስቀመጠው መስፈርት ከፍተኛ ደረጃ ነው። የማይለዋወጥ (አቋመ-ጽኑ) ክርስቲያን አዲስ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በክርስቶስ የሱስ ክቡር ፍጡርም ነው። እርሱ ወደ መንግሥተ ሰማያትና ወደ እግዚአብሔር የሚወስደውን መንገድ ለሌሎች ለማሳየት የማይጠፋ ብርሃን ነው። ወደ ክርስቶስ ሕይወቱ የተሳበ ሰው፣ ከንቱውንና እርካታ የለሹን የዓለም መዝናኛ አይመኝም። ”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 88.
አርብ
መስከረም 10
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. በተለምዶ የገሃነም እሳት ተብሎ ስለሚጠራው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ያብራሩ።
2. አምላክ በማይጠፋው ነበልባሎች መካከል ምን ተአምር ያደርጋል ?
3. ክርስቲያናዊ ተሞክሮዬ እንዴት የጠለቀ መሆን ይችላል ? ይህስ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
4. ድነትን በተለከተ በሥጋ ክንድ መደገፍ የሚያስከትለውን አደጋ ይግለፁ።
5. በዘላለም ላይ የበለጠ ትኩረት ለማድረግ በግሌ ምን እርምጃዎችን መውሰድ አለብኝ?