እሁድ
ሐምሌ 14
1. ከተፈጥሮ ፍቅር በላይ እና ባሻገር
ሀ. ፍቅር፣ ከወንድማዊ መዋደድ በኋላ የተጠቀሰዉ ለምንድነው? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡7 (የመጨረሻው ክፍል)። ሮሜ 5:7፣ 8፤ ያዕቆብ 3፡17
“ስለ ክርስቶስ ስንል ሰዎችን መውደድ አለብን። ለተፈጥሮ ልብ ጥቂት ተወዳጆችን መውደድና ለእነዚያ ጥቂቶች ማዳላት ቀላል ነው፤ ክርስቶስ ግን እርሱ እኛን እንደወደደን እርስ በርሳችን እንድንዋደድ አዞናል።”—Testimonies to Ministers, p. 156.
ለ. የሱስ ከፍጽምና ጋር የሚያገናኛቸው ነገሮች ምንድናቸው? ማቴዎስ 5:43-48፤ ሉቃስ 6:36፤ ቆላስይስ 3፡14
ሰዎች በአዳኛችን ንጽህና እና ሞራላዊ ጨዋነት ተደንቀው ነበር፣ ደግሞም ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅሩ እና የዋህነት ቸርነቱ ልባቸውን አሸንፏል። እሱ የፍጽምና መገለጫ ነበር።”—Gospel Workers, p. 73. [1892 edition.]
“ራስህን ከሌሎች በተሻለ መንገድ በማሰብ ራስህን በበላይነት አትመልከት። ‘ማንም የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።’ ፈቃድህን ለክርስቶስ ፈቃድ ስታስገዛ ሰላምና ዕረፍት ወደ አንተ ይመጣል። ያኔ የክርስቶስ ፍቅር ልብህን ይገዛል።”—Messages to Young People, p. 73.
ሰኞ
ሐምሌ 15
2. የተሰጠን መለኮታዊ አመለካከት
ሀ. አንድ እውነተኛ ክርስቲያን ለሌሎች ያለውን አመለካከት ግለጽ። መዝሙረ ዳዊት 101:2፤ ፊልጵስዩስ 2፡1-4
“ችኮላ፣ በቀላሉ የሚነድ ቁጣ በክርስቶስ የጸጋ ዘይት ይረጋጋል እና ይሰክናል። ኃጢአትህ መሰርየቱን የማወቅ ስሜት፣ ማስተዋል (አዕምሮን) ሁሉን የሚያልፍ ሰላምን ያመጣል። ከክርስቲያናዊ ፍጹምነት ጋር የሚቃረኑትን ነገሮች ሁሉ ለማሸነፍ ልባዊ ጥረት ይኖራል። ልዩነት ይጠፋል። በአንድ ወቅት በዙሪያው ባሉት ሰዎች ላይ ስህተት ይፈልግ የነበረ ሰው በራሱ ባሕርይ ላይ ከዚህ የበለጠ ስህተት እንዳለ ይገነዘባል።”—Messages to Young People, p. 73.
ለ. ከላይ የተገለጸው የአመለካከት አይነት በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ሊኖር የምችልበት ብቸኛው መንገድ እንዴት ነው? ፊልጵስዩስ 2:5–8፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡16
“ሰላማችንን የሚያጠፋው ራስ ወዳድነታችን ነው። እራስነት በህይወት ካለ፣ እርሱን ከማንቋሸሽና ከስድብ ለመጠበቅ ያለማቋረጥ ዝግጁ እንሆናለን። ነገር ግን ከሞትን በኋላ ህይወታችን ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር በተሰወረ ጊዜ፣ ቸልተኝነትን ወይም ግደየለሽነትን በልባችን አንቀበልም። ለነቀፌታን የደነቆርን፤ ለንቀትና ለስድብ የታወርን እንሆናለን። . . .
“የክርስቶስ ሰላም የማያቋርጥና የማይለወጥ ሰላም ነው። በማንኛውም የህይወት ሁኔታዎች፣ በምድራዊ ንብረቶች ብዛት ወይም በምድራዊ ጓደኞች ብዛት ላይ የተመካ አይደለም። ክርስቶስ የሕይወት ውኃ ምንጭ ነው፣ ከእሱ የተቀዳ ደስታ ፈጽሞ ሊጠፋ አይችልም።
“በቤት ውስጥ የሚገለጠው የክርስቶስ የዋህነት ቤተሰቦቻችን አባላቶች ያስደስታቸዋል። ጠብ አይጭርም ፣ ቁጡ መልስ አይመልስም ፣ ግን የሌሎችን ቁጣ ያስታግሳል እንዲሁም በዙሪያው ያሉ ሁሉ የሚጋባ የዋህነትን ያሰራጫል። በተቀበሉበት በየትኛውም ቦታ፣ የምድርን ቤተሰቦች ከላይ ካለው ከአንድ የታላቅ ቤተሰብ አካል ያደርጋቸዋል።
“በጠላቶቻችን ላይ የበቀል መንፈስ ተጠናዉቶን ከምንሰቃይና ከምንጎዳ የሃሰት ክስ በእኛ ላይ ተከፍቶ ብንሰቃይ ይሻለናል። የጥላቻና የበቀል መንፈስ የሚመጣው ከሰይጣን ነው፣ እናም እሱን ለሚወደው ሰው ክፉን ነገር ብቻ ነው ሊያመጣ የምችልው። የልብ ትሕትና፣ ያ የዋህነት በክርስቶስ የመኖር ፍሬ የሆነው፣ የበረከት እውነተኛ ምስጢር ነው። `የዋሆችን በመዳን ያስውባቸዋል።`”—Thoughts From the Mount of Blessing, pp. 16, 17.
ማክሰኞ
ሐምሌ 16
3. ፍቅር፡ እውነተኛው ከሐሰተኛው ጋር ስነጻጸር
ሀ. እግዚአብሐር ለሚፈልጉት በሙሉ ሊሰጣቸው የሚመኘዉን እውነተኛውን ፍቅር ግለጽ። ማቴዎስ 5:6፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4-8
“ቤተ ክርስቲያን እንድትበለጽግ በምእመናን በኩል ውድ የሆነውን የፍቅር ተክል ለመንከባከብ በጥናት የተሞላ ጥረት መደረግ አለበት። በልብ ውስጥ እንዲለመልም ዘንድ በሙሉ አቅም ተንከባከቡት። እያንዳንዱ እውነተኛ ክርስቲያን በሕይወቱ ውስጥ የዚህን መለኮታዊ ፍቅር ባህሪያት ሲያዳብር ፤ እርሱ የትዕግሥት ፣ በጎነት፣ እንዲሁም ከቅናትና ከተንኮል የራቀ መንፈስን ይገልጣል። ይህ በቃልም ሆነ በድርጊት የዳበረው ባህሪይ ሌሎችን አይፀየፍም፣ እንዲሁም ለመቅረብ የሚከብዱ፣ ቀዝቃዛና ለሌሎች ጥቅም ደንታ የሌለው አይሆንም። ውድ የሆነውን የፍቅር ተክል የሚያለማ ሰው በመንፈስ ራሱን ዝቅ ያደረገና በሚያናድድ ሁኔታ ዉስጥም ቢሆን እንኳ ራሱን የሚገዛ ይሆናል። በሌሎች ላይ የተሳሳቱ አመለካከቶችንና መጥፎ ሀሳቦችን አይቆጥርም፣ ነገር ግን በማናቸውም የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ውስጥ ሲታወቅ ኃጢአትን የሚጸየፍ ጥልቅ ስሜት እንዳለው ነው።
“ፍቅር በራሱ አይመካም። ትሑት ነው፤ ሰው እንዲመካ ራሱን ከፍ እንዲያደርግ በፍጹም አያነሳሳውም። ለአምላክና ለሰዎች ያለን ፍቅር በችኮላ ድርጊቶች አይገለጽም፣ ስህተት ፈላጊ ወይም አምባገነን እንድንሆን አያደርገንም። ፍቅር አይታበይም። ፍቅር የነገሠበት ልብ ለሌሎች፣ ለፍላጎታችን ተስማሚም ባይሆኑም፣ ቢያከብሩን ወይም ባያከብሩንም ሌሎችን ወደ ገራገር፣ ጨዋነት፣ ርኅራኄ መንገድ ይመራቸዋል። ፍቅር ንቁ መርህ ነው፤ የሌሎችን መልካምነት ዘወትር በፊታችን ይጠብቃል፣ ስለዚህም ነፍስን ወደ ክርስቶስ በማሸነፍ ረገድ ያለንን ነገር እንዳንወድቅ ከግምታዊ ድርጊቶች ይጠብቀናል። ፍቅር የራሱን አይፈልግም። ሰዎች የራሳቸውን ምቾትና የራሳቸውን ደስታ እንዲፈልጉ አይገፋፋም። ብዙውን ጊዜ የፍቅርን እድገት የሚያደናቅፈው ለእኔነት (ለራሳችን) የምንሰጠው አክብሮት ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 123, 124.
ለ. ከሐሰት ፍቅር እንድንጠበቅ እንዴት ያለ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል? ያዕቆብ 2:19፤ ይሁዳ 11-13
“ሽማግሌው ቢ-----ት እጅግ ቅዱስ ሰው መስሎ ታየ። ስለፍቅር ብዙ ነገር አወራ። ስለ እምነት ሲናገር እንዲህ አለ፡ 'እኛ ማድረግ ያለብን ማመን ብቻ ነው፣ ከዚያም ከእግዚአብሔር የምንለምነው ሁሉ ይሰጠናል።' ወንድም ኋይት እንዲህ ሲል መለሰ፡- `በረከቶች ቃል የተገቡልን በቅድሜ ሁኔታዎች ነው።` ዮሐንስ 15፡7 በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ለምኑ ይሰጣችሁማል። የእምነት ፅንሰ-ሀሳብህ ከሁለቱም በኩል ክፍት እንደሆነ ዱቄት በርሜል ባዶ ነው። እውነተኛ ፍቅርን በተመለከተም እሷ ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጎዳና ፈጽሞ የማትወጣ በጣም ጨዋ ሰው ነች።' ”—Spiritual Gifts, vol. 2, pp. 46, 47.
ረቡዕ
ሐምሌ 17
4. ወሳኝ ጉዳይ
ሀ. በጴጥሮስ መሰላል ውስጥ በተዘረዘሩት ክርስቲያናዊ ጸጋዎችን ሁሉ ማብዛታችን ምን ያህል አስፈላጊ ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡8
“የክርስቲያን ጸጋዎች ይኑሯችሁ እና ይብዛላችሁ። ለአዳኝህ ምርጥና የተቀደሰ ፍቅርህን ስጥ። ለፈቃዱ ሙሉ በሙሉ ታዘዝ። እሱ ከዚህ ያነሰ ምንም ነገር አይቀበልም። አእምሯቸው ለከንቱነት በተሰጡ ሰዎች ስድብና ስላቅ ከጽናትህ አትራቅ። በክፉና በደጉ ሁሉ አዳኝህን ተከተል፤ የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም ሁሉንም ነገር እንደ ሙሉ ደስታ እና እንደተቀደሰ ክብር ቁጠር። የሱስ ይወድሃል። ለአንተ ሞቶልሃል። ባልተከፋፈለ ፍቅርህ እሱን ለማገልገል ካልፈለግህ በቀር፣ በፍርሃት ቅድስናን ፍጹም ማድረግ ይሳንሃል፣ እንዲሁም በመጨረሻም ሂድ ከእኔ ራቅ የሚለውን አስፈሪ ቃል ለመስማት ትገደዳለህ።”—Testimonies for the Church, vol. 2, p. 237.
ለ. ዛሬ አስጨናቂ በሆነው ዓለም ውስጥ ብዙ ጊዜ የምናየው ነገር ምንድን ነው? መኃልየ መሓልይ 2:15
“አስቸኳይ በሆኑ እንክብካቤዎች፣ ሸክሞች እና ግዴታዎች ተጨናንቀሃል፤ ነገር ግን በአንንተ ላይ የሚኖረው ጫና እና ሸክሞች በከበደ መጠን፣ የመለኮታዊ እርዳታ ፍላጎትህ እየጨመረ ይሄዳል። የሱስ ረዳትህ ይሆናል። የአንተን መንገድ ለማብራት ያለማቋረጥ የህይወት ብርሃን ያስፈልግሃል፣ እና ከዚያም መለኮታዊ ጨረሮቹ በሌሎች ላይ ይንፀባርቃሉ። የእግዚአብሔር ሥራ ፍጹም ሙሉ ነው፣ ምክንያቱም በሁሉም በኩል ፍጹም ነው። የህይወትን ታላቅ ውበትና ስኬት የሚያመጣው፣ አለም ትንንሽ ነገሮች ብሎ የሚጠራቸው ህሊናዊ ትኩረቶች ናቸው። ትንንሽ የፍቅር ስራዎች፣ ትንሽ የደግነት ቃላት፣ ትንሽ ራስን የመካድ ተግባራት፣ የጥቂት እድሎች ጥበባዊ መሻሻል፣ ትንሽ ተሰጥኦዎችን በትጋት ማልማት፣ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ሰዎች ያደርገናል። ትንንሾቹን ነገሮች በታማኝነት ከተከታተሉ፣ እነዚህ ጸጋዎች በእናንተ ውስጥ ቢሆኑና ቢበዙ፣ በበጎ ስራ ሁሉ ፍጹማን ያደርጓችኋል።
“ለእግዚአብሔር ጉዳይ ያለህን ነገር በልግስና ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን ብቻውን በቂ አይደለም። የሁሉንም ሀይሎችህን ያልተቆጠበ መቀደስ እንድኖርህ ይጠራሃል። ራሳችሁን አሳልፋችሁ አለመስጠታችሁ የሕይወታችሁ ስህተት ነው። ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት ለመጠበቅ አሁን ባለህበት ቦታ በጣም ከባድ እንደሆነ ታስብ ይሆናል፣ ነገር ግን ይህን ማድረግ ካልቻልክ ስራህ በአስር እጥፍ ከባድ ይሆናል። . . .
“እግዚአብሔር ፍጹምና ሙሉ ቅድስናን ጠይቋል፣ እናም ከዚህ ውጭ የሆነ ማንኛውንም ነገር አይቀበለውም። ሁኔታህ ይበልጥ አስቸጋሪ በሆነ መጠን የሱስም ይበልጥ ያስፈልግሃል።”—Ibid., vol. 4, pp. 543, 544.
ሐሙስ
ሐምሌ 18
5. አደገኛ መዘንጋት (መርሳት) = ዓይነ ስውርነት
ሀ. ከክርስቲያናዊ ጸጋዎች አንዳቸውም ቢጎድሉን ምን ይሆናል? 2ኛ ጴጥሮስ 1:9፤ ራእይ 2፡4።
“በዕድገት መሰላል ላይ ያልወጣና ጸጋን ያልጨመረ ‘እውር ነው፣ ሩቅም ማየት አይችልም’፣ እነዚህን ተከታታይ እርምጃዎች ካልወጣ ከደረጃ ወደ ደረጃ መሰላሉን በመውጣት ካላየ፣ በጸጋ እያደገና እየጨመረ መሆኑን መገንዘብ ይሳነዋል። ስለ ጌታችን የሱስ ክርስቶስ እውቀት ራሱን ከመሰላሉ በላይ ያለውን የእግዚአብሔር ብርሃን በሚያንጸባርቅበት ቦታ ላይ አያስቀምጥምና። በጸጋ ላይ ጸጋን ስለማይጨምር፣ እግዚአብሔር በእሱ ላይ ያለውን የይገባኛል ጥያቄ ይረሳል፣ ግን የእግዚአብሔርን መስፈርቶች በመታዘዝ የኃጢአትን ስርየት ማግኘት አለበት። በእግዚአብሔር ፊት በኃጢአተኛ ነውና። የክርስቶስ ጸጋዎች ካሉት ያዳብርና ያበዛቸዋል፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ክብር በበጎ ሥራ ፍሬ ካላፈራ በእውርነትና በድንቁርና፣ ራስን ባለመግዛትና በኃጢአት ሁኔታ ውስጥ ይኖራል። 'ሩቅ ማየት አይችልም'። ዓይኖቹ በምድር ላይ እንጂ ከመሰላሉ በላይ ባለው አምላክ ላይ አይደሉምና።
“ይህ ክፍል ምድራዊ ጥቅሞች ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ከመሰላሉ በላይ ከእግዚአብሔር በሚወጣው ብርሃን ውስጥ የመኖር እድል እና በረከቶችን አይረዳም። ለሰላማቸው የሚጠቅመውን ነገር አያውቁም። ነገሮችን በሰማይ ብርሃን ስለማይመለከቱ ጥርት ባለው መንፈሳዊ እይታ ወደ ኋላ ማየት አይችሉም። በአንድ ወቅት በእግዚአብሔር ፍቅር ተደስተው ነበር፤ ከኃጢአታቸው ንስሐ ገብተው የየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ለመሆን ተመዝግበዋል፤ ነገር ግን በተጠመቁበት ወቅት ለአምላክ የገቡትን ቃል ኪዳን ማለትም ጸጋን፣ ክብርንና ዘላለማዊነትን ለማግኘት የተጣለባቸውን ከባድ ግዴታዎች በሙሉ ረስተዋል።”—Manuscript Releases, vol. 19, pp. 350, 351.
አርብ
ሐምሌ 19
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. ፍትሃዊ ያልሆነ አድሎአዊነት ስጋት ውስጥ የሚገባው ለምንና በምን አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ነው?
2. የፍቅር መንፈሴ የመውደቅ አዝማሚያ ያለው በምን አይነት ሁኔታዎች ነው?
3. የውሸት ፍቅርን ከእውነት ፍቅር እንዴት ለይተ እንችላለን?
4. ምን ዓይነት ትናንሽ የፍቅር ምልክቶችን ችላ ለማለት እወዳለሁ?
5. ለምንድነው በፍቅር መስክ ውስጥ አሁንም ደካማ የሆንኩት - እና ይህ ለምን በጣም አስፈላጊ ሆነ?