እሁድ
ሐምሌ 21
1. ለትጋት ጥሪ
ሀ. በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ከሁሉ የበለጠ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ነገር ምንድን ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 1:10 በእኛ ልምድ ውስጥ ይህ ለምን መስቀልን ይጨምራል? ማቴዎስ 10፡38
“እግዚአብሔር የተወሰነ የላቀ ባሕርይ መርጧል፤ እና በክርስቶስ ጸጋ በኩል ወደሚፈለገው መስፈርት የሚደርስ ሁሉ ወደ ክብር መንግስት መግቢያ በር ይኖረዋል። ወደዚህ የባህሪይ ደረጃ የሚደርሱ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ለዚህ ዓላማ ያዘጋጀውን መንገድ መጠቀም አለባቸው። ለእግዚአብሔር ልጆች የቀረውን ዕረፍት ልትወርስ ከፈለግህ ከእግዚአብሔር ጋር ተባባሪ መሆን አለብህ። የክርስቶስን ቀንበር እንድትቀበል ሸክሙን ለመሸከም፣ መስቀሉንም ለማንሳት ተመርጠሃል። ‘መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ’ ትጉ። ቅዱሳት መጻሕፍትን ስትመረምሩ የአዳም ወንድ ወይም ሴት ልጆች የእግዚአብሔርን ሕግ በመጣስ ለመዳን አንዳልተመረጡ ታያላችሁ። ዓለም የእግዚአብሔርን ሕግ ባዶ ታደርጋለች፤ ክርስቲያኖች ግን ለመቀደስ የተመረጡት ለእውነት በመታዘዝ ነው። መስቀልን ለመሸከም ተመርጠዋል፤ ያንን ካደረጉ ደግሞ በመጨረሻ አክሊልን ይለብሳሉና።”— Fundamentals of Christian Education, p. 126.
“መስቀልን መሸከምን አሻፈረኝ ያለ ለታማኞቹ ቃል የተገባውን ሽልማት ያጣል።”—Sons and Daughters of God, p. 248.
ሰኞ
ሐምሌ 22
2. ከእግዚአብሔር ጋር መታገል
ሀ. መጠራታችንና መመረጣችንን በማጽናት የባህርይ ጉድለቶቻችንን ለማሸነፍ ስንፈልግ - የሰው ልጅ ሆኖ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ በየሱስ ምን ምሳሌ ተሰጠን? ዕብራውያን 5:7፣ 8
“ከተማዋ በጸጥታ በተረጋጋችበት፣ ደቀ መዛሙርቱም በእንቅልፍ ራሳቸውን ለማደስ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፣ የሱስ ግን አልተኛም። የእርሱ መለኮታዊ ልመና ደቀ መዛሙርቱ በዓለም ላይ በየቀኑ ከሚያጋጥሟቸው ክፉ ተጽእኖዎች እንዲጠበቁ እና የገዛ ነፍሱ የሚመጣውን ተግባርና ፈተና ለመቀበል እንድትበረታና ኃይል እንድታገኝ ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ አባቱ ይወጣ ነበር። ሌሊቱን ሙሉ፣ ተከታዮቹ ተኝተው ሳሉ፣ መለኮታዊ መምህራቸው ሲጸልይ ያድራል። የሌሊት ጤዛና ውርጭ ለጸሎት በተደፋዉ ራሱ ላይ ያልፍ ነበር። የእርሱ ምሳሌ ለተከታዮቹ የተተወ ነው።
“የሰማዩ ባለግርማ፣ በተልእኮው ላይ እያለ፣ ብዙን ጊዜ በትጋት ይጸልይ ነበር። ሁልጊዜ ደብረ ዘይት ተራራን አይጎበኝም ነበር፣ ምክንያቱም ደቀ መዛሙርቱ ለጽሞና የሚወደውን ቦታ አውቀዋልና ብዙን ጊዜ ይከተሉት ነበር። መቆራረጥ (ረብሻ) የማይኖርበትን ጊዜ የሌሊት ጸጥታን መረጠ። የሱስ የታመሙትን መፈወስና ሙታንን ማስነሳት ይችላል። እርሱ ራሱ የበረከትና የብርታት ምንጭ ነበር። ማዕበሉንም እንኳ አዘዘ፣ ማዕበሉም ታዘዘለት። በከፋት ያልተበከለ፣ ለኃጢአት እንግዳ የሆነ፤ እርሱ ግን ብዙን ጊዜ በጠንካራ ልቅሶና እንባ ይጸለይ ነበር። ለደቀ መዛሙርቱና ለራሱ ጸልዮአል፣ በዚህም በሰው ልጅ ላይ በጣም የተለመዱ ከሆኑ ፍላጎቶቻችን፣ ድክመቶቻችንና ውድቀቶቻችን ጋር እራሱን አስተዋወቀ። እርሱ ኃያል ጠያቂ ነበር፣ የእኛ የሰው ልጆች፣ የወደቀ የተፈጥሮአችን መሻት አልነበረውም፣ ነገር ግን እንደደካሞች፣ እንደ እኛ ደግሞ በሁሉም ነገር የተፈተነ ነው። የሱስ ከአባቱ እርዳታና ድጋፍ የሚያስፈልገውን ስቃይ ተቋቁሟል።
“ክርስቶስ ምሳሌያችን ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 508, 509.
ለ. የእንደዚህ ዓይነት ኃያል የጸሎት ሕይወት ውጤቱን ይግለጹ። የሐዋርያት ሥራ 4፡13
“የየሱስ ሕይወት የማያቋርጥ እምነት፣ በማያቋርጥ ኅብረት የሚደገፍ ሕይወት ነበር። ለሰማይና ለምድር ያገለገለው አገልግሎት ያልተሳካለት ወይም የሚደናቀፍ አልነበረም።
“ሰው ሆኖ የሰውን ልጅ ከመለኮትነት ጋር በሚያገናኘው ሰማያዊ ሞገድ እስኪሞላ ድረስ ሰውነቱ የእግዚአብሔርን ዙፋን ለመነ። ከአምላክ ሕይወትን በመቀበል ለሰው ልጆች ሕይወትን ሰጥቷል።”—Education, pp. 80, 81.
ማክሰኞ
ሐምሌ 23
3. በእምነት መጽናት
ሀ. መጠራታችንንና መምረጣችንን ለማጽናት ሳናቋርጥ መትጋት ሲያቅተን ምን ይሆናል? ሕዝቅኤል 33፡13 አንድ ምሳሌ ስጥ።
“እግዚአብሔር ለዳዊት ብዙ ሚስቶች ስለነበሩት፣ በፍርድ በመጎበኘት፣ ከቤቱም ክፉ ነገር እንዲነሣበት በመፍቀድ በዳዊት ላይ መከፋቱን ገለጸ። እግዚአብሔር በአንድ ወቅት እንደ እግዚአብሔር ልብ ያለ ሰው ተብሎ በተጠራው በዳዊት ላይ እንዲደርስ የፈቀደው አስከፊ ጥፋት፣ እግዚአብሔር ትእዛዙን በመተላለፍ ማንንም እንደማያጸድቅ የሚያሳይ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የሚኖር ማረጋገጫ ነው። ጌታን በንፁህ ልብ ሲከተሉ አንድ ወቅት ጻድቅና የእግዚአብሔር ሞገስ የነበራቸው ቢሆንም ግን ጥፋተኞች ሲሆኑ ጌታ በእርግጥም ይቀጣቸዋል። ጻድቃን ከጽድቃቸው ተመልሰው ክፋትን በሠሩ ጊዜ ያለፈው ጽድቃቸው ከጻድቅና ከቅዱስ አምላክ ቍጣ አያድናቸውም።”—The Spirit of Prophecy, vol. 1, p. 379.
“ነፍሶች ስድኑ የሚቀበሉት እውነት አለ። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ለተቀባዩ የዘላለምን ሕይወት የሚሰጥ ነው። ነገር ግን እነዚያ በአንድ ወቅት የሕይወትን መንገድ የሚያውቁና በእውነት የሚደሰቱ የነበሩ ሰዎችም እንኳ በክህደት የመውደቅና የመጥፋት አደጋ እንደሚጋረጠባቸው ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ ያሳያሉ። ስለዚህ በየቀኑ ወደ እግዚአብሔር የሚደረግ የመለወጥ ቁርጥ ውሳኔ ያስፈልጋል።
“አንድ ጊዜም፣ ሁል ጊዜም በጸጋ የመመረጣቸውን ትምህርት ሊያጸኑ የሚሹ ሁሉ ይህን በግልጽ ያደርጋሉ፡ ይላል ጌታ።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 6, pp. 1114, 1115.
ለ. በአንጻሩ ደግሞ አመለካከታችን ምን መሆን እንዳለበትና አስፈላጊ የሆነውን እውነት ማስታወስ ያለብን ለምን እንደሆነ ግለጽ። ሕዝቅኤል 18:21፤ 1 ቆሮንቶስ 15:1፣ 2 (የመጀመሪያ ክፍል)
“ብዙዎች ለከባድ ስህተቶች የመርሳትን በቂ ምክንያት ነው ብለው ያስባሉ። ግን እነሱም ሆኑ ሌሎች የእውቀት ችሎታዎች የላቸውም? ከዚያም አእምሮአቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ መገሠጽ አለባቸው። መርሳት ኃጢአት ነው፣ ቸልተኛ መሆን ደግሞ ኃጢአት ነው። የቸልተኝነት ልማድ ካዳበርክ የነፍስህን መዳን ችላ ልትል ትችላለህ፤ በመጨረሻም ለአምላክ መንግሥት ዝግጁ እንዳልሆንክ ታውቅ ይሆናል።”—Christ’s Object Lessons, pp. 358, 359.
“መጽሐፍ ቅዱስህን ከአንተ ጋር ያዝ። ለማንበብ እድሉን ባገኘኄዉ ጊዜ ሁሉ አንብበው፤ ጽሑፎቹን በማስታወሻዎ ውስጥ ያስተካክሉ። በጎዳና ላይ በምትሄድበት ጊዜም እንኳ አንድን አንቀጽ አንብበህ ልታሰላስልበት ትችላለህ።--Steps to Christ, p. 90.
ረቡዕ
ሐምሌ 24
4. በምርጫዎቻችን የተመረጠ
ሀ. መጠራታችንና መመረጣችንን የሚናጸናበትን ቅድመ ሁኔታ ካከበርን ውጤቱ ምንድ ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 1:10 (የመጨረሻው ክፍል)፣ 11.
“እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው ሃሳብ ከፍተኛ የተባለ የሰው ሃሳብ እንኳ ሊደርስበት ከሚችለው እጅግ የበላይ ነው። በሰማያት ያለው አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። ይህ ትእዛዝ የተስፋ ቃል ኪዳን ነው። የመዳን እቅድ ከሰይጣን ኃይል ሙሉ በሙሉ ማገገምን ያሰላስላል። ክርስቶስ ሁልጊዜ የተጸጸተችውን ነፍስ ከኃጢአት ይለያታል። እርሱ የመጣው የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስ ነው፣ እናም ኃጢአት እንዳይሠራ መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ ንስሐ ለገባ ነፍስ እንዲሰጥ ዝግጅት አድርጓል።
“የፈታኙ ወኪል ለአንድ ጥፋት ድርጊት ሰበብ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም። የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ ሰዎች ለባሕርይ መበላሸታቸው ምክንያት ሲያቀርቡ ሲሰማ ሰይጣን ደስ ይለዋል። ወደ ኃጢአት የሚመሩት እነዚህ ሰበቦች ናቸው። ኃጢአትን ለመስራት ምንም ሰበብ የለም። ቅድስና፣ ክርስቶስን የመሰለ ሕይወት፣ ንስሐ ለሚገቡና ለሚያምኑ የአምላክ ልጆች ሁሉ ተደራሽ ነው።”— The Desire of Ages, p. 311.
ለ. በእኛ ምርጫ ኃይል በጸጋ መመረጥ በያዕቆብና በዔሳው ሕይወት ውስጥ የሚታየው እንዴት ነው? 1ኛ ጴጥሮስ 1:2 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ ሮሜ 9፡10–14፤ 11:4፣ 5
“ዔሳው እና ያዕቆብ እግዚአብሔርን አውቀው እንደማደጋቸው ሁለቱም የእርሱን ትእዛዛት ለመጠበቅና በጥበቃው ስር ለመኖር ነጻ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሁለቱም ይህን ለማድረግ አልመረጡም፡፡ ሁለቱም የተጓዙት በተለያዩ መንገዶች ሲሆን አቅጣጫቸውም ልዩነቱ ይበልጥ እየሰፋ የሚሄድ ይሆናል።
“ዔሳው ከደኅንነት በረከት ተቆርጦ ሲቀር እግዚአብሔር በጭፍን የወሰደው ምርጫ አልነበረም፡፡ በክርስቶስ በኩል የሚሰጡ የፀጋ ስጦታዎች ለሁሉም ነጻ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የሚጠፋው እንዲጠፋ ስለተመረጠ ሳይሆን ነገር ግን የሚጠፋበትን መንገድ ስለመረጠ ነው፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ እያንዳንዱ ነፍስ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ስለሚመርጥባቸው ሁኔታዎች ማለትም በክርስቶስ እምነት በኩል ለትዕዛዛቱ መገዛት እንደሚያስፈልግ ገልጾአል፡፡ እግዚአብሔር ከሕጉ ጋር የሚጣጣም ባህሪን ይመርጣል፡፡ እርሱ የሚጠይቃቸውን ሁኔታዎች የሚያሟላ ማንኛውም ሰው ወደ ሰማያዊ መንግሥት እንዲገባ ይፈቀድለታል። . . . “ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስና በበሮቿም በኩል ወደ ከተማይቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው” (ራዕ 22፡14)፡፡ ከሰው ልጆች ደኅንነት ጋር በተያያዘ በእግዚአብሔር ቃል የቀረበው ብቸኛ ምርጫ ይኸው ነው።”—Patriarchs and Prophets, pp. 207, 208.
ሐሙስ
ሐምሌ 25
5. ከአሸናፊዉ ጋር መጣበቅ
ሀ. ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ላይ ጉዞውን የገለጸው እንዴት ነው? ፊልጵስዩስ 3፡12-14
ለ. ድል በክርስቶስ እንደሚቻል ለምን እናውቃለን? ፊልጵስዩስ 1:6፣ ይሁዳ 24፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡30
“እኛ የዳንነው የመሰላሉን ደረጃ በደረጃ በመውጣት፣ ክርስቶስን በመመልከት፣ ከክርስቶስ ጋር በመጣበቅ፣ ደረጃ በደረጃ ወደ ክርስቶስ ከፍታ በመውጣታችን፣ በእርሱ ጥበብና ጽድቅ፣ ቅድስናና ቤዛነት ስለሆነልን ነው። እምነት፣ በጎነት፣ እውቀት፣ ራስን መግዛት፣ ትዕግስት፣ እግዚአብሔርን መምሰል፣ የወንድማማችነት ደግነት፣ እና ፍቅር የዚህ መሰላል ደረጃዎች ናቸው። . . .
“በዋጋ የማይተመን የዘላለም ሕይወት ሀብት ማግኘት ቀላል አይደለም። ማንም ሰው ይህን ማድረግና በተመሳሳይ ደግሞ ከዓለም ሞገድ ጋር መጓዝ አይችልም። ከዓለም ወጥቶ የተለየ መሆን አለበት፣ ርኩሱንም አይንካ። ማንም ሰው ከአለም ሞገድ ጋር ካልተወሰደ በስተቀር እንደ ዓለማዊ መሆን አይችልም። ያለ ጽኑ ጥረት ማንም ወደላይ ማደግ አይችልም። ድል ማድረግ የሚፈልግ ማንም ክርስቶስን አጥብቆ መያዝ አለበት። ወደ ኋላ ማየት የለበትም፣ ነገር ግን ዓይንን ሁልጊዜ ወደ ላይ ያድርገው፣ ከአንዱ ጸጋ ወደ ሌላዉ እየተሸጋገረ ይሄዳልና። ግላዊ ትጋት ለደህንነቱ ዋጋው ነው። ሰይጣን በነፍስህ የሕይወትንና የሞትን ጨዋታ እየተጫወተ ነው። በእናንተ እንዳይጠቅም ወደ እርሱ ጥቅትም ፈቀቅ አትበሉ።
“መንግሥተ ሰማያት ከደረስን ያ የሆነው ነፍሳችንን ከክርስቶስ ጋር በማገናኘት፣ በእርሱ ላይ በመደገፍ፣ እና ከዓለም፣ ሞኝነትና ተንኮሎች በመላቀቅ ይሆናል። በእኛ በኩል ከመለኮት ጋር መንፈሳዊ ትብብር ሊኖረን ይገባል።”—Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 147, 148.
አርብ
ሐምሌ 26
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. መስቀል ከህይወቴ ጋር ምን አገናኘው?
2. የጸሎት ሕይወቴ ጥንካሬ ለመዳን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
3. አንድ ሰው በፈተና ውስጥ እንዲወድቅ የሚያደርገው ምንድን ነው?
4. ያዕቆብ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው ለምን እንደሆነ ግለጽ፤ ዔሳው ግን ተቀባይነት ያላገኘሁስ።
5. ለማሸነፍ በምትሞክርበት ጊዜ ማስታወስ ያለብህን አንዳንድ ተስፋዎች አንብብ።