እሁድ
ነሐሴ 12
1. አመለካከታችንን መጠንቀቅ
ሀ. አምላክ የሙሴን እህት በቅናቷ ምክንያት የቀጣው እንዴት ነው? ይህስ ዛሬም ማስጠንቀቂያ የሚሆነው እንዴት ነው? ዘኍልቍ 12:1፣ 2፣ 6–10፤ ያዕቆብ 4:11፤ 2ኛ ጴጥሮስ 2፡9 (ሁለተኛ አጋማሽ)፣ 10.
“የማርያም ምቀኝነትና አለመርካት በወቅቱ ባይገሰጽ መጠነ ሰፊ እርክስና በተከተለ ነበር፡፡ ምቀኝነት በሰብዓዊው ልብ ውስጥ ከሚፈጠሩ የሰይጣን
ባህሪዎች አንዱና የከፋ ውጤት የሚያስከትለው ነው፡፡ ጠቢቡ እንዲህ ይላል “ንዴት ጨካኝ፣ ቁጣም ጎርፍ ነው፤ በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?” (ምሳ. 27፡4)፡፡ መጀመሪያ በሰማይ ውዝግብ እንዲፈጠር ያደረገው ቅናት ሲሆን፤ ይኸው ኃጢአት ሊነገር የማይችል የእርክስና ሥራ እንዲፈጠር መንስኤ ሆኗል፡፡ “ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይገኛሉ” (ያዕ. 3፡16)፡፡
“ሌሎችን ክፉ መናገር ወይም በእነርሱ ዓላማ ወይም ድርጊት ላይ እራሳችንን ፈራጅ ማድረግ እንደ ብርሃን ሊቆጠር አይገባም፡፡ “…ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙም ላይ የሚፈርድ በሕግ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል፡፡ በሕግ ላይ ብትፈርድ ፈራጅ እንጂ ሕግን አድርጊ አይደለህም” (ያዕ. 4፡11)፡፡ እነሆ አንድ ብቻ ፈራጅ አለ። . . . ማንም ፍርድን ለራሱ በመውሰድ ወንድሙን ቢኮንን የፈጣሪን መብትና ሥልጣን ይቀማል።”—Patriarchs and Prophets, pp. 385, 386.
ሰኞ
ነሐሴ 13
2. ትምክህተኝነት
ሀ. እግዚአብሔር በፍትወታቸው ከሚመኩ ትዕቢተኞች በተለይም በሕዝቡ መካከል ሾልከው ለመግባት ቢሞክሩ እንዴት ያስጠነቅቃል? 2ኛ ጴጥሮስ 2፡11-13
“የሰይጣን የማታለል ኃይል ሰውን ሲቆጣጠር፣ እግዚአብሔር ይረሳል፣ እናም በብልሹ ዓላማ የተሞላው ሰው ይወደሳል። ሚስጥራዊ ሴሰኝነት በነዚህ በተታለሉ ነፍሶች እንደ መልካም ነገር ይወሰዳል። ይህ አንዱ የጥንቆላ (የመተት) ዝርያ ነው። የገላትያ ሰዎች የሐዋርያው ጥያቄ ‘በዓይናችሁ ፊት የሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?’ የሚል ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል። በመናፍቃንነትና በሴሰኝነት ውስጥ ሁል ጊዜ የመተት (የአዚም) ኃይል አለ። አእምሮ በጣም ከመታለሉ የተነሳ በብልሃት ማመዛዘን አይችልም፣ እና ይህ የቅዠት ዓለም ያለማቋረጥ ከንጽሕና መንገድ ወደ ውጭ ይመራዋል። መንፈሳዊው እይታ ይደበዝዛል፣ እናም እስከ አሁን በስነ ምግባር ያልረከሱ ሰዎች በእነዚያ የብርሃን መልእክተኞች ነን በሚሉት የሰይጣን ወኪሎች አሳሳች ውስብስብነት ግራ ይገባቸዋል። ለእነዚህ ወኪሎች ኃይል የሚሰጠው ይህ ማታለያ ነው። በድፍረት ቢወጡ እና ሥራቸውን በግልፅ ቢያሳዩ ለአፍታም ሳይቆዩ ተቀባይነታቸውን ያጡ ነበር፤ ነገር ግን መጀመሪያ የሚሠሩት ርኅራኄን ለማግኘት እና እንደ ቅዱሳን ራሳቸውን የሚሠዉ የእግዚአብሔር ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው በመታየት አስተማማኝ የሆነ መተማመንን ለማግኘት ነው። እንደ ልዩ መልእክተኞቹ ሆነው በመታየት ግን የእግዚአብሔርን ሕግ ለማፍረስ በመሞከር ነፍሳትን ከቀና መንገድ የማራቅ ጥበባዊ ሥራቸውን ይጀምራሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 142, 143.
ለ. እንዲህ ያሉ አደጋዎች ሲያጋጥሙን ምን ላይ ማተኮር አለብን? ኢሳይያስ 51:7፣ 8፤ ቲቶ 1፡15
“ጠላታችን ዲያብሎስ እንደሚያገሣ አንበሳ የሚውጠውን ፈልጎ በሚመላለስበት በዚህ ክፉ ዘመን፣ የማስጠንቀቂያ ድምፄን ማሰማት እንደሚያስፈልግ አይቻለሁ። ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ፣ ጸልዩም። በክፋት ለሰይጣን አገልግሎት የሚያውሉ ድንቅ ችሎታ ያላቸው ብዙዎች አሉ። ከዓለም ወጥቻለሁ ለሚለውና የጨለማውን ሥራ ትቶ ለወጣ ሕዝብ ምን ማስጠንቀቂያ መስጠት እችላለሁን? . . . ብዙዎቹ ርኩስ አስተሳሰቦችን፣ ያልተቀደሱ ሐሳቦችን፣ ያልተቀደሱ ምኞቶችን እና ተራ ፍላጎቶችን ይንከባከባሉ። አምላክ በእንደዚህ ዓይነት ዛፍ ላይ የሚያፈራውን ፍሬ ይጠላል። ንጹሕና ቅዱሳን መላእክቶች የእነዚያን አካሄድ በጥላቻ ይመለከቷቸዋል፣ ሰይጣን ግን ደስ ይለዋል። ኧረ ወንዶችና ሴቶች የእግዚአብሔርን ሕግ በመጣስ የሚገኘው ጥቅማቸው ምን ያህል አጸያፊ እንደሆነ ቢያስቡ! በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ፣ ሕግን መተላለፍ በእግዚአብሔር ፊት ውርደት ነው፣ ለሰውም እርግማን ነው። የሁኔታው መልኩ ምንም ይሁን ምን እንዲሁም የፈጸመው ሰው ማንም ይሁን ማን እኛ ሕጉን ልንጠብቅ ይገባናል።”—Ibid., p. 146.
ማክሰኞ
ነሐሴ 14
3. ለታላቁ ብርሃን ተጠያቂ
ሀ. የእግዚአብሔር ቃል የአምላክን ሕዝቦች ለማርከስ የሚጥሩ አዳኞችን ዕጣ ፈንታ የሚገልጸው እንዴት ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 2:14፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3:5-9
“የሴሰኝነትን ባቡር ተከትሎ የሚመጣው ደስታ ማጣትና ውርደትን ለመገመት ከባድ ነው። ዓለም በነዋሪዎቿ ሥር ረክሳለች። የኃጢአታቸውን ጽዋ ልሞሉ ተቃርበዋል፤ ነገር ግን እጅግ የከፋ ቅጣትን የሚያመጣው እግዚአብሔርን የመምሰል መጎናጸፊያ ተጀቡኖ ግን ውስጥ ለውስጥ የሚደረግ የበደል ተግባር ነው። በደላቸው ምን ቢበዛም የዓለም ቤዛ ግን እውነተኛ ንስሐን ፈጽሞ አልናቀም፤ ነገር ግን በፈሪሳውያንና በግብዞች ላይ የሚያቃጥል ነቀፋን ያወርዳል። ከእነዚህ ክፍሎች ይልቅ ለግልጽ ኃጢአተኛ ሰው ብዙ ተስፋ አለው።
“ስለዚህም ምክንያት (የእውነትን ፍቅር ባለመቀበል) ውሸትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር ስሕተትን ይልክባቸዋል፤ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን ይቀበሉ ዘንድ። ይህ ሰውና በእርሱ የተታለሉ ሰዎች እውነትን አይወዱም ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸዋል። በዝሙትና በሴሰኝነት እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ነገር የለም ከማለት የበለጠ ምን ማታለል ይደርስባቸዋል? መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ኃጢአቶች ላይ ብዙ ማስጠንቀቂያዎችን ይዟል።”—Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 144, 145.
“የክርስቶስ አምባሳደር እንደመሆናችሁ፣ የወቅቱን እውነት የምትናገሩ እናንተ ከማንኛውም የርኩሰት አቀራረብ እንድትቆጠቡ እና ርኩስ የሆነ ሀሳብ የሚተነፍሱትን ማህበረሰብ እንድትተው እለምናችኋለሁ። እነዚህን ርኩስ ኃጢአቶች በጣም በጥላቻ ተጸየፉአቸው። . . .
“እነዚህ የሚያረክሱ ኃጢአቶች በዓለም ውስጥ እየጨመሩ ወደ ቤተ ክርስቲያናችንም ዘልቀው እንደሚገቡና ለእነርሱም ምንም ክፍተት እንዳትሰጡ እኔም አስጠንቅቃችኋለሁ። ከአሳሳቾች ዞር በሉ። እንደዚህ ዓይነቱ የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ብል እንኳ በሰው አምሳል የቆመ ሰይጣን ነውና።”—Ibid., p. 146.
ለ. ታላቅ ብርሃን አለን ለሚሉ የሚጋረጥባቸውን ልዩ አደጋን ጥቀስ። ሮሜ 2፡21-23
“ለሟች ለሰው ልጆች ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የተከበረው መልእክት ለዚህ ህዝብ በአደራ ተሰጥቶታል፣ እና በእሱ ከተቀደሱ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። ከፍ ባለው የዘላለም እውነት መድረክ ላይ እንደቆሙ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ሁሉ እንደሚጠብቁ ይናገራሉ። እንግዲያው ኃጢአት ቢሠሩ፣ ዝሙትና ሴሰኝነት ቢፈጽሙ፣ የአምላክ ሕግ በእነርሱ ላይ እንደሚሠራና ከማያምኑት ክፍሎች በላይ ጥፋታቸው አሥር እጥፍ እንደሚበልጥ ይወቁ።”—Ibid., vol. 2, pp. 450, 451.
ረቡዕ
ነሐሴ 15
4. የምንንከባከበውን ኃጢያታችንን የምናስወግድበት ጊዜ!
ሀ. በግትርነት ማንኛውንም የኃጢአት ልማድ ብንከተል ከማን ጋር እንነጻጸራለን—ለምንስ? 2ኛ ጴጥሮስ 2:15፣ 16፤ ዘኍልቍ 22:9፣ 12፣ 21፣ 27፣ 28፤ 31፡16።
“ዛሬ ለእግዚአብሔር ሰዎች ምንም ዓይነት ክርስቲያናዊ ያልሆነ ባሕርይ በልባቸው ውስጥ እንዲኖር አምላክ እንዳማይፈቅድ ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶናል። የምንንከባከበው ኃጢአት ይለመዳል፣ እንዲሁም በመደጋገም ይጠናከራል፣ ብዙም ሳይቆይ ተጽእኖ ቁጥጥር ሥር ያደርገናል፣ ሁሉንም ክቡር ኃይሎችን ለራሱ ያስገዛል። በለዓም የዓመፅን ደሞዝ ወደደ። እግዚአብሔር ከጣዖት አምልኮ ጋር የፈረጀውን የመጎምጀት ኃጢአትን እርሱ አልተቃወመውም፣ ድልም አላደረገበትም። ሰይጣን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው በዚህ አንድ ጥፋት ሲሆን ይህም ባህሪውን አበላሽቶታል።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 1, p. 1116.
ለ. የበለጠ ብርሃን አለን ለሚሉ ሰዎች አደጋው ምንድን ነው? ሮሜ 2፡21-23።
“ትምክህተኛ መናፍስታዊ አብዝቶ ስለታላቅ ነፃነት ይናገራል፣ እንዲሁም ለስላሳና በሚያማምሩ ቃላቶች ከጠባቡና ከቀጥተኛ መንገድ ይልቅ፣ ሰፊውን የተድላና የኃጢአት ምኞትን ለመምረጥ ያልተጠነቀቁ ነፍሳትን ለመማረክና ለማታለል ይፈልጋል። መናፍስታዊያን የእግዚአብሔርን ሕግ መስፈርቶች ባርነት ብለው ይጠሩታል፣ ስለዚህ እነርሱን የሚታዘዙት በባርነት ፍርሃት ውስጥ ይኖራሉ ይላሉ። በለስላሳ ቃላቶችና ንግግሮችን እያደረጉ በነጻነታቸው ይመካሉ፣ በዚህም አደገኛ ኑፋቄያቸውን በጽድቅ ልብስ ለመሸፈን ይፈልጋሉ። በጣም አመፅ የሚቀሰቅሱ ወንጀሎች ለሰው ዘር በረከት ተደርገው እንዲወሰዱ ያደርጋሉ።
“የሥጋዊ ልብ መነሳሳትን እንዲከተል በኃጢአተኛው ፊት ሰፊ በር ይከፍታሉ፣ እናም የእግዚአብሔርን ህግ ይጥሳሉ፣ በተለይም ሰባተኛውን ትእዛዝ። እነዚህን ታላቅ የሚመስሉ ከንቱ ቃላት በመናገርና በኃጢአታቸው ነፃነታቸውን እንዳገኙ በማስመሰል፣ በተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ በማመፅ የነፃነት ደስታ ይገኛል ብለው፣ ለሚያታልሏቸው ሰዎች ቃል ይገባሉ። እነዚህ የተሸነገሉ ነፍሳት ራሳቸው፣ በሰይጣን ባርነትና በኃይሉ ቁጥጥር ስር ያሉ ናቸው፣ በዚህም እነሱ ራሳቸው የመረጡትን የኃጢአት ጎዳና ለመከተል ለሚደፍሩ ግን ነፃነታቸው ተስፋ ሰጭ መስሎ እንዲታይ የሚያደርጉ ናቸው።
“በመጽሕፍ ቅዱስ ዕዉሮች፣ ዕውሮችን ይመራሉ የሚለው በርግጥም ተፈጸመ። ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና። እነዚህ የተሸነገሉ ነፍሳት እጅግ አስከፊ በሆነው የአጋንንት ፈቃድ ባርነት ሥር ናቸው። ራሳቸውን ከጨለማ ኃይሎች ጋር ተባብረዋል እና የአጋንንትን ፈቃድ ለመቃወም የሚያስችል ጥንካሬ የላቸውም።”—The Review and Herald, April 15, 1875.
ሐሙስ
ነሐሴ 16
5. በመገሰጹ የተባረከ
ሀ. ያለንን ምርጫ ምን ምን እንደሆነ ያብራሩ። 2ኛ ጴጥሮስ 2:19፤ ሮሜ 6:16፣ 19፤ ምሳሌ 10፡17
[ዮሐንስ] ብዙ ጊዜ በአዳኙ ማስጠንቀቂያና ግሳጼ ተሰጥቶታል ፤ እርሱም እነዚህንም ተግሣጾች ተቀብሏል። የመለኮት ባሕርይ እንደተገለጠለት፣ ዮሐንስ የራሱን ጉድለት አይቶ፣ በመገለጡም ተዋረደ። ከቀን ወደ ቀን፣ ከራሱ የአመጽ መንፈስ በተቃራኒ፣ የየሱስን ርህራሄ እና ትዕግስት አይቷል፣ እንዲሁም የትህትናና ትዕግስት ትምህርቱን አዳመጥ። ለጌታው ባለው ፍቅር ራሱን መመልከት እስኪያቅተው ድረስ ልቡ ከቀን ወደ ቀን ወደ ክርስቶስ ተሳበ። በእግዚአብሔር ልጅ የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ያየው ኃይልና ርኅራኄ፣ ግርማና የዋህነት፣ ብርታትና ትዕግሥት ነፍሱን በአድናቆት ሞላው። ቂመኛነቱንና ቁጣውን እንዲያስተካክለዉ ለክርስቶስ የመቅረጽ ኃይል አሳልፎ ሰጠ፣ በመለኮታዊ ፍቅርም የባሕርይ ለውጥን አደረገ።
“በዮሐንስ ሕይወት ውስጥ ከታየው ቅድስና ጋር ስተያይ አብሮት የነበረው ደቀ መዝሙር የሆነው የይሁዳ ተሞክሮ እጅግ የተለየ ነው። . . . ብዙ ጊዜ፣ የአዳኙን ቃል ሲያዳምጥ ፣ ጥፋተኝነት ስሜት ወደ አዕምሮው ይመጣ ነበር፣ ነገር ግን ልቡን አያዋርድም ወይም ኃጢአቱን አይናዘዝም። መለኮታዊውን፣ የመንፈስን ተጽዕኖ በመቃወም እወደዋለሁ ያለውን ጌታውን አዋረደ። ዮሐንስ ከስህተቶቹ ጋር አጥብቆ ተዋግቷል፤ ነገር ግን ይሁዳ ሕሊናውን ባለማዳመጥ ለፈተና ራሱን አዘነበለ። . . .
“ዮሐንስና ይሁዳ የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ ተወካዮች ናቸው። ሁለቱም እነዚህ ደቀ መዛሙርት መለኮታዊውን እቅድ ለመማርና ለመከተል ተመሳሳይ እድሎች ነበሯቸው። ሁለቱም ከየሱስ ጋር በቅርበት አብረው ነበሩ እንዲሁም ትምህርቱን የማዳመጥ እድል ነበራቸው። እያንዳንዳቸው ከባድ የባህሪ ጉድለቶች አሏቸው፤ እንዲሁ እያንዳንዳቸው ባህሪን ወደ ሚለውጠው መለኮታዊ ጸጋ መዳረሻ መንገድ ነበራቸው። . . . አንዱ፣ ዕለት ዕለት ለራሱ የሚሞትና ኃጢአትን የሚያሸንፍ፣ በእውነት የተቀደሰ ነው፤ ሌላው ደግሞ የጸጋን ኃይል በመቃወም የራስ ወዳድነት ምኞቶችን በመንከባከብ ለሰይጣን ባርነት ተገዛ።”—The Acts of the Apostles, pp. 557, 558.
አርብ
ነሐሴ 17
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. ማርያም ከለምጽ ውርደት መዳን የምትችለው እንዴት ነው?
2. በዛሬው ጊዜ ላለው ኅብረተሰብ የጴጥሮስ ማስጠንቀቂያዎች አሁን ለእኛ በጣም ጠቃሚ የሆኑት እንዴት ነው?
3. ጠማማ በሆነ ዓለም ውስጥ የአምላክ ሕዝቦች ልዩ የሚሆኑት በየትኞቹ መንገዶች ነው?
4. የበለዓምን እጣ ፈንታ ማስወገድ ብቸኛው መንገድ እንዴት ነው?
5. በተሳሳቱት በዮሐንስና በይሁዳ መካከል ያለውን የአመለካከት ልዩነት ግለጽ።