እሁድ
ነሐሴ 05
1. እምነት፣ እንጂ ተረት አይደለም
ሀ. ጴጥሮስ የየሱስ ክርስቶስን አምላክነት ማረጋገጥ የቻለው ለምንድን ነው? ማቴዎስ 17፡1-7
“በተራራው ላይ የወደፊቱ የክብር መንግሥት በትንንሽ መልክ ተመስሏል—ክርስቶስ ንጉሥነት፣ የተነሱት ቅዱሳን ተወካይ ሙሴ፣ እንዲሁም የተለወጠው ኤልያስ።
“ደቀ መዛሙርቱ ትዕይንቱን ገና አላስተዋሉም፤ ነገር ግን ትዕግሥተኛው ፣ ትሑት እና ደጉ፣ ረዳት አልባ ተንከራታች መምህራቸውን፣ በሰማያት የተወደዱ ሰዎች ስላከበሩ ደስ ብሏቸዋል።”—The Desire of Ages, p. 422.
“ሌሊቱ ሁሉ በተራራው ላይ አለፈ። ፀሐይም በወጣች ጊዜ የሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ሜዳ ወረዱ። ደቀ መዛሙርቱ በሐሳብ ተውጠው ዝም አሉ። ጴጥሮስ እንኳ የሚናገረው ቃል አልነበረውም።”—Ibid., p. 426.
ለ. ጴጥሮስ በልበ ሙሉነት ምን ማወጅ ችሏል - እኛስ የእርሱን ልበ ሙሉ ምሳሌውን በመከተል ይህንን ማስተጋባት የምንችለው እንዴት ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 1፡16-18
“ሐሰት ከእውነት አይደለም። በተንኮል የተነደፉ ተረቶች ከተከተልን በእግዚአብሔርና በክርስቶስ ላይ ከተሰለፉ ከጠላት ኃይሎች ጋር እንተባበራለን። . . .
“እያንዳንዱ የክፋት አይነት እኛን ለማጥቃት እድል እየጠበቀ ነው። ሽንገላ፣ ጉቦ፣ ማበረታቻ፣ አስደናቂ አጓጊ ተስፋዎች፣ በጣም በትጋት እኛ ላይ በጥቅም ላይ ይውላሉ።
“ይህንን ክፉውን በመቃወም ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ የሚለውን ግንብ በመካከል ለማቆም የአምላክ አገልጋዮች ምን እያደረጉ ነው?”—Selected Messages, bk. 1, p. 194.
ሰኞ
ነሐሴ 06
2. የትንቢት ተጽእኖ
ሀ. ግራ መጋባት ሲበዛ፣ ክርስቶስ ወደ ኤማሁስ በሚወስደው መንገድ ላይ ተስፋ ለቆረጡ ደቀ መዛሙርት እንዴት ተስፋ እንዳመጣላቸው እንደተገለጸው ስለምን ነገሮች አመስጋኞች መሆን እንችላለን? ሉቃስ 24:15–21፣ 27፣ 32፤ 2ኛ ጴጥሮስ 1:19
“የደቀ መዛሙርቱ ልብ [ወደ ኤማሁስ በሚወስደው መንገድ ላይ] ታወከ። እምነታቸዉም ተቀጣጠለ። የሱስ ገና ራሱን ሳይገልጥላቸው “ለሕያው
ተስፋ” [1ኛ ጴጥ 1÷3] እንደገና ተወለዱ። መረዳታቸውን ቦግ ሊያደርገው፣ “እጅግ [በ]ፀና የትንቢት ቃል” [2ኛ ጴጥ 1÷10] ላይም እምነታቸውን ሊያፀናው አላማው ነበር። እውነት በአዕምሯቸው ጠንካራ ሥር እንዲሰድ የተመኘው በራሱ ግላዊ ምስክርነት በመደገፋቸው ምክንያት ብቻ ሳይሆን እርግጥ በሆኑት፣ ወደፊት ሊሆን ላለው ጠቋሚ በነበረው የሕጉ ተምሳሌቶችና ጥላዎች፣ እንዲሁም በብሉይ ኪዳን ትንቢታት ጭምር ነበር። የክርስቶስ ተከታዮች በእውቀት ላይ የተመሠረተ እምነት ያስፈልጋቸዋል፤ ይህም ለግላቸው ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን እውቀት ወደ ዓለም እንዲያሰራጩት ነው። ይህንንም እውቀት ለማካፈል እንደመንደርደሪያ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ “ሙሴና ነብያት” አመላከታቸው። የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አስፈላጊነትና ዋጋ፣ በእንዲህ መልኩ በተነሳው አዳኝ ምስክርነት ምን ያህል እንደሆነ ታይቷል።”—The Great Controversy, p. 349.
“በየሱስ ክርስቶስ በኩል የዚህ ታላቅ መዳን ተካፋዮች የሆኑት የእሱ ሚስዮናውያን እንዲሆኑ [የእግዚአብሔር] እቅድ ነው። . . . ህዝቡ ለመጪው ፍርድ እንዲዘጋጅ ማስጠንቀቅ አለብን። ተረትን ብቻ ለሚያዳምጡ ሰዎች፣ እግዚአብሔር የጸናውን የትንቢት ቃል ለመስማት እድል ይሰጣል፣ ለዚህም በጨለማ ስፍራ ብርሃን እንዲበራ ቢያደርጉ መልካም ያደርጋሉ። የጸናውን የእውነት ቃል ለሚሰሙ ሁሉ ግንዛቤ ይሰጣል። ሁሉም እውነትን የአምላክን ቃል እንደሚረዱና በጨለማ ያሉትን ለማስተማር ብቁ እንደሆኑ በሚናገሩ ሰዎች ከሚቀርቡላቸው ተረቶች ጋር ሊያነጻጽሩ ይችላሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 631, 632.
ለ. ዛሬ በጣም ጠቃሚ የሆነውን ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የተናገረውን ማስጠንቀቂያ ጥቀስ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6:20፣ 21
“የአረማውያን የጣዖት አምልኮ መንፈስ በዛሬው ጊዜ ተስፋፍቷል፣ እንዲሁም በሳይንስና በትምህርት ተጽዕኖ ሥር ይበልጥ የጠራና ማራኪ መልክ ያዘ። በየዕለቱ፣ በጸናው የትንቢት ቃል ላይ ያለው እምነት በፍጥነት እያሽቆለቆለ መምጣቱን እንዲሁም በእርሱ ምትክ የሰይጣን ጥንቆላና አስማት የሰዎችን አእምሮ እንደሚማርክ መታየቱ የሚያሳዝን ማስረጃ ነው።”—Ibid., vol. 5, p. 192.
ማክሰኞ
ነሐሴ 07
3. ለነፍሳችን መልሕቅ
ሀ. እውነተኛውን ትንቢት እንደ መልሕቅና ለክርስቲያናዊ እምነት መሠረት አድርገን እንዴት ልንገነዘበው እንችላለን? አሞጽ 3:7፤ 2ኛ ጴጥሮስ 1:20፣ 21
“ብዙ፣ በጣም ብዙ፣ የቅዱሳን ጽሑፎችን ትክክለኛነትና እውነትኛነትን ይጠራጠራሉ። ሰበአዊ ምክንያታዊነትና የሰው ልብ ምናብ እያሽቆለቆለ በመምጣቱ ፤ እንደ ተሰጠን ልንቀበለው የሚገባውን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈውን የእግዚአብሄርን ቃል፣ በምስጥር ጭጋግ እንድከበብ አድርጓል። በዐለቱ ግርጌ ላይ በግልጽና በተለዩ መስመሮች ሆኖ ምንም ነገር አይታይም። ይህ የመጨረሻው ቀን ምልክት ከሆኑት ምልክቶች አንዱ ነው።”—Selected Messages, bk. 1, p. 15.
“ኦሪጅናል ለመሆን የሚጣጣሩ፣ ከተጻፈው በላይ ጥበበኞች የሆኑ ሰዎች አሉ። ስለዚህም ጥበባቸው ሞኝነት ነው። የእግዚአብሄርን መለኮታዊ ፈቃድና አላማዎች በመረዳት ረገድ እጅግ ኋላ ቀር መሆናቸውን የሚያሳዩ አስደናቂ ነገሮችን አስቀድመው ያገኛሉ። ከሰው ከዘመናት የተሰወረውን ምስጢር ሊገልጹ ወይም ሊፈቱ ሲፈልጉ፣ በጭቃ ውስጥ እንደሚንከራተቱ፣ ራሱን ማውጣት ሳይችሉ፣ ነገር ግን ሌሎች ራሳቸውን ካሉበት ከጭቃማ ባሕር እንዴት ማውጣት እንደሚችሉ ለሌሎች እንደሚናገር ሰው ናቸው። ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን ስሕተቶች የሚያርሙ አድርገው ራሳቸውን ለሚመለከቱ ሰዎች ተስማሚ ምሳሌ ነው። ማንም ሰው ጌታ ሊናገር የፈለገውን ወይም መናገር የፈለገው ይህ ነው በማለት መጽሐፍ ቅዱስን ማሻሻል አይችልም።
“አንዳንዶች በትኩረት ይመለከቱና 'በቅጂው ወይም በትርም ላይ የሆነ ስህተት ሊኖር ይችላል ብላችሁ አታስቡምን?' ይሉናል። ይህ ሁሉ ሊከሰት የሚችል ነው፣ እናም በዚህ አጋጣሚ ወይም ሁኔታ ላይ የሚያመነታና የሚሰናከልበት፣ እሱ ጠባብ አእምሮ ያለውና በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው በእግዚአብሔር ቃል ምስጢራት ላይ ለመሰናከል ዝግጁ የሆነ ሰው ነው።”—Ibid., p. 16.
“ጌታ ለሰዎች የሚናገረው የተበላሸው የምድር ስሜት፣ የደነዘዘዉ የምድር እይታ፣ ቃላቱን ይረዳው ዘንድ ፍጹም ባልሆነ ንግግር ነው። የእግዚአብሔር ትሕትናም እንዲሁ ይታያል። የወደቁትን ሰዎች ባሉበት ደረጃ ያገኛቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ በቀላልነቱ ፍጹም፣ ለእግዚአብሔር ታላላቅ ሀሳቦች መልስ አይሰጥም። ወሰን የለሽ ሐሳቦች፣ ወሰን ባላቸው የሐሳብ ተሽከርካሪዎች (ሰው) ውስጥ ፈጽሞ ሊካተቱ አይችሉም። ብዙ ሰዎች እንደሚገምቱት የመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጾች የተጋነኑ ከመሆን ይልቅ፤ ምንም እንኳ ጸሐፊው የከፍተኛ ሃሳብ እውነቶችን ለማስተላለፍ በጣም ገላጭ የሆኑ ቋንቋዎችን ቢመርጥም እንኳን፣ እነዚያ ጠንከር ያሉ አገላለጾች ከሐሳቡ ታላቅነት ጋር ሲተያዩ ከምንም የማይገቡ ይሆናሉ።”—Ibid., p. 22.
“ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለመንቀፍ ሲሞክሩ፣ በተቀደሰ፣ ቅዱስ ሥፍራን ይደፍራሉ፣ ስለዚህ ቢፈሩና ብንቀጠቀጡ እንዲሁም ጥበባቸውን እንደ ሞኝነት ቢደብቁ ይሻላቸዋል። አምላክ ማንንም ሰው፣ ከቃሉ አንዳንድ ክፍሎችን መርጦ በመንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፉ ተቀብሎ ሌሎቹን ደግሞ መንፈሳዊ ያልሆኑ እንደሆኑ አድርጎ በማንቋሸሽ በቃሉ ላይ እንዲፈርድ ፈቃድ አይሰጥም።”—Ibid., p. 23.
ረቡዕ
ነሐሴ 08
4. እግዚአብሔር ለልጆቹ ያዘጋጀው
ሀ. በዛሬው ጊዜ ብዙውን ጊዜ የሚያጋጥመንን አንድ አስጨናቂ ሁኔታና ጉዳዩን እንዴት መጋፈጥ እንዳለብን ግለጽ። 2ኛ ጴጥሮስ 2:1-3፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 4:1፣ 2፤ ዘዳግም 6:24፣ 25
“ከእነዚህ የመጨረሻ ቀኖች ይልቅ በሰዎች የተሳሳተ ግንዛቤ የተነሳ በእውነት ላይ የተዛባ ትርጉም ፣ ንቀትና ጥፋት የሚደርስበት ጊዜ ከዚህ በፊት ፈጽሞ አልነበረም። ሰዎች ለሕዝብ አንደበተ ርቱዕ ሆነው የሚወክሉትን ብዙ መናፍቃን ይዘው ራሳቸውን አምጥተዋል። ሰዎቹ በአንዳንድ እንግዳ፣ አዲስ ነገር የተማረኩ ሆነዋልና ፤ ሰዎች እንደ አንድ ነገር ሊቀርጹ የሚችሉትን የሃሳቦችን ባህሪ ለይተው ለማወቅ በልምድ ጥበበኞች አይደሉም። ነገር ግን ይህንን ነገር ትልቅ መዘዝ ያለው ነገር ብሎ መጥራትና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ማገናኘት ነገሩን እውነት አያደርገውም። . . .
“የእግዚአብሔርን ድምፅ ከተገለጠው ቃሉ፣ እርግጠኛ ከሆነው ከትንቢት ቃል መስማት አለብን። ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉና አስደናቂ ነገር ለማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ ወደ ጤናማ አእምሮ ቢመጡ ይሻላቸዋል።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 6, pp. 1064, 1065.
“የእግዚአብሔር ሕግ የዘላለም ተሐድሶ ሁሉ መሠረት ነው። ይህንን ህግ የመታዘዝን አስፈላጊነት በግልፅና በተለዩ መስመሮች ለአለም እናቀርባለን። የእግዚአብሔርን ህግ መታዘዝ ለሥራ፣ ለኢኮኖሚ፣ ለእውነት እንዲሁም ለሰው - ለሰው ፍትሃዊ ግንኙነት ትልቁ ማበረታቻ ነው። . . .
“የጌታን ድምፅ በትጋት የሚሰሙና በደስታ ትእዛዛቱን የሚጠብቁ እግዚአብሔርን ከሚያዩት መካከል ይሆናሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 8, p. 199.
ለ. ጴጥሮስ አምላክን ለሚወዱትና ለሚፈሩት በጸጋ ነፃ የመውጣት አስፈላጊነት ምን ያህል አስፈላጊና የጸና እንደሆነ ለማሳየት ምን የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎችን ጠቅሷል? 2ኛ ጴጥሮስ 2፡4-8
“ስለዚህ ለአታላዩ ኃይልና ለማያንቀላፋው ለጨለማው ልዑል ክፋት የተጋለጡ፣ ከክፉ ኃይላት ሁሉ ጋር ለሚታገሉት የእግዚአብሔር ወገኖች የማያቋርጥ የሰማይ መላእክቶች ጥበቃ እንዳለላቸው ተረጋግጦላቸዋል። ይህ የጥበቃ ዋስትና ሳያስፈልግ የተሰጠ አይደለም። እግዚአብሔር ለልጆቹ የፀጋና የጥበቃ የተስፋ ቃል የሚሰጥበት ምክንያት፤ ቁጥራቸው የበዛ፣ ለክፋት ቆርጠው የተነሱ፣ የማይታክቱ፤ ከክፋታቸውና ከኃይላቸው የተነሳ ቸልተኛና የማይሰማ የሆነ ማንም ሰው ደህና ሊሆን የማይችልበት፣ መመከት ያለባቸው የክፋት ሰራዊቶች ስላሉ ነው።”—The Great Controversy, p. 513.
ሐሙስ
ነሐሴ 09
5. አዳኛችንን መንከባከብ
ሀ. አምላክ የሚሰጠን ከሁሉ የላቀ መዳን (ነጻ መዉጣት) ምንድን ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 2:9 (የመጀመሪያ አጋማሽ)፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 10:13፤ መዝሙር 50:15
“እግዚአብሔር በመታዘዝ መንገድ የሚሄዱትን ሁሉ ይጠብቃቸዋል፤ ከዚያ መውጣት ግን በሰይጣን መሬት ላይ መስፈር ነው። እዚያ እንደምንወድቅ እርግጠኛ ነን። አዳኝ ‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ እና ጸልዩ› ብሎ አዞናል። ማርቆስ 14፡38። ማሰላሰል እና ጸሎት ወደ አደጋው መንገድ እንዳንሮጥ ይጠብቀናል፣ እና ስለዚህ ከብዙ ሽንፈት መዳን እንችላለን።
“ነገር ግን በፈተና ስንጠቃ ድፍረት ማጣት የለብንም። ብዙ ጊዜ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስንገባ የእግዚአብሔር መንፈስ እየመራን መሆኑን እንጠራጠራለን። ነገር ግን የሱስ በሰይጣን እንዲፈተን ወደ ምድረ በዳ የመጣው በመንፈስ መሪነት ነው። እግዚአብሔር ወደ ፈተና ሲያስገባን ለጥቅማችን የሚሆን አላማ አለው። የሱስ ወደ ፈተና በመግባቱ የተሰጠውን ተስፋዎች አልረሳም፣ ፈተናም በእርሱ ላይ በመጣ ጊዜ በተስፋ መቁረጥ አልቆዘመምም። እኛም ደግሞ እርሱን መከተል አለብን።”—The Desire of Ages, pp. 126–129.
“ፈተና ኃጢአት አይደለም። የሱስ ቅዱስ እና ንጹህ ነበር፤ እርሱ ግን እንደ እኛ በሁሉም ነገር ተፈትኗል፣ ነገር ግን ሰው በገዛ ጥንካሬውና በኃይሉ እንዲጸና ፈጽሞ አይጠራም። በእሱ የተሳካ ፈተናን የመቋቋም ሂደት ውስጥ የእርሱን እርምጃዎች እንድንከተል ጥሩ ምሳሌ ትቶልናል። በራሳችን የምንተማመን ከሆንን ወይም ራሳችንን የምናጸድቅ ከሆንን በፈተና ኃይል ሥር እንድንወድቅ እንቀራለን፤ ነገር ግን ወደ የሱስ ከተመለከትን እና በእርሱ ከታመንን በጦር ሜዳ ጠላቱን ያሸነፈውን ኃይል እንረዳዋለን፣ እናም ከማንኛውም ፈተና የማምለጫ መንገድን ያዘጋጅልናል። ሰይጣን እንደ ጎርፍ ሲመጣ ፈተናዎቹን በመንፈስ ሰይፍ ልንጋፈጥ ይገባናል፣ የሱስም ረዳታችን ይሆናል፤ በእርሱም ላይ ስለእኛ ይነሳልናል። የእውነት አባት እንደ እሳት በሚነደው ኃይሉ በፊቱ ሲነሳ፣ የሐሰት አባት ባለበት ይንቀጠቀጣል።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 426.
አርብ
ነሐሴ 10
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች መረዳቴ በመጪዎቹ ዘመናት ሊረዳኝ የሚችለው እንዴት ነው?
2. የሱስ ወደ ኤማሁስ ለሚጓዙ ደቀ መዛሙርት ትንቢት ያጋራው ለምን ነበር?
3. ሰይጣን በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ያለንን እምነት ለማዳከም የሚፈልገው በየትኞቹ መንገዶች ነው?
4. በአምላክ ቃላቶች ላይ በጥብቅ መጣበቅ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው?
5. በፈተና ስንጠቃ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ማስታወስ ይኖርብናል?