ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2) << >> መቅድም የኃጢአት ችግር በፕላኔቷ ምድር ላይ እየተባባሰ በሄደ መጠን፣ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ሰይጣን ሕዝቡ እንዲበሳጭ በሚያደርግበት በዚህ ጊዜ፣ የአምላክ ሕዝቦች የሱስን አትኩሮ በመመለከት የሚታዩትን ሳይሆን የማይታዩትን፣ ዘላለማዊ እውነታዎችን መመልከታቸው ምንኛ አስፈላጊ ነገር ነው። ስለዚህ በዚህ ሩብ አመት በአለም ዙሪያ ያሉ የሰንበት ተማሪዎች የእውነት ውድ ቅርሶች ተከታታይ የሆነዉን ክፍል 2 "ደማቅ የብርሃን ጨረሮች" በሚል ርዕስ መማር ይቀጥላሉ። ሕገ ወጥነት እና ግራ መጋባት በሁሉም ቦታ አለ፣ ስለዚህ በሕይወታችን ወዴት መሄድ እንዳለብን ለማወቅ በእርግጥም የእግዚአብሔርን እርዳታ እንፈልጋለን። የሞራል ኮምፓስ ያስፈልገናል። “አንድ ጸሐፊ የአምላክን ሕግ ለመቀየር የተደረገውን ሙከራ ሁለት መንገዶች በሚገናኙበት አንድ አስፈላጊ መስቀለኛ መንገድ ላይ ያለን ምልክት ከቆመበት ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ በማዞር ከሚደረግ ከጥንት ተንኮለኛ ልማድ ጋር አመሳስለውታል። ይህ ተንኮልም ብዙ ጊዜ ያስከትል የነበረዉ ግራ መጋባትና ችግር ትልቅ ነበር። “ለዚህ ዓለም ጉዞ እግዚአብሔር የአቅጣጫ ምልክት አቁሟል፤ አንዱ የአቅጣጫ ምልክት እግዚአብሔርን መታዘዝ ወደ ደስታና ወደ ዘላለም ሕይወት እንደሚያደርስ ሲያሳይ፣ ሌላው የአቅጣጫ ምልክት ደግሞ አለመታዘዝ ወደ ስቃይና ወደ ሞት እንደሚያደርስ ያሳያል። የደስታ ጎዳና ምልክት፣ ለአይሁዶች ወደ መማጸኛ ከተማ እንደሚያሳየው ምልክት ግልጽ ነበር። ነገር ግን ለሰው ዘር ሁሉ መከራ ባስከተለ ድርጊት ሰይጣን የአቅጣጫውን ምልክት ቀየረው። በዚያ ምክንያት እልፍ አዕላፋት ገደል ገቡ።”—ነቢያትና ነገሥት ገጽ. 179. የሱስ ክርስቶስ ብቸኛው የሰው ልጅ አዳኝ ነው— ስለእርሱ ስናጠና እና እርሱ በሚሰጠን ጥንካሬ ህጉን በመኖር እንለወጣለን። “እርሱ የአምላክን ሕግ የኖረ ሲሆን በራሱ ምሳሌ አምላክን እንዴት መታዘዝ እንዳለብን አሳይቶናል።”—The Desire of Ages, p. 649. አዲስ ልብ - አዲስ አእምሮን በሚሰጠን ከመንፈሱ ጋር ከተባበርን ለዘለአለም ለመዘጋጀት የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ተዘጋጅቷል። ፍቅራችንን ከዚህ ዓለም በማላቀቅና በሰማዩ በየሱስ ላይ በማሰር፣ ዘላለማዊነትን በማሰብ የህይወታችንን አላማ እናዳብራለን። “ኃጢአትን የሚጠላ እግዚአብሔር ሕጉን እንጠብቃለን የሚሉትን ከኃጢአት ሁሉ እንዲርቁ ይጣራል። ንስሐ መግባትንና ቃሉን መታዘዝን ችላ ማለት በጥንቷ እስራኤል ላይ እንዳደረገው ይኸው ኃጢአት በዛሬው ጊዜ በአምላክ ሕዝቦች ላይ ከባድ መዘዝ ያስከትላል።”—The Signs of the Times, February 12, 1880, Art. B.፣ (2ኛ አንቀጽ) “ሰይጣን የወደፊቱን ዓለም ክብር ለመጋረድና የሕዝቡን አጠቃላይ ትኩረቱን ወደ ምድራዊ ሕይወት ነገሮች ለመሳብ ያለማቋረጥ ሰርቷል። ሀሳባችን፣ ጭንቀታችን፣ ድካማችን በጊዜአዊ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ተወጥረው እንዲቀሩ ፈተናዎችን ለማብዛትና የዘላለም እውነታዎችን ዋጋ እንዳንመለከት ወይም እንዳንገነዘብ ለማድረግ ጥረት አድርጓል ። ዓለምና ሀሳቦቹ የያዙት ቦታ በጣም ትልቅ ነው፣ የሱስና ሰማያዊ ነገሮች ግን በአስተሳሰባችንና በፍቅራችን ውስጥ ያላቸው ድርሻ በጣም ትንሽ ነው። የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን በሙሉ በትጋት መወጣት አለብን፤ ነገር ግን ከምንም ነገር በላይ ለጌታችን ለየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ፍቅር ማዳበራችን በጣም አስፈላጊ ነው።”—The Adventist Home, pp. 404, 405. የጀኔራል ኮንፈረንስ ሰንበት ትምህርት ክፍል መምሪያ << >>