ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2) << >> ሰንበት፣ መጋቢት 23፣ 2015 1ኛ ትምህርት ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት (መግባባት) የመታሰቢያ ጥቅስ፡-“በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን።” (1ኛ ዮሐንስ 5:14, 15) ለንባብ የተመረጠዉ፡ Steps to Christ, pp. 93–104. “ለወዳጅ የልብን እንደሚያጫውቱ፣ ጸሎትም ለእግዚአብሔር የልብን ማጫወት ነው፡ የምንጸልየው ስለ እኛ ሁኔታ ለእግዚአብሔር የሚያውቀውን መረጃ ለመስጠት ሳይሆን፣ እርሱን በልባችን ለመቀበል እንዲያግዘን ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርን ወደ እኛ አያወርደውም ነገር ግን እኛን ወደ እርሱ ከፍ ያደርገናል።”—Steps to Christ, pp. 93. 1. ናሙና ጸሎት እሁድ መጋቢት 17 ሀ. ከአዳኛችን ጋር መገናኘት በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድነው? ዮሐንስ 15:4–7; ምሳሌ 18፡24 “እግዚአብሔር በፈጠረው ተፈጥሮ፣ በቃሉ እንዲሁም በፍቅር እንክብቤውና በመንፈሱ አማካይነት በሚያሳድረው ተጽእኖ ይናገረናል፡፡ እነዚህ ግን በቂ አይደሉም፡ እኛ ደግሞ ልባችንን በፊቱ ማፍሰስ ያስፈልገናል፡፡ መንፈሳዊ ህይወትና ብርታት እንዲኖረን ከፈለግን ከሰማያዊ አባታችን ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ሊኖረን ይገባል፡ አሳባችን ወደ እርሱ ሊሳብ ይችል ይሆናል ስለ እጁ ስራዎች፣ ስለ ምህረቱ ስለባርኮቱ እናሰላስል ይሆናል። በዚህ ብቻ ግን ከእግዚአብሔር ጋር በሙላት ተገናኝተናል ለማለት አይቻልም። ከዚህ በተጨማሪ ስለ አለንበት ትክክለኛ ሁኔታ ለእርሱ የምንናገረው ነገር ሊኖረን ይገባል።”—Steps to Christ, pp. 93. ለ. ደቀ መዛሙርቱ የሱስን ከልቡ ሲጸልይ ብዙ ጊዜ አይተውት ስለነበር እንዲያስተምራቸው ምን ጠየቁት እና ምን ምሳሌ አቀረበላቸዉ? ሉቃስ 11:1፤ ማቴዎስ 6:9-13 ሐ. ይህ የናሙና ጸሎት በቃላት እንዲሸምደድና እንዲደጋገም ታስቦ ነበር? ከዚህ መመሪያስ ምን ሌላ ትምህርት እናገኛለን? ማቴዎስ 6፡7 2. በክብር መጥራት(ADDRESS) እና አክብሮት መስጠት(ADORATION) ሰኞ መጋቢት 18 ሀ. በዚህ የናሙና ጸሎት መጀመሪያ ላይ ካለዉ "አባታችን" ከሚለዉ ቃል ምን እንረዳለን? ሮሜ 8፡15–17; ዮሐንስ 20፡17 “ክርስቶስን የግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ ሁሉ እንደ ሙት ልጅ የሕይወት ፈተናዎችን ብቻቸውን እንዲጋፈጡ አልተተውም። የሰማያዩ ቤተሰብ አባል አድርጐ ይቀበላቸዋል አባቱንም አባታችን እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡" እግዚአብሔር የሚያፈቅራቸው «ትንንሽ» ልጆቹ ስለሆኑ ክፍተኛና ዘላለማዊ በሆነ ፍቅር ወደ እርሱ ይጠጋሉ። እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ሥጋዊ ወላጆቻችን ገና አቅመቢስ በነበርን ጊዜ ለእኛ ከነበራቸው ፍቅር ጋር ሲነጻጸር መለኮት ከሰብአዊነት የላቀውን ያህል የበለጠ ነው።The Desire of Ages, p. 327. ለ. እግዚአብሔር "አባታችን" ከሚለዉ ከወዳጅነት ቃል ሌላ ምን ጠቃሚ ሚና አለው? መዝሙረ ዳዊት 5:1, 2 ሐ. በዚህ ጸሎት ውስጥ በሚቀጥለው ክፍል መሠረት አምላክን እርዳታ ከመለመናችን በፊት በመጀመሪያ ምን አስፈላጊ ነጥብ መግለጽ አለብን? መዝሙረ ዳዊት 140:13፤ 92፡1። “በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ የሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5:18 ይህ ትዕዛዝ እኛን የሚቃወሙ የሚመስሉ ነገሮች እንኳን ለጥቅማችን እንደሚሰሩ ማረጋገጫ ነው። አምላክ ለሚጎዳን ነገር አመስጋኞች እንድንሆን አላዘዘንም።”—The Ministry of Healing, p. 255. መ. በኢዮሣፍጥ ምሳሌ የዉዳሴ እና የምስጋና አስፈላጊነት በጦርነት መካከል እንኳን የተገለጠው እንዴት ነው? 2ኛ ዜና 20:1-30 (6–12, 21, 22) “በመስቀሉ ዙሪያ ልንሰበሰብ ይገባናል ክርስቶስና ስቅላቱ በአእምሮአችን የምናስበው ነገር የንግግራችን እንዲሁም የደስታችን ሁሉ የተቀበልናቸውን ማእከል ሊሆኑ ይገባል ከእግዚአብሔር ስጦታዎችም ሁልጊዜ - ማስታወስ ያስፈልገናል። ፍቅሩንም ስናስተውል በመስቀል ላይ ስለ እኛ በተቸነከሩት የጌታ አጆች ላይ ሁሉንም ነገራችንን ለማስረከብ ፈቃዷኞች እንሆናለን፡፡ ነፍስ በምስጋና ክንፍ ወደ ሰማይ ትበራለች። በላይ በሰማይ አደባባዮች እግዚአብሔር በመዝሙርና በሙዚቃ ይመለካል፡፡ እኛ ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ምስጋናችንን በመግለጥ ስናመልክየሰማይ ሠራዊትን አምልኮ እየተጠጋን እንሄዳለን። “ምስጋናን የሚስዋ ሁሉ» እግዚአብሔርን ያከብራል። (መዝ 50፡23)፡፡ ምስጋናና በዜማ ድምጽ›› በአክብሮት በተሞላ ደስታ ወደ ፈጣሪያችን እንቅረብ፡፡ ”— Steps to Christ, pp.. 103, 104 3. ጸሎት እና መደምደሚያ ማክሰኞ መጋቢት 19 ሀ. ምንም እንኳን እንደ የእለት እንጀራችን ያሉ ጊዜያዊ ፍላጎቶቻችን ቢኖሩንም፣ ከጊዜአዊ ፍላጎቶቻችን እንኳን ቀዳሚ ጉዳያችን መሆን ያለበት ምን መንፈሳዊ ተግባር ነው? 1ኛ ነገሥት 17:12–14; ዮሐንስ 6:48; 14:13, 14; 15፡7። እኛ የተቀሰ ሕይወት መኖር የምንችለዉ ጌታ የሱስ ለእኛ ሲል በቀራኒዮ መስቀል ላይ አሳልፎ የተሰጠዉን ሕይወቱን ስንቀበል ነዉ። ይህን ሕይወት የምናገኘዉ ቃሉን በመቀበልና ያዘዘንን ሁሉ በመፈጸም ነዉ። ይህን ካደረግን ከእርሱ ጋር አንድነት ይኖረናል።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 696በየሱስ ስም መጸለይ በጸሎት መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ይህን ስም ከመጥቀስ ያለፈ ነገር ነው። የገባውን ቃል አምነን በጸጋው እየተደገፍን እና ስራውን እየሠራን በየሱስ አእምሮና መንፈስ መጸለይ ነው።”—Steps to Christ, pp. 100፣101 ለ. የጸሎት ዋና ዓላማ በባሕርይው መንፈሳዊ ስለሆነ ፈጽሞ መረሳት የሌለበት ልመና የትኛው ነው? ሉቃስ 11:4፤ ማቴዎስ 26፡41 ደቀ መዛሙርቱ እንቅልፍ ተጫጭኖአቸው ስለነበር በክርስቶስና በሰማያዊ መልእክተኞቹ መካከል ስለተካሔደው ውይይት የሰሙት በጣም ጥቂቱን ብቻ ነበር። ስላልተጉና ስላልጸለዩ እግዚአብሔር ስለ ክርስቶስ ስቃይና ከዚያም በኋላ ስለሚመጣው ክብር እንዲያገኙ የፈለገውን እውቀት ሊያገኙ አልቻሉም። በዚህም ምክንያት የየሱስን የራስ መስዋዕትነት በመካፈል የሚገኘውን በረከት አጡ።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 425 (436)እግዚአብሔር ሁልጊዜ ለሰዉ ልጆች ስለሚመጣው ፍርድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። በዘመናቸው በተሰጠዉ የወቅቱ መልእክት ያመኑና ለትእዛዛቱ በመታዘዝ እምነታቸውን በተግባር ያደረጉ፣ በማይታዘዙና በማያምኑ ላይ ከወደቀው ፍርድ አምልጠዋል።”—ኢቢ . 634.ጴጥሮስ ለሠራ ው ትልቅ ኃጢአት በር የከፈተለት የሱስ ተግተህ ጸልይ ሲለው ባንቀላፋ ጊዜ ነው። በዚያች ወሳኝ ሰዓት ሁሎም ደቀ መዛሙርት የሚጐዳቸውን ነገር ፈጸሙ። ክርስቶስ ተከታዮቹ የሚያላሳልፉትን ከባድ የመከራ ጊዜ ያውቅ ነበር። ለፈተናው ዝግጁ ሆነው እንዳይገኙ ሰይጣን የስሜት ሕዋሳታቸውን ለማደንዘዝ ምን ያህል እንደሚጥር ያውቅ ነበር።ስለዚህ ነበር ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው፣ በአትክልቱ ቦታ በትጋት ጸልየው ቢሆን ኖሮ ጴጥሮስ የደረሰበትን ፈተና ለመጋፈጥ ደካማ ጉልበቱን መተማመን አይኖርበትም ነበር። ጌታውንም ወደ መካድ አይደርስም ነበር። ደቀ መዛሙርቱ የሱስ በሚzልይበት ሰዓት ተግተው ቢሆን ኖሮ በመስቀል ላይ የሚደርስበትን ስቃይ ለማየት ዝግጁ ይሆኑ ነበር። በመጠኑም ቢሆን የከባድ ስቃዩን ምስጢር መረዳት ይችሉ ነበር።”—ኢቢድ ፣ ገጽ 713፣ 714(751) 4. የጸሎት መልሶች ረቡዕ መጋቢት 20 ሀ. ጸሎት ሁልጊዜ ተስፋ እንዳደረግነዉ የማይመለስባቸው አንዳንድ ዋና ዋና ምክንያቶች ምንድን ናቸው? ያእቆብ 4:3; መዝሙረ ዳዊት 66:18; ምሳሌ 28፡9 ክፋትን በልባችን ከሰወርን፣ የሙጥኝ ያልነው የታወቀ ኀጢአት ካለ' እግዚአብሔር አይሰማንም።ስለ _ ኃጢአቱ የሚናዘዘውንና ራሱን የሚያዋርደውን ነፍስ ጸሎት ግን ጌታ ሁልጊዜ ይቀበላል የምናውቃቸውን የተበላሹ ነገሮቻችንን ስናስተካክል፣ እግዚአብሔር ደግሞ ልመናችንን እንደሚሰማ ልናምን እንችላለን። የእኛ መልካም ሥራ መቼም ቢሆን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ እንድናገኝ አያደርገንም የሚያድነን የክርስቶስ ብቃት ነው፤ የሚያነጻንም ደሙ ነው፡ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች የራሳችን አድርገን በመቀበል ረገድ ልንሰራው የሚገባን ስራ አለ።”—Steps to Christ, pp. 95.ኦ፣ እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸውን እጅግ የበለጸጉ ጤናና የመንፈሳዊ ስጦታዎችን በረከት የሚያጡ ስንቶቹ ይሆኑ! ልዩ ድሎችንና ልዩ በረከቶችን ለማግኘት አንድ ታላቅ ነገርን ለማድረግ የሚታገሉ ብዙ ነፍሳት አሉ። ለዚህም ሁል ጊዜ በጸሎትና በእንባ ከባድ ትግል ማድረግ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል። እነዚህ ሰዎች የተገለጸውን የእግ ዚአ ብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ቅዱሳት መጻሕፍትን በጸሎት ሲመረ ምሩ እና ከዚያ በኋላ አንዷንም ሳያጎድሉ ሲታዘ ዙ ወይም ሳይሰስቱ ፈቃዱን ከልባቸው ሲያደርጉ፣ የሚፈልጉትን (የቀረዉን ጉዳይ) ሁሉ ያገኙታል። ያ ሁሉ ስቃይ፣ እንባና ተጋድሎ የናፈቁትን በረከት አያመጣላቸውም። ራሳቸዉን ሙሉ በሙሉ አሳልፈዉ መስጠት አለባቸዉ። በእምነ ት የሚለምኑ ሁሉ የተስፋ ቃል የተገባለትን ወደር የሌለዉን የእግዚአብሔርን ጸጋ እንዲያገኙ የተገቡ የሚያደርጋቸዉን ሥራ መሥራት አለባቸው ። ”—Testimonies for the Church, vol. 9, p. 165. ለ. ለጸሎታችን መልስ ለማግኘት ምን አስፈላጊ ነው—ለምንስ? ያእቆብ 1:6, 7 ቃል ኪዳነ ስፊና ወሰን የለሽ ነው፤ ቃል የገባውም የታመነ ነው። የጠየቅነውን ነገር፣ በጠየቅነው ጊዜ ማግኘት ሳንችል ብንቀር እንኳ፣ ጌታ ጸሎታችንን እንደሰማና ደግሞም እንደሚመልሰው ማመናችንን መቀጠል አለብን። አርቀን የማናይና በቀላሉም የምንስት ከመሆናችን የተነሳ፣ አንዳንዴ ሊባርኩን የማይችሉ ነገሮችን እንጠይቃለን፡፡ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችን ለጸሎታችን መልስ አድርጎ በፍቅሩ የሚሰጠን የነገሮችን ትክክለኛ ምንነት ማየት የምንችልበትን መለኮታዊ ማስተዋል ቢሆን የምንመርጠው እጅግ የሚጠቅመንን ኖሮ፣ ነገር ብቻ ነው፡፡ ጸሎታችን ያልተመለሰ ሲመስለን ፣ የሚመለስበት ጊዜ በእርግጥ ይመጣልና፣ የተስፋውን ቃል ልንጠማጠም ይገባል፡፡ በጣም የሚያስፈልገንን ባርኮትም እንቀበላለን፡፡ በጸሎት እኛ የምንፈልገው ነገር ሁሉ በምንፈልገው መንገድ መልስ ያገኛል ብሎ ማሰብ አጉል ምኞት ነው፡፡ እግዚአብሔር ጥበቡ ጥልቅ ነውና አይሳሳትም መልካምነቱም ታላቅ ነውና በቅንነት ለሚመላለሱት ምንም መልካም ነገር አያጎልባቸውም፡፡ እንግዲያውስ ለጸሎታችሁ አፋጣኝ ምላሽ ባታዩም እንኳን በእርሱ ለመታመን አትፍሩ።”—Steps to Christ, pp. 96 5. ሳታቋርጡ ጸልዩ ሐሙስ መጋቢት 21 ሀ. በሁሉም ጸሎቶች ውስ ጥ፣ ምን ጊዜም ልንገነዘበው የሚገባን እና ለማድረግም ዝግጁ መሆን የምንችለው የትኛውን ጠቃሚ ነጥብ ነው? 1ኛ ዮሐንስ 5:14, 15 አጠያየቃችን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት መሆን እንዳለበት ግልጽ ያደርጋል። እርሱ ቃል የገባልንን ነገሮች ነዉ መጠየቅ ያለብን። የምናገኘዉንም ሁሉ መልሰን የእርሱን ፈቃድ ለማሟላት ተግባራት እንዲዉሉ ማድረግ አለብን። ለሚገጥሙ ሁኔታዎች ሁሉ የገባልን የተስፋ ቃል እኩልና ተመጣጣኝ ነዉ።ኃጢአታችን ይቅር እንዲባልልን፣ መንፈስ ቅዱስ እንዲመጣልን፣ የክርስቶስ ዓይነት መንፈስ ለማግኘት፤ የርሱን ሥራ ለመሥራት የሚያስፈልገን ጥበብና ብርታት፤ እርሱ እንደሚሰጠን ቃል የገባልንን ማንኛዉም ነገር ሁሉ ልንጠይቅ እንችላለን። ከዚያ በኋላ እንደምናገኘዉ ማመንና ለሰጠን አምላክም ምስጋና ማቅረብ ይገባናል። -ሥነ ትምህርት፣ ገጽ. 258. ለ. ለምን ያህል ጊዜ መጸለይ አለብን? ዳንኤል 6:10፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 5:17 እግዚአብሔር እርሱን እናመልከው ዘንድ ከዓለም ውስጥ ወጥተን እንድንመንን አሳቡ አይደለም፡፡ ሕይወታችን ልክ እንደ የሱስ ሊሆንልን ይገባል፤ እርሱ ለጸሎት ወደ ተራራ ይወጣ ነበር፤ ለማገልገል ደግሞ ከህዝቡ ጋር ይቀላቀል ነበር፡፡ ከመጸለይ ውጪ ሌላ ምንም የማያደርግ ሰው ፈጥኖ መጸለዩን ይተዋል፤ ወይም ጸሎቱ ዘልማዳዊ ብቻ ይሆናል፡፡ ሰዎች ከማህበራዊ ህይወት ሲገለሉ፣ ከክርስትና ተግባርና መስቀልን ከመሸከም ሲሸሹ፣ እንዲሁም ስለ እነርሱ ለተጋው ጌታ መትጋት ሲያቆሙ፣ የጸሎትን ፍሬ ነገርና ለመጸለይ የሚያነቃቃቸውን ነገር ያጣሉ። ጸሎታቸው በራስ ወዳድነት የተሞላ ይሆናል። ስለሰብአዊ ፍጥረት ፍላጎት ወይም ስለ ክርስቶስ መንግስት መቋቋም፣ ለመንግስቱም መስራት እንዲችሉ ኃይል ለመቀበል መጸለይ አይችሉም፡፡”—Steps to Christ, pp. 101. ሐ. የመግባቢያ መንገዱ ሁል ጊዜ ክፍት እንዲሆን የሚሹ ልዩ ሁኔታዎች አሉን እንዲሁም በፈጣሪያችን ፊት ስንቀርብ አመለካከታችን ምን መሆን አለበት? ነህምያ 2:4, 5; ዕብራውያን 4፡16 የግ ል ግ ምገ ማጥያ ቄዎች አርብ መጋቢት 22 1. ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ያስተማራቸው የናሙና ጸሎት ዓላማ ምን ነበር? 2. አምልኮና ውዳሴ ለፈጣሪያችን ምን ያህል አስፈላጊ ነው? 3. ጊዜያዊ ፍላጎቶች አስፈላጊ ቢሆኑም ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ነገር ምንድን ነው? 4. ለጸሎት ትልቁ እንቅፋት ምን ምን ሊሆን ይችላል? 5. ለተወሰኑ ጉዳዮች ከመጸለያችን በፊት የአምላክን ፈቃድ ማወቅ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? << >>