ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2) << >> ሰንበት፣ ሰኔ 10፣ 2015 12ኛ ትምህርት ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ግቡ መታሰቢያ ጥቅስ ፡- የምቀድሳቸውም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ምልክት ይሆኑ ዘንድ ሰንበታቴን ሰጠኋቸው።” (ሕዝ 20፡ 12)። ለንባብ የተመረጠዉ፡ The Desire of Ages, pp. 281–289. እግዚአብሔር የዓለም ፈጣሪ እንደሆነ ምልክት ሆና የተሰጠች ሰንበት የሚቀድሰዉም እርሱ እንደሆነም ጭምር ምልክት ናት። ሁሉን የፈጠረው ኃይል ነፍስን በራሱ አምሳል እንደገና የሚፈጥር ራሱ ኃይል ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 350. 1. የአዲሱ ኪዳን ምልክት እሁድ ሰኔ 04 ሀ. እግዚአብሔር ኪዳኑ ለምን ያህል ጊዜ እንዲቆይ አስቧል እና ይህ የሚያመለክተው የትኛውን ቃል ኪዳን ነው? ዘጸአት 31:16; ዕብራውያን 8፡10 ለ. እግዚአብሔር በፍጥረት ሳምንት ያረፈው ከምንድን ነው እንዲሁም ዕረፍቱንስ ከአዲሱ ኪዳን ጋር ምን የሚያገናኘው ነገር አለ? ዘፍጥረት 2:2, 3፤ ዘጸአት 35:2፤ 20፡ 11። ሐ. ከሥጋዊ ሥራ ማረፍ የመንፈሳዊ ሁኔታ ዕረፍትን የሚያሳየው እንዴት ነው? ዕብራውያን 4:4, 10; ኤፌሶን 2:8, 9፤ ሕዝቅኤል 20፡12 መ. አንድ ሰው ዳግመኛ ሲወለድ (ዮሐንስ 3:5, 6) በሕይወታቸው ውስጥ የሚያቆሙት (የሚተዉት) ምን ዓይነት ሥራዎችን ናቸው? ገላትያ 5:19-21፤ ዘጸአት 31፡15 የሰንበትን ቀን ለሚቀድሱት የመቀደሳቸዉ ምልክት ነው። እውነተኛ መቀደስ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት፣ በባሕርይ ከእርሱ ጋር አንድ መሆን ነው። ይህም የሚገኘዉ የባህሪው ግልባጭ ለሆኑት መርሆች በመታዘዝ ነው። ሰንበትም የመታዘዝ ምልክት ነው። አራተኛይቱን ትእዛዝ ከልብ የሚጠብቅ ሁሉ ሕግን ይፈጽማል። በመታዘዝም የተቀደሰ ነው።”—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 350. 2. መለኮታዊ ኃይል ሰኞ ሰኔ 05 ሀ. እስራኤላዊያን ወደ አምላክ መንፈሳዊ ዕረፍት መግባት ያልቻሉት ለምንድን ነው? ዕብራውያን 4:1, 2፤ 3:12, 19፤ 4፡4–6 የእስራኤላዊያን ድክመት ትእዛዛቱን ባለመታዘዝ ከእግዚአብሔር መለየታቸው ነው። የዘመናችን እስራኤላዊያን የድክመት እና የኋሊት መሸሽ ምክንያት መለኮታዊውን ህግ ለማክበር ችላ ማለታቸው ነው። እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ሁሉ ለትእዛዙ መታዘዝን ይፈልጋል። በምክንያታዊነት ወይም በወግ ወይም በጽሑፍ ቢሆን ሕጉን ለማወቅ ባገኙት አጋጣሚ መሠረት መላው ዓለም የሚዳኘው በሥነ ምግባር ሕግ ነው።”—The Signs of the Times, June 9, 1881. ለ. እስራኤል በአለማመናቸው እንዴት እዚህ ደረጃ ላይ ደረሱ? በድንገት የተከሰተ ነዉን? እና እንዴት ነበር የተጀመረዉ? ዕብራውያን 3:8-11, 15–18 “ሰዎች ልባቸውን ለአለማመን አሳልፈዉ ሲሰጡ፣ ራሳቸውን በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ያደርጋሉ ፣ እና እስከ ምን ድረስ እንደሚመራቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም።”—አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 389 ሐ. በሕይወታችን መንፈሳዊ ድል ማደረግን ካልተለማመድን ሰንበትን በቅድስና መጠበቅ ይቻላልን? አብራራ። 1ኛ ዮሐንስ 5፡4 በእግዚአብሔር ልጆች ላይ የ ሚደርስ ማንኛውም ውድቀት በእምነታቸው ማነስ ምክንያት ነው።”—አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 657.ሰማይና ምድ ር ጸንተዉ እስከኖሩ ድረስ፣ ሰንበት የፈጣሪ ኃይል ምልክት ሆኖ ይኖራል። … . .ለአይሁዶች ከተሰጡት መመሪያዎች ሁሉ እንደ ሰንበት በአካባቢያቸው ከነበሩት ሕዝቦች የተለዩ እንዲሆኑ ያደረጋቸው የለም። የእግዚአብሔር ዕቅድ ሰንበትን በማክበር አይሁዶች እርሱን አምላኪ መሆናቸው እንዲታወቅ ነበር። ዕቅዱ ሰንበት የእሥራኤል ልጆች ከጣዖት አምልኮ ተላቅቀው ከእውነተኛው አምላክ ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው ምልክት እንዲሆን ነበር። ነገር ግን ሰንበትን በቅድስና ለማክበር ሰዎች የተቀደሱ መሆን አለባቸው። በሃይማኖት የክርስቶስ ጽድቅ ተካፋይ መሆን አለባቸው። የሰንበትን ቀን አስብ ትቀድሰው ዘንድ» የሚለው ትእዛዝ ለእሥራኤላውያን በተሰጠ ጊዜ አምላከ በተጨማሪ «ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ» አላቸው። ዘጸ.20:8122:31። በዚህ ሁኔታ ብቻ ነበር ሰንበት እሥራኤላውያን እግዚአብሔርን አምላኪ መሆናቸውን ለይቶ የሚያሳውቃቸው።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 283(278) 3. መጽደቅ ማክሰኞ ሰኔ 06 ሀ. መጽደቅ የሚጀምረ ው በመታዘዝ ነውን? ይህስ ሰንበትን በመጠበቅ የሚገለጸዉ እንዴት ነዉ? ሮሜ 3:28; ዘዳግም 5:15 በእምነት መጽደቅ ምንድን ነው? የሰው ልጅን ክብር በአፈር ትቢያ ላይ በመጣል እና ሰዉ ለራሱ ማድረግ የማይችለውን ለሰው ልጅ ያደረገበት የእግዚአብሔር ስራ ነው። ሰዎች የራሳቸውን ከንቱነት ሲያዩ የክርስቶስን ጽድቅ ለመልበስ ይዘጋጃሉ።”—The Faith I Live By, p. 111.የእግዚአብሔር ሕግ የሚጠይቀዉን ለማሟላት የራሳችን የሆነ ጽድቅ ባይኖረንም ክርስቶስ ግን ማምለጫዉን መንገድ አዘጋጀልን። እርሱ በኖረዉ ምድራዊ ሕይወቱ እኛ በምናልፈበት ፈተናና መከራ ዉስጥ አልፏል። ይሁንና ኃጢአት የሌለበትን ሕይወት ኖረ። ስለዚህም ስለእኛ ሞቶ ኃጢአታችንን ለመዉሰድ ራሱን በመስጠት ጽድቁን አወረሰን። ራሳችሁን ለእርሱ ብትሰጡና እንደ አዳኛችሁ ብትቀበሉት የፈለገዉን ያህል ኃጢአተኛ የነበራችሁ ቢመስላችሁም፤ ስለ ራሱ ሲል እንደ ጽድቅ ይቆጥራችኋል። የክርስቶስ ባሕርይ በእናንተ ምትክ ተቆጥሮ በእግዚአብሔር አብ ፊት ምንም ኃጢአት እንዳልሠራ ሰዉ ሆናችሁ እንድትታዩ ያደርጋችኋል።”— ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ፣ ገጽ. 62.የሱስ ከነኃጢአታችን፣ ረዳተቢስና ጥገኛ እንደሆንን፣ ባለንበት ሁኔታ ወደ እርሱ እንድንመጣ ይወዳል፡፡ ከነደካማነታችንና መተላለፋችን በንስሃ እግሮቹ ስር መዉደቅ እንችላለን፡፡ እርሱም በፍቅር እጆቹ ያቅፈናል፤ ቁስላችንን ይጠርግልናል፤ ከእርኩሰታችንም ሁሉ ያጠራናል፤ ይህንንም ማድረግ ለእርሱ ክብሩ ነዉ፡፡” —ኢቢአዲ . 52. ለ. የፍጥረት ሳምን ት ይቅርታን እና የባሕርይ ለውጥ ለማምጣት ያለውን መለኮታዊ ኃይል እንዴት ያሳያል? ዘጸአት 31:16, 17፤ መዝሙረ ዳዊት 51:10 ሰንበት እኛን የሚቀድሰዉን የክርስቶስን ኃይል የሚያመለክት ምልክት ነው።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 288. ሐ. በመለወጥ ሂደት ላይ ከፍጥረት ሂደት ጋር ተመሳሳይ ሂደት ይከናወናል ማለት እንችላለንን? 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17 በክርስቶስ ኃይል ወደ እርሱ የመጣ ኃጢአተኛ ከፍ ከፍ ወዳለዉ መስቀል በመቅረብ፤ ራሱን በመስቀሉ ላይ በመዘርጋት አዲስ ፍጥረት ይሆናል። የዚያን ጊዜ አዲስ ልብ ይሰጠዋል። በክርስቶስ የሱስ አዲስ ፍጡር ይሆናል።”—የክርስቶስ ምሳሌያዊ ትምህርቶች፣ ገጽ. 163.ነፍስ እራሷን ለክርስቶስ አሳልፋ ስትሰጥ፣ አዲስ ሀይል አዲሱን ልብ ይቆጣጠራል። ሰው ለራሱ ሊያደርገው የማይችለው ለውጥም ይከሰታል ። ከተፈጥሮ በላይ በሆነ ሥራ፣ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ነገርን ወደ ሰው ተፈጥሮ ያመጣል።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 324. 4. መቀደስ ረቡዕ ሰኔ 07 ሀ. ሰንበት መቀደስን የ ሚገልጸው እንዴት ነው? ዘሌዋውያን 20:7, 8; ዘጸአት 31፡13 ለ. እንደ እግዚአብሔር ካህንነታችን (1ኛ ጴጥሮስ 2:9) በሳምንቱ በስድስተኛው ቀን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት በየሳምንቱ ምን ማድረግ አለብን? ነህምያ 13:22, 19 ሐ. ገጸ ኅብስቱ ሲዘጋጅ ምንን ያመለክታል—ይህስ ለመቀደስ የሚረዳው እንዴት ነው? 1ኛ ዜና መዋዕል 9:32; ዮሐንስ 6:48, 53, 54, 56, 63፤ ዕብራውያን 4፡12 የእግዚአብሔርን ልጅ ሥጋ መብላትና ደም መጠጣት ማለት የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት ማለት ነው።”—The Ellen G. White 1888 Materials, p. 1683.ደምበሰውነት ውስጥ እንደምዘዋወር፣ እንዲሁ የክርስቶስ ሕይወት ቃሉን በሚያቀርቡት ውስጥ እንደ ጉልበት ሰጪ ኃይል ሆኖ መኖር አለበት። ሰውየው ለራሱ ከፍ ከፍ ሊል አይገባም። የኃጢአተኞችን ልብ የሚለውጥ፣ በደሉንና ኃጢአቱን ይቅር የሚል፣ በጌታ ሰላምን ፣ ደስታን፣ ብርሃንን የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስ ነው። በየሱስ ካለው እውነት በቀር ምንም ዓይነት ኃይል ልብን ሊቀድስ አይችልም።”—Letters and Manuscript, vol. 12 (1897), Ms 138, 1897መጽሐፍ ቅዱስ በጆሯችን የምንሰማውን ያህል እርግጠኛ በሆነ ድምጽ ለእኛ የሚናገረን የእግዚአብሔር ድምፅ ነው። ይህን ብንገነዘብ ኖሮ የእግዚአብሄርን ቃል እንዴት ባለ ፍርሃት እንከፍት ነበር እንዲሁም ትእዛዛቱን እንዴት ባለ ትጋት እንመረምር ነበር! ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብና ማሰላሰል ወሰን ከሌለዉ አምላክ ጋር እንደ መታደም ይቆጠራል።”—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 393. መ. በተለይ ወደ ዘመኑ ፍጻሜ ስንቃረብ በሰንበት ምን ጠቃሚ ተግባር ማድረግ ያስፈልጋል? ዘሌዋውያን 23:3; ዕብራውያን 10፡24-26 ወንድሞቻችን ከሃይማኖት ስብሰባዎች በገዛ ፈቃዳቸው ሲቀሩ፣ እግዚአብሔር አማካሪያቸውና ጠንካራ የመከላከያ ግንባቸው መሆኑ በማይታሰብበት ጊዜ፣ ወዲያዉኑ ዓለማዊ አስተሳሰቦችና ክፋት አለማመን አስተሳሰባቸዉን ይቆጣጠርና፤ ከንቱ መተማመንና ፍልስፍና የትሕትናንና ፣ የታመነ እምነትን ቦታ ይረከባል።—Testimonies for the Church, vol. 5, pp. 426, 427ጥቅት ወደኋላ አፈግፍጋችሁም ግን ክርስቲያኖች መሆን እንደምትችሉ አታስቡ። እያንዳንዳቸው የታላቁ የሰው ልጅ ድር አካል ናቸው፣ እናም የልምድዎ ባሕርይና ጥራት በአብዛኛው የሚወሰነው እርስዎ በሚገናኙዋቸው ሰዎች ልምዶች ነው።”—Ibid., vol. 7, p. 190. 5. የሰንበት በረከት ሐሙስ ሰኔ 08 ሀ. በህይወታችን ሰንበትን በደንብ ብናከብር ምን እንቀበላለን? ኢሳይያስ 56:2; 58:14; መዝሙረ ዳዊት 144:15 ሰንበትን የክርስቶስ የመፍጠርና የማዳን ኃይሉ ምልክት አድርገው ለሚቀበሉት ሁሉ ያስደስታቸዋል። በሰንበት አማካይነት ክርስቶስን ስለሚያዩት በእርሱ ይደሰታሉ። ሰንበት የፍጥረት ሥራ ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ትልቅ ኃይል እንዳለው ማስረጃ መሆኑን ያመለክታቸዋል። በኤደን የታጣውን ሰላም ለማስታወስ ሲረዳ በአዳኛችን አማካይነት ስለሚታደሰው ሰላም ይነግረናል።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 289(285) ለ. ሰንበት የተነደፈው ለማን ነው እና ቃል በቃልም ሆነ በመንፈሳዊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ስንቀበለው ምን ይሆናል? ማርቆስ 2:27, 28; ሕዝቅኤል 20:20; ዕብራውያን 4፡9 እግዚአብሔር የዓለም ፈጣሪ እንደሆነ ምልክት ሆና የተሰጠች ሰንበት የሚቀድሰዉም እርሱ እንደሆነም ጭምር ምልክት ናት። ሁሉን የፈጠረው ኃይል ነፍስን በራሱ አምሳል እንደገና የሚፈጥር ራሱ ኃይል ነው። የሰንበትን ቀን ለሚቀድሱት የመቀደሳቸዉ ምልክት ነው። እውነተኛ መቀደስ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት፣ በባሕርይ ከእርሱ ጋር አንድ መሆን ነው። ይህም የሚገኘዉ የባህሪው ግልባጭ ለሆኑት መርሆች በመታዘዝ ነው። ሰንበትም የመታዘዝ ምልክት ነው። አራተኛይቱን ትእዛዝ ከልብ የሚጠብቅ ሁሉ ሕግን ይፈጽማል። በመታዘዝም የተቀደሰ ነው።”—Testimo¬nies for the Church, vol. 6, p. 350. የግ ል ግ ምገ ማጥያ ቄዎች አርብ ሰኔ 09 1. አዲሱ ቃል ኪዳንና አዲስ መወለድ ሰንበትን ለማክበር ምን ያህል አስፈላጊ ናቸው? 2. ሰንበትን ለመቀደስ ምን ዓይነት ልምድ ያስፈልገናል? 3. አምላክ እራኤላውያንን ከግብፅ ነፃ ያወጣበት መንገድ መጽደቅ የተገለጸው እንዴት ነው? 4. አንድ ሰው የተቀደሰ ቅዱስ ተሞክሮን እንዴት መጠበቅ ይችላል? 5. እግዚአብሔር እንዳሰበ ሰንበትን በእውነት ስናከብር ምን ልዩ በረከት እናገኛለን? << >>