Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ግንቦት 05፣ 2015 7ኛ ትምህርት
የቅዱሳን ርስት የመታሰቢያ ጥቅስ፡- ነገር ግን ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን። (1ኛ ቆሮ 2:9).
ለንባብ የተመረጠዉ፡   ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 355–374። 
እግዚአብሔር ክርስቶስን ለዓለማችን በሰጠ ጊዜ፣በዚህ አንድ ስጦታ የሰማይን ሀብት ሁሉ ሰጠ። ምንም አላስቀረም። ሰዎችን ወደ ንስሐ ለማምጣት ከዚህ በላይ ምንም ማድረግ አይችልም። ለመዳናቸው የሚሆን ግን በግምጃ ቤቱ ያስቀረዉ ምንም የቀረ ሀብት የለውም።”—The Review and Herald, September 17, 1901.

1. የመጀመሪያዉ ዕቅድ እሁድ ሚያዝያ 29
ሀ. አምላክ ለፍጥረቱ ዘዉድ እንዲሆን ምን አዘጋጀ—ለምንስ? ዘፍጥረት 1:1ኢሳይያስ 45:18፤ 43፡7። ከሁሉም የበታች ፍጥረታት ላ፣ እግዚአብሔር የፈጠረው ሰው፣ የፍጥረቱ ሥራ ዘዉድ በመሆን ሀሳቡንና ክብሩን እንዲገልጥ ነው። ነገር ግን ሰው ራሱን እንደ አምላክ ከፍ ከፍ እንዲያደርግ አይደለም።”—The Ministry of Healing, p. 415ምድርና በውስጧ ያሉት አራዊት ከተፈጠሩ በኋላ፥ አብና ወልድ ሰውን በራሳቸው አምሳል ለመፍጠር ከሰይጣን ውድቀት በፊት የተነደፈዉን ዕቅዳቸውን ፈጸሙ። ምድርንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ሲፈጠሩ አብረ ው ሠሩ።”—The Spirit of Prophecy, vol. 1, p. 24. ለ. (ዘፍጥረት 3:9–14) በእግዚአብሔር የመጀመሪያ ዕቅድ ላይ በተነሳዉ አመጽ ምክንያት ምን እንደሆነ ግለጽ? ዘፍጥረት 2:17ሮሜ6፡23 ሐ. ሰው ከኃጢአቱ በኋላ በሕይወት የቀጠለው ለምንድን ነው- እና በመዋጀት እቅድ ውስጥ ምን ተካትተዋል? ሉቃስ 19:10ራእይ 13:8 (የመጨረሻውክፍል)፤ ሚክያስ 4፡8 [ክርስቶስ] ከሥጋ መገለጡ አስቀድሞም አዳኝ ነበር። ልክ ኃጢአት እንደገባ፣ አዳኝም እዚያዉ ነበር።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 210.

2. ሦስተኛው ሰማይ ሰኞ ሚያዝያ 30
ሀ. ስንት ሰማያት አሉ? 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡2 (የመጨረ ሻው ክፍል)። የመጀመሪያውን ሰማይ ይግለጹ። ዘ ፍጥረት 1:6–8; 6፡7 ለ. በሁለተኛው ሰማይ ውስጥ ምንድን ነው? ዘፍጥረት 15:5፤ መዝሙረ ዳዊት 8:3፤ ዘዳግም 4፡19 ሐ. እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚወስድበት ቦታ የት ነው- እና እዚያ የሚኖረው ማን ነው? 2ኛ ቆሮንቶስ 12:2, 4፤ ራእይ 2:7፤ 22:1, 2፤ 1ኛ ነገሥት 8፡30 የወደፊቱ ውርስ ከሚገባው በላይ ቁሳዊ ሆኖ እንዳይታይ ያለው ስጋት፣ የራሳችን ቤት እንደሆነ አድርገን እንድንናፍቀው ከሚያደርጉን እውነቶች እንዲሸሹ ብዙዎችን መርቶአል [የሰማይ ቤታችን የተገለጸበት አውድ መንፈሳዊ ትርጉም ያለው (ምሳሌያዊ የሆነ) እንጂ እንደተብራራው በትክክል እንደዚያው አይነት አይደለም ብለው እንዲያስቡ መርቷቸዋል]። በአባቱ ቤት እልፍኞችን ሊያዘጋጅላቸው እንደሄደ ደቀ-መዛሙርቱ እርግጠኛ እንዲሆኑ ክርስቶስ ነግሯቸዋል። የእግዚአብሔርን ቃል አስተምህሮ የሚቀበሉ ሁሉ በሰማይ ስላለው ቤት ሙሉ በሙሉ እውቀት የሌላቸው አይሆኑም። ሆኖም "አይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው" ነው[1ኛ ቆሮ 2÷9]። ፃድቃን የሚወርሱትን ሽልማት የሰው ቋንቋ ይገልጸው ዘንድ ይሳነዋል። የሚያዩት ብቻ የሚያስተውሉት ይሆናል። ይህ ውስን የሆነ አእምሮ የእግዚአብሔርን ገነት ክብርና ግርማ ሞገስ ይረዳው ዘንድ አይችልም።የዳኑት ውርስ በመጽሐፍ ቅዱስ አገር ተብሎ ይጠራል [ዕብ 11÷14-16]። በዚያ ቦታ ሰማያዊው እረኛ መንጋውን ወደ ሕያው ምንጮች ይመራቸዋል። የሕይወት ዛፍ በየወሩ ፍሬ ትሰጣለች፤ ቅጠሎችዋም ለአሕዛብ አገልግሎት ይውላሉ። ሳያቋርጡ የሚፈሱ እንደ መስታወት ድንጋይ የነጹ ጅረቶች፣ ባጠገባቸው ቅጠላቸውን የሚያውለበልቡ ጥላቸውን ለዳኑት ባዘጋጀው መንገድ ላይ የሚያሳርፉ ዛፎችም አሉ። ወደ ውብ ኮረብታማ ስፍራዎች የሚለወጡ የተነጣጠሉ ሜዳዎች አሉበት፤ የእግዚአብሔር ተራራዎችም ግዙፍ ቁንደዶአቸውን አምጥቀው ገዝፈው ይታያሉ። በነዚያ ፀጥታ በሰፈነባቸው ሜዳዎች በሕያው ምንጮች አፋፍ ለረዥም ጊዜ ተጓዥና ተቅበዝባዥ የነበሩት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ቤታቸውን ያገኛሉ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 674, 675 መ. የሱስ በዚያ ቦታ ምን ሥራ እየሠራ ነው? ዕብራውያን 8:1፤ 9:27፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 በላይ ባለው መቅደ ስ ውስጥ የክርስቶስ ሰውን ወክሎ ያቀረበው ምልጃ ለደኅንነት እቅድ በመስ ቀል ላይ እንደሞተው ሁሉ ያህልአስፈላጊ ነው።”—Ibid., p. 489.የክርስቶስ አማላጅነት ስለ እኛ ምትክና ዋስ ሆኖ እራሱን ለአብ በማቅረብ መለኮታዊ ጸጋውን ማቅረብ ነው። ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ ወደ ላይ ዐረገ።”—Faith and Works, p. 105.

3. በአዲሲቷ ምድር ማክሰኞ ግንቦት 01
ሀ. የሱስ እንደምንሄድ ቃል የገባልን እውነተኛ ቦታ ነዉን—ታማኝ ከሆንንስ ወዴት እንሄዳለን? ዮሐንስ 14:1-3ማቴዎስ 5፡12 ለ. በሕይወታችን ውስጥ ከሁሉ የላቀ ደስታ የሚያመጣው ምንድን ነው—ታማኝ የቀድሞ አባቶቻችንስ ምን ተስፋ ነበራቸው? ሉቃስ 10:20፤ ዕ ብራውያን 11፡13-16 በቅዱሷ ከተማ _ ፍጹም የሆነ ሥርዓትና ውህደት አለ፡፡ ምድርን እንዲጎበኙ የሚላኩ መላእክት በሙሉ ከሰማያዊው ከተማ ሲወጡና ሲገቡ በራፍ ላይ ላሉት መላእክት የሚያሳዩትን ወርቃማ ካርድ ይይዛሉ። ሰማይ ግሩም ስፍራ ነው።”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገጽ. 39. ሐ. በአዲሲቷ ምድር ምን ያህል እንቆያለን? ማቴዎስ 5:5ሮሜ4፡13 የእግዚአብሔር ቃል ግን በከንቱ እንዲቀር ወይም አይሁዳዊያን ከነዓንን ተቆጣጥረው የቃሉ ፍጻሜ እንዲሆንም አላደረገም፡፡ “የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃም እና ለዘሩ ነበር” (ገላ 3፡16)፡፡ አብርሃም እራሱ ከርስቱ ተካፋይ ይሆን ነበር፡፡ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ሳይፈጸም ረዥም ጊዜ ቆየ፡፡ ምክንያቱም “በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፤ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነው” (2ኛ ጴጥ. 3፡8)፡፡ የዘገየ ቢመስልም በተቆረጠለት ቀን መፈጸሙ አይቀርም፡፡ “በእርግጥም ይመጣል ከቶም አይዘገይም” (ዕንባ 2፡3)፡፡ ለአብርሃም እና ለዘሮቹ የተሰጠው ስጦታ የከነዓንን ምድር ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ምድርን የሚሸፍን ነበር፡፡ ሐዋርያው እንዲህ ይላል “እርሱ የዓለም ወራሽ እንዲሆን አብርሃም እና ዘሩ ተስፋን የተቀበሉት በሕግ በኩል አልነበረም፡፡ነገር ግን በእምነት ከሆነው ጽድቅ ነው፡፡” (ሮሜ 4፡13)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚያስተምረው ለአብርሃም የተገቡት የተስፋ ቃሎች የሚፈጸሙት በክርስቶስ በኩል እንደሆነ ነው፡፡ “የክርስቶስ ከሆናችሁ እናንተ የአብርሃም ዘር ናችሁ፤ እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።” “እንዲሁም በሰማይ ለማይጠፋ ለማይበላሽና ለማይለወጥ ርስት እንደገና ወለደን” (ገላ. 3፡29፣ 1ኛ ጴጥ. 1፡4)፡፡ ምድርም ከኃጢአት እርኩሰት ነጻ ሆነች፡፡ “ከዚያም ከሰማይ በታች ያሉት መንግሥታት ልዕልና ሥልጣንና ታላቅነት ለልዑል ሕዝብ ለቅዱሳን ይሰጣል፤” (ዳን. 7፡27) “ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በታላቅ ሰላምም ሐሴት ያደርጋሉ” (መዝ. 37፡11)፡፡ እግዚአብሔር ለአብርሃም የዚህን ዘላለማዊ ርስት እይታ ሰጥቶት እርሱም በዚህ ተስፋ ተደሰተ፡፡ “በባዕድ አገር እንዳለ መጻተኛ በተስፋይቱ ምድር በእምነት ተቀመጠ፤ የተስፋውን ቃል አብረውት እንደሚወርሱት እንደ ይስሐቅ እና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ኖረ፡፡ ምክንያቱም መሰረት ያላትን እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር” (ዕብ 11፡9-10)፡፡”—የሃይማኖት አባቶችና ነቢያት ገጽ 187, 188

4. ደስተኛ ቦታ ረቡዕ ግንቦት 02
ሀ. የሱስ እኛን በኃጢአታችን ሳይሆን ከኃጢአታችን ለማዳን የመጣው ለምንድ ነው? ማቴዎስ 1:21ራእይ 21:27; 22፡14። የሱስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ህዝቡን ከኃጢአታቸው ለማዳን ነው። እርሱ የኃጢአት አገልጋይ አይደለምና በኃጢአታችን አያድነንም። ለክርስቶስ መለኮታዊ ጥሪ ምላሽ ልንሰጥና ከኃጢአታችን ንስሐ መግባትና ቅርንጫፉ ከወይኑ ጋር አንድ እንደሆነ ራሳችንን ከክርስቶስ ጋር አንድ ማድረግ አለብን።የሱስ እን ዲ ህ አ ለ ፡- “እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። የሱስ ሰዎችን ሁሉ እየሳበ ነው፤ ታዲያ ለዚህ ስበት ምላሽ የሚሰጠውስ ማን ነው? ሰውን ልብ እየሳበ ላለው ለዚህ መለኮታዊ ፍቅር ምላሽ ሰጡ በሚሉት ሰዎች ሕይወትና ምሳሌ ብዙዎች በእጅጉ ይማረካሉ። እርስዎን የተሻሉ እንደሚያደርግዎት ለማየት ስሙን ስመሰክሩ ብዙዎች ይመለከቷችኋል። በቤተሰባችሁ ውስጥ ክርስቶስን በመምሰል፣ ደግና ጨዋ መሆንዎን ለማየ ት ብዙዎች ይመለከታሉ። ጌታ እንዲህ ብሏል፡- ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ።”—The Signs of the Times, February 15, 1892.በእውነት ስሜትህ መቀስቀሱና መንፈስህ መነካቱ ክርስቲያን ስለመሆኖህ ምንም ማረጋገጫ አይሰጥም። ጥያቄው፣ ራስህ ወደ ክርስቶስ ሙላት እያደግክ ነው ወይ? የክርስቶስ ጸጋ በሕይወታችሁ ተገልጧልን? ጸጋውን አብዝተው እንዲመኙ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ጸጋውን ሰዉ ልጆች ይሰጣል። የእግዚአብሔር ጸጋ በሰው ልብ ላይ ሁልጊዜ ይሰራል፣ ሲቀበለውም የመቀበያው ማስረጃ በተቀባዩ ሕይወትና ባሕርይ ውስ ጥ ይታያ ል፣ ምክንያቱም መንፈሳዊ ሕይወት ከውስ ጥ ሲጎለብት ይታያልና። በልብ ውስጥ ያለው የክርስቶስ ጸጋ መንፈሳዊ ሕይወትን ያበረታታል፣ እናም መንፈሳዊ እድገት ይሆናል። እያንዳንዳችን የግል አዳኝ ያስፈልገናል አለበለዚያ በኃጢአ ታችን እንጠፋለንና። በነፍሳችንን እንጠይቅ፡ ወደ ሕያው ራስ ወደ ክርስቶስ እያደግን ነውን? ስለእግዚአብሔርና እርሱ ላከውን የሱስ ክርስቶስን እውቀት እያገኘን ነውን? ተክሎቹ በሜዳ ላይ ሲያድጉ አናያቸውም፣ ነገር ግን እንደሚያድጉ እርግጠኞች ነን፣ እና የራሳችንን መንፈሳዊ ጥንካሬና እድገት አናውቅምን?”— That I May Know Him, p. 163. ለ. በዚያ አዲስ ቦታ ምን ዓይነት ሁኔታን ተስፋ እናደርጋለን? ኢሳይያስ 33:24፤ 35:1–10፤ ራእይ 21:4፤ 22፡3። ሁሉም መከራና ጠብ ያበቃሉ (አይኖሩም)። የተዋጁት በእግዚአብሔር ዙፋን ዙሪያ ሲቆሙ የድል መዝሙሮች ሰማይን ሁሉ ይሞላሉ።”—My Life Today, p. 348.

5. ዝግጅት ሐሙስ ግንቦት 03
ሀ. ሦስተኛውን ሰማይ በሰው ቋንቋ እንዴት እንገልጸዋለን? 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡9 በዚህ ህይወት ውስጥ እንኳን [የእግ ዚአብሔርን] መገኘ ት በጨረፍታ ልናይ እና ከሰማይ ጋር የመገናኘትን ደስታ ልንቀምስ እንችላለን፣ ነገር ግን የደስታው እና የበረከቱ ሙላት በመጨረሻው ዓለም ይደርሳል። ዘላለማዊ ነ ት ብቻውን ወደ አምላክ መልክ የተመለሰው ሰው ሊደርስበት የሚችለውን ክቡር እጣ ፈንታ ሊገልጥ ይችላል። ”— Patriarchs and Prophets, p. 602.ክብርን ለመግለጥና የእግዚአብሔርን ቃል ውድ ሀብቶች ለማውጣት ዘላለማዊ ዘመንን ይጠይቃል።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Com¬ments], vol. 6, p. 1107. ለ. እግዚአብሔር ስለ መንግሥተ ሰማያት እነዚህን አስደናቂ ነገሮች እንድንሰማ ዕድል የሰጠን ለምንድን ነው? ዮሐንስ 3:16, 17፤ ማቴዎስ 6፡19-21 ክርስቶስ ተስፋ የለሽ የሚመስሉ ነገሮችን ሰይጣን ያዋረደቸውንና በእነርሱም በኩል የሰራባቸውን ወስዶ የጸጋው ተገዢዎች ሊያደርጋቸው ይወዳል። ከመከራና በማይታዘዙት ላይ ከሚወድቅ ቁጣ ሊያድናቸው ይደሰታል። ልጆቹን ለዚህ ስራ መፈፀም ወኪሎቹ ያደርጋቸዋል፣ እና በስኬቱ፣ በዚህ ህይወትም ቢሆን ፣ ውድ ሽልማት ያገኛሉ። ነገር ግን ይህ በመጨረሻው መገለጥ ታላቅ ቀን ከሚኖራቸው ደስታ ጋር ሲወዳደር ምን አላት? "ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ። 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡12።——Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 308, 309.

የግ ል ግ ምገ ማጥያ ቄዎች አርብ ግንቦት 04
1. ሰው በኃጢአት ከወደቀ በኋላ በሕይወት መቀጠል የቻለው ለምን እንደሆነ ግለጽ። 2. በእውነት "ገነት" በሚባል ቦታ ዘላለማዊ ነትን እናሳልፋለንን? እባክዎን ያብራሩ። 3. የተቤዠውን ዘላለማዊ ርስት እና የአብርሃምን ተስፋ በዚህ ቦታ አብራራ። 4. አዲሱን ሰማይና አዲስ ምድር ግለጽ። 5. እንደዚህ ባለ ቦታ ዘላለማዊ ነትን እንዴት ማሳለፍ ይቻላል?
 <<    >>