ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2) << >> ሰንበት፣ ግንቦት 19፣ 2015 9ኛ ትምህርት የአዲስ ኪዳን ሰንበት የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “እንግዲያስ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ቀርቶላቸዋል።” (ዕብ. 4፡9)። ለንባብ የተመረጠዉ፡ አበዉና ነቢያት፣ ገጽ 44–51። ሰንበትን የክርስቶስ የመፍጠርና የማዳን ኃይሉ ምልክት አድርገው ለሚቀበሉት ሁሉ ያስደስታቸዋል። በሰንበት አማካይነት ክርስቶስን ስለሚያዩት በእርሱ ይደሰታሉ። ሰንበት የፍጥረት ሥራ ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ትልቅ ኃይል እንዳለው ማስረጃ መሆኑን ያመለክታቸዋል።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 289(285) 1. ምሳሌያችን እሁድ ግንቦት 13 ሀ. የሱስን ከልብ የምንወደውና ምሳሌውን የምንከተል ከሆነ እንዴት እንኖራለን? ዮሐንስ 14:15 15፡10። እርሱ በሰንበት ምን አደረገ? ሉቃስ 4:16, 31 የመለወጥ ማስረጃ ምንድን ነው? “የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ጠብቁ” (ዮሐ. 14:15)። "ከወደዳችሁኝ ፍቅራችሁ በሰዎች መካከል እንደሚታሰበው የመተሳሰብ ስሜት ብቻ አይሁን። እውነተኛ ፍቅር ትእዛዜን በመጠበቅ ላይ ነው። 'በፈቃደኝነት መታዘዝን የሚያስገኝ ፍቅር የሚለዋወጥ ነገር አይደለም፣ ነገር ግን በቃልና በተግባር የሚገለጥ ጠንካራና ቋሚ መሠረታዊ ሥርዓት ያለዉ ነው። ”— Manuscript Releases, vol. 10, p. 291.የሱስ ወደር የሌለውን መስዋዕትነት ከፍሏል። የእግዚአብሔርን ህግ በመጣስ የገባንበትን ከባድ ዕዳ ለመክፈል ከእግዚአብሄር ልጅ ህይወት ያነሰ ምንም ነገር አይበቃም። ‹ያለፉት የኃጢያ ት ስርየት› እንድናገኝና በመለኮታዊ ኃይሉና ፀጋው የሕግን የጽድቅ መስፈርቶች እንድንፈጽም ክርስቶስ ተፈጥሮአችንን በመወሰድ ስለእኛ ኃጢአት ሆነ። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ብንጠብቅም ባንጠብቅ ምንም ለውጥ አያመጣም ብሎ የሚናገር ሁሉ ክርስቶስን አያውቀዉም። የሱስ እንዲህ ብሏል፡- “የአባቴን ትእዛዛት ጠብቄአለሁ በፍቅሩም እኖራለሁ።” ስለዚህ የሱስን የሚከተሉ ሁሉ ደግሞ እርሱ እንዳደረገው ያደርጋሉ።”—The Review and Herald, March 6, 1888.ለ . በእርሱ ምሳሌ ምን ማድረግ አለብን? 1ኛ ጴጥሮስ 2:21፤ 1ኛ ዮሐንስ 2፡6 2. ስቅለት ሰኞ ግንቦት 14 ሀ. የሱስ በዝግጅት ቀን እንደተሰቀለ እንዴት እናውቃለን - ቀኑስ የትኛው ቀን ነው? ሉቃስ 23:52–56፤ ማርቆስ 15:42 ያ ሰንበት ላኑት ደቀ መሙርት ለካህናቱ፣ ለሹማምንቱ፣ ለጸሐፍትና ለመላው ሕዝበ እሥራኤል ፈጽሞ የማይረሳ ሰንበት ነበር። በሰንበት መዘጋጃ ቀን ጀምበርዋ በምትጠልቅበት ሰዓት ሰንበት መግባቱን የሚያበስረው መለከት ተነፋ ለብዙ ዘመናት ይደረግ እንደነበረው ሁሉ የፋሲካ በዓል ተከበረ፣ ነገር ግን ይህ በዓል ምሳሌ የሆነለቱ ጌታ በኃጢአተኞች እጅ ተገድሎ በዮሴፍ መቃብር ውስጥ ተጋደሞ ነበር።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 774(820)የሐፍረትና የስቃይ ቀን ካለፈ በኋላ የሱስ እረፍት አገኘ። በምዕራብ ለመጥለቅ ካዘቀዘቀችው ጀምበር የፈነጠቀው ጨረር የሰንበትን መግባት በሚያበስርበት ወቅት የእግዚአብሔር ልጅ ጸጥታ በሰፈነበቱ በዮሴፍ መቃብር ተጋድሞ ነበር። ...የሱስ ሰውን ከማዳን ሥራው ባረፈ ጊዜ የሚወዱት ሰዎች በምድር ላይ ቢያዝኑም በሰማይ ግን ደስታ ነበር። የወደፊቱ ተስፋ በሰማይ ነዋሪዎች ዓይን ሲታይ እጅግ የተከበረ ነበር። ክርስቶስ በፈጸመው ሥራ ምክንያት እግዚአብሔርና መላእክት ሥነ ፍጥረት እንደገና ታድሶ፣ኃጢአት ለአንደና ለመጪረሻ ጊዜ ስለተሸነፈ መላው ሰብአዊ ዘር ሁለተኛ በኃጢአት ላለመውደቅ ከኃጢአት ድኖ ታያቸው። የሱስ ያረፈበት ቀን ከዚህ ትይንት ጋር ለዘላለም የተቆራኘ ነው። «እግዚአብሔር…በመንገዱ ሁሉ ፍጹምና ትክክለኛ ነው።» «እግዚአብሔር የሠራው ነገር ሁሉ ዘላለማዊነት Aንዳለው ዐውቃለሁ።» ዘዳ.32:41 መክብብ 3:14። «እግዚአብሔር አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደተናገረው ዓለም ሁሉ» በሚታደስበት ጊዜ (የሐስራ 3:21) የሱስ በዮሴፍ መቃብር አርፎ የዋለባት በፍጥረት ጊዜ የተቋቋመችው ሰንበት ያንጊዜም የደስታና የእረፍት ቀን ትሆናለች። «በየሰንበቱ» (ኢሳ.66:23) ከየብሔሩና ብሔረሰቡ የዳኑት ሁሉ በአንድ ላይ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በደስታ በሚሰግዱበት ጊዜ ሰማይና ምድር በሕብረት የውዳሴ ድምጻቸውን ያሰማሉ። 769”—ኢቢድ .፣ ገጽ 769, 770(814) ለ. ምእመናን የክርስቶስን ሥጋ አዘጋጅተው በዚህች በመጀመሪያው ሰንበት ከስቅለቱ በኋላ ለምን አልጨረሱም? ሉቃስ 23:56፤ ማርቆስ 15:42-47 “ስለጌታቸው ሞት አዝነው የነበሩ ደቀመዛሙርቱ፣ የክብር ንጉሥ የሱስ በመቃብር ተኝቶ ሳለ በሰንበት ቀን ዐርፈዋል።”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገጽ. 181 ሐ. በእቅዳቸዉ መሠረት ተግባራቸውን ለመጨረ ስ መቼ ሄዱ? ማርቆስ 16:1, 2 3. ቀደምት ክርስትያን ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ግንቦት 15 ሀ. ቤተክርስቲያንቷ የሱስ ከሞት ከተነሳ ከ40 ዓመታት በኋላ ሰንበትን እንደምታከብር የሚያሳየው የትኛው የየሱስ ትንቢት ነው? ማቴዎስ 24:15-20፤ 5፡17። ሰንበትን የፈጠረዉ እርሱ በመስ ቀል ላይ በመቸንከር አልሻረውም። በሞቱ ሰንበት ከንቱና ባዶ አልተደረገም። ከተሰቀለ ከአርባ ዓመታት በኋላ አሁንም የተቀደሰ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ ሽሽታቸው በሰንበት ቀን እንዳይሆን ለአርባ ዓመታት ያህል መጸለይ ነበረባቸው።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 630.ክርስቶስ ሰንበትን ፈጥሮታል፣ እናም እርሱ ፈጽሞ አልሻረውም። ብዙዎች እንደሚሉት ሰንበት በስቅለቱ ከንቱ አልተደረገም። የክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት ለእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቅዱስ ህግ አይለወጠነት ባህሪን የሚገልጽ ምላሽ ሊሰጥበት የማይቻል መከራከሪያ ነጥብ ነው። . . .የሰበአዊ ቤተሰብ ራስ እንደመሆኑ ክርስቶስ የእያንዳንዱን ትእዛዛት፣ ቅንጣት ያህል ሳያሸራርፍ ኖረ። እርሱ፣ ተከታዮቹ እንዲኖሩ የሚፈልገውን ሕይወት በሰበአዊነት ራሱ ኖሯል፣ ስለዚህም ማንም ሰው ወደ ፍጽምና ደረጃ ላይ ለመድረስ እንዲሳነው የሚያደርግ ምንም ምክንያት የለም።”—The Review and Herald, December 20, 1898. ለ. በሰባተኛው ቀን የመጽሐፍ ቅዱስ ሰንበት የሐዋርያት የዘወትር ልማድ ምን ነበር? የሐዋርያት ሥራ 18:1-4 [ጳውሎስ] ንግግሩን በፈጸመ ጊዜ፣ አይሁድም ከምኵራብ ከወጡ በኋላ፥ አሕዛብ ግን በማመንታት ወደኋል ቀርተዉ በቀጣዩም ሰንበት ተመሳሳይ ቃል እንዲነግራቸው ጳዉሎስን ለመኑት። በአይሁድም ሆነ በአሕዛብ መካከል ሐዋርያት በጣም ተፈላጊ ሆኑ። ምእመናንና ከአሕዛብ የተመለሱትን በእምነታቸው ጸንተው በእግዚአብሔር ጸጋ ወደፊት እንዲቀጥሉ አበረታተዋል። የሐዋርያትን ቃል ለመስማት ከፍተኛ ፍላጎት ስለነበረው መላው ከተማ በሚቀጥለው ሰንበት አንድ ላይ ተሰበሰበ።”—Sketches from the Life of Paul, pp. 48, 49. ሐ. ጳውሎስ በሚሄድበት ቦታ ምኩራብ በማይኖርበት ጊዜ ካደረገው ልምምድ ምን እንማራለን? የሐዋርያት ሥራ 16:12, 13 ልጆቻችንን በሰንበት ቀን ደስተኛ መሆን እንደሌለባቸው፣ ከቤት ውጭ መሄድ ስህተት እንደሆነ ልናስተምራቸዉ አይገባም። በፍፁም እንደዛ መሆን የለበትም። ክርስቶስ በሰንበት ቀን ደቀመዛሙርቱን ወደ ሀይቅ ዳርቻ ወስዶ አስተማራቸው። በሰንበት ቀን የሚያደርጋቸዉ ስብከቶች ብዙን ጊዜ በግድግዳዎች መካከል በታጠረ ቦታ (በቤት ዉስጥ) አልነበሩም።”—Child Guid¬ance, pp. 533, 534 4. የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ረቡዕ ግንቦት 16 ሀ. ክርስቶስ ከትን ሣኤው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተገለጠ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለምን ተሰበሰቡ? ሁለተኛ ጉብኝቱ የተለየ የአምልኮ ቀን እንዳላቋቋመ የሚያረጋግጠው እንዴት ነው? ዮሐንስ 20:19, 26 ክርስቶስ በሰንበት ቀን በመቃብር አርፎአል፣ እና የሰማይም የምድርም ቅዱሳን ከሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በማለዳ በተነሱ ጊዜ፣ እርሱም ደቀመዛሙርቱን የማስተማር ስራውን ለማደስ ከመቃብር ተነሳ። ነገር ግን ይህ እውነታ የሳምንቱን የመጀመሪያ ቀን አይቀድስም እንዲሁም ሰንበትም አያደርገውም።”—Spirit of Prophecy, vol. 3, p. 204. ለ. ገንዘብ የማዋጣቱ ሥራ በዚያ ቀን መደረጉ የሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን የተለየ የአምልኮ ቀን እንዳልሆነ የሚያሳየው እንዴት ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 16:1፣ 2 ዳቦ መቁረስ አንድ ቀን ወይም ሌሊት ልዩ የሳምንት አምልኮ ቀን ተብሎ መወሰኑን ያሳያል? የሐዋርያት ሥራ 2:42, 46 ሐ. በጢሮአዳ የተደረገው ስብሰባ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የተካሄደው ለምን ነበር? የሐዋርያት ሥራ 20:8-12 በዘመናችን የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን እኩለ ሌሊት መቼ ነው? ዘፍጥረት 1:5; ዘሌዋውያን 23:32 የ ሚወዱ ት መምህራቸው ተለይቷቸዉ ሊሄድ ሲለሆነ ከወትሮው የበለጠ ብዙ ወዳጆች ተጠራርተው ነበር። ለእንደዚህ ዓይነቱ ስብሰባ በዚያ ሞቃታማ የፀደይ ምሽ ት በጣም ቀዝቃዛና አስደሳች ቦታ በሆነዉ በሶስተኛው ፎቅ ላይ ባለው ክፍል ውስጥ ተሰበሰቡ። በዚያን ጊዜ ምሽቱ ጨለማ ነበር፣ ነገር ግን በክፍሉ ውስጥ ብዙ መብራቶች ይበሩ ነበር።የጳውሎስ አእምሮ ስለሚጠብቀው አደጋና ከእነዚህ ወንድሞቹ ጋር እንደገና የመገናኘቱን ነገር እርግጠኛ አለመሆኑን በማወቁ በፊታቸው ለማቅረብ ትልቅ ፍላጎትና አስፈላጊነት ያላቸው ጉዳዮች ነበሩት፤ እና ለእነርሱ ባለው ፍቅርና ልባዊ ፍላጎት የተነሳ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ሰበከ።”—Sketches from the Life of Paul, pp. 196, 197. መ. የጌታ ቀን የትኛውቀን ነው—ይህንስ መገንዘባችን ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ራእይ 1:10፤ ማር ቆስ 2:28፤ ኢሳይያስ 58:13 የአራተኛይቱን ትእዛዝ ሰንበትን በተመለከተ የእውነት ብርሃን ከተገለጸላችሁ በኋላ ግን እግዚአብሔር "የተቀደሰች ቀኔ" ብሎ የጠራት ሰንበትን በቅድስና ላለመጠበቅ፣ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ምንም መሠረት እንደሌለዉ እያያችሁ ከሐሰተኛው ሰንበት እሑድ ጋር የሙጥኝ የምትሉ ከሆነ የአውሬዉን ምልክት ትቀበላላችሁ። ይህ መቼ ነው የሚሆነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እሑድ ከተራ የሥራ ቀንነት የተለየ ነገር እንደሌለዉ እያወቃችሁ፤ በዕለተ እሑድ ከድካማችሁ አርፋችሁ እግዚአብሔርን አምልኩ የሚለውን ትእዛዝ ስትፈጽሙ የእግዚአብሔርን ማኅተም እምቢ በማለት የአውሬውን ምልክት ለመቀበል ተስማምተሃል ማለት ነዉ።”—Evangelism, p. 235. 5. መታሰቢያ ሐሙስ ግንቦት 17 ሀ. ሰንበት መታሰቢያው ምንድን ነው? ዘጸአት 31:13፤ ዘፍጥረት 2:1-3 “የሰንበት እንደ የፍጥረት መታሰቢያነት አስፈላጊ የሆነው፣ አምልኮ የሚገባው እግዚአብሔር እንደሆነ እውነተኛውን ምክንያት ሁልጊዜ አዲስ ስለሚያደርገው ነው"፤ ምክንያቱም እርሱ ፈጣሪ እኛ ደግሞ የእርሱ ፍጡራን ነንና። . . . ይህንን እውነት በሰዎች አዕምሮ ምንጊዜም ለማስቀመጥ ነበር እግዚአብሔር ሰንበትን በኤደን ገነት ያስቀመጠው፤ እርሱን ልናመልከው የሚገባን ምክንያቱ ፈጣሪያችን ስለሆነ የመሆኑ እውነታ እስካላቋረጠ ድረስ፣ ሰንበት የዚህ እውነት ምልክትና መታሰቢያ ሆና ትቀጥላለች። ሰንበት በአለማቀፋዊነት ሁሉ ተጠብቃ ቢሆን ኖሮ አምልኮና ክብር የሚገባው ፈጣሪ መሆኑን ያስተውል ዘንድ የሰው ሃሳብና ፍላጎት ወደ እርሱ ይመራ ነበር፤ ጣዖት አምላኪ፣ እምነት የሌለው ወይም ከኃዲም በፍፁም አይኖርም ነበር። ሰንበትን መጠበቅ “ሰማይንና ምድርን ባህርንም የውኃንም ምንጮች ለሰራው” ለእውነተኛው እግዚአብሔር ታማኝ የመሆን ምልክት ነው። ከዚህም በመነሳት እግዚአብሔርን እንዲያመልኩና ትዕዛዛቱንም እንዲጠብቁ የሚያዘው መልእክት፣ አራተኛውን ትዕዛዝ በተለየ ሁኔታ እንዲጠብቁት ይጠራቸዋል።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 437, 438 ለ. የግል ቤዛችን መታሰቢያ የሆነው እንዴት ነው? ዘዳግም 5:15 ይህ የልብ ለውጥ እንዴት ይከናወናል? ሕዝቅኤል 36:26, 27፤ መዝሙረ ዳዊ ት 51:10 እግዚአብሔር የሚያከብረዉ የፍቅርን አገልግሎት ነዉ። ፍቅር የጎደለዉ ተራ አገልግሎት ያስቀይመዋል። ሰንበትም በተመለከተም እንደዚሁ ነዉ። ሰንበት የታቀደዉ ሰዉን ከእግዚአብሔር ጋር ለማገናኘት ነበር። ነገር ግን ሕሊና በአሰልቺ አገልግሎት ሲወጠር የሰንበት ዓላማ ይሰናከላል። የሰንብት ተራ የታይታ አገልግሎት ፌዝ ነዉ።”—የዘ መና ት ምኞት፣ ገ ጽ. 286 የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ግንቦት 18 1. ክርስቶስ የሰንበትን ማክበር በተመለከተ ምን ምሳሌ ሰጥቷል? 2. በስቅለቱ ዙሪያ የተከናወኑት ድርጊቶች ሰንበት ሳይበላሽ መቆየቱን በግልጽ የሚያሳዩት እንዴት ነው? 3. ሐዋርያት ሰንበትን በተመለከተ ምን ዓይነት ልማድ ነበራቸው? 4. የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ይፋዊ የአምልኮ ቀን ተብሎ ያልተጠቀሰበትን ምክንያት አስረዳ። 5. የሰንበት ማክበር በጣም አስፈላጊው ገጽታ ምንድን ነው? << >>