ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2) << >> ሰንበት፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 6ኛ ትምህርት የሺህ ዓመታት የምድር ባዶ መሆን (II) የመታሲያ ጥቅስ ፡- ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።” (ራዕ ይ 20፡4)። ለንባብ የተመረጠዉ፡ Early Writings, pp. 289–295. መልአኩ እንዲህ ሲል ተናገረ «ለኃጥአን ጥፋትና ሞት መንስኤ የእግዚአብሔርና የበጉ ቁጣ ነው፡፡ አምላካዊውን ሰንደቅ ያነገበው የእግዚአብሔር ሠራዊት በእግዚአብሔር ድምፅ ብርቱ ቢሆንም ነገር ግን የተጻፈው ፍርድ በዚያን ወቅት ገቢራዊ አይሆንም፡፡ ፍርዱ ገቢራዊ የሚሆነው በአንድ ሺሁ ዓመት መዝጊያ ላይ ነው፡፡'”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገጽ. 52. 1. የሰይጣን ሁኔታ እሁድ ሚያዝያ 22 ሀ. በሺህ ዓመቱ ሰይጣን ምን አጋጠመው? ራእይ 20:1-3 ‹ሰንሰለቶቹን› እና እንዴትና መቼ እንደሚወገዱ ያብራሩ። ራእይ 20:5, 7, 8 ምድር የተተወች ምድረበዳ መሰለች። ከተሞችና መንደሮች በርዕደ መሬት ተራሮች ታላላቅ ሸለቆዎችን እየተዉ ከስራቸው እየተነቀሉ ተነሱ። ታላላቅ ዐለቶች ከባህርም ሆነ ከደረቁ መሬት እየተተፉ በመበተን ስፍራውን ሁሉ ሞሉት ግዙፍ ዛፎች ከነሥራቸው በመነቀል በምድሪቱ ላይ ተንጋለሉ። እንዲህ ያለው የተመሰቃቀለና የወደመ ምድር የሰይጣንና መላእክቱ የሚቀጥሉት አንድ ሺህ ዓመታት መኖሪያ ይሆናል። ሰይጣን በዚህ መልኩ በግዞት በመኖር በወደመው የምድር ገጽ ላይ ወዲያና ወዲህ እየተቅበዘበዘ በእግዚአብሔር ሕግ ላይ የማመጹን ውጤት ይመለከታል፡፡ ለአንድ ሺህ ዓመት እርሱ መንስዔ የሆነበትን የእርግማን ፍሬ ይቀምሳል፡፡ ሰይጣን ወዳልወደቁት ዓለማት በመሄድ እንዲበጠብጥ ስለማይፈቀድለት በምድር ላይ ብቻውን ይወሰናል፡፡”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገጽ. 290.በሺህ ዓመት ማብቂያ ላይ፣ ክርስቶስ እንደገና ወደ ምድር ይመለሳል። . . . በሚያስደንቅ ግርማ ሲወርድ ክፉ ሙታን ጥፋታቸውን ይቀበሉ ዘንድ ይነግራቸዋል።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 662. 2. በአሕዛብ እና በመላእክት ላይ መፍረ ድ ሰኞ ሚያዝያ 23 ሀ. ቅዱሳን በሺህ ዓመት ምን ያደርጋሉ? ራእይ 20:4፤ 3:21፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6:2, 3 ጻድቃን የማይሞተውን ለብሰው ተለውጠውና ከየሱስ ጋር በአንድነት በደመና ከተነጠቁ በኋላ፣ በገናዎቻቸውን፣ መጎናጸፊያቸውንና ዘውዳቸውን ተቀብለው ወደ ከተማዋ ይገባሉ። የሱስና ጻድቃን ለፍርድ ይቀመጣሉ--- የህይወትና የሞት መጽሐፍትም ይከፈታሉ። የህይወት መጽሐፍ የቅዱሳኑን መልካም ተግባራት የያዘ ሲሆን የሞት መጽሐፍ ደግሞ የኃጥአኑን ክፉ ተግባራት ይዞአል። እነዚህ መጻሕፍት ከሕግ መጻሕፍት፣ ከመጽሐፍ ቅዱስና ሰዎች ከሚዳኙባቸው መንገዶች ጋር ይስተያያሉ፡፡ ጻድቃን ከየሱስ ጋር በአንድ ድምጽ በሟች ኃጥአን ላይ ፍርዳቸውን ይሰጣሉ፡፡» መልአኩ ልብ ብለሽ ተመልከች በማለት ከየሱስ ጋር በፍርድ የተቀመጡት ጻድቃን---ኃጥአን በምድራዊ ህይወታቸው በሠሩት መጠን ይፈርዷቸዋል፡፡ ይህ እነርሱ የሚቀበሉት ፍርድ በስሞቻቸው ተርታ ተቀምጦአል፡፡» አለኝ፡፡ የተመለከትኩት ነገር ቅድስቲቱ ከተማ ወደ ምድር ከመውረዷ አስቀድሞ ቅዱሳኑ ለአንድ ሺህ ዓመት ከየሱስ ጋር በሚነግሡበት ወቅት የሚሠሩትን ሥራ ነበር።”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገጽ 52፣53 ለ. ይህ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ የሰማያዊ ት መዲና የሆ ነችው አዲሲቱ የሩሳሌም ምን ትሆናለች? ራእይ 21:2, 10፤ ገላ 4፡26 ከዚያም በአንድ ሺሁ ዓመት መዝጊያ ላይ የሱስ ከመላእክቱና ከመላው ጻድቃን ጋር በአንድነት በመሆን ቀድስቲቱ ከተማ ትተው ሲወርዱሞተው ሙታን-በተለይም የነበሩ እርሱ «የወጉት» ሰዎች ይነሳሉ---ከመላእክቱና አብረውት ከነበሩት ቅዱሳን ጋር ሆኖ በሙሉ ግርማው በሩቁ ይመለከቱታል- ከእርሱ የተነሳም ዋይ ዋይ ይላሉ።”—ኢቢ . 52.ክርስቶስ ከትንሳኤው በኋላ ባረገበት፣ መላእክትም የመመለሱን ተስፋ በደገሙበት በደብረዘይት ተራራ ላይ ወረደ። ነብዩ እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔርም አምላኬ ይመጣል ቅዱሳኑም ሁሉ ካንተ ጋራ።”፤ “በዚያም ቀን እግሮቹ በየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ… እጅግም ታላቅ ሸለቆ ይሆናል።” “እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ይነግሳል፤ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ ይሆናል፣ ስሙም አንድ (there shall be one Lord, and his name one)” [ዘካ 14÷5፣4፣9]። አዲሲቱ የሩሳሌም፣ በሚያስገርም ውበትዋ ከሰማይ ስትወርድ ፀድቶና ተዘጋጅቶ በሚቀበላት ስፍራ አረፈች፤ ከዚያም ክርስቶስ ከሕዝቦቹና ከመላእክቱ ጋር ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ገቡ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 662፣ 663 3. ተፈፃሚው ፍር ድ ማክሰኞ ሚያዝያ 24 ሀ. ሰይጣን መዲናዋን ለመያዝ ቢያቅድም ይህ እንዴት ሌላ ፍርድ ያስከትላል? ራእይ 20:9 (የመጀመሪያ ክፍል)፣ 11, 12 አሁን ሰይጣን ለመጨረሻው ታላቅ የበላይነት ግብግብ ይዘጋጃል። ኃይሉ የተወሰደበት፣ ከማታለል ሥራውም ተገልሎ የክፋት ልዑል ጎስቋላና ኃዘንተኛ ሆኖአል፤ ሆኖሞ የሞቱት ኃጥአን ሲነሱና እልፍ አዕላፋት በእሱ ጎን ሆነው ሲያይ ተስፋው አንሰራራ፤ እናም ታላቁን ተጋድሎ ላለመሸነፍ ቆረጠ። የጠፉትን የጦር ሰራዊት በባንዲራው ስር አሰልፎ በመምራት፣ በእነርሱ አማካኝነት እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ይጥራል። ኃጥአን የሰይጣን ምርኮኞች ናቸው። ክርስቶስን ባለመቀበላቸው የአማፂውን መሪ አስተዳደር ተቀብለዋል። የሚያቀርባቸውን ኃሳቦች ለመቀበል ትዕዛዛቱንም ለማድረግ የተዘጋጁ ናቸው። ሆኖም ልክ እንደመጀመሪያው አታላይነቱ እሱ ራሱ ሰይጣን እንደሆነ እውቅና አይሰጥም። የተገባው የዓለም ባለቤት፣ ርስቱም ያለአግባብ የተወሰደበት ልዑል እንደሆነ ይናገራል። ለተሞኙት ተገዥዎቹ ራሱን አዳኝ አድርጎ በማቅረብ ኃይሉ ከመቃብር እንዳስነሳቸው፣ እጅግ ጨካኝ ከሆነው አንባገነንም ሊያድናቸው እንደሆነ ይነግራቸዋል። የክርስቶስ መገኘት ከዚያ ስለተወገደ፣ ንግግሩን ለመደገፍ ሰይጣን ተዓምራትን ያደርጋል። ደካማውን አጠንክሮ፣ ሁሉንም በራሱ መንፈስና ኃይል ያነሳሳቸዋል። የቅዱሳንን ሰፈር ለማጥቃት ሊመራቸው፣ የእግዚአብሔርንም ከተማ ለመያዝ ኃሳብ ያቀርባል። በዲያብሎሳዊ ትዕቢት ተሞልቶ ከሞት ወደ ተነሱት የማይቆጠሩ ሚሊዮኖች በመጠቆም መሪያቸው እንደመሆኑ ከተማዋን ለመገልበጥ በእርግጥ የሚቻለውና ዙፋኑንና መንግሥቱን እንደገና ለመያዝ የሚችል መሆኑን ያውጃል።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 663. ለ. ፍርዱ እንዴት ይፈጸማል? ራእይ 20:9 (የመጨረሻውክፍል)፣ 10፤ ኢሳይያስ 34:8-10 እሳት ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ ወረደ። ምድር ተሰባበረች፤ በውስጥዋ የተደበቁት መሳሪያዎች ወደ ላይ ወጡ። የሚፋጁ ነበልባሎች ከእያንዳንዱ ከተከፈተ የምድር ገደል ወጡ። ቋጥኞቹ ራሳቸው ተቃጠሉ። እንደ ምድጃ እሳት የሚያቃጥለው ቀን ደርሶአል። የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኩሳት ቀለጠ፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ተቃጠለ [ሚል 4÷1፤ 2ኛ ጴጥ 3÷10]። የምድር ፊት አንድ የቀለጠ ግዙፍ አካል መሰለ – ሰፊ የሚፈላ የእሳት ሐይቅ። የፍርድ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን የማይመስሉ ሰዎች መጥፊያ ሰዓት ነው።”—ኢቢድ፣ ገጽ 672፣ 673 ሐ. ይህ እሳት ለዘላለምእንዳልሆነ እንዴት እናውቃለን? ኤርምያስ 17:27፤ ይሁዳ 1፡7 4. የክፉዎች ጥፋት ረቡዕ ሚያዝያ 25 ሀ. የመጨረሻ ው ጥፋት (ጽዳት) በኖኅ ዘመን ከነበረው የጥፋት ውሃ ጋር ሲነጻጸር እንዴት ነው? 2ኛ ጴጥሮስ 3፡10-13 ምድር በአጥፊው እሳት ተጀቡና ሳለ፣ ፃድቃን ግን በቅድስቲቱ ከተማ በደህና ኖረዋል። በመጀመሪያው ትንሳኤ እድል ፈንታ ባላቸው ላይ ሁለተኛው ሞት ኃይል የለውም [ራዕይ 20÷6]። እግዚአብሔር ለኃጥአን የሚፋጅ እሳት ሆኖ ሳለ ለሕዝቦቹ ግን ብርሃንና ጋሻ ነው። [መዝ 84÷11]። ——ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 673.ኃጥአንን የሚበላው እሳት ምድርን አንጽቷታል። እያንዳንዱ የእርግማን ምልክት ተጠርጓል። የሚያስፈራውን የኃጢአትን ውጤት ያሳይ ዘንድ በተዋጁት ፊት ለዘላለም የሚቃጠል ሲኦል አይኖርም።”—Ibid., p. 674. ለ. ይህ ጥፋት ምን ያህል ጥልቅ ነው? ሚልክያስ 4:1-3፤ መዝሙረ ዳዊ ት 37:10 «ቅዱሳን በቅድስቲቱ ከተማ በማረፍ እንደ ነገሥታትና ካኅናት ለአንድ ሺህ ዓመት ይነግሣሉ፡፡ ከዚያም የሱስ ከእነዚህ ቅዱሳን ጋር በመሆን ደብረዘይት ተራራ ላይ ይወርዳል፤ ተራራውም ተለይቶ የእግዚአብሔር ገነት የሚያርፍበት ኃያልና ግዙፍ መስክ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቀሪው የምድር ክፍል ኃጥአን ከሞት ተነስተው ከተማዋን እስከሚከቡበት እስከ አንድ ሺሁ ዓመት መጨረሻ አይነጻም። የኃጥአን እግሮች አዲሲቱን ምድር ፈጽሞ አያረክሱም፡፡ እሳት ከእግዚብሔር ዘንድ ከሰማይ ይወርድና ይበላቸዋል---ሥርና ቅርንጫፍም አይተውላቸውም። ሰይጣን ሥር ሲሆን ልጆቹ ደግሞ ቅርንጫፎቹ ናቸው። ኃጥአንን የሚበላው ያው እሳት ምድርን ያነጻል።”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገ ጽ 51፣ 52አንድ ማስታወሻ ብቻ ይቀራል፦ አዳኛችን ለዘላለም የስቅላቱን ጠባሳ እንደያዘ ይኖራል። በቆሰለው ራሱ፣ በጎኑ፣ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ ብቻ ኃጢአት ያመጣው ጨካኝ ሥራ ምልክት ይቀራል። ክርስቶስን በክብሩ ሲመለከት ሳለ ነብዩ እንዲህ አለ፦ “ፀዳሉ እንደ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል” [ዕንባ 3÷4]። ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀው ቀዩ ጅረት የወጣበት ያ የቆሰለ ጎን የአዳኙ ክብር እዚያ ነው። “ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል።” “ለማዳን የበረታ”ው [ኢሳ 63፥1]፤ በመዋጀት መስዋዕት አማካኝነት የእግዚአብሔርን ምሕረት ባቃለሉት ላይ ፍርድን ይተገብር ዘንድ ብርቱ ሆነ። የመዋረዱ ምልክቶችም የእርሱ የክብሩ ከፍታ ጥግ ናቸው፤ ወደፊት ባሉት የዘላለም ዘመናት የቀራንዮ ቁስሎች ምስጋናውን ይገልጣሉ፤ ኃይሉንም ያውጃሉ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 674. 5. ምድር ጸዳ ች ሐሙስ ሚያዝያ 26 ሀ. እኛ እንደ የምናውቀው ዩኒቨርስ ምን ይሆናል? ራእይ 21:1, 5 ዩኒቨርስ አንድ የሚሆነው በምንድን ነው? ራእይ 5:13 የዘላለም ዓመታት እየተጠቀለሉ ሲያልፉ ሳለ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ክርስቶስ ጥልቅ፣ ብሎም የበለጠ ግሩም ድንቅ መገለጦችን ያመጣሉ። እውቀት እየጨመረ እንደሚሄድ ሁሉ ፍቅርም፣ አክብሮትም፣ ደስታም ይጨምራሉ። ሰዎች ስለ እግዚአብሔር የበለጠ እየተማሩ ሲሄዱ ለባህርይው ያላቸው አድናቆት የላቀ ይሆናል። የሱስ የድነትን ባለጠግነት በፊታቸው ሲገልጽላቸው፣ ከሰይጣንም ጋር በነበረው ታላቁ ተጋድሎ የተቀዳጃቸውን አንፀባራቂ ስኬቶች ሲያሳያቸው የተዋጁት ልቦች በበለጠ መሰጠት ይፈነድቃሉ። በሚያፍነከንክ ደስታም የወርቅ በገናዎችን ይደረድራሉ። አሥር ሺህ ጊዜ አሥር ሺህ፣ ሺህ በሺህ የሆኑ ድምፆች ኃያሉን የምስጋና መዝሙር ያደምቁ ዘንድ አንድ ይሆናሉ። . . .ታላቁ ተጋድሎ (ተቃርኖ) አብቅቷል። ኃጢአትና ኃጢአተኞች ከእንግዲህ የሉም። መላው ዩኒቨርስ ንፁህ ነው። አንድ የመስማማትና የደስታ ትርታ በሰፊው ፍጥረት ሁሉ ይመታል። ወሰን በሌለው ህዋ ዳርቻዎች ሁሉ ሕይወት፣ ብርሃንና ደስታ ሁሉን ከፈጠረ ከእርሱ ዘንድ ይፈሳሉ። እጅግ ደቃቅ ከሆነችው ክፍለ-ቁስ (atom) እስከ ግዙፉ ዓለም፣ ሕይወት ያለውም ሆነ ሕይወት የሌለው፣ ባልደበዘዘ ውበታቸውና ፍፁም ደስታቸው፣ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ብለው ያውጃሉ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 678 ለ. ከዚህ እውነታ አንጻር ራሳችንን ምን ብለን መጠየ ቅ አለብን? ዕብራውያን 3:7, 8 “መንቃትና ክርስቶስን ለመምሰል ቆራጥ ጥረት ማድረግ ያለብን አሁን ነዉ። ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ። . . . “ወንድሞች፣ በታላቁ የዝግጅት ስራ ጊዜ ላይ እናንተ ምን እያደረጋችሁ ነው?”—Tes¬timonies for the Church, vol. 5, p. 216. የግ ል ግ ምገ ማጥያ ቄዎች አርብ ሚያዝያ 27 1. ሰይጣንን የ ሚያስረው ምንድን ነው? የ ሚፈታውስ እንዴት ነው? 2. ቅዱሳን ለሺህ ዓመታት የተሳተፉት በምን ዓይነት ሥራ ነው ውጤቱስ ምን ይመስላል? 3. ሰይጣን የአምላክን ከተማ ለመቆጣጠር ቢሞክርም ይህ የመጨረሻው ፍርድ የሚያመጣው እንዴት ነው? 4. መላው አጽናፈ ሰማይ የሚጸዳው እንዴት ነው? 5. የእግዚአብሔር ጽንፈ ዓለም የመጨረሻ ሁኔታ ምንድን ነው? << >>