Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ ለዓለም ተልእኮዎች ሰንበት፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 የሱስ ቶሎ እንዲመጣ ትፈልጋለህ? ይህ ሊሆን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ይነግረናል፡- “ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል። ያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል” (ማቴ 24፡14) ወንጌልን ለአለም ሁሉ ልናደርስ ይገባናል፣ነገር ግን ከፊታችን ካለው ታላቅ ስራ ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ትንሽ ነው የተሰራው! የእግዚአብሔር መላእክት በሰዎች አእምሮ ላይ እየተንቀሳቀሱና ማስጠንቀቂያውን እንዲቀበሉ እያዘጋጃቸው ነው። ገና እምብዛም ባልተገቡ መስኮች ሚስዮናውያን መላክ ያስፈልጋል። አዳዲስ መስኮች በየጊዜው ይከፈታሉ።”—Evangelism, pp. 408, 409 ከእነዚህ አዳዲስ መስኮች አንዳንዶቹ የት ናቸዉ? በቅርቡ የተከፈቱት አዲስ ተልእኮዎች መካከለኛው አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ሌሶቶ፣ ጋቦን፣ ጊኒ ቢሳው፣ በቅርቡ አባላትን ያጠመቁትን ቤኒን እና ኮትዲ ቧርን ይጨምራል። በአሁኑ ጊዜ አጠቃላይ ጉባኤው በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 85 ሚሲዮኖች ለፓስተሮችና የመጽሐፍ ቅዱስ ሰራተኞች ደሞዝ እየረዳ ነው። ይህ ምን ያህል ገንዘብ ይፈልጋል? በ2021፣ US$647,000 ለዚሁ ዓላማ ተልኳል። ለእዚህ ዓላማ በሥጦታ መልክ ምን ያህሉን ተቀበልን? የአሜሪካ ዶላር 132,826 (ይህ ትክክለኛው ቁጥር ነው እና ይህም የማያዛልቅ እንደሆነ ማየት ይችላሉ!) ውድ ወንድሞች እና እህቶች ይህ እውነታ ነው። ተልእኮዎቹ የሁሉንም ሰው ድጋፍ ይፈልጋሉ - እና ብዙ ተጨማሪ። መልእክቱ ወደ አዲስ ቦታዎች ሲሄድ ማየት ይፈልጋሉን? ለዓለም ተልዕኮ ፈንድ የምንሰጠውን ገን ዘብ ከጨመርን ይሄ ሊከሰት ይችላልና። አዳዲስ መስ ኮች በተከፈቱ መጠን፣ የእርዳታ ጥሪዎች በየጊዜው እየጨመሩ ይሄዳሉ። ኢኮኖሚን ማመጣጠን መለማመድ ካስፈለገን ጊዜዉ አሁን ነው። . . . አንዲት ሳንትም ብቻዋን ዋጋ የሌላት ትመስላለች፣ ነገር ግን መቶ ሳንትሞች አንድ ላይ ሲሆኑ ግን አንድ ብር ይሆናሉ፤ እናም በትክክለኛ ሁኔታ ሥራ ላይ ከዋለ ነፍስን ከሞት የሚያድን ሀብት ሆኗል ማለት ነዉ። ሕዝቦቻችን የግል ፍላጎታቸዉን ለማርካት ያለ አግባብ የሚያጠፏቸዉ ሀብት ለእግዚአብሔር ዓላማ ቢዉሉ ኖሮ ይህን ጊዜ የእግዚአብሔር ግምጃ ቤትም ባዶ አይሆንም፣ በእያንዳንዱ የዓለም ክፍላትም ተልዕኮዎች ይደራጁ ነበር።” —Counsels on Stewardship, pp. 290, 291. እባካችሁ ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ የመጀመርያውን የሰንበት ሥጦታ ለአለም ተልእኮዎች ሲሰበሰቡ በጨለማ ውስጥ ያሉትን ነፍሳት አስታውሱና አዲስ አከባቢዎች የወቅቱን እውነት እንዲቀበሉ በልግስና ስጡ። የቤተ ክርስቲያናችን አባላት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ተልእኮዎች ጥልቅ ፍላጎት ሊሰማቸው ይገባል። የእውነትን መሥፈርት በአዳዲስ አካባቢዎች ለመትከል የራስን ጥቅም የመሠዋት ጥረት ካደረጉ ታላቅ በረከት ያገኛሉ።”—Christian Service, p. 184. አምላክ ስጦታዎችንና ሰጭዎችን አብዝቶ ይባርክ! ወንድሞቻችሁ ከጄነራል ኮንፈራንስ
 <<    >>