Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሰኔ 03፣ 2015 11ኛ ትምህርት
የተሰበረዉ ድልድይ (አገናኝ) የ መታሰቢያ ጥቅስ፡- “ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና።” (2ኛ ተሰሎን ቄ 2፡3)
ለንባብ የተመረጠዉ፡   ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ. 49–60, 433–450. 
አስፈላጊና ወሳኝ በሆነ ስራ ላይ ተሰማርተናል፣ እናም ኃይለኛ ጦርነት ማድረግ አለብን። ለእውነተኛ ፕሮቴስታንት መርሆዎች መቆም አለብን፤ ጳጳሳዊዉ ስርዓት የሕሊና ነፃነትን ለመከልከል ወደሚቻለው ቦታ ሁሉ ይጎርፋልና።”—The Review and Herald, September 9, 1909.

1. የብረት ጥርስ ያለው አስፈሪ አውሬ እሁድ ግንቦት 27
ሀ. ስለቀጣዩ ትንቢታዊ አውሬ፣ ስለ ኃያሉ የሮማ ግዛት የተሰጠው መግለጫስ ምንድን ነው? ዳንኤል 7:7; ማቴዎስ 27፡27-35 የሮም መንግሥት በግዛቱ ክልል የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ እንዲመዘገቡ ያወጣዉ መመሪያ በገሊላ የሚኖሩትንም ያጠቃልል ነበር። . . . በሕዝብ ተጣብባ በነበረችዉ እንግዳ ማረፊያ [ለዮሴፍና ማርያም] ቦታ አልተገኘላቸውም። ለእንስሳት ማደሪያ በተሰራዉና ምቾት በሌለዉ በረት መጠለያ አገኙ፤ እዚያም የዓለም አዳኝ ተወለደ።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 32ሕዝቡ በከፍተኛ ጩኸትና ሁካታ የየሱስን ደም በመሻት፤ በጭካኔ እየተራገሙ ቀይ አሮጌ ንጉሣዊ መጎናጸፊያ አጠለቁለት እንዲሁም በተቀደሰው አናቱ ላይ የእሾህ አክሊል ደፉበት። …ሕዝቡ በየሱስ ላይ የከፋ ጉዳት ሲያደርስበት ሳለ እርሱ ግን በትህትና ቆሞ ነበር። ያ ከጸሐይ ይልቅ በሚያንጸባርቀው፣ ለእግዚአብሔር ከተማ ብርሃን የሚሰጠውንና አንድ ቀን አመጸኞች ሸሽጉን በሚሉት ፊቱ ላይ ይተፉበት ነበር።”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገ ጽ. 170. ለ. በመጨረሻ በዚያ ግዛት ውስጥ ምን የተለየ ልዩነት ተፈጠረ? ዳንኤል 7፡19-24

2. የእግዚአብሔርን ህግ ለመለወጥ ያስባል ሰኞ ግንቦት 28
ሀ. የእግዚአብሔር ሕግ ሊለወጥ እንደማይችል እንዴት እናውቃለን? መዝ ሙር 111:7, 8፤ ማቴዎስ 5:17-19ሉቃስ 16:17ራእይ 22:14 የእግዚአብሔር ህግ በራሱ ጣት በድንጋይ ገበታዎች ላይ ተጽፎአል፣ ስለዚህም ፈጽሞ ሊለወጥ ወይም ሊሻር እንደማይችል ያሳያል። እንደመንግሥቱ መርሆች የማይለወጥ፣ ለዘላለማዊ ው ዘመን ተጠብቆ የሚቆይ ነው።”—Counsels to Parents, Teachers, and Students, p. 248..የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው፣ እና ህጉ ለወንጀለኛው ማምለጫ መንገድ ለማድረግ አንድት ቅንጣት ያህል ሊለወጥ አይችልም። በቀራንዮ መስ ቀል ላይ የነበረዉ የክርስቶስ ጭንቀት የሕጉ የማይለወጥ መሆኑን ለማረጋገጥ ከሚቀርቡት መከራከሪያዎች ሁሉ በበለጠ ጮክ ብሎ የሚናገር ማረጋገጫ ነዉ።”—The Review and Herald, July 19, 1892.ክርስቶስ ሲሞት ሕጉን ሽሮታል በማለት ሰይጣን ክርስቲያኑን ዓለም አታልሏል። ይልቁንስ የቀራኒዮ መስቀል የእግዚአብሔርን ሕግ ከፍ ከፍ አድርጎ አክብሮታል። . . . እግዚአብሔር ከሕጉ አንዷን ቅንጣት እንኳን ቢለዉጥ ኖሮ የክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መምጣትና በስቃይ መሞት ባላስፈለገ ነበር። —The Signs of the Times, November 24, 1887. ለ. በሮም ግዛት ውስጥ ምን ዓይነት ኃይል ማዳ በር ነበረበት? ምን ለማድረግ ያስብ ነበር፣ እና በዕቅዱ የተጎዱት የትኞቹ ትእዛዛት ናቸዉ? ዳንኤል 7:23– 25; ዘጸአት 20:4–6, 8–11 ሮም የስዕልና ምሳሌ አምልኮ የሚከለክለውን ሁለተኛውን ትዕዛዝ ከእግዚአብሔር ሕግ በማስወገድ፣ የትእዛዛቱ ቁጥር ግን እንዳይጎድል አስረኛውን ትዕዛዝ ለሁለት ለመክፈል ሮም የድፍረት ሃሳብ ወጠነች።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 52ጳጳሳዊያኑ ሁለተኛውን ትዕዛዝ ስለመተዋቸው ምክንያት ሲያቀርቡ በመጀመሪያው ትዕዛዝ ውስጥ ስለተጠቃለለ አላስፈላጊ ነው ይላሉ፤ ሕጉ ይስተዋል ዘንድ እግዚአብሔር እንዳቀደው፣ እንደዛው አድርገው እንዳቀረቡት ይናገራሉ። ይህ በነብዩ የተተነበየው ለውጥ ሊሆን አይችልም። ሆን ተብሎ ታስቦበት የተደረገ ለውጥ ይስተዋላል። "ዘመናትንና ሕግን ይለውጥ ዘንድ ያስባል።" በአራተኛው ትዕዛዝ ላይ የሚደረገው ለውጥ ትንቢቱን በትክክል ይፈጽመዋል። ለዚህ ድርጊት ጥቅም ላይ እንደዋለ የተጠቀሰው ብቸኛ ስልጣን የቤተ ክርስቲያን ነው። እዚህ ላይ ጳጳሳዊው ስልጣን በገሃድ ራሱን ከእግዚአብሔር በላይ ያስቀምጣል።”—Ibid., p. 446.ታላቁ ከሃዲ “አምላክ ከተባለው ሁሉ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ” [2ኛ ተሰሎ 2÷4] ራሱን ከፍ ከፍ ማድረግ ተሳክቶለታል። የሰውን ዘር ሁሉ ወደ እውነተኛውና ሕያው አምላክ በማያወላዳ ሁኔታ የሚጠቁመውን የመለኮታዊውን ሕግ ብቸኛ መመሪያ ይቀይር ዘንድ ደፍሯል። አራተኛው ትዕዛዝ እግዚአብሔር የሰማያትና የምድር ፈጣሪ እንደሆነ ስለሚገልጽ፣ ጌታ ከሌሎች ሐሰተኛ አማልክት የሚለይበት ነው።”—ኢቢድ ፣ ገጽ 53, 54

3. በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል የሚናገር አውሬ ማክሰኞ ግንቦት 29
ሀ. በዳንኤል ምዕራፍ 7 ላይ ያለው የቀንድ ሃይል “በልዑል ላይ ታላቅ ቃል የሚናገረው” እንዴት ነው? ዳንኤል 7:25 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ 2ኛ ተሰሎንቄ 2፡4 ሊቀ-ጳጳሱ በአካል (በገሃድ) የሚታይ የዓለም-አቀፋዊትዋ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መሪ እንደሆነና በምድር ዳርቻ ሁሉ ባሉ ጳጳሳትና ፓስተሮች ላይ ጠቅላይ ስልጣን እንዳለው የሚናገረው ቀኖናቸው፣ ከግንባር ቀደም የሮማዊነት አስተምህሮዎች ውስጥ አንዱ ነው። ይባስ ብሎም ሊቀ-ጳጳሱ የአምላክ የሆኑትን እነዚያኑ ስያሜዎች ለራሱ ወስዷል። ራሱን “ጌታ እግዚአብሔር ሊቀ-ጳጳስ/Lord God the Pope” አድርጓል፣ ስህተት መሥራት የማይቻለው የመሆን ሥፍራ ይዟል፤ የሰው ዘር ሁሉ ክብር እንዲሰጡት ይጠይቃል። ስለዚህ በምድረ በዳው ፈተና ሰይጣን ያቀረበውን መጠይቅ ዛሬም በተመሳሳይ ሁኔታ በሮም ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት እያቀረበው ነው፤ አያሌ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም ክብር ሊሰጡት የተዘጋጁ ሆነዋል።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 50.ለኃጢአት ይቅርታና ለዘላለማዊ ድነት በእግዚአብሔር ልጅ በማመን ፈንታ ሰዎች ወደ ሊቀ-ጳጳሱና እርሱ ወደ ሾማቸው ቀሳውስትና የኃይማኖት መሪዎች ተመለከቱ። ምድራዊ አማላጃቸው ሊቀ-ጳጳሱ እንደሆነና በእርሱ በኩል ካልሆነ በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንደማይቻል ተማሩ። በተጨማሪም፣ ለእነርሱ፣ በእግዚአብሔር ቦታ የተቀመጠ ከመሆኑ የተነሳ በፍጹም መታዘዝ እንዲከተሉት ተማሩ።”—ኢቢድ ፣ ገ ጽ. 55.እግዚአብሔር ማንንም ሰው የቤተክርስቲያን ራስ አድርጎ እንደሾመ በቃሉ ፍንጭ አልሰጠም። የጳጳስ የበላይነት መሠረተ ትምህርት ከቅዱሳን ጽሑፎች ትምህር ት ጋር በቀጥታ ይቃረናል።”—ኢቢድ ፣ ገጽ. 51.በአሥራ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግሪጎሪ 7ኛ የሮማዊቷን ቤተ ክርስቲያን ፍጹምነት ሲያውጅ፣ ሌላ ተጨማሪ የጳጳሳዊ ስልጣን ሚና ሥራ ላይ ዋለ። ካቀረባቸው ሃሳቦች መካከል፣ መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው መሰረት፣ ቤተ ክርስቲያንዋ ከአሁን በፊት ስህተት ሰርታ አታውቅም፣ ከአሁን በኋላም ፈጽማ ጥፋት አትሰራም የሚለው ይገኝበታል። ለንግግሩ ማረጋገጫነት ግን መጽሐፍ ቅዱስ በማስረጃነት አልተጠቀሰም ነበር።”—ኢቢድ፣ ገጽ 57 ለ. ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ መገለጥ ወደፊት የሚመጣ ክስተት ብቻ ሳይሆን በሐዋርያት ዘመንና ክርስትና ገና ሲቋቋም የጀመረ መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 2ኛ ተሰሎንቄ 2:3, 7፤ 1ኛ ዮሃንስ 2:18, 19፤ 4:1–3፤ የሐዋርያት ሥራ 20፡28-30 ሐዋርያው ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች በጻፈው ሁለተኛ መልእክቱ ላይ የጳጳሳቱ ሥልጣን የ ሚቋቋምበትን ታላቅ ክህደ ት ተንብዮአል። . . . [2 ተሰሎን ቄ 2:3, 4, 7 ተጠቅሷል።]”—ኢቢ . 49.እግዚአብሔር ይዋረድ ዘንድ ሐሰተኛው ሰንበት ከሰው በላይ በሆነ አካል በኩል ጸንቷል። ይህ በምድር ላይ የሰይጣን የበላይነ ት ምልክት ይሆን ዘንድ ነው።”— The Signs of the Times, March 12, 1894.

4. ደም የተጠማች ቤተክርስቲያን ረቡዕ ግንቦት 30
ሀ. ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች የሚያደርጉትን ነቢዩ ሲመለከት ምን ነበር ያስደነቀዉ? ዳንኤል 7:25 (የመጨረሻው ክፍል); ማቴዎስ 24:21, 22; ራእይ 13:7; 17፡6። በአሥራ ሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሁሉም የጳጳሳዊ መሳሪያዎች የሚበልጠው፣ እጅግ አሰቃቂ የሆነው ችሎት (the Inquisition) ተቋቋመ። የጨለማው ልዑል በጳጳሳዊ ስልጣን እርከን ውስጥ ካሉ መሪዎች ጋር ይሰራ ነበር። ምስጢራዊ ስብሰባቸውን ሲያካሂዱ፣ የእግዚአብሔር መልአክ በመካከላቸው ቆሞ በኃጢአት የተሞሉትን አዋጆቻቸውን፣ በፍጡር አይን ተገልጦ ለመታየት እጅግ ዘግናኝ የሆነውን የሥራቸውን ታሪክ፣ በአስፈሪው መዝገብ ላይ ሲጽፍ ሳለ፣ ሰይጣንና መላዕክቱ የክፉ ሰዎችን አእምሮ ይቆጣጠሩ ነበር። ። “ታላቋ ባቢሎን” “በየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ” [ራዕይ 17÷6] ነበር። አካላቸው የተቆራረጠው፣ በሚሊዮን የሚቆጠረው የሰማዕታት ግዝም፣ በዚያ ከሃዲ ኃይል ላይ የበቀል እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጮህ ነበር።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ59, 60ጳጳሳዊ ሥርዓት፣ ምን እንደምትሆን ትንቢት ያወጀው፣ የኋለኛው ዘመን ክህደት ነው [2ኛ ተሰሎ 2÷3፣4]። አላማዋን በተሻለ መንገድ የሚያሳካላትን ባህርይ መላበስ የመርሃ ግብርዋ አካል ነው፤ በሚለዋወጠው የእስስት ገጽታ ስር ግን የማይለወጠውን የእባቡን መርዝ ደብቃለች።”— Ibid., p. 571. ለ. ሌሎች አማኞች ነን በሚሉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ግፍ የሚደርስባቸው ክርስቲያኖች ተስፋ የሚሰጣቸውን ምን ማስታወስ ይኖርባቸዋል? 2ኛ ጢሞቴዎስ 3:12፤ ራእይ 2:10ሉቃስ 21፡28። ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች ይገቡ ነበር። ነገር ግን ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ ተስፋቸውን በክርስቶስ ላይ ያተኮሩ ሰዎችን ተስፋ ሊያስቆርጡ አልቻሉም። ጴጥሮስ በሚያበረታታና በደስታ ቃል የምእመናንን አእምሮ ከአሁኑ ፈተናና ወደፊት ከሚመጣዉ መከራ ወደ ‘የማትጠፋ፣ ርኩስ ወደማትሆንና ወደማትደበዝዝ ርስት’ ተስፋ መራ።”— The Acts of the Apostles, p. 528.እግዚአብሔር ለሕዝቡ በምሕረቱ የመከራ ጊዜያቸውን አሳጠረ። . . . በተሃድሶው ተጽዕኖ ከ1798 በፊት ስደቱ እንዲቆም ሆነ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 266, 267በዘመናት ሁሉ ሰይጣን የእግዚአብሔርን ዕዝቦች አሳድዶ ነበር ። አሠቃይቶ ገድሎአቸዋል ነገር ግን ሲሞቱ ድል አድራጊዎች ሆነዋል። ከሰይጣን የሚበልጠውን አንድ ኃይል መስክረዋል። ክፉ ሰዎች ሥጋን ያሰቃዩና ይገድሉት ይሆናል ነገር ግን በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር የተሰወረውን ሕይወት መንካት አይችሉም። ወንዶችንና ሴቶችን በእስር ቤት ግድግዳዎች መካከል ማሰር ይችላሉ፣ ነገር ግን መንፈስን ማሰር አይችሉም።በፈተናእና በስደ ት የእግዚአብሔር ባህሪ-ክብር-በተመረጡት ውስጥ ተገልጧል።”—The Acts of the Apostles, p. 576.

5. የኃይሉ መጨረ ሻ ሐሙስ ሰኔ 01
ሀ. በትንቢት የተነገረው አንድ ቀን ዓመትን እንደሚያመለክት ስለምናውቅ (ዘኍልቍ14:34፤ ሕዝቅኤል 4:6) ይህ ኃይል ይህን የመሰለ የስደት ሥልጣን ያለው እስከመቼ ነበር? ዳንኤል 7፡25 የመጨረሻው ክፍል (ዳንኤል 4፡23፣ 25፣ 32)፤ ራእይ 12:6, 14; 13፡5። በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የጳጳሳዊው ሥርዓት በጠንካራ መሰረት ላይ ቆመ። መቀመጫውን የንጉሠ ነገሥታዊቷ ከተማ ተድርጎ የሮም ጳጳስ የጠቅላላዋ ቤተ ክርስቲያን መሪ እንደሆነ ታወጀ። ጣዖት አምላኪነት ለጳጳሳዊ ሥርዓት ቦታ ለቀቀ። ዘንዶው “ሃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ስልጣን” ለአውሬው ሰጠው [ራዕ 13÷2]። በዚህ ጊዜ በዳንኤልና በራዕይ የተነገሩት የ1260 የጳጳሳዊው ሥርዓት የጭቆና ዓመታት ጀመሩ። [ዳን 7÷25፤ ራዕይ 13÷5-7]። ታማኝነታቸውን ሰውተው የጳጳሳዊ አምልኮና ሥርዓት መቀበልን አለበለዚያ በወህኒ ቤት መማቀቅን፤ እጅና እግር ተወጥሮ ታስሮ (ግራ እጅና እግር በአንድ በኩል ቀኝ እጅና እግር በሌላ በኩል ታስሮ በመመንጨቅ) ተሰቃይቶ መሞትን፤ መቃጠልንና አንገትን በፋስ መቀላትን ይመርጡ ዘንድ ክርስቲያኖች ተገደዱ። አሁን የየሱስ ቃላት ተፈጸሙ፦ “ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ። በሁሉም ስለስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።” [ሉቃ 21÷16፣17]። ከምንጊዜውም በላይ በበለጠ ቁጣ አማኞችን ማሳደድ ተጀመረ፤ ዓለም ሰፊ የጦርነት ቀጠና ሆነች። የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በመገለልና ከእይታ ውጪ በመሆን ውስጥ መጠጊያ(ደህንነት) አግኝታ ለብዙ መቶ ዓመታት ኖረች። ስለዚህም ነብዩ ይላል፦ “ሴቲቱም ሺህ ሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሃ ሸሸች።” [ራዕይ 12÷6]።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 54፣ 55እዚህ ላይ የተጠቀሱት “አርባ ሁለት ወር” እና “ሺህ ከሁለት መቶ ስልሳ ቀናት” የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በሮም እጅ የምትሰቃይበትን ዘመን የሚወክሉ አንድ አይነት ናቸው። የ1260 ዓመታቱ የጳጳሳዊ ሥርዓት የበላይነት የጀመረው ስርዓቱ ሲቋቋም ማለትም ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ538 ዓ.ም ሲሆን ያበቃው ደግሞ በ1798 ዓ.ም ነው። በዚያን ጊዜ የፈረንሳይ ጦር ሮም ገብቶ ሊቀ ጳጳሱን እስረኛ ካደረገው በኋላ ሊቀ ጳጳሱ በእስር እንዳለ ሞቷል። ብዙም ሳይቆይ አዲስ ሊቀ ጳጳስ ቢመረጥም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ግን ጳጳሳዊ መዋቅሩ በፊት የነበረውን ኃይሉን መጠቀም አልተቻለውም።”—ኢቢድ, ገጽ. 266.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ሰኔ 02
1. በጣም ጨካኝ የሆነው ግዛት በትንቢት የተገለጸው እንዴት ነው? 2. የዚህ አውሬ ልዩ ጥቃት የሚያደርገዉ በየትኛው የአምላክ ሕግ ክፍል ነው—ለምንስ? 3. የክርስቶስ ተቃዋሚ ከየት መጣ እና ዋና ዓላማው ምንድን ነው? 4. ይህ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ኃይል የአምላክ ታማኝ ሕዝቦችን እንዴት ይመለከታቸዋል? 5. በትንቢቱ መሠረት የጭቆና ኃይሉ በተወሰነ ደረጃ የቀነሰው መቼ ነበር?
 <<    >>