Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 4ኛ ትምህርት
ፀሐይ ስትጠልቅ የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “ቃሉ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው፤ ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን።” (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡11)።
ለንባብ የተመረጠዉ፡   The Great Controversy, pp. 551–562. 
የሚሞተው ሰውነታችን ሊሞትና በመቃብር ውስጥ ሊቀመጥ ይችል ይሆናል። ነገር ግን የተባረከው ተስፋ የየሱስ ድምጽ የሚያንቀላፋውን ከምድር ትቢያ እንኪጠራ እስከ ትንሳኤ ድረስ ሕያዉ ሆኖ ይኖራል። ከዚያም የተባረከውንና የከበረውን ተስፋ በሙላት እናጣጥማለን።”—In Heavenly Places, p. 352.

1. ያለመሞት ፍላጎት እሁድ ሚያዝያ 08
ሀ. ሞት በዚህ ዓለም ውስጥ ያለዉ ለምንድነው —እና ጌታ በልባችን ውስጥ ያስቀመጠዉ ተስፋ ምንድነዉ? ሮሜ5:12; 6:23; መክብብ 3:11 (ህዳግ) መታዘዝን በቅድመ ሁኔታነት አስቀምጦ የተገባው የዘላለማዊነት (immortality) ተስፋ፣ ሕግን በመተላለፍ ቅጣት ምክንያት ተወሰደ። አዳም እርሱ ለራሱ የሌለውን ለዘሮቹ ማስተላለፍ አልቻለም። እናም እግዚአብሔር በልጁ መስዋዕትነት ዘላለማዊነትን ይደርሱበት ዘንድ በሚችሉበት ሁኔታ ባያቀርብላቸው ኖሮ በኃጢአት ለወደቀው ሰብአዊ ዘር አንዳች ተስፋ ባልኖረ ነበር። . . . እናም ዘላለማዊነትን ማግኘት የሚቻለው በክርስቶስ ብቻ ነው።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 533ሰው የዘላለማዊ ህይወት ባለቤት መሆን ይችል ዘንድ ከህይወት ዛፍ መብላቱን መቀጠል ነበረበት፡፡ ነገር ግን ይህን የሚነፈግ ከሆነ የሰብዓዊው ፍጡር አካላዊ ብርታትም ሆነ ህልውና እያነሰና እየቀጨጨ ሄዶ በስተመጨረሻ መጥፋት ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡ የሰይጣን ዕቅድ አዳም እና ሔዋን አምላካዊውን ሕግ ተላልፈው እግዚአብሔርን እንዲያሳዝኑ ካደረገ በኋላ ይቅርታ ካልተሰጣቸው፤ ከህይወት ዛፍ ደግመው በመብላት በኃጢአት እና በሥቃይ መኖራቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ ነበር፡፡ ነገር ግን ከሰው ውድቀት በኋላ ቅዱሳን መላዕክት የህይወትን ዛፍ እንዲጠብቁ ታዘዙ፡፡ በመላእክቱ ዙሪያ በየአቅጣጫው የሚገለባበጥ አንጸባራቂ ነበልባላዊ ሠይፍ ተደረገ፡፡ ማናቸውም የአዳም ቤተሰብ ይህንን ድንበር ተሻግሮ ህይወት ከሚሰጠው ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አልተፈቀደለትም፡፡ ስለዚህም ዘላለማዊ ህይወት ያለው ኃጢአተኛ የለም።” —አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 55.

2. ነፍስ ሰኞ ሚያዝያ 09
ሀ. ነፍስ ከሸክላ በተሰራው ነገርና በተሰጠ የእግዚአብሔር እስትንፋስ የተዋቀረ ች ስለሆነች ፍጥረት (ዘፍጥረት 2:7) በሞት ጊዜ ስለሚሆነው ነገር ምን ማስተዋል አለብን? መክብብ 12:7፤ ያእቆብ 4:14 በትዕቢት አትናገሩ፡- ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህች ከተማ ገብተን በዚያ ለአንድ ዓመት እንቀመጣለን እንሸጣለንማለንም። እግዚአብሔር ለእርስዎ የተለየ እቅድ ሊኖረው ይችላል። ሕይወት ትነት (ጭስ) ነች።”—The Review and Herald, De-cember 23, 1902. ለ. ሞት ሲደርስባቸው በሰዎችና በእንስሳት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? መዝሙር 49:16, 17፤ መክብብ 2:15, 16፤ 3:19, 20 የሥነ ፍጥረታችን መነሻም ወደ ጀርሞች፣ ህዋሶች ወይም ወደ ሌላ ፍጥረት ሀረግ ሳይሆን ወደ ታላቁ ፈጣሪ የሚያመራ ነው፡፡ አዳም ምንም እንኳ ከአፈር ቢሠራም ነገር ግን “የእግዚአብሔር ልጅ” ነበር፡፡”“እርሱ በሌሎች ፍጥረታት ላይ እንደ የእግዚአብሔር ተወካይ ሆኖ ተቀምጦ ነበር። ከሰዉ ልጅ ጋር ተዋደዉ እንዲኖሩና እንዲያገለግሉት ስለተፈጠሩ የእግዚአብሔርን ታላቅነት ሊገነዘቡ አይችሉም።—አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 36.ኦ፣ ኃጢአተኛዉንና በሕመም የሚሠቃየዉን ሰዉ ለመፈወስ ጎንበስ ያለዉ የየሱስ ፍቅሩ እንዴት አስገራሚ ነዉ! መለኮትም ለሚሰቃዩት ሰበአዊ ፍጡራን ሁሉ በማዘን ማስታገሱስ! የመዳንን መልዕክት መጠራጠር የሚችል ማነዉ?ያን በመፍረስ ላይ የነበረዉን አካል መልሶ ጤነኛ ለማድረግ ከመፍጠር ያነሰ ኃይል አልጠየቀም፡፡ ከመሬት አፈር ለተፈጠረዉ ሰዉ ሕይወትን የሰጠዉ ቃል ለመሞት ተቃርቦ የነበረዉን ሽባ ሰዉ ሕያዉ አደረገዉ፡፡ በአካል ሕይወትን የሰጠዉ ኃይል ልቡንም አደሰዉ፡፡ በመናገርና በማዘዝ ዓለምን የፈጠረዉ አምላክ (መዝ 33፡9) በመተላለፍና በኃጢአት ለሞተች ነፍስ ሕይወትን ይሰጣል።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 269, 270በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ። ዘፍጥረት 3፡15። ይህ የመጀመሪያ ወላጆቻችን እየሰሙ የተነገረዉ ዓረፍተ ነገር ለእነርሱ የተስፋ ቃልም ነበር። እጣ ፈንታቸዉ ስለሚሆነዉ ስለ እሾህና አሜኬላ፣ ስለ ላብ ማፍሰስ ጣርና ስለ ሐዘን ወይም በኋላ ተመልሰዉ ስለሚገቡበት አፈር ከመስማታቸዉ በፊት ተስፋ የሚሰጠዉን ቃል ሰሙ። ወደ ሰይጣን በማዘንበላቸዉ ምክንያት ያጡትን ሁሉ በክርስቶስ እንደሚመልስላቸዉ ተገነዘቡ።”—ሥነ ትምህር ት፣ ገጽ 27

3. የሟቹ ሁኔታ ማክሰኞ ሚያዝያ 10
ሀ. የሞቱ ሰዎች ምን እንደሚያውቁና ይህን ነጥብ ለምን በግልጽ መረዳት እንዳለብን ግለጽ። መክብብ 9:3–6፤ መዝሙረ ዳዊት 115:17፤ 146፡4። መ ናፍስታዊነት የሰይጣን ዋነኛ የማታለል ስራ ነው። የሚወዷቸውን ሰዎች በመቃብር ውስ ጥ ያኖሩትን ሰዎች ሐዘኔታ ለማግኘት የተሰላው የሰይጣን በጣም የተሳካና አስደናቂ ማታለያ ነው። እርኩሳን መላእክቶች በእነዚያ በሚወዷቸው ሰዎች መልክ ይመጣሉ፣ እናም ከህይወታቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ያወራሉ፣ እንዲሁም በህይወት እያሉ ያከናወኗቸውን ተግባራት ያከናውናሉ። በዚህ መንገድ ሰዎች የሞቱ ወዳጆቻቸው በእነርሱ ላይ የሚያንዛብቡ (የሚዞሩ) እና ከእነርሱ ጋር የሚያወሩ መላእክት እንደሆኑ እንዲያምኑ ይመራሉ። እነዚህ ክፉ መላእክትን የሞቱ ወዳጆች እንደሆኑ አድርገው የሚገምቱት፣ እንደ ጣዖት አምልኮ ያመልኳቸዋል፣ እንዲሁም ቃላቸውን ከእግዚአብሔር ቃል የበለጠ ክብደት እንዳለዉ አድርገዉ ይቀበሏቸዋል።”—This Day With God, p. 247.መ ናፍስታዊነት ዓለምን ምርኮ አድርጎ ሊይዝ ነው። መ ናፍስታዊያን በተንኮልና በማታለል የሚደገፍ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፤ ይህ ግን ከእውነት የራቀ ነው። ከሰው በላይ የሆነ ኃይል በተለያዩ መንገዶች እየሰራ ነው፣ እና ጥቂቶች ወደ ፊት የመናፍስታዊነት መገለ ጫዎች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ምንም ሀሳብ የላቸውም። ለመ ናፍስታዊነት ስኬት መሰረ ት የተጣለው ከምድራችን የመስበኪያ ሰገነቶች ነው። አገልጋዮቹ እንደመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት አድርገዉ ከዋነኛው አታላይ የመነጨዉን ውሸት አውጀዋል።ከሞት በኋላ ያለው የንቃተ ህሊና (ሙታን ሁሉንም ያዉቃሉ የሚለዉ)፣ እንዲሁም የሙታን መናፍስት ከሕያዋን ጋር እንደሚገናኙ የሚገልጽዉ ትምህርት፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ምንም መሠረት የለውም፣ ነገር ግን እነዚህ ንድፈ ሐሳቦች እንደ እውነት ተቆጥረዋል። በዚህ የውሸት ትምህርት የዲያብሎስ መናፍስት እንደ ሙታን በመወከል ህዝቡን እንዲያታልሉ መንገዱ ተከፍቷል። የሰይጣን ወኪሎች ሙታንን በመወከል ነፍሳትን ወደ ምርኮ እያጋዙ ነዉ። ሰይጣን ሃይማኖት አለው፣ መቅደስና አጥባቂ አምላኪዎችም አሉት።”—Evangelism, pp. 602, 603 ለ. ሙታን ምንም ስለማያውቁ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል እንዲያማልዱ ወደ ቀደሙት ቅዱሳን መጸለይ እንችላለን? 1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 የሙታን መገለጥ በሁሉም የአህዛብ ስርአት ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው፣ ልክ ከሙታን ጋርም ኅብረት አላቸዉ ተብሎ ይታሰባል። አማልክቶቹ ፈቃዳቸውን ለሰዎች ያስተላልፋሉ፣ እንዲሁም ሲያማከሯቸዉም ምክር ይሰጣሉ ተብሎ ይታመን ነበር። ከዚህ ሰዎች ውስጥ ታዋቂዎቹ የግሪክና የሮም ፈላስፋዎች ነበሩ።” —Evangelism, pp. 603

4. በመቃብር ውስ ጥ ተስፋ ረቡዕ ሚያዝያ 11
ሀ. ወደ መቃብር ሲወርዱ በሁለት የተለያዩ ሰዎች መካከል ያለውን የተስፋ ደረጃ አነጻጽር ። ምሳሌ 11:7፤ 14:32; ሮሜ8፡11 ለ. በጻድቃንና በክፉዎች መካከል ያለውን ልዩነት ግለጽ። ዮሐንስ 5፡21-29 ከመቃብር በሚነሱት ሁለት መደቦች መካከል ግን ልዩነት ተደርጎአል። . . . “ለሕይወት ትንሳኤ ይነሱ ዘንድ የተገባቸው ሆነው የተቆጠሩ እነርሱ የተባረኩና የተቀደሱ ናቸው። ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ስልጣን የለውም” [ራዕይ 20÷6]። ንስሐ በመግባት በእምነት ይቅርታ ያላገኙ እነርሱ ግን የመተላለፍን ቅጣት – የኃጢአትን ዋጋ መቀበል አለባቸው። በሚፈጀው ጊዜና በጥንካሬው የተለያየ የሆነ እንደሥራቸው መጠን ይቀጣሉ። ነገር ግን በስተመጨረሻ ዕጣቸው በሁለተኛው ሞት የሚደመደም ይሆናል። ከፍርዱና ከምህረቱ ጋር ስምሙ በሆነ መልኩ፣ ኃጢአተኛውን ከነኃጢአቱ ያድነው ዘንድ ለእግዚአብሔር የማይቻለው ስለሆነ፣ የተገባው እንዳልሆነ ራሱ (ኃጢአተኛው) ያረጋገጠውን፣ በመተላለፉ ምክንያት ያጣውን ሕያውነት እንዳይኖረው ያስቀርበታል። በመንፈስ የተመራው ፀኃፊ እንዲህ ይላል፦ “ለኃጢአተኛ ጥቂት ጊዜ ቀረው፣ አይገኝም። ቦታውን ትሻለህ አታገኘውም።” ሌላውም እንዲህ ይናገራል፦ “እንዳልሆኑም [እንዳልነበሩም] ይሆናሉ/they shall be as though they had not been” [መዝ 37÷10፤ አብድ 16]። በክፉ ሥራቸው ተሸፍነው ተስፋ ወደ ሌለው ወደ ዘላለማዊ መረሳት ይዘቅጣሉ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 544, 545 ሐ. መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቃን ስለሞቱበት ጊዜ የሚናገረው እንዴት ነው? መዝሙረ ዳዊ ት 13:3; ማርቆስ 5:39 ዮሐንስ 11፡11-14 ክርስቶስ ሞትን ለአማኝ ልጆቹ እንደ እንቅልፍ ይወክላል። ሕይወታቸው ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ተሰውሯል፣ እናም የመጨረሻው መለከት እስኪነፋ ድረስ የሚሞቱት በእርሱ ይተኛሉ።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 527.ለሚያምን ሰው ሞት ከባድ ነገር አይደለም። ክርስቶስ ሞት የአጭር ጊዜ ጉዳይ መሆኑን ይናገራል። «ቃሌን የሚጠብቅ ከቶ አይሞትም» ፣ «ሕይወታችሁ የሆነው ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእርሱ ጋር ትገለጣላችሁI የክብሩም ተካፋዮች ትሆናላችሁ።» ዮሐ.8:511 ቆላ.3:4። ...ለሁለተኛ ጊዜ ሲመጣ ግን በእርሱ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሙታን ሁሉ ክቡርና ዘላለማዊ ሕይወት ለመኖር ይነሳሉ። ክርስቶስን ከሞት እንዲነሳ ያደረገው ኃይል የእርሱን ቤተ ክርስቲያን በዚህም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም ከማንኛውም ስልጣን፤ ኃይልና ስም ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋታል። -ኢቢድ ገጽ. 787(835)

5. የትንሳኤው ሁኔታ ሐሙስ ሚያዝያ 12
ሀ. ልክ እንደ አዳም በፊታችን ልንጠብቀው የሚገባው ተስፋ ምንድን ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡12-23 ከኤደን ከተባረረ በኋላ በምድር የነበረው የአዳም ሕይወት በሃዘን የተሞላ ነበር። እያንዳንዱ የሚረግፍ ቅጠል፣ እያንዳንዱ የመስዋዕት ተጠቂ (እንስሳ)፣ በምድር መልካም ገጽታ የወረደው እያንዳንዱ ዋግ፣ በሰው ንጽህና ላይ የመጣው እያንዳንዱ እንከን፣ አዳም የሰራውን ኃጢአት ሁልጊዜ አዲስ አድርጎ ያስታውሰው ነበር። ኃጢአት ሲበዛ ሲያይ፣ ማስጠንቀቂያ ሲሰነዝርም በምላሹሰ የዚህ ኃጢዓት መንስኤ ራሱ እንደሆነ ወቀሳ ሲወርድበት፣ የፀፀት ሕይወቱ እጅግ ከባድ ነበር። ትዕግስት በተሞላበት ደግነት የመተላለፉን ቅጣት ለአንድ ሺህ ዓመት የተቃረበ ዘመን ተሸከመ። በእምነት ኃጢአቱን ተናዘዘ። ቃል ኪዳን በተገባለት አዳኝ ስጦታ አምኖና ከጥፋቱ ተመልሶ፣ ከሞት እንደሚነሳ ተስፋ አድርጎ አንቀላፋ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 647. ለ. የአምላክ ታማኝ ሕዝቦች ትንሣኤ የሚፈጸመው እንዴት እንደሆነ ግለጽ። 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡42–55 በመቃብር ያንቀላፉትን ቅዱሳን የሚጣራ የእግዚአብሔር ልጅ ድምጽ ሲሰማ ምድር ትርዳለች ቅዱሳኑ በክብር የተሞላውን የማይሞት አካል ለብሰው ‹ድል በሞት ላይ! ሞት ሆይ ድል መንሳትህ የት አለ? ሞት ሆይ መንደፊያህስ የት አለ?» እያሉ በመጮኽ ለጥሪው ምላሽ ሰጡ። ከዚያም በህይወት ያሉትና ከመቃብር የተነሱት ቅዱሳን በህብረት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የድል ድምጽ አሰሙ እነዚያ የህመምና የሞት ተምሳሌት የነበረውን አካል ይዘው ወደ መቃብር የወረዱ ቅዱሳን አሁን ግን የማይሞተውን፣ ጤነኛና ብርቱ አካል ይዘው ተነሱ፡፡ በህይወት ያሉት ቅዱሳን በዐይን ቅጽበት በመለወጥ ከመቃብር ከተነሱት ጋር ጌታን ለመቀበል በአየር ተነጠቁ፡ እንዴት ያለ በአምላካዊ ክብር የተሞላትዕይንት ነው! ሞት የለያያቸው ጓደኛሞች ከእንግዲህ ዳግመኛ ላይለያዩ ሆነው ተገናኙ።”—የቀደምት ጽሑፎች፣ ገጽ. 287.

የግ ል ግ ምገ ማጥያ ቄዎች አርብ ሚያዝያ 13
1. ሰዎች ለመኖር የሚፈልጉትና መሞት የ ማይፈልጉት ለምንድን ነው? 2. የነፍስ የመጀመሪያ አካል በሞት ጊዜ የሚከፋፈለው እንዴት ነው? 3. የ ሙታን ንቃተ ህሊናዊ ሁኔታ የተሳሳተ ሀሳብ ወደ ምን ይመራል? 4. ሞት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዓለም ከገባ በኋላ የሁ ሉምአማኞች ተስፋ ምንድን ነው? 5. አካሉ በመጨረ ሻ ከሕይወት እስትንፋስ ጋር ለዘላለም የ ሚዋሃደው እንዴት ነው?
 <<    >>