ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2) << >> ሰንበት፣ ሚያዝያ 07፣ 2015 3ኛ ትምህርት ማን ልቋቋመዉ ይችላል? የመታሰቢያ ጥቅስ፡- “የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እንጠባበቃለን።” (ቲቶ 2፡ 13)። ለንባብ የተመረጠዉ፡ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 635–652። እጅግ ክቡር ብሎም እጅግ አንፀባራቂ ከሆኑ፣ ከተገለፁ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች መካከል አንዱ፣ ታላቁን የመቤዠት ሥራ ለማጠናቀቅ የሚመጣበት የክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ነው። . . . የዳግም ምፅዓቱ አስተምህሮ የተቀደሱት መጻሕፍት አንኳር ጭብጥ ነው።” —ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ. 299. 1. ቀጥተኛ መመለስ እሁድ ሚያዝያ 01 ሀ. በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ እጅግ የተባረከዉን ተስፋ ጥቀስ። ዮሐንስ 14:1-3; 2ኛ ጢሞቴዎስ 4:8 የክርስቶስ መምጣት ለእውነተኛ ተከታዮቹ በዘመናት ሁሉ ተስፋቸው ሆኖ ኖሮአል። እንደገና እንደሚመጣ የተናገረበት፣ የአዳኙ የደብረዘይት የመሰናበቻ ተስፋ በፊታቸው ያለውን የደቀ-መዛሙርቱን ዘመን አፈካው፤ ሃዘን ሊያዳፍነው፣ ፈተና ሊያደበዝዘው በማይችል ሁኔታ ልባቸውን በደስታና በተስፋ ሞላው። በስቃይና በስደት መሃል “የታላቁ አምላካችንንና የመድሃኒታችንን የየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ” መጠባበቅ “የተባረከው ተስፋ” [ቲቶ 2÷13] ነበር። የክርስቶስን መምጣት በሕይወት እያሉ ማየት ይመኙ የነበሩትን ወገኖቻቸውን ሲቀብሩ የተሰሎንቄ ክርስቲያናት በሃዘን በትር ሲመቱ ሳለ መምህራቸው ጳውሎስ በክርስቶስ ምፅዓት ስለሚሆነው ትንሳኤ አመላከታቸው። —ታላቁ ተጋድሎ. 302. ለ. በክርስቶስ ዳግም ምጻት ትንቢቶች ውስጥ ያሉት ዝርዝሮች በጣም አስፈላጊ የሆኑት ለምንድነው? ማቴዎስ 24:30, 31; 9፡28 አጽፏል። የዓለም መለወጥና የክርስቶስ መንፈሳዊ ግዛት አስተምህሮ በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት አልነበረውም። እስከ አሥራ ስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ በአብዛኛው በክርስቲያኖች ተቀባይነት አላገኘም ነበር። እንደሌላው ስህተት ሁሉ የዚህም ውጤት ክፋት ነበር።. . . ጽኑ መሰረት የሌላቸውን፣ ልበ ሙሉነትና ደህንነት እንዲሰማቸው በማድረግ ጌታቸውን ይገናኙ ዘንድ አስፈላጊ የሆነውን መዘጋጀት ከማድረግ የሚያዘናጋቸው ነው።”—ኢቢድ ፣ ገጽ 321፣ 322 2. ቀጥተኛና የሚታይ ሰኞ ሚያዝያ 02 ሀ. የሱስ ዳግመኛ የሚመጣው በምን ዓይነት ሁኔታ ነው? የሐዋርያት ሥራ 1፡9-11 የክርስቶስ ዳግም ምጻት ተስፋ በደቀመዛሙርቱ አእምሮ ውስጥ ትኩስ ሆኖ ይጠበቅ ነበር። ወደ ሰማይ ሲወጣ ያዩት የሱስ እዚህ የቀሩትንና ለእርሱ ለማገልገል ራሳቸውን አሳልፈዉ የሰጡትን ሊወስድ ዳግመኛ ይመጣል። “እነሆ ፣ እኔ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ፣ እስከ ፍጻሜም ድረስ ያሏቸዉ ያድምፅ፣ በሰማያዊው መንግሥት ፊት እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ ይቀበላቸዋል።”—The Acts of the Apostles, p. 33.በሁሉም ዘንድ እጅግ የተወደደውን የሱስን ዳግመኛ ያዩት ዘንድ ለእነዚያ ደቀ መዛሙርት የተሰጣቸዉ የተስፋ ቃል በእውነት እጅግ ዉድ (ከበረ) ነበረ። ይህ የተስፋ ቃል ደግሞ ለእውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ሁሉ እጅግ የከበረ ነው። የሱስን በእውነት የሚወድ ማንም ሰው ዳግም በመምጣቱ አያዝንም። . . .የሱስ ወደ ሰማይ እንዳረገ እንዲሁ ይመጣል፣ በተጨማሪ ግን ግርማ ሞገስን ለብሶ ነዉ። በመንገዱም በአባቱ ክብር በቅዱሳን መላእክትም ሁሉ አጅበዉት ይመጣል። በቅዱስ ግንባሩም ላይ ቅዱሳን መቅደሶቹን ለመውጋት በተደረጉ ከጨካኙ የእሾህ አክሊል ሳይሆን፣ የክብር አክሊልን ያጌጣል። . . . ከበረዶ በላይ የነጣና የሚያብረቀርቅ መጎናጸፊያ እንጂ፣ የተቆራረጠ ልብስ ለብሶ አይደለም። የሱስ እየመጣ ነው! ነገር ግን የሚመጣዉ እንደ ጊዜያዊ ልዑል ለመንገስ አይደለም። ጻድቃን ሙታንን ያስነሣል፣ ሕያዋን ቅዱሳንን ወደ የማይሞት ሕያዋን ይለውጣል፣ ከቅዱሳንም ጋር፣ ከሰማይ ሁሉ በታች ያለውን መንግሥት ይወስዳል።”—The Faith I Live By, p. 351. ለ. ይህ ማለት የሱስ በተጨባጭ ሰውነቱ (በሚታይ አካሉ) ከሞት ተነስቷል ማለት ነውን? ዮሐንስ 2፡19-21 ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ የአይሁድ ካህናትና ሹማምንት ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንዳልሞተ ነገር ግን ሕሊናውን ስቶ በመዝለፍለፍ የሞተ እንደመሰለና ቆይቶ ከሰመመኑ እንደነቃ አስመስለው አስወሩ። በመቃብር ውስጥ የተቀበረው የሰው አስከሬን የሚመስል ቅርጽ እንጂ ሥጋና አጥንት ያለው እውነተኛ አስከሬን አልነበረም የሚል ወሬም ተሰራጭቶ ነበር። ነገር ግን ክርስቶስ አስቀድሞ ስለሞተ የሮም ወታደሮች እግሩን አለመስበራቸው እነዚህ ወሬዎች አሉባልታ መሆናቸውን ያስረዳል። በተጨማሪም ካህናቱን ለማስደሰት ሲሉ የየሱስን ጎን በጦር ወግተውታል። ሕይወቱ አስቀድሞ ባያልፍ ኖሮ በጦር እንደተወጋ ወዲያውኑ መሞቱ አይቀርም ነበር።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 772 (817)ከትንሣኤው በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ከሞት ከተነሳውና ክብር ከተጐናጸፈው አካሉ ጋር እንዲለማመዱ ለማድረግ በመሬት ላይ ለተወሰነ ጊዜ ቆየ። አሁን ግን ተሰናብቶ ለመሔድ ተዘጋጀ። ሕያው አዳኝ መሆኑን ስላረጋገጠላቸው ደቀ መዛሙርቱ እርሱን ከመቃብር ጋር ማዛሙድ አልነበረባቸውም። ስለ እርሱ ባሰቡ ቁጥር ትዝ የሚላቸው እርሱ በመላው ዩኒቨርስ (ዓለማት) የተከበረ መሆኑ ነው። ”—ኢቢድ ፣ ገጽ. 829(880) 3. ግርማ ሞገስ ያለው መታየ ት ማክሰኞ ሚያዝያ 03 ሀ. የየሱስ ክርስቶስን ቃል በቃል(literal) ከሰማይ የመመለሱን አኳኋን ግለጽ። ማቴዎስ 25፡31 የትዕይንቱን በክብር መሞላት አንዳችም ቋንቋ ሊገልጸው አይችልም ነበር። ህያውና በንጉሱሣዊ ክብር የተሞላው ደመና አሁንም እየቀረበ ሲመጣ ተወዳጁን የየሱስ ማንነት በግልጽ መመልከት ችለን ነበር፡፡ የሱስ በዚህን ወቅት በዐናቱ ላይ የእሾህ አክሊል ሳይሆን ነገር ግን የክብር ዘውድ ደፍቶ ነበር። በልብሱና በጭኑ ላይ «የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ» የሚል ስም ተጽፎአል። የፊቱ ገጽታ እንደ ቀትር ጸሐይ የሚያበራ ዐይኖቹ ደግሞ እንደ እሣት ነበልባል ይመስሉ ነበር። እግሮቹ በእቶን እሳት የጋለ ናስ…ድምፁም እንደ ብዙ ወራጅ ውሃ ድምፅ ነበር፡፡ ምድር በፊቱ ተንቀጠቀጠች። ሰማይ እንደ ጥቅል መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፤ ተራሮችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወገዱ፡፡”—ቀደምት ጽሑፎች፣ ገጽ 286፣ 287 ለ. በምድር ላይ ካሉት ሰዎች መካከል እንዲህ ያለውን መምጣት ሊያውቁ(ሊሰሙ) የማይችሉት ስንቶቹ ናቸዉ? ማቴዎስ 24:24–27፤ ራእይ 1:7፤ 6፡16, 17። ይህ ጸሎታቸው በታላቁ የፍርድ ቀንም በአስከፊ ሁኔታ ምላሽ ያገኛል። የሱስ በሥርዓተ አልበኛ ሰዎች እንደተከበበ እስረኛ ሳይሆን እንደ ሰማያዊ ንጉሥ ሆኖ ወደዚች ዓለም ተመልሶሶ ሲመጣ ዓይን ሁሉ ያየዋል። ጌታ የሱስ በራሱ ክብር፣ በአባቱና በቅዱሳን መላእክት ክብር ታጅቦ ይመጣል። እርሱ ተመልሶ ሲመጣ ቁጥራቸው እልፍ አእላፍ የሆነ መላእክትና የተዋቡና ድል አድራጊ የሆኑ እንዲሁም ወሰን የሌለው ተወዳጅነትና ክብር ያላቸው የእግዚአብሔር ልጆች ያጅቡታል። ያን ጊዜ እርሱ በክብር ዙፋን ላይ ሲቀመጥ የሰው ዘር ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ- ያን ጊዜ ከወጉት ጭምር ዓይን ሁሉ ያየዋል። ያን ጊዜ በሾህ አክሊል ፈንታ የክብር ዘውድ ይደፋል። በአሮጌው የመሳለቂያ ንጉሣዊ ቀይ ቀሚስ ፈንታ «በዓለም ላይ ማንም አጣቢ ያን ያህል ሊያነጣ እስከማይችል ድረስ ነጭ የሆነ ልብስ፣» ይጐናጸፋል። ማር.9:3። «በልብሱና በጭኑ ላይ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶች ጌታ የሚል ስም፣» ይጻፋል። ራእይ 19:16። በዚያን ጊዜ በስቅለቱ ወቅት ያፌዙበትና የደበደቡት ሁሉ ይገኛሉ። የአይሁድ ካህናትና ሹማምንት በጲላጦስ የፍርድ አዳራሽ ውስጥ ያዩትን ትርኢት እንደገና በዓይነ ሕሊናቸው ያዩታል። በዚያን ወቅት የተፈጸመው እያንዳንዱ ድርጊት በሳት ሆሔያት የተጻፈ መስሎ ይታያቸዋል። ያን ጊዜ «ደሙ በእኛ በልጆቻችንም ላይ ይሁን፣» ብለው የጸለዩ ሁሉ የጸሎታቸውን መልስ ያገኛሉ። በዚያን ጊዜ እነዚያ ምስኪን፣ ደካማና ውስን የሆነ ሰብአዊ ፍጡራን ከማንና ከምን ጋር ይፋለሙ እንደነበር ይገነዘባሉ። እነዚህ ሰዎች በዚያን ጊዜ በከፍተኛ ፍርሃትና መሸማቀቅ «ተራራዎቹንና አለቶቹንም በላያችን ውደቁ! በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቁጣ ሰውሩን! ምክንያቱም ታላቁ የቁጣ ቀን መጥቶአል! ማን መቆም ይችላል?» ይላሉ። ራእይ። 6:1፣17”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 739, 740(783-784) 4. ዳግም የመምጣቱ ዓላማ ረቡዕ ሚያዝያ 04 ሀ. የየሱስ ዳግም መምጣት ዋና ዓላማ ምንድን ነው? ማቴዎስ 16፡27 በመለኮታዊ ዝግጅቱ፣ በማይገባ ሞገስ፣ ጌታ ለመልካም ስራዎች ሁሉ ዋጋ እንዲሰጥ ወስኗል። ተቀባይነት ያገኘነው በክርስቶስ ቸርነት ብቻ ነው፤ እናም የምንሰራቸው የምሕረትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች የእምነት ፍሬዎች ናቸው። ለእኛም በረከት ይሆናሉ፤ ምክንያቱም ሰዎች እንደየሥራቸው ዋጋ ይገባቸዋልና። መልካሙን ስራችንን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚያደርገን የክርስቶስ መልካም መዓዛ ሲሆን ያንን ሥራ እንድንሠራ የሚያስችለን ደግሞ ጸጋዉ ነው። የእኛ ስራዎች በራሳቸው ምንምጥቅም የላቸውም። ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ካደረግን በኋላ እራሳችንን እንደ የማይጠቅሙ አገልጋዮች መቁጠር አለብን። ከእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና አይገባንም። እኛ ማድረግ ያለብንን ብቻ ነው ያደረግነው፣ እና ስራዎቻችን በራሳችን የኃጢአተኛ ተፈጥሮ ጥንካሬ ሊደረጉ የሚቻሉ አይደሉምና።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 5, p. 1122. ለ. የሱስ ዳግመኛ ሲመጣ ለማየ ት ተስፋ አድርገው ስለሞቱትስ ምን ለማለት ይቻላል? 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡13–18 የጳውሎስ መልእክት እንደተከፈተ እና እንደተነበበ፣ የሙታንን እውነተኛ ሁኔታ በሚገልጡ ቃላቶች ታላቅ ደስታና መጽናናት ወደ ቤተክርስቲያን መጣ። ጳውሎስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ በሕይወት ያሉ ሰዎች በየሱስ አንቀላፍተው ከነበሩት አስቀድሞ ጌታቸውን እንደማይቀበሉ ተናግሯል። የመላእክት አለቃ ድምፅ እና የእግዚአብሔር መለከት ላንቀላፉት ስለሚደርስ፣ ለህያዋን የማይሞትን አካል ከመሰጠቱ በፊት በክርስቶስ የሞቱት አስቀድመዉ ይነሳሉ።”—The Acts of the Apostles, p. 258. ሐ. ንስሐ የማይገቡ ሰዎች ምን ይሆናሉ? ማርቆስ 8:38፤ ራእይ 6:14-17 እውነትን አንቀበልም በሚሉ ሰዎች ሁሉ ሕይወት ውስጥ፣ ንቃተ ህሊና የሚነቃባቸው፣ ትዝታ የግብዝነት ሕይወትን ገራፊ ትውስታ የሚያቀርብበት፣ ነፍስም በከንቱ የፀፀት [ድግግሞሽ] የምትዝልበት አፍታዎች አሉ፤ ነፍስም በከንቱ ፀፀት ትታወካለች። ነገር ግን “ድንጋጤ እንደ ጎርፍ” በደረሰ ጊዜ “ጥፋትም እንደ አውሎ ነፋስ” በመጣ ጊዜ በዚያን ቀን ከሚሆነው ፀፀት ጋር ሲነፃፀሩ እነዚህ ምንድን ናቸው! [ምሳሌ 1÷27]። እነዚያ ክርስቶስንና ታማኝ ሕዝቦቹን ያጠፉ የነበሩ እነርሱ፣ አሁን በላያቸው ያለውን ክብር ተመለከቱ።”—The Great Controversy, p. 644. 5. ዝግጁነት ሐሙስ ሚያዝያ 05 ሀ. እነዚህን የመጨረሻ ክስተቶችን ለመመስከር ስንዘጋጅ በዝግጅቱ ሁኔታ ውስጥ ምን አይነት ባህሪ አስፈላጊ ነው? 1ኛ ዮሐንስ 2:28፤ 3፡1– 9። የጽድቅ መነሻው እግዚአብሔርን መምሰል ነው። ማንም ሰው በእግዚአብሔር ላይ እምነት ከሌለውና ከእርሱ ጋር ያለውን ግንኙነት ካላስጠበቀ ጻድቅ ሊሆን አይችልም። የሜዳ አበባ በአፈር ውስጥ ሥር እንዳለው፤ አየርን፣ ጤዛን፣ ዝናብንና ፀሐይን በሥሩ በኩል መቀበል እንዳለበት እንዲሁ ለነፍሳችን ሕይወት ከሚያገለግለው ከእግዚአብሔር መቀበል አለብን። ትእዛዙን ለመታዘዝ ኃይልን የምንቀበለው የእርሱን ባሕርይ ተካፋዮች በመሆን ብቻ ነው። ማንም ሰው ታላቅም ሆነ ታናሽ፣ ልምድ ያለው ወይም ልምድ የሌለው፣ ህይወቱ ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ካልተሰወረ በቀር በባልንጀሮቹ ፊት ንፁህ፣ አቅም ያለዉ ህይወትን በቋሚነት ሊጠብቅ አይችልም። በሰዎች መካከል ያለው እንቅስቃሴ በጨመረ መጠን ከእግዚአብሔር ጋር የልብ ቁርኝትና መቀራረብ መጨመር ይኖርበታል።” —Testimonies for the Church, vol. 7, p. 194. ለ. የክርስቶስን መምጣት የሚጠባበቁ ሁሉ ምን እያደረጉ ነው? ማርቆስ 13:35–37፤ ያእቆብ 5:7, 8፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 5:1-6 ጊዜዉ አጭር ስለሆነ በትጋት እና በእጥፍ ጉልበት መስራት አለብን። . . .“በጸሎት ፀንተህ ጠብቅ” የሚለው ትእዛዝ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ብዙ ጊዜ ይደጋገማል። ይህንን በሚታዘዙ ሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚያገኟቸዉን ሁሉ የሚባርክ ደስታ ይኖራል። ጎምዛዛ የሆኑ እና በባህሪያቸው ሸካራ የነበሩት ጣፋጭና ገር ይሆናሉ፤ ትዕቢተኞች ትሑቶችና ራሳቸዉን ዝቅ የሚያደርጉ ይሆናሉ። ” —Counsels to Parents, Teachers, and Students, p. 293. የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ሚያዝያ 06 1. የ መጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ከኤደን ገነት ከተባረሩበት ጊዜ ጀምሮ የሁሉም አማኞች ቀጣይነት ያለው ተስፋ ምንድን ነው? 2. የ ክርስቶስ መምጣት ቃል በቃል መሆኑን እንዴት እናውቃለን? 3. በምድር ላይ ከሚኖሩት መካከል ማን ዳግመኛ መመለሱን ማየ ት ይችላል? 4. የሱስ እንደገና የሚመጣው ለምንድን ነው? 5. የሱስን ለማየት እንዴት እየተዘጋጀህ ነው? << >>