Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ግንቦት 26፣ 2015 10ኛ ትምህርት
ግዛቶች (Empires) ለበላይነት ይዋጋሉ የመታሰቢያ ጥቅስ ፡- “አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ወጡ፥ እያንዳንዲቱም ልዩ ልዩ ነበረች።” (ዳንኤል 7፡3)
ለንባብ የተመረጠዉ፡   ነቢያት እና ነገሥታት፣ ገጽ 522–538 
ቅዱስ ታሪክ በነቢያ ት ትምህር ት ቤቶች ውስጥ ከተደረጉ ጥናቶች አንዱ ነው። ከብሔራት (ነገዶች) ጋር ባደረገው ግንኙነት የአምላክ ዳና ተመዝግቧል። ስለዚህ ዛሬ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ጋር ያለውን ግንኙነት እንመለከታለን። የትንቢቱን ፍጻሜ በታሪክ ውስጥ ስንመለከት፣ በታላላቅ ተሐድሶ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማጥናትና ለታላቁ ተጋድሎ የመጨረሻ ግጭት ብሔራትን በማሰባሰብ ሂደት ውስጥ ያሉትን ክስተቶች እንዴት ማሻሻል እንደምንችል እንረዳለን። —Testimonies for the Church, vol. 8, p. 307.

1. ንፋስ እንደ ምልክት እሁድ ግንቦት 26
ሀ. በትንቢቱ ውስጥ ነፋስ ብዙውን ጊዜ ምንን ይወክላል? ኤርምያስ 25:32, 33; 4፡13። ‹ ነፋሳት ደግሞ የጥል ተምሳሌቶች ናቸው።› - ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ. 439.[በራእይ መጽሐፍ ውስጥ] ዮሐንስ የተፈጥሮን ክፍሎች ማለትም የመሬት መንቀጥቀጥ፣ አውሎንፋስ እና የፖለቲካ ጠብ በአራት መላእክት እንደተያዙ ተመልክቷል። እግዚአብሔር እንዲለቁ ቃሉን እስኪያሰማ ድረስ እነዚህ ነፋሳት በቁጥጥር ስር ናቸው። የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ደኅንነት ትሆናለች። የእግዚአብሔር ባሪያዎች በግምባራቸው እስኪታተሙ ድረስ ንፋሱ በምድርም ሆነ በባሕር ላይ ወይም በማናቸውም ዛፍ ላይ እንዳይነፍስ የእግዚአብሔር መላእክት የምድርን ነፋሳት በመከልከል ትእዛዙን ያደርጋሉ። ኃያሉ መልአክ ከምሥራቅ (ከፀሐይ መውጫ) ሲወጣ ይታያል። ይህ ኃያል መልአክ በእጁ የሕያው እግዚአብሔር ማኅተም ወይም እርሱ ብቻ ሕይወትን የሚሰጥ፣ ምልክቱን ወይም ጽሕፈቱን ግንባሮች ላይ የሚጽፍለት፣ የማይሞት፣ የዘላለም ሕይወት የሚሠጥለት ማኅተም በእጁ አለው። ይህ ሥራ እስኪፈጸም ድረስ አራቱን ነፋሳት እንዲቆጣጠሩ እና እንዲለቁ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ አራቱን መላእክት የማዘዝ ሥልጣን ያለው የልዑል መልአክ ድምፅ ነው።”—Testimonies to Ministers, pp. 444, 445.

2. ውሃ ፣ አራዊት፣ እና ክንፎች ሰኞ ግንቦት 21
ሀ. በአንድ ዓይነ ት ውሃ ወይም ባህር ዙሪያ በተለ ይም ከነፋስ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ትንቢታዊ ምሳሌዎችን ብዙ ጊዜ እናገኛለን። ይህ ምንን ይወክላል? ራእይ 17፡15። ነፋሳት ደግሞ የጥል ተምሳሌቶች ናቸው። በታላቁ ባህር ላይ የሚጋጩት አራቱ የሰማይ ነፋሳት፣ መንግሥታት ወደ ኃይልና ስልጣን ሲመጡ የሚያደርጉትን የወረራና የአብዮት አሰቃቂ ትዕይንት የሚወክል ነው።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 440 ለ. አምላክ ምድራዊ መንግሥታትን ወይም ግዛቶችን ለማሳየት ምን ይጠቀማል? ዳንኤል 7:17, 23 ለዳንኤል የምድርን ኃያላን የሚወክሉ ጨካኞች አራዊት ራእይ ታየ ው። የ መሲሑ መንግሥት ምልክት ግን በግ ነው። ምድራዊ መንግሥታት በሥጋዊ ኃይል ወደ ላይ ሲገዙ፣ ክርስቶስ ግን ሥጋዊ የሁነዉንና ለማስገደድ የሚጠቅመዉን መሣሪያን ሁሉ ያጠፋዋል። መንግሥቱም የወደቀውን የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ለማድረግና ለማስከበር ይመሠረታል።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 4, p. 1171. ሐ. ብዙ ጊዜ አንድ ነቢይ አንድ አውሬ በክንፍ ሲበር አይቷ ል፤ ይህም ከእንስሳው ተፈጥሯዊ ሕልውና ጋር የሚቃረን ነው። በንስር ክንፍ የተገለጹት እነዚህ ክንፎች ፍጥነትን እና ጥንካሬን እንዴት ያመለክታሉ ? ዕንባቆም 1፡6-10 ንስር ወደቤቷ ለመድረስ በምታደርገዉ ጥረት ብዙን ጊዜ በወጀቡ ኃይል ወደ ጠባቡ የተራራ ሸለቆዎች ትወረወራለች። ደመናዎች ጠቁረዉና ቁጡ ቁልል ሰርተዉ በእርሷና ጎጆዋን ከሰራችበት ፀሐያማ ኮረብታዎች መካከል ይሄዳሉ። ለአንድ አፍታ ንስርዋ ግራ የተጋባች በመምሰል እነዚያን ጥቁር ደመናዎች ወደኋላ የምትጠርግ ይመስል ጠንካራ ክንፎቿን በማርገብገብ ወዲያና ወዲህ ትበራለች። ከእስር ቤቷ ነጻ የምትወጣበትን መንገድ በምታደርገዉ ከንቱ ጥረት የምታሰማዉ ያልተለመደ ጩኸት የተራራ እርግቦችን ታባንናችዋለች። በመጨረሻም በጨለማዉ ዉስጥ ወደላይ በኃይል ትቀዝፍና ከአፍታ በኋላ ከላይ ካለዉ ፀጥ ያለ የፀሐይ ብርሃን ካለበት ብቅ ስትል ድልን የሚያበስር የፉጨት ጩኀት ታሰማለች። ጨለማዉና ወጀቡ ከበታችዋ ቀርቶ በዙሪያዋ የሰማይ ብርሃን ያበራላታል። እጅግ ከፍ ብሎ ባለዉ በአለት ንቃቃት ወዳለዉ ተወዳጁ ቤትዋ በመድረስ ትረካለች። ወደ ብርሃን የደረሰችዉ ጨለማዉን አልፋ ነዉና።”—የወጣቶች መልእክት፣ ገጽ 102, 103“እውነትን ለነገድ፣ ለቋንቋና ለሕዝብ ሁሉ በፍጥነት ይደርስ ዘንድ ክንፍ እንዲያገኝ፣ የሕትመት ሥራን በጥሩ ሁኔታ መጥቀም የሚችሉ ሰዎች በጣም ያስፈልጋሉ።”—Gospel Workers, p. 25.

3. አንበሳ ማክሰኞ ግንቦት 22
ሀ. አውሬዎች መንግሥታትን የሚወክሉ በመሆናቸው በዳንኤል 7:4 ላይ በተገለጸው አንበሳ የተመሰለው የትኛው ብሔር ነው? ይህ ብሔር በታሪክ ውስጥ ያለውን ሚና የተወጣው እንዴት ነው? ኤርምያስ 4:6, 7፤ 50:17, 43, 44 [እግዚአብሔር] ከእርሱ ፊቱን አዙሮ አሕዛብን አማልክት በመለከው መንግሥት ላይ ቅጣት እንደሚያወርድ እግዚአብሔር በታማኝ ቃል አቀባዮቹ አማካይነት ተናገረ። የወደፊቱ ሁኔታ ምን ይሆን እያሉ ይጠይቁ ከነበሩት መካከል በሕይወት እያሉ እግዚአብሔር በታምሩ የዓለምን ነገሥታት ሁኔታ መንገድ አስይዞ ባቢሎዎናውያንን አገነነ። “የሚያስደነግጡትን የሚያስፈሩትን ከለዳውያንን የቅጣት አለንጋ እንደሆኑ በይሁዳ ላይ አወረደ። (ዕንባቆም፡ 1፡7) የይሁዳ መሳፍንትና ያገሯ ምርጦች፣ ወደ ባቢሎን ተማርከው ተወሰዱ። የባቢሎን ከተሞችና መንደሮች የለሙት ማሳዎቻቸውም ውድማ ሆኑ። ምንም አልተረፈም።””—ነቢያት እና ነገሥታት፣ ገጽ 385, 386(260) ለ. አምላክ በናቡከደነፆር መሪነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰችበት ወቅት ኃያል የሆነውን የባቢሎንን ግዛት የገለጸው እንዴት ነው? ለምንስ? ኤርምያስ 27:4-8 ናቡከደነጾርን መጸሐፍ ቅዱስ “ንጉሠ ነገሥታት” (ሕዝቅኤል 26፡7) ብሎ ሰይሞታል። ታዲያ ግዛቱ ታላቅነትና ክብር ምክንያቱ እግዚአብሔር መሆኑን አንዳንድ ጊዜ ሳይገነዘብ አልቀረም። …በትውልድና ባሰተዳደግ ጣዖት አምላኪ ቢሆንም፣ የጣዖት አምላኪ ሕዝብ መሪ ቢሆንም፣ የፍትህና የዕውነት ዝንባሌ ነበረው። እግዚአብሔር አጥፊዎችን ለመቅጣት መሣሪያ አደረገው። የእግዚአብሔር ዕቅድ በእርሱ አማካይነት ተፈጸመ። “የአሕዛብ ጨካኝ” በመባል የታወቀው ናቡከደነጾር (ሕዝቅኤል 28፡7) ጢሮስን ከብዙ ዘመን ትግልና ትዕግስት አሸነፈ። ግብጽም በድል አድራጊ ሠራዊቶቹ ተማረከች። ከሕዝብ ላይ ሕዝብ በግዛቱ ላይ ጨመረ፤ በዘመኑ ከሁሉም የበለጠ ገዥ በመባል ታወቀ።ይህ ታላቅ ንጉሥ፣ በኩራትና በትዕቢት ልቡ አብጦ የእውነተኛ ታላቅነት ከሆነው ከትህትና መንፈስ መራቁ አያስገርምም። በጦር ሜዳዎች ከድል ላይ ድል በጨመረ ቁጥር መዲናውን በበለጠ እያሳመራት ሄደ። በባቢሎን የመንግሥቱ ሁሉ እንቁ ሆነች። “ወርቃዊት ከተማ” “የምድር ሁሉ ክብር” በሚባሉ ስሞች ተሰየመች። ' ”—ኢቢድ .፣ ገጽ 514፣ 515

4. ድብ ረቡዕ ግንቦት 23
ሀ. ድቡ አንበሳውን ሲከተል፣ ከመጀመሪያ በኋላ የትኛው ብሔር በቦታው ላይ መጣ? በብሔሮች ታሪክ ውስ ጥ ያለውን ሚና ይግለጹ። ኢሳይያስ 14:3, 4; ዳንኤል 7:5; 5:30, 31 ገዥዎቹ የመንግሥታቸውን ክብርና ኃያልነት በራሳቸው ኃይል የመሣ ስለመሰላቸው ባቢሎን በመጨረሻ ወድቃ ተሰባበረች።”—ነቢያት እና ነገሥታት፣ ገጽ 501፣ 502(336)የፋርስ አሸናፊው የጦር ሠራዊት ሳይታሰብ በወንዙ በኩል መጥቶ ባቢሎንን ያዛት የከተማዋ በር በግዴለሽነት ዘበኛ አልነበረውም። የጨቋኛቸውን በድንገት መሸነፍ ሲያዩ አይሁዶች ትንቢቱ በገሃድ ሲፈፀም የዓይን ምስክር ሆኑ። ለእነርሱ ሲል እግዚአብሔር የዓለምን ታሪክ ሲያካሂድ ምልክት ሊሆንላቸው ይገባ ነበር።”—ኢቢዲ. 552(372) ለ. ሜዶ ፋርስ ባቢሎንን እንደሚታሸንፍ (እንደምትገለብጥ) ትንቢት የተተነበየበት ጊዜ መቼ ነበረ፤ እና ዓለምን በሙሉ አጠቃልሎ የመግዛቱ ስፋቱስ ምን ያህል ነበር? ኤርምያስ 25:12; ኢሳይያስ 44:26–28; 45:1–6, 13; አስቴር 1፡1 የባቢሎን መንግሥት በወደቀና ቂሮስ ከነገሠ ከሁለት ዓመት በኋላ [ዳርዮስ] ሞተ። ያኔ ዕብራዊያን ተማርከው ወደ ባቢሎን ከተጓዙ ሰባ ዓመታት ሆነ።የዳንኤል ከአንበሳዎች ጉድጓድ መትረፍ (መዳን) በታላቁ ቂሮስ ላይ መልካም ስሜት አሳድሮ ነበር። የእግዚአብሔር ሰው አርቆ አስተዋይነትና ታላቅ ያስተዳደር ችሎታው አስተያየቱን እንዲያከብርና ማንነቱን ታላቅ ግምት እንዲሰጠው አስገደደው። አሁን ኢየሩሳሌም ትጠገናለች ብሎ እግዚአብሔር የተናገረው ጊዜ ሲደርስ ቂሮስን መሣሪያ አድርጎ ሊጠቀምበትና ትንቢቱ እንዲፈፀም ለማድረግ ተሰለፈ። የአይሁድ ሕዝቦች ነፃነታቸውን እንዲቀዳጁ አደረገ።ከመወለዱ በፊት አንድ መቶ ዓመት ቀድሞ የተነገረውን ትንቢት ሰማ። የባቢሎን መማረክ ተገነዘበ። የዩኒቨርስ ገዥ (እግዚአብሔር) ስለ እርሱ እንዲህ ያለውን ሲያነብ … ልቡ ተነካ። መለኮታዊ ተልዕኮውን ለመፈፀምም ወሰነ።”—ኢቢድ.፣ ገጽ 556, 557

5. ነብር ሐሙስ ግንቦት 24
ሀ. ነብር ድብን ስለተከተለ ሜዶፋርስን እንደ ቀጣዩ ታላቅ ግዛት የተከተለው ብሔር የትኛው ነው? ዳንኤል 7:6; 8:5–7, 20, 21 የእግዚአብሔርን ሕግ በእግሩ ስለረገጠ የሜዶ ፋርስ መንግሥት ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ወረደበት። አብዛኛው ሕዝብ በልቡ ፈሪሃ-እግዚአብሔር አልነበረበትም።”—ነቢያትና ነገሥታት፣ ገጽ. 502(336) ለ. ቀንዶች ምንን ያመለክታሉ? በዚህ እንስሳ ላይ ካሉት አራት ራሶች ጋር እንዴት ይመሳሰላሉ? ዳንኤል 8:8, 22 የእነርሱ የትዕቢት ፍልስፍና በዓለም ላይ ምን ተጽዕኖ አሳደረ? ወንጌልስ ከእንዲህ ዓይነቱ ፍልስፍና የሚጻረረው እንዴት ነው? 1ኛ ቆሮንቶስ 1:19–25፤ ቆላስያስ 2፡8“በጥንቶቹ ግሪክና ሮም እዉነተኛ ደራሲዎች ይልቅ ጥንታዊ ግሪክና ሮም ጸሐፊዎች የጻፏቸዉን ቅዱስ ናቸዉ የሚባሉትን የአፈ ታሪክ መጻሕፍትን የሚያጠኑ እውራን መሪዎች በሚሰጡት መመሪያ እንዲመሩ እነርሱን አምነን ወጣቶችን ለእነርሱ መተዉ ተገቢ ነውን?”— The Review and Herald, October 30, 1900.“ግሪኮች ሰውን ዘር ከፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያምኑ ነበር፣ ነገር ግን የፍልስፍና እና የሳይንስ ጥናትን ወደ እውነተኛ ከፍታና ክብር ለመድረስ ብቸኛው መንገድ አድርገው ይመለከቱት ነበር።”—The Acts of the Apostles, p. 244.ጳውሎስ የአይሁድ ትምህርትም ሆነ የግሪክ አንደበተ ርቱዕነት በክርስቶስ የሱስ ወዳለው ከፍተኛ ጥሪ ምልክት ላይ መድረስ እንደማይችል ተናግሯል። ከፍተኛው አንደበተ ርቱዕ ሆነ ትልቁ አካላዊ ጥንካሬ፣ የሰውን ነፍሱ እንዲወቅሰዉና እንዲለወጥ ኃይል ሊሰጠው አይችልም። ሰውን ለእግዚአብሔር ክብር የሚያደርሰው የወንጌልንጹሕ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በልብ መቀበል ብቻ ነው።”—The Central Advance, April 8, 1903.

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ግንቦት 25
1. በዛሬው ጊዜ በአሕዛብ አሠራር ውስጥ የአምላክን ዓላማዎች ማስተዋል የ ምንችለው እንዴት ነው? 2. የምድር ብሔራት ባህሪያት በትንቢት ውስጥ የተገለጹት እንዴት ነው? 3. የባቢሎን ብሔር አሠራሩን እንዲቀይር ያደረገው ምንድን ነው? 4. ትንቢቱ አምላክ በብሔራት ጉዳዮች ላይ እንደሚያስብ የሚያሳየው እንዴት ነው? 5. የግሪክ ሥርዓት ዛሬም በኅብረተሰቡ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው በየትኞቹ መን ገዶች ነው?
 <<    >>